Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7992
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by Wedi » 25 Nov 2021, 00:18

እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?
:shock: :shock:
Please wait, video is loading...

Educator
Member
Posts: 2004
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by Educator » 25 Nov 2021, 01:39

I believe she is Tigrian. But if she happened to be Amhara, then she must be one of the Hodam Amharas that include Agegnew Teshager, Demeke Mekonen and Degu Andargachew who served woyane with the highest level of loyalty.
Wedi wrote:
25 Nov 2021, 00:18
እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?
:shock: :shock:
Please wait, video is loading...

Wedi
Member+
Posts: 7992
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by Wedi » 25 Nov 2021, 02:16

Educator wrote:
25 Nov 2021, 01:39
I believe she is Tigrian. But if she happened to be Amhara, then she must be one of the Hodam Amharas that include Agegnew Teshager, Demeke Mekonen and Degu Andargachew who served woyane with the highest level of loyalty.
Wedi wrote:
25 Nov 2021, 00:18
እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?
:shock: :shock:
Please wait, video is loading...
Defiantly she is Agame. If she was half Amhara and Half Wolyaita as she claimed to be, their shouldn't be more unitarist than her than being tribalist.
I say this because most if not not all persons who are from mixed ethnics have big problem to choose either of their parents side. For them to choose either of their parents ethnics is like dividing their body parts into two equal halves and denying half of your DNA.

ethioscience
Member
Posts: 3897
Joined: 01 Nov 2019, 17:37

Re: እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by ethioscience » 25 Nov 2021, 02:27

ኢሌኒ ባለፈው 27 አመት ከወያኔ ጋር በጥቅም ከተሳሰሩ ዘራቸው ሆዳቸው የሆኑ ሰዎች ምሳሌ ነች፥፥ ኢሌኒና ለጥቅም ሲሉ ወገኖቻቸውን የሚሸጡ የወያኔ ፍርፍራፊ ተጠቃሚዎች እንደ ኢሌኒ መድረክ ላይ ወጥተው ባይናገሩትም የሚናፍቁት የወያኔን ወደ ስልጣን መመለስ ነው:: ዘር የማያውቁ ሆዳቸው ዘራቸው የሆኑ የስው ዝቃጮች ናቸው:: ለዚህ ደግሞ በተገኘው አጋጣሚ የገዛ ወገኖቻቸውን የሚጎዳ ነገር ከማድርግ የማይመለሱ የቀን ጅቦች ናቸው:: ነገ ደግሞ ልደቱ ፣ ሀብታሙ ፣ ኤርምያስ ከብርሀነ መስቀል ስር ቢገኙ ምንም አያስደንቅም
Last edited by ethioscience on 25 Nov 2021, 02:55, edited 3 times in total.

Wedi
Member+
Posts: 7992
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by Wedi » 25 Nov 2021, 02:28

Educator wrote:
25 Nov 2021, 01:39
I believe she is Tigrian. But if she happened to be Amhara, then she must be one of the Hodam Amharas that include Agegnew Teshager, Demeke Mekonen and Degu Andargachew who served woyane with the highest level of loyalty.

The facts are coming out!! Fitsum Berhane, younger brother of Daniel Berhanie, once wrote this fact about Agame Elenei Geberhmedin

Last edited by Wedi on 25 Nov 2021, 03:00, edited 1 time in total.

Educator
Member
Posts: 2004
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by Educator » 25 Nov 2021, 02:58

She must be pure Tigrian. She wouldn't be trusted to commit the worst crime against Ethiopian farmers if she wasn't one of them. I am sure Azeb Mesfin is now claiming to be wolkite Amhara after living born again Tigre for her entire life.

You know Eleni sold each commodity trading license for three million Birr for selected TPLFist leaving the farmers at the mercy of greedy traders.
Wedi wrote:
25 Nov 2021, 02:28
Educator wrote:
25 Nov 2021, 01:39
I believe she is Tigrian. But if she happened to be Amhara, then she must be one of the Hodam Amharas that include Agegnew Teshager, Demeke Mekonen and Degu Andargachew who served woyane with the highest level of loyalty.

