Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 06 Jan 2022, 04:37

አሁን ሁሉ ነገር ዞሮ ገጥሟል!

ድፍን አራት የኢትዮጵያ ትውልዶች ከዘመነ ሃይለ ስላሤ እስከ ዘመነ አቢይ አህመድ ያሉት ዛሬ ተመልሰው አንድ ሆነዋል! ዛሬ በሙሉ ድፍረትና ኩራት ማለት የሚቻለው ቃል ኢትዮጵያ የሚባለው ዘላለማዊና የሰው ልጅ ቅርስ የሆነው ሃሳብና ማህበር ነው ።

እኔ ሆረስ ቃላት መሸንሸን አይመቸኝም፤ እስቲ በጥሞና ለ50 እና ለ60 የብሄር ጥያቄ ላይ የሞቱት እስከ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች፤ ለ60 አመታት በብሄር ጥያቄ ላይ የወደመ የሰው ሃይል፣ የቁስ እና የቴክኖሎጂ፣ የሰው እስኪል፣ እና ሃብት በስንት ትሪሊዮን እንደ ሚለካ አስቡት ። ለ60 አመታት ሳይሰራ የቀረው እድገት፣ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ሞቶ የበሰበሰው የሰው እውቀትና ክህሎት እስቲ አስቡት!

ዛሬ ላይ ቆመን ያለፈውን ዘመነ ብክነትና እና ዘመነ እብደት ብናጤን አንድ ግልጽና ነዋሪ ፋይዳዊ ለውጥና እድገት መሬት ላራሹ መደረጉ ብቻ ነው። ሌላው በሙሉ ባዶ ነገር ነው ። ዛሬ አራት የኢትዮጵያ ትውልዶች ተዋህደው አንድ የኢትዮጵያ አጀንዳ ሲዘምሩ ለማንም ምንግዜም ግልጽ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ በብሄር ጥያቄ የጭለማና መድረሻ አልባ ሃሳብ ፋይዳ ቢስነት፣ አውዳሚነት፣ ጎታችነት እና ሲብስበትም እብደት መሆኑን ነው።

ለዚህ ሁሉ የመጨረሻው ግዙፍ ምሳሌ በትግሬ ህዝብ ላይ ላለፉት 50 አመታት የሰፈነው ጭለማና የደረሰው ሰቆቃ ነው ። አንድም የኢትዮጵያ ጎሳ የትም የሄደ የትም የደረሰ የለም፤ እዚያው ሰቆቃው ውሰጥ ነው የሚማቅቀው! በብሄር ጥያቄ አራት ትውልድ ያስፈጁት ብሄረተኞች ምን አተረፉ? ህዝባቸው ምን እድገት ላይ ደረሰ?

ከወሎ ረሃብ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ትግሬ በልመና ስንዴ ነው የሚማቅቀው! ይህን አስቦ የማያፍር የትግሬ ልሂቅ እንዴት ሊኖር ይችላል? ይህ የጭለማ ጉዞ ሄዶ ሄዶ አሁን ትግራይ ትስዕር ለሚባል ትርጉሙን እንኳ ለማያውቁት ቃል እንደ ቆሻሻ በየሙጃው ውስጥ የቀረው ስንት የትግሬ ጨቅላ አንጎል ነው? ትስዕር ፣ ስርዕየት ፣ መሰረዝ ከአንድ ነገር ነጻ መሆን የሃጢያታችን መሰረዝ ማለት ነው እንጂ ማሽረንፈ ማለት አይደለም! የትግሬ ሕዝብ በመቶ ሺዎች የሚሞተው ትርጉሙን እንኳ ለማያወቀ ቃል ነው! ከዚህ የላቀ ስካርና እብደት ምን አለ!

የብሄር ጥያቄ የሚባል የደንቆሮ ዘፈን እና ነጻ አውጪ ጦርነት የሚባል ስካር ባይኖር የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዛሬ የት በደረሱ!

ለምሳሌ አሜሪካንን ተመልከቱ ለ75 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲባክኑ ይህን ሲረዱ ያንን ሲከዱ ዛሬ ሃ ብለው ከኢትዮጵያ ጋራ መጀምር አለባቸው!

ግዜ ሁሉን ነገር ይበላል! ግዜ የሁሉም ነገር ድክመትና ውድቀት እንደ ብርሃን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል ! ግዜ አይዋሽም ! ግዜ አያዳላም!

መልካም ልደት ለኢትዮጵያ! ብርሃን ይሁን!
Last edited by Horus on 11 Jan 2022, 03:43, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 06 Jan 2022, 13:53

ገና የብርሃን መወለድ ነው።

ብርሃን እውቀት ነው።

እውቀት እውነትን ከዉሸት የመለየት ብቃትና ስጦታ ነው።

ስህተት ማለት አንድ የያዝነው እውነት (እምነት) ዉሸት ሆኖ ሲገኝ ነው።

ለምሳሌ የብሄር ጥያቄ እንደ እውነት ያመንነው ዉሸት ነው ።

የብሄር ጥያቄ ዉሸት ነው። የብሄር ጥያቄ የሚባል እውነት የለም ። ይህን ዉሸት ነው ዛሬ በአዲስ ብርሃን፣ በአዲስ እውቀት መታረም ያለበት ግዙፍ፣ እጅግ ግዙፍ የርዕዮት፣ የሃሳብ፣ የእምነት፣ የካልቸርና የፖለቲካ ቀውስ!

