የቢዘኑ መንፈስ [ሰሞንኛው ግርድፍ ኤርትራዊ ግጥም]
የኤርትራ ደጀን ያባሃኒ መንፈስ፣
የኤርትራ ግርማ የአዳሉ መንፈስ፣
የኤርትራ ምሽግ የደንደኑ መንፈስ፣
የኤርትራ ዋልታ የቢዘኑ መንፈስ፣
ያገሬን ጠላቶች ሚደመስስ፣
ያገሬን ልጆች ልብ፡ ሚያረሰርስ፣
ማነው የምትሉ፡ አንዱ ነው ፍሊጶስ!
የኤርትራ አንበሳ የአሶሳው ንጉስ፣
ተወልዶ ያደገው በውጊያ ቁርቁስ፣
ሃብት እንዳካበተ እንዳመለከ ቁስ፣
ስሙን ለማጠልሸት ማነው ሚያለቃቅስ?
ይልቅስ ይልቅስ ይልቅስ ይልቅስ፣
ጉድፎቻችሁን አጥሩ ያላንዳች መቅለስለስ፣
ይቺ ኣጭር ግጥም ነች የኤርትራችን መልስ።
ኤርትራ እንደሆነች ልጆቿን ታውቃለች፣
ሃገሬ እንደሆነች ሸረኛን ታውቃለች፣
ለዛም ነው መንና ዓለምን የተወች፣
አባሃኒ ደንደን ቢዘን የሰፈረች፣
ጠቀራና ሶይራ አዳል የመሸገች።
ብዙነው ዓይነቱ ሰው ሲባል ጀነራል፣
የፍሊጶስ ግና እጂጉን ይለያል፣
ለኤርትራ ሲባል መች ህይወቱን ሳስቷል፣
የኤርትራን ጠላቶች ባይኖቹ ያደባያል፣
የኤርትራ ህዝብም ከሱ ጋር ዘብ ቆሟል፣
ግራም ነፈሰ ቀኝ ጁንታ ይቀበራል፣
ትናንት ዛሬም ነገም እውነት ያሸንፋል።
-
- Member
- Posts: 3044
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Re: የቢዘኑ መንፈስ . . . [ሰሞንኛው ግርድፍ ኤርትራዊ ግጥም]
ሃገሬ ኤርትራ ልትኮሪ ይገባሻል፣
ዓለም አናጋሪ ጀነራል ወልደሻል።
ጠላትሽን ሁሉ ዘርሮ ሚያደባይ፣
ፍሊጶሰ-ቢዘን የሃገሩ አገልጋይ።
ጦርነት ሳይንስ ነው ቢባልም አስሬ፣
ይልቅስ ጥበብ ነው በኤርትራ አገሬ፣
አናምንም ካላችሁ ይሀው ምስክሬ፣
ወራሪን ዘራሪ የጦሩ ገበሬ፣
ጥንቁቁ ጀነራል ፊሊጶስ ‘ኣጅሬ’!
ዓለም አናጋሪ ጀነራል ወልደሻል።
ጠላትሽን ሁሉ ዘርሮ ሚያደባይ፣
ፍሊጶሰ-ቢዘን የሃገሩ አገልጋይ።
ጦርነት ሳይንስ ነው ቢባልም አስሬ፣
ይልቅስ ጥበብ ነው በኤርትራ አገሬ፣
አናምንም ካላችሁ ይሀው ምስክሬ፣
ወራሪን ዘራሪ የጦሩ ገበሬ፣
ጥንቁቁ ጀነራል ፊሊጶስ ‘ኣጅሬ’!