The facts are coming out!! Fitsum Berhane, younger brother of Daniel Berhanie, once wrote this fact about Agame Elenei Geberhmedin once wrote


Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by Horus » 25 Nov 2021, 03:00

ይህቺ ድብቅ ኮክሮች ባንዳ ሁለተኛ የኢትዮጵያ አፈር እንዳትነካ መታገድ አለባት ።

Wedi
Member+
Posts: 7992
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by Wedi » 25 Nov 2021, 03:38


ካሳ አንበሳው

እሌኒ ገ/መድህን (reposted for the fourth time)
------------------------------------------------
መግቢያ፦ ይህን ጽሑፍ ከዚህ በፊት ሶስቴ ለጥፌዋለሁ (18 March 2020፣ 20 May 2018 እና 17 November 2018)፤ ለውጥ መጥቷል፣ መንግስት ተቀይሯል ብዬ የሀገርቷ ኢኮኖሚ ላይ አሻጥር የፈጸሙ ሰዎች እንዲጠየቁ ጥቆማ መስጠቴ ነበር፤ መሪው አብይ አህመድ ሆነና ጩህቴ የቁራ ጩህት ሁኖ ቀረ፤ ይህቺ ሴት “የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ” ሆነችና አብይን ልትወቅስ ወደ ሾሻል ሚዲያ ብቅ ብላ ህዝቡን ስታንጫጫ ለ3ተኛ ጊዜ ለመለጠፍ ወደድኩ፤ ዛሬ መንግስት ግልበጣ ማሴሯ ይፋ ሲሆን ለአራተኛ ጊዜ መለጠፌ ነው፣

ይህች ሴት ከምዕራቡ ሀገር ሰላዬችና ከወያኔው አምባሳደር ብርሀነ ገ/ክርስቶስ ጋር ስለ መፈንቅለ መንግስትና የሽግግም መንግስት ስትዶልት የሚያሳይ ቪዲዬ ዛሬ Twitter ላይ ተመለክትኩ፣ ከስር ተራ ቁጥር 5 ላይ የተሰጠውን ማስፈንጠሪያ ተከትለው የምትለውን ይስሙ፣ "ትግሬም ሆነ ኦሮሞ አይደለሁም፣ ለምን ቤቴ ተፈተሻ" ብላ መርዘኛ አስተያየት መስጠቷም ተሰምቷል፣

አብይ አህመድ ከአርቲስቶችና ከሰባኪ ወንጌላን ጋር በጥምረት፣ በናትናኤል፣ ሙክታሮቪች፣ ስዩም ተሾመ አይነት ሀባብ ራስ አሸብሻቢነት የሚመራውን መንግስት አምርሬ የምጠላው እንዲሁ አይደለም፣ basic sophistication የሌለው ይህ ቀትረ ቀላል መንግስት ሀገር እዳያሳጣን እሰጋለሁ፣

ስለ እሌኒ ገ/መድህንና ዘመዴነህ ንጋቱ ጥቆማ የሰጠሁት ወያኔ መራሹ መንግስት ሞት ዋዜማ ላይ ነበር፣ በአይነ ቁራኛ እንዲጠበቁ፣ ካልሆነም እንዲታፈኑ፣ ከፍ ካለም እንዲያሰናብቷቸው የፈለኩት ከወያኔ ጋር ሁነው ለፈፀሙት ወንጀል ሳይሆን ሊፈጥሩት የሚችሉት የኢኮኖሚ አሻጥር (sabotage) ለውጡን በአፍጢሙ እንደሚደፋው ስለገባኝ ነው፣ ደግሞም አቅሙና መንገዱ አላቸው፣

ለማንኛውም ንባቡ የሚከተለው ነው
___________________________________________________
ዜጎችን በማራቆት የህወሓትን የኢኮኖሚ ጡንቻ ካፈረጠሙ ሰዎች መካከል ዘመዴነህ ንጋቱን እና እሌኒ ገ/መድህንን የሚስተካከል አይገኝም፤ የኢትዮጵያን ገጸ-ምድር እና ከርሰ-ምድር ዶላር መክፈል ለሚችል ለውጭ ዜጋ አሻሽጦ ሰለከበረው፣ የወያኔ ባለስልጣናትን የገንዘብ ባህር ውስጥ ስለነከረው፣ ዜጋውን የደም እንባ ስላስለቀሰው ዘመዴነህ ንጋቱ ከዚህ ቀደም የተወሰነ ብያለው፤ ዛሬ የእሌኒ ገ/መድህንን ሸፍጥ በጥቂቱ ልንገራችሁ::