ይህ ጉዳይ አንድ የዶክቶራል ዲሰርቴሽን ሳይሆን አስር መጻህፍት ይወጣዋል። ለምሳሌ ...

(1) በትግሬ የመጀምሪያው ወያነ አመጽ ስንት ትግሬ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(2) በመንግስቱ ነዋይ መፈንቅለ መንግስት ስንት አዋቂ፣ ምሁርና ወታደር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(3) በሁለቱ የሱማሌ ጦርነቶች ስንት ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(4) ለ30 አመት በተካሄደው የኤርትራ ነጻነት ጦርነት ስንት ሰው፣ ስንት ምሁር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(5) ከሜጫ ቱለማ ማህበር እስከ ዋቆ ጎቱ እስከ ኦነግና ቄሮ ስንት ስንት ወጣት፣ ስንት አዋቂ፣ ስንት ምሁር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(6) ከየካቲት አብዮት እስከ ደርግ መፍረስ ስንት ብርቅዬ የኢትዮጵያ ወጣት፣ ልሂቅ፣ ምሁር፣ መሪ ሞተ፣ ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(7) ከ1975 እስከ ዛሬ 2022 በትግሬ በቀጠለው አላማ ቢስ ጦርነት ስንት ወጣት፣ ወንድ ሴት፣ ምሁር፣ ጨዋ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(8) በባድመ ጦርነት ስንት ሰው ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(9) የትግሬ የዘር አገዛዝ ስልጣን ከያዘበት 1990 እስከ ዛሬ 2022 ድረስ በመላ ኢትዮጵያ በጎሳ፣ በክልል፣ በዘር፣ በቋንቋ ሳቢያ ስንት ሚሊዮን ሕዝብ ተፈናቀለ፣ ተሰደደ፣ ተበተነ፣ ደሀየ፣ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(10) ከ1960ው የመንግስቱ ነዋይ መፈንቅል ጀምሮ እስከ አሁኑ 2022 ቅጽበት ድረስ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ተሰደደ፣ በረሃ በላው፣ ዉሃ በላው፣ በሽፍታ ተገደለ፣ አካሉ ተሸጠ፣ ስንት ወጣት ሴት በስደር ተደፈረች፣ ሞተት፣ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(11) ከ1960 እስከ ዛሬ 2022 ድረስ ኢትዮጵያ ስንት መቶ ሺ ምናልባት ሚሊዮን የተማረ፣ የሰለጠነ የሰው ሃይሏ ወደ ውጭ ፈልሶ በአንጎል ሽሽት (ብሬይን ድሬይን) ተበላ? ያ ሁሉ እውቀትና ክህሎት ኢትዮጵያ ላለፉት 60 አመት ተጠቅማ ቢሆን ዛሬ ምን እንደርስ ነበር?

እነዚህና መሰል እንቅልፍ ነሺ ጥያቂዎችን የማያነሳ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ምሁር ገና የሪያሊቲ ንቃተ ህሊና ደረሰ ለማለት አይቻልም!

መልካም ገና ለኢትዮጵያ! ብርሃን ይሁን !!
Last edited by Horus on 07 Jan 2022, 16:27, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 06 Jan 2022, 17:51

ለምሳሌ ትላንት ባለቀው የሚኒቴሮች ግምገማ ላይ ጠቅላይ አቢይ ያቀረባቸውን ቁልፍ ማጠቃለዎችን እንመልከት!

(1) የኢትዮጵያ ሚሊታሪ ሃይል በሚመለከት ፤ ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ነች ፣ ኢትዮጵያ ነጻ አገር ነች ። የኢትዮጵያ ሚሊታሪ ሃይል ይህችን ታላቅና ነጻ አገር ከማንኛውም ጠላት ለመጠበቅ ሃይል ያለው ጦር መሆን አለበት ። ይህ የኢትዮጵያ እንጂ የማንኛውም ቡድን ሰራዊት አይደለም!

(2) ባለፈው 6 ወራት ምን አሳካን? ኢትዮጵያ ማንኛውም ፈተና መቋቋም የምትችል አገር እንደ ሆነች አስመስከናል!

(3) ምን ገጠመን?
(ሃ) ጦርነት
(ለ) ጣልቃገብነት
(ሓ) የኢኮኖሚ ጫና
(መ) ኢፍትሃዊነት (ኢንጀስቲስ)

(4) ምን ተማርን?
(ሃ) ችግርን ወደ እድል መለወጥ (እኔ ይህ አንቲፍራጂሊቲ ወይም ጸረ ተሰባሪነት እለዋለሁ)
(ለ) ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር እንደ ሆነች
(ሓ) የኢትዮጵያ ዋስ ጠበቃ እራሳቸው ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ!
(መ) የመደመር ጉልበት ፣አንድነት ሃይል እንደ ሆነ

በቸኛው ድላችን ምንድን ነው?
የሁሉም ጠላት የሆነው ጠላትን በጋራ ትግል አሸንፈን የጋራ ድል ማግኘታችን

ከድል በኋላስ?
ብቸኛ አላማችን አገር ማጽናት ነው ፣ ማንኛውም ነገር ስንወስን ለዚህ አላማ እንጂ የግል ጉዳይ ስላልሆነ ከድል በኋላ የጀግና ባህሪ መላበስ አለብን! ይህ ማለት አገር ማጽናት የኩርፊያ ነገር አይደለም ። ዳይናሚክ የሆነ ህሳቤና ተግባር ማለት ነው ። ከነገሮች ጋር መፍሰስ ማለት ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 06 Jan 2022, 19:59

እስቲ ስለ በአገር አቀፍ መግባባቱ ውይይት ውስጥ ስለሚነሱት ነገሮች አንድ ሁለት ማለት እንጀምር።

አንደኛ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ነው። ይህ ጥያቄ ብዙ ማከራከር የለበትም! አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ባንዲራ ነው። በውስጡ ኮከብ ያለው የኢህአዴግ አሁን ደሞ የብልጽኛ ፓርቲ ባንዲራ ነው ። ስለዚህ አቢይ ከፈለገ ባለኮከቡን በፓርቲው ዝግጅቶች ላይ ሊያደርግ ይችላል፤ ወይም ከላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ከስር የፓርቲውን ባንዲራ ሊያደርግ ይችላል።

የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ባንዲራ ግን ምንግዜም መነካት የለበትም ።
Last edited by Horus on 06 Jan 2022, 23:14, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 06 Jan 2022, 23:23

ሌላው የሪፎርም ሃስብና የብሄራዊ ወይይት ጉዳይ ፌዴራል ክልሎች በጎሳ ወይም በቋንቋ የሚያደርገው ስህተት ነው። ይህ ጉዳይ የሰዎች ፍላጎት፣ የስሜት፣ የታሪክ ጉዳይ አይደለም ። አንድ አገር ጸንቶ እንዳገር ለመቆም ያስተዳደር ሲስተሙ በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ መከፋፈል ፍጹም ስህተት ስለሆነ የዚህ ወይይት አላማ የቱን እንምረጥ የሚል አይደለም። ውይይቱ የመፍትሄ ውይይት ስለሆነ ያገሪቱን ክልሎች ስንት ይሁኑ? በጂኦርግራፊ እንዴትና የት የት በከፋፈሉ ነው ለህዝቡ እድገትና ላስተዳደር የሚያመቸው በሚሉት የካርታ መፍትሄ ኤክስፐርት ውይይት ነው መሆን ያለበት!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 07 Jan 2022, 04:44

በትግሬ ህዝብ ውስጥ ምሁር የለም፤ የባንዶች ተከታይ ፊደል የቆጠረ ተላላኪ ብቻ ነው ያለው

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 07 Jan 2022, 15:19

መቼም የኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲከኞች ፖለቲካ ያውቃሉ ለማለት አይቻልም። አቢይ እነጃዋርን እና የተውሰኑት የትግሬ ወያኔዎችን በመፍታቱ አንዳንዶች ለምን እንደ ተገረሙ አይገባኝም ። አቢይ የኦነግና የትህነግ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሃይል ከደመሰሰ በኋላ ምን እንደ ሚያደርግኮ እኛ እናውቃለን ። አቢይ አሁን የሚያደርገው 3 ነገሮችን ነው ፤ (1) በትግሬ ውስጥ የፖለቲካ ክፍፍልና ክርክር እንዲነሳ ማድረግ ነው ። ትግሬ የማዕከላዊ መንግስትና ወታደራዊ አደጋው ስለተመታ አሁን ያለው ትግሬዎች እርስበርስ እንዲከራከሩ ማድረግ ነው። ያ ነው የነስባሃት መፈታት ትርጉም። (2) ኦነግን በሚመለከት የሚሆነው ተመሳሳይ ነገር ነው። አቢይን ለሚቀጥለው 5 አመት የጃዋር ተገንጣዮች አይነኩትም ። ከዚያ በተረፈ ስለቀረው የኦሮሞ ብሄረተኞች የውስጥ ንትርክ ነው ። እነሱን ከማሰር በመፍታት ነው ይበልጥ እንዲዳከሙ የሆነው። (3) የትግሬን ወረራ ለመቃወም የተነሳው የአንድ ኢትዮጵያ ንቅናቄ መላ የጎሳ ፖለቲካው ካምፕን ስላንቀጠቀጠ፣ ይህ አቢይን ሳያስፈራው አልቀረም ። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት ካምፕን ባላንስ የሚያደርግ የጎሳው ካምፕ እንዲኖር መፈለጉ አይቀሬ ነው፣ አቢይ ማለት ነው። ይህ የጎሳና የዜጋ ፖለቲካ ሽኩቻ እንዲህ ባጭር ግዜ የሚያልቅ አይደለም ! የአቢይ አቋም ሴንተሪስት ወይም የሁለቱ አስታራቂ ለመሆን እንደ ሆነ የማያውቅ ሰው ካለ ያገሪቱ ፖለቲካ የማይገባው ነው። እየሆነ ያለው ይህ ነው። ጃዋር ሲታሰር የነበረችው ኢትዮጵያንና ዛሬ ሲፈታ ያለቸው ኢትዮጵያ በጣም የተለያዩ ናቸው! የብሄር ጥያቄ ሞቶ እየተቀበረ ያለ ሃሳብ ነው! ይህን ሃቅ እነጃዋር ነገ ይገነዘቡታል!