ስሟ በብዛት የሚነሳው የኢትዮጵያን ምርት ገበያ ድርጅት (ECX) ጋር ተያይዞ ነው፤ ሙሉ ስሟ እሌኔ ዘውዱ ገ/መድህን ይባላል፤ የተወለደችው አዲስ አበባ ሲሆን ዜግነት ከሲዊዘርላንድ ወስዳለች፤ በስታንፎርድ፣ በሚችጋን እና በኮርኔል ዩኒሸርስቲዎች ትምህርቷን ተከታትላለች፤ [don't let her qualifications fool you; keep on reading]፤ ኢትዮጵያ ከመግባቷ በፊት ለአለም ባንክ ሰርታለች፤ ወደ ሀገር ቤት ያመጣትን ጉዳይ ስትገልጽ <<የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት መልክ እንዳሲዝ ከጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ጥሪ ደረሰኝ>> ትላለች፤ ጥሪውን ተቀብላ ጨርቄን ማቄን ሳትል ወደ አዲስ አበባ አቀናች፤ ጠቅላይ ሚንስቴሩ ጽ/ቤት አንድ ቢሮ ተሰጥቷት ስራዋን ጀመረች፤ የኢትዮጵያን ምርት ገበያ ድርጅት (ECX) ተብሎ የሚጠራው ድርጅት በዚህ መልክ ተጸነሰ፤ እሌኒ እና መለስ ቢሮ ዘግተው የጸነሱት ይህ ድርጅት የዛሬ 12 ዓመት በአዋጅ ቁጥር 550/2000 ተወለደ፤

ይህ ድርጅት ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ (Macro Economic Significance) እንደሌለው በተለያዩ ምሁራን ተነግሯል፤ ጊዜ ያለው ከስር በተራ ቁጥር አንድ ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተከትሎ ፕሮፌሰር ሰይድ ሀሰን “The dangerous hype behind Ethiopian Commodity Exchange” በሚል ርዕስ ያተሙትን ጽሑፍ ያንብብ፤ በአጭሩ እሌኒ የገነባችሁ መጋዘንና የዘረፋ መዋቅር ነው፤ ይህን ገለጥለጥ አድርገን እንመልከት፤

የECX "የክርስትና" ተግባር በመላ ኢትዮጵያ የሚመረቱትን የቡና፣ ጥራጥሬ እና የቅባት እህሎችን ለውጭ ገበያ አቅራቢዎች ማጫረት ነው፤ በመጀመሪያ የቡና፣ ጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ተሰብስበው ECX መጋዘን ይገባሉ፤ በመቀጠልም የጥራት ደራጃ ይወጣላቸዋል፤ በመጨረሻም የመነሻ ዋጋ ይሰጣቸውና የድርጅቱ አባል የሆኑ ላኪዎች እንዲጫረቱ ይደረጋል፤ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ላኪ አሸንፏል ተብሎ ጨረታው ይዘጋል፤ የዚህ ድርጅት አባል እና ተጫራቾች የህወሓት እና የህወሓት አጋፋሪዎች መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፤ በብሉንበርግ (bloomberg) ዘገባ መሰረት የኢትዮጵያን የብና እና የቅባት እህሎች በዋነኝነት ለውጭ ገበያ እያቀረበ ያለው የኢፈርቱ ጉና ትሬዲንግ ነው፤ በአጭሩ ECX የጉና መጋዘን ነው ብንል ከእውነታው አንርቅም፤ የሀገሪቱን ጠቅላላ የውጭ ንግድ በዚህ መልኩ በአንድ እዝ አስገብታ ስታበቃ ወያኔን እነሆ በረከት አለችው፤ ECX ምን ያህል በሙስና የነቀዘ መሆኑን ለመረዳት ከስር በተራ ቁጥር 2 ላይ የተሰጠውን ማስፈንጠሪያ ተከትለው ያንቡ::

የይስሙላው ጨረታ ሳያያቸው የውሃ ሽታ የሚሆኑ ምርቶች ቁጥር ስፍር የላቸውም፤ የዛሬ 8 ዓመት ገደማ 10 ሺህ ቶን (10 ሚሊየን ኪሎ) ቡና ከECX መጋዘን ጠፋ ተባለ፤ ምጥ ይግባ ስምጥ አልታወቀም፤ ይህ ያበገናቸው ውስጥ አዋቂዎች ጉዳዩን ለግል ጋዜጦች ሹክ አሉ፤ በአለም አቀፍ ደረጃም መነጋገሪያ ሆነ፤ ይህን ጊዜ መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን ብቅ ብሎ <<ያለፈው አልፏል ከንግዲህ መደገም የለበትም>> ብሎ ፋይሉን ዘጋው፤ ከስር በተራ ቁጥር 3 ያለውን ማስፈንጠሪያ ተከትለው የመለስን መልስ ይመልከቱ::