(2)

Roha
Member
Posts: 2120
Joined: 17 Feb 2011, 00:38

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Roha » 07 Jan 2022, 16:19

Thank you Horus, well said.
መልካም ገና ።
እንኳን አደረሳቹህ።
Horus wrote:
06 Jan 2022, 13:53
ገና የብርሃን መወለድ ነው።

ብርሃን እውቀት ነው።

እውቀት እውነትን ከዉሸት የመለየት ብቃትና ስጦታ ነው።

ስህተት ማለት አንድ የያዝነው እውነት (እምነት) ዉሸት ሆኖ ሲገኝ ነው።

ለምሳሌ የብሄር ጥያቄ እንደ እውነት ያመንነው ዉሸት ነው ።

የብሄር ጥያቄ ዉሸት ነው። የብሄር ጥያቄ የሚባል እውነት የለም ። ይህን ዉሸት ነው ዛሬ በአዲስ ብርሃን፣ በአዲስ እውቀት መታረም ያለበት ግዙፍ፣ እጅግ ግዙፍ የርዕዮት፣ የሃሳብ፣ የእምነት፣ የካልቸርና የፖለቲካ ቀውስ!

ይህ ጉዳይ አንድ የዶክቶራል ዲሰርቴሽን ሳይሆን አስር መጻህፍት ይወጣዋል። ለምሳሌ ...

(1) በትግሬ የመጀምሪያው ወያነ አመጽ ስንት ትግሬ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(2) በመንግስቱ ነዋይ መፈንቅለ መንግስት ስንት አዋቂ፣ ምሁርና ወታደር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(3) በሁለቱ የሱማሌ ጦርነቶች ስንት ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(4) ለ30 አመት በተካሄደው የኤርትራ ነጻነት ጦርነት ስንት ሰው፣ ስንት ምሁር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(5) ከሜጫ ቱለማ ማህበር እስከ ዋቆ ጎቱ እስከ ኦነግና ቄሮ ስንት ስንት ወጣት፣ ስንት አዋቂ፣ ስንት ምሁር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(6) ከየካቲት አብዮት እስከ ደርግ መፍረስ ስንት ብርቅዬ የኢትዮጵያ ወጣት፣ ልሂቅ፣ ምሁር፣ መሪ ሞተ(1) በትግሬ የመጀምሪያው ወያነ አመጽ ስንት ትግሬ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(7) ከ1975 እስከ ዛሬ 2022 በትግሬ በቀጠለው አላማ ቢስ ጦርነት ስንት ወጣት፣ ወንድ ሴት፣ ምሁር፣ ጨዋ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(8) በባድመ ጦርነት ስንት ሰው ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(9) የትግሬ የዘር አገዛዝ ስልጣን ከያዘበት 1990 እስከ ዛሬ 2022 ድረስ በመላ ኢትዮጵያ በጎሳ፣ በክልል፣ በዘር፣ በቋንቋ ሳቢያ ስንት ሚሊዮን ሕዝብ ተፈናቀለ፣ ተሰደደ፣ ተበተነ፣ ደሀየ፣ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(10) ከ1960ው የመንግስቱ ነዋይ መፈንቅል ጀምሮ እስከ አሁኑ 2022 ቅጽበት ድረስ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ተሰደደ፣ በረሃ በላው፣ ዉሃ በላው፣ በሽፍታ ተገደለ፣ አካሉ ተሸጠ፣ ስንት ወጣት ሴት በስደር ተደፈረች፣ ሞተት፣ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(11) ከ1960 እስከ ዛሬ 2022 ድረስ ኢትዮጵያ ስንት መቶ ሺ ምናልባት ሚሊዮን የተማረ፣ የሰለጠነ የሰው ሃይሏ ወደ ውጭ ፈልሶ በአንጎል ሽሽት (ብሬይን ድሬይን) ተበላ? ያ ሁሉ እውቀትና ክህሎት ኢትዮጵያ ላለፉት 60 አመት ተጠቅማ ቢሆን ዛሬ ምን እንደርስ ነበር?

እነዚህና መሰል እንቅልፍ ነሺ ጥያቂዎችን የማያነሳ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ምሁር ገና የሪያሊቲ ንቃተ ህሊና ደረሰ ለማለት አይቻልም!

መልካም ገና ለኢትዮጵያ! ብርሃን ይሁን !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 07 Jan 2022, 16:56

Roha wrote:
07 Jan 2022, 16:19

Roha,

አንተንም እንኳን አደረሰህ! መልካም ገና!

አው ይብቃን፣ ይህን የውድመት ጉዞ አንድ ቦታ በቃ ብለነው ይህን ውብ ህዝብ ወደ ትልቅነት ከፍ የማድረግ የሞራል ግዴታ አለብን !

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Za-Ilmaknun » 07 Jan 2022, 17:13

(3) የትግሬን ወረራ ለመቃወም የተነሳው የአንድ ኢትዮጵያ ንቅናቄ መላ የጎሳ ፖለቲካው ካምፕን ስላንቀጠቀጠ፣ ይህ አቢይን ሳያስፈራው አልቀረም ። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት ካምፕን ባላንስ የሚያደርግ የጎሳው ካምፕ እንዲኖር መፈለጉ አይቀሬ ነው፣ አቢይ ማለት ነው። ይህ የጎሳና የዜጋ ፖለቲካ ሽኩቻ እንዲህ ባጭር ግዜ የሚያልቅ አይደለም ! የአቢይ አቋም ሴንተሪስት ወይም የሁለቱ አስታራቂ ለመሆን እንደ ሆነ የማያውቅ ሰው ካለ ያገሪቱ ፖለቲካ የማይገባው ነው። እየሆነ ያለው ይህ::

The PM, as a leader of a country as diverse as Ethiopia (without forgetting the outside influence), what do you think he thinks that centrist position should be?

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 07 Jan 2022, 18:16

Za-Ilmaknun wrote:
07 Jan 2022, 17:13
(3) የትግሬን ወረራ ለመቃወም የተነሳው የአንድ ኢትዮጵያ ንቅናቄ መላ የጎሳ ፖለቲካው ካምፕን ስላንቀጠቀጠ፣ ይህ አቢይን ሳያስፈራው አልቀረም ። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት ካምፕን ባላንስ የሚያደርግ የጎሳው ካምፕ እንዲኖር መፈለጉ አይቀሬ ነው፣ አቢይ ማለት ነው። ይህ የጎሳና የዜጋ ፖለቲካ ሽኩቻ እንዲህ ባጭር ግዜ የሚያልቅ አይደለም ! የአቢይ አቋም ሴንተሪስት ወይም የሁለቱ አስታራቂ ለመሆን እንደ ሆነ የማያውቅ ሰው ካለ ያገሪቱ ፖለቲካ የማይገባው ነው። እየሆነ ያለው ይህ::

The PM, as a leader of a country as diverse as Ethiopia (without forgetting the outside influence), what do you think he thinks that centrist position should be?
በቃ ትክክለኛ ጥያቄ ያ ነው ። ኢትዮጵያ ውስብስብ ግዙፍ እና ለ60 አመታት ያለ ማቋረጥ ፖለቲካና ጦርነት ያካሄዱ ህዝብ አገር ነች ። ምኒልክ የመራት ኢትዮጵያ እንኳ በጣም ትንሽና ቀላል የማነጅመንት ችግር ነበረች ። ለዚህ ነው ትግሬዎች ለ30 አመት ሲገዙ ይህን እውነተኛ የኢትዮጵያ ፈታኝነት በጣታቸው ሳይኩት የራሳቸውን ቀበሌ አድረገው ክሽንት ቤት ጠባቂው እስከ መለስ ትግሬ ሾመው ወርደው የተዋረዱት ።

አቢይ እየሞከረ ያለው ኢትዮጵያ የምትባል ኮምፕሌክስ ሲስተም ማኔጅ ለማድረግ ነው ። አሁን ትልቁ ጥያቄው ይህ ሚዛን ያለው ፣ ከዘላለማዊ ጦርነት የተለየ ስርዓት እንዴት ይዋቀር ነው ። ለምሳሌ ዛሬ እነስብሃትን መፍታቱ የሲስተሙን ፕሬሸር ለማስተንፈስ ነው ። የተወሰነ የትግሬ ማህበረሰብ ከሱ ጋር ቆመው ባንዳዎቹን የሚገዳደሩ ቡድን ይፈልጋል ። ለምን ቢባል ትግሬ እስካለች ድረስ ችግሩ የትም አይሄድም ። ኦርሞም እንዲሁ ነው ።

አቢይ ሴንተሪስት መቆሚያ ይፈልጋል ያልኩት በሁለት መንገድ ነው ። እንደ ኦሮሞ ፖለቲከኛ ሆኖ ከቆመ የሲስተሙ መሰረታዊ መቆሚያ ብሄረሰቦች ሆነው ግለሰቦችና ዜጋዎች የዚያ አዳማቂ በሚሆኑበት መንገድ ሪፎርም ለማድረግ ይጥር ይሆናል። ይህ አይሰራም።

ሌላው መንግስቱ፣ ሕገ መንግስቱ ክልሎች በዜጋ፣ በጂኦግራፊ ላይ አቁሞ የብሄረሰቦች ፖለቲካ የዜጋውን አዳማቂ እንዲሆን ረፎርም ለማድረግ ይሞከር ይሆናል ። ይህ ለእድገት በጣም ያመቻል ። የግለሰቡ ክፍል፣ የነጋዴው፣ የከበርቴው ክፍል ይወደዋል ። የካልቸርና ቋንቋ ፖለቲከኞች አይደሰተበትም።