የዛሬ አመት ደግሞ 19 ሺህ ቶን (19 ሚሊየን ኪሎ) ቡና ከእሌኒ መጋዘን እንደጉም ተኖ ጠፋ ተባለ፤ ይህን አስመልክቶ አዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰራውን ሪፖርት ከስር በተራ ቁጥር 4 ያለውን ማስፈንጠሪያ ተከትለው ያንቡ፤ ከሁሉ የሚገርመው ለይስሙላ እንኳን ህግ ፊት የቀረበ ሰው አለመኖሩ ነው፤ እንግዲህ እነዚህ ለሚድያ የበቁ ዘረፋዋች ናቸው፤ የወያኔ መንግስት ሲገረሰስ የሚጋለጡ ብዙ ዘረፋዎ እና ምዝበራዎች መኖራቸው አይጠረጠርም::

ለማንኛውም የወያኔ መንግስት ወደ መቃብር ሲወርድ ካቴን ከሚጠልቅላቸው ውስጥ እሌኒ ገ/መድህን ከፊት መስመር ትገኛለች፤ ይህ እንደሚመጣ ስለሚያውቁ እሌኒም ሆነች ዘመዴነህ የውጭ ዜግነታቸውን ሳይመልሱ አድፍጠው እየጠበቁ ነው፤
-------------------------------------------------------
እሌኒ ዛሬ ምን እየሰራች ነው?

ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ “ዛሬም ደም እየመጠጠች ነው” የሚል ነው፤ ዛሬ ደግሞ “BlueMoon” ተብሎ የሚጠራ shady business ከፍታለች፤ ግብረ ሰናይ ድርጅት (civil organization) ይሁን የግል ኩባን የሚታወቅ ነገር የለም፤ የግብርና ንግድ (agribusiness) ላይ ነው የምሰራው ትላለች፤ በዚህ ዘርፍ የሚታይና የሚዳሰስ ነገር ግን አታሳይም፤ የድርጅቱ ድረ ገጽ ላይ የሚታየው የሚከራዩ የስብሰባ አዳራሾች ከነ ዋጋቸው ነው፤

ከስር ፎቶው ላይ እንደሚታየው አጋሮቼ የምትላቸው ግዙፍ የምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ናቸው፤ ሌሎቹን እንተዋቸውና Save the Children የግብርና ገበያ ውስጥ ምን ይዶለዋል?? የከፈተችው የምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው እንዳንል ህዝቡን ስትረዳ አይቻለው የሚል ተፈልጎ አልተገኝም፤ ቁጥጥር የሚያደርግ የመንግስት አካል የለምና እሌኒ እንዳሻት እየሆነች ነው፤ በዚህ ሁሉ ውስጥ አንድ ነገር በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፤ ከአለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችና ኢንባሲዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ስም በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር እየሰበሰበች እንደሆነ በልበ ሙሉነት መናገር እችላለሁ፤

(update:- "BlueMoon" የሚሰኝው የእሌኒ ድርጅት የሲአይኤ ድብቅ ፅህፈት ቤት መሆኑ አያጠራጥርም፣ ወትሮም ግራ የሚያጋባ አወቃቀርና ሽርክና የያዘ ድርጅት ነው)

በመጨረሻም:-

እሌኒ አብይን ጎሸም ማድረጓ ሊገርመን አይገባም፤ ወደ ፊት በአይጋ ፎረም ወይም በሌላ ሚዲያ ስራዓቱን የሚያጠለሽ ጽሑፍ ማውጣቷ አይቀርም፤ ይህ ደግሞ የአብይ መንግስት ወደ ቀልቡ ተመልሶ የበላሽውን ትፊ፣ በወንጀልሽ ተቀጭበት ያለ ጊዜ የታሰርኩት ሀሳቤን በመግለጼ ነው ለማለት ይጠቅማታል፤ [በነገራችን ላይ በወያኔ ዘመን በተለይ ዲያስፖራውን የሚወቅጥ ጽሑፍ አይጋ ፎረም ላይ ታወጣ ነበር]



Please wait, video is loading...

Wedi
Member+
Posts: 7992
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን!!! እውን አማራ ናት?

Post by Wedi » 25 Nov 2021, 04:07

The case of alleged fraud and corruption at Ethiopia Commodity Exchange

https://ecadforum.com/2012/03/20/the-ca ... -exchange/

Post Reply