በእኔ ግምት ቢያንስ ኢትዮጵያ በሰፊው ኢንዱስትራላይዝ እስከ ምታደርግና የዘር ስሜት እስከ ሚቀዘቅዝ ባለ ሁለት (2) ምክር ቤቶች ፓርላማ ማቋቋም ነው ። አገሪቱን በጂኦግራፊ ከከፋፈልን እና በግለሰብ ዜጋ አንድ ድምጽ ላይ የቆመ ፌዴራል ሲስተም ከቀረጽን በኋላ፤ ሁለተኛ የካልቸር (ጎሳዎች) የታች ምክር ቤት የቋንቋ ቡድኖች የሚሞሉበት ምክር ቤት አቁመን ይህ ምክር ቤት ከዜጋዎቹ ፓርላማ ጋር የባህል፣ ቋንቋ ወዘተ ላይ እንዲነታረክ ማድረግ ነው።

ዞሮ ዞሮ ሲስተሙ ቅይጥ መሆኑ አይቀሬ ነው። አቢይ እነጃዋርን የፈታው በሚቀጥለው ውይይት የኦሮሞ ጎሳ ድምጽ እንዲወከል ለማድረግ ነው ። የትግሬንም እንዲሁ ። ማለትም በጎሳ የሚደራጁ ፓርቲዎች መኖር ይቀጥላል ማለት ነው። ባንድ ቃል የዜጋ አምላክም፣ የጎሳ አምላክም መስዋዕት ይፈለጋሉ ማለት ነው።

ይህን የኢትዮጵያ ሪያሊቲ ያላጤኑ ሰዎች የራሳቸውን የልብ ፍላጎት ስላላገኙ አቢይን ይዘምቱበታል! ስህተት ነው! በአቢይ ቦታ ቆመን የኢትዮጵያን ችግሮች መመልከት አለብን! የሚቀጥለው ብሄራዊ ምክክር ብዙ ነገር ያሳየናል! ቁም ነገሩ የትግሬ ባንዳና ኦሮሞ ባንዳ ወታደርዊ ሃይል መክሰምና ያሜርካ ጣልቃ ገብነት መሸነፉ ነው።

የቀረው በሙሉ በፖለቲካቅ ጨዋታ ውስጥ ያሉ ምትና ፋውሎች ናቸው ። ሊኖሩም ግድ ይላል! አፍሪካን እመራለሁ የምትል ግዙፍ አገር ማድረግ ያለባት የፖለቲካ ብስለትና ክህሎት ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 08 Jan 2022, 09:36

የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?
ይህ የመንግስት ጥያቄ ነው። መንግስት (እስቴት) እና አገዛዝ (ሪጂም) ይለያያሉ። የትግሬ አገዛዝ እስከ ወደቀበት 2018 ድረስ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት (እስቴት) የጎሳዎች ከበርቴና ንዑስ ከበቴዎች ጥርቅም ቅንጅት ነበር ። አገዛዙ፣ የመለስ አገዛዝ (ሪጂም) በሞላ ጎደል የትግሬ ጎሳ ሪጂም ነበር።
ከበርቴዎቹ ብሄራዊ የግል ከበርቴና ንዑስ አለ፤ በመንግስትና ሪጂም ስልጣን ላይ ያሉት የቢሮ ከበርቴና ንዑስ ከብርቴዎች አሉ ። ሁሉም የጎሳ ከበርቴዎች ናቸው። በመንግስት ስም ቀረጥና ኪራይ ሰብሳቢ ብቻ ሳይሆን ያገሪቱን መሬት ይቆጣጠራሉ፣ በመንግስት ስም ያገሪቱን እርሻና ኢንዱስትሪን ይቆጣጠራሉ ። ስለዚህ እነዚህ የጎሳ ከበርቴዎች ሁሉ መንግሳታዊ ከበርቴዎች ናቸው ፤ እስቴት ቡርዡዋ ናቸው ።

ስለዚህ ነው በያንዳንዱ ጎሳ ውስጥ የፈሉት የጎሳ ከበርቴና ንዑስ ከበርቴዎች በትግሬ ጎሳ ንዑስ ከበርቴ የዛሬ 30 አመት የቆመው የጎሳ ሰርዓት እንዳይለወጥ የሚከላከሉት። የትግሬ ብቸኛ ሪጂምና በትግሬ የጎሳ ቁጥጥር ስር የነበረው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከተናጋ በኋላ፣ ትግሬን የተካው የኦሮማራ የጎሳ ከበርቴ የኢትዮጵያ ብሄረተኛ ሪጂም እንዲሆን ያስገደደው ነገር አለ ። እሱም ከትግሬ ጎሳ ከበርቴ፣ ከግብጽ እና አሜሪካ መንግስት የተቃጣበትን አደጋ ለመቋቋም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህልውና ዘመቻ በማስነሳት መንግስቱን ወደ ኢትዮጵያ ብሄረተኘት እንዲጠጋ ገፍቶታል።

አሁን ትግሬ ከተሸነፈ፣ ግብጽና አሜሪካም ያሰቡት ከከሸፈ በኋላ የኢትዮጵያዊነት ንቅናቄ ከጎሳው ፌዴራሊዝም ጋር ፊት ለፊት መፋጠጣቸው አይቀሬ ነው፣ ባቢይ ዙሪያ ያለው ሃይል ግልጽ የሆነ ዝማሜው አሁን በያዘው የአንድ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ርዕዮት ካልጸና ።

በዚህ ምክንያት መንግስታዊ ከበርቴዎቹ ገሚሱ (ባቢይ የሚመራው) ወደ ኢትዮጵያ አንድነትና ኢትዮጵያዊ ብሄረተኘነት ሲቦድኑ ገሚሱ ከበርቴዎች በጎሳ ብሄረተኘነት ጸንተው አሉ። አንዱ በገዢው መደቦች ውስጥ ያለው ቅራኔ ግጭት ይህ ነው ። ባቢይ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሄረተኛ መንግስታዊ ከበርቴና የግሉ ዘርፍ ብሄራዊ ከበርቴ በብዙ መንገድ ትብብርና ቅንጅት አላቸው ።

ይህን መሰል ኢትዮጵያዊ፣ አገራዊ ብሄራዊ የመደብ ትብብር የቅኝ ገዥ ኢኮኖሚ ባለቤቶችን አላስደሰተም። ለምሳሌ ያሜርካና አውሮጃ አለም አቀፍ ከበርቴ ከትግሬ ጎሳ ብሄረተኛ ና ጸረ ኢትዮጵያ ከበርቴ ጋር የተቆራኙት በዚህ ምክኛት ነው።

በአቢይ አህመድ የሚመራው መንግስታዊ የቢሮና ንዑስ ከበርቴ በአገር አዳኝነትና የውጭ ጠላት መካችነት ከስሩ ካሉት ጎሳዎች ቁጥጥር የተወሰነ ነጻነት ስለያዘ (እስቴት አውቶኖሚ) ስላገኘ አንዳንዴ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ለብዙ ሰው ግር ያሰኛል ። ለምሳሌ ...

ይህ መንግስት እነጃዋርን፣ እስክንድርን፣ ስብሃት ነጋን ሲያስር ወይም ሲፈታ ያለው ክስተት ይህ የመንግስት አንጻራዊ ተጻነት ነው። ሌላ ግዜ ወደ ዜጋ መደቦችና የግል ብሄራዊ ከበርቴዎች ጋር ሲሻረክ ያለው ክስተት ይህ የመንግስት አንጻራዊ ነጻነት ነው።

በአንድ ቃል ይህ በስልጣን ላይ ያለው በኦሮሞ ከበርቴ የሚመራው መንግስት ከጎሳ መሰረቱ መላቀቅ ስለሚሳነው፣ በሌላ በኩል በግድ ከዜጋ የግሉ ዘርፍ ከበርቴዎች ጋር መሻረክ ስላለበት ሁልግዜ የቅራኔዎች አስተናጋጅ ነው። ለምሳሌ የክልል ልዩ አይሎችና ሚሊሺያዎች በኢትዮጵያ ሰራዊት ስር ለመዋጥ አለመፈለጋቸው የዚህ የጎሳ ከበርቴዎ ውስጥ ያለው ውጥንቅጥ የስልጣንና የሃብት ምንጭ ፍትጊያ ነው።

ይህን የማያባራ ፍትጊያን የሚያቆመው የመሬት ይዞታ ከመንግስት ወጥቶ የግል ሲሆን እና መንግስት ከኢኮኖሚው እንዲወጣ ሲደረግ ብቻ ነው ። እንዲሁን የፖለቲካ ስልጣን፣ ዝናና የክብር ምንጭ ከጎሳ ባለቤትነትና ማንነት ወጥቶ የልዑላዊ ግለሰብ ዜግነት ሲሆን ነው።

ስለዚህ አሁን ያሉት ሶስት የትግል አሰላለፎች ናቸው፤ የመንግስት ክንፍ፣ የጎሳ (ክልል) ክንፍ እና የዜጎች የግሉ ክንፍ ናቸው ።
በአ ሆረስ
Last edited by Horus on 08 Jan 2022, 10:22, edited 1 time in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 11551
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Selam/ » 08 Jan 2022, 10:20

Indeed! This is your best, Horus

Horus wrote:
06 Jan 2022, 13:53
ገና የብርሃን መወለድ ነው።

ብርሃን እውቀት ነው።

እውቀት እውነትን ከዉሸት የመለየት ብቃትና ስጦታ ነው።

ስህተት ማለት አንድ የያዝነው እውነት (እምነት) ዉሸት ሆኖ ሲገኝ ነው።

ለምሳሌ የብሄር ጥያቄ እንደ እውነት ያመንነው ዉሸት ነው ።

የብሄር ጥያቄ ዉሸት ነው። የብሄር ጥያቄ የሚባል እውነት የለም ። ይህን ዉሸት ነው ዛሬ በአዲስ ብርሃን፣ በአዲስ እውቀት መታረም ያለበት ግዙፍ፣ እጅግ ግዙፍ የርዕዮት፣ የሃሳብ፣ የእምነት፣ የካልቸርና የፖለቲካ ቀውስ!

ይህ ጉዳይ አንድ የዶክቶራል ዲሰርቴሽን ሳይሆን አስር መጻህፍት ይወጣዋል። ለምሳሌ ...

(1) በትግሬ የመጀምሪያው ወያነ አመጽ ስንት ትግሬ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(2) በመንግስቱ ነዋይ መፈንቅለ መንግስት ስንት አዋቂ፣ ምሁርና ወታደር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(3) በሁለቱ የሱማሌ ጦርነቶች ስንት ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(4) ለ30 አመት በተካሄደው የኤርትራ ነጻነት ጦርነት ስንት ሰው፣ ስንት ምሁር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(5) ከሜጫ ቱለማ ማህበር እስከ ዋቆ ጎቱ እስከ ኦነግና ቄሮ ስንት ስንት ወጣት፣ ስንት አዋቂ፣ ስንት ምሁር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(6) ከየካቲት አብዮት እስከ ደርግ መፍረስ ስንት ብርቅዬ የኢትዮጵያ ወጣት፣ ልሂቅ፣ ምሁር፣ መሪ ሞተ፣ ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(7) ከ1975 እስከ ዛሬ 2022 በትግሬ በቀጠለው አላማ ቢስ ጦርነት ስንት ወጣት፣ ወንድ ሴት፣ ምሁር፣ ጨዋ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(8) በባድመ ጦርነት ስንት ሰው ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(9) የትግሬ የዘር አገዛዝ ስልጣን ከያዘበት 1990 እስከ ዛሬ 2022 ድረስ በመላ ኢትዮጵያ በጎሳ፣ በክልል፣ በዘር፣ በቋንቋ ሳቢያ ስንት ሚሊዮን ሕዝብ ተፈናቀለ፣ ተሰደደ፣ ተበተነ፣ ደሀየ፣ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(10) ከ1960ው የመንግስቱ ነዋይ መፈንቅል ጀምሮ እስከ አሁኑ 2022 ቅጽበት ድረስ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ተሰደደ፣ በረሃ በላው፣ ዉሃ በላው፣ በሽፍታ ተገደለ፣ አካሉ ተሸጠ፣ ስንት ወጣት ሴት በስደር ተደፈረች፣ ሞተት፣ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

(11) ከ1960 እስከ ዛሬ 2022 ድረስ ኢትዮጵያ ስንት መቶ ሺ ምናልባት ሚሊዮን የተማረ፣ የሰለጠነ የሰው ሃይሏ ወደ ውጭ ፈልሶ በአንጎል ሽሽት (ብሬይን ድሬይን) ተበላ? ያ ሁሉ እውቀትና ክህሎት ኢትዮጵያ ላለፉት 60 አመት ተጠቅማ ቢሆን ዛሬ ምን እንደርስ ነበር?

እነዚህና መሰል እንቅልፍ ነሺ ጥያቂዎችን የማያነሳ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ምሁር ገና የሪያሊቲ ንቃተ ህሊና ደረሰ ለማለት አይቻልም!

መልካም ገና ለኢትዮጵያ! ብርሃን ይሁን !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 11 Jan 2022, 02:01

Selam/
በትክክል አንድ የታሪክ ተማሪ ወይም ተመራማሪ እነዚህ 11 የታሪክ ኩነቶችን በትንሹም ቢሆን አጥንቶ...
(1) የሞተው ሰው ቁጥር
(2) የቆሰለው ሰው ቁጥር
(3) በሰው መሞትና መቁሰል የተጎዱት ቤተሰቦች ቁጥር
(4) የወደመው የሰው ሃይል ልክ
(5) የወደመው የእውቀት መጠን
(6) የወደመው የአዋቂዎች፣ ምሁራን፣ጥበበኞች ልምድ መጠን በአመታት ቢለካ (measured in years of experience)
(7) እነዚህን ጦርነቶች ላይ የወደመው ግዜ እድገት ላይ ባለመዋሉ የጠፋው እድል (opportunity cost)
(8) እነዚህ ጦርነቶች እና ውደመቶች ተከትሎ የተከሰተው ድህነት፣ በሽታ፣ የሳይኮሎጂ ቀውስ፣ሌሎች የተከፈሉ እዳዎች
እና ሌሎችም እንደ ስዕል የሚያሳይ ጥናት መደረግ ይኖርበታል ። ይህ እስካልሆነ ድረስ ሕዝባችንም በጭለማ ውስጥ ይኖራል ፣ ከታሪካችንም ምንም ነገር ሳንማር ያንኑ ስህተት ስንደግም እነኖራለን !

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ4ቱ ኢትዮጵያ ትውልዶች ውህደትና ለ50 አመታት በብሄር ጥያቄ የወደመው ሕዝብና ስልጣኔ !

Post by Horus » 14 Jan 2022, 12:29

ኢትዮጵያ ችግሯን ፈትታ ሰላም የምታገኘው ጎሳ ከሚባለው የንዑስ ከበርቴ የዉሸት እግዚአብሄር አምላኪነት ስትላቀቅ ብቻ ነው ! በቃ!!

Post Reply