Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Horus » 22 Aug 2021, 12:50

በመላ ኢትዮጵያ የጉራጌ ሕዝብ የሚከፍለው ታክስና በፌዴራልና በደቡብ ክልል የሚደርስበትን ግፍ ስሙ !

eden
Member+
Posts: 9269
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by eden » 22 Aug 2021, 13:20

በየቅዬው ስንት የሲቪል እና ታጣቂ ህይወት እንደዋዛ እየጠፋ፣ መላው የአገር ኢኮኖሚ ተቃጥሎ እየተንቦገቦገ ባለበት ግዜ፣ ስለሳንቲም ታነሳለህ?!

With all due respect, ይህ ከይሲ ሃሳብ ነው። ማለት፣ ለሁሉም ግዜ አለው።

ምነው ትንሽነትን የሙጥኝ አልክሳ?

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Horus » 22 Aug 2021, 15:02

ኤደን
የትግሬ ልሂቃን ባህላቸው መዋጋት ስለሆነ አለም ሁሉ ከነሱ ድራማ ጋር እየደነሰ፣ የነሱ ሆስቴጅ አይደለልም ። ያ ደሞ የነሱ ምርጫ ነው። ልብ በል ይትግሬ ሽፍታ ይህን ሁሉ በከንቱ አቧራ እያስነሳ ባለበት ግዜ የቀረው የኢትዮጵያ ስራና ህይወት እንደ ድሮው እየተካሄደ ነው ። የኢትዮጵያ ፓርላማ የ2014 ባጀት እያደረገ ነው ። ያን ነው ፖስት ይደረት ። የትግሬ ጦርነት ቀጠለም፣ አቆመ አንድ ትንሽ የግዜው ግርግር ነው ። ኢትዮጵያ ሙሉ ህይወቷን እየኖረች ነው፣ የዚያ አንዱ ክፍል ባጀት ነው ። ዝሮ ዞሮ ይህ ሁሉ ድራማና ሆያ ሆዬ የሚዘፈነው ከስልጣን፣ ለገንዘብ (ሃብትና መሬት፣ ለዝና እና ለመከበር፣ አንቱ ለመባል ነው ፤ ማለትም ስልጣን ይዞ ባጀት ለመዝረፍ ነው !! ኬር !

eden
Member+
Posts: 9269
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by eden » 22 Aug 2021, 15:56

Horus wrote:
22 Aug 2021, 15:02
የቀረው የኢትዮጵያ ስራና ህይወት እንደ ድሮው እየተካሄደ ነው ።
የቀረው ስትል? አንተ የምጣህበት ሰፈር? lol

ለመሆኑ ጦርነቱ ያልደረሰበት ህዝብ አለ?

አንተን ብሆን ዝም እል ነበር። ባወራህ ቁጥር፣ ካካ አመለካከት እንደያዝክ ያሳብቅብሃል። እስቲ ዝምታ ሞክር?

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Horus » 22 Aug 2021, 16:07

ኤደን
ደግሜ ልንገርህ በአንድ አገር ውስጥ በአንድ ግዜ ገበሬ ያርሳል፣ ወታደር ይዋጋል፣ እናት ትወልዳለች፣ ተማሪ ይማራ፣ ሳይንቲስት ይፈለስፋል፣ ነጋዴ ይነግዳል! ይህ ነው የማሀበረ ሰብ ዲቪሽን ኦፍ ሌበር ! አንድ ሽፍታ ሁከትና ድራማ ባስነሳ ቁጥር ሙሉ ማህበረ ሰብ ሕይወቱን ያቆማል የሚሉ ለሽፍታ አሸባሪዎች መለኮታዊ ሃይል የሚሰጡ ሞኞች ናቸው ። ትግሬ ፈረንጅ ይቀልበዋል፣ የቀረው ሕዝቦ ሰርቶ ራሱን መቀለብ አለበት። ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የትግሬ ጦርነት እስፔክታተርስ አይደሉም ፣ የራሳቸው ህይወት አላቸው ። ደሞ ደጋግሜ ልንገርህ!! የዘር ፖለቲካ እስካለ ድረስ ይህ ጦረነት አያበቃም፣ አይቆምም፣ ተዋጊዎችና ቦታ ይለውጣል እንጂ ! ይህን አትርሳ !!

eden
Member+
Posts: 9269
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by eden » 22 Aug 2021, 16:25

አሁን'ኮ ጦርነቱ አንድ ጥግ ቦታ እየተካሄደ ያለ አስመሰልከው። ጦርነቱ እየጠበበ የመጣም አስመሰልከው። እውነታው ግን በተቃራኒው ነው። ብዙ የአገሪቱ ክፍሎች ተማሪ፣ ነጋዴና ገበሬ ከስራው እንደተፈናቀለ ግልፅ ነው። እየሰፋና እየተባባሰም ነው።

ምነው ከእውነት ጋር ለመፋታት ምለሃል እንዴ?

ለመሆኑ፣ የዘር ፖለቲካ አይበጅም ብለህ ማሳመን አለመቻልህ ያንተና መሰሎችህ ድክመት አይደለም? ነው ሰው የማይበጀውን ይፈልጋል ብለህ ታምናለህ? ሰው ለማይበጀው ነገር ጦርነት ይሄዳል?

ሌላውን ስትራገም ሳይሆን ራስህን ስትመረምር ነው ወደ መፍትሄ የምትዳረሰው። መራገጡን ከተውክ፣ ሌላውም ራሱን እንዲመረምር እድል አገኘ ማለት ነው። ዝም ብለህ የድርቅናና የድንቁርና የአብቹን የጦርነት መንገድ አትከተል።
Last edited by eden on 22 Aug 2021, 16:40, edited 1 time in total.

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9924
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by DefendTheTruth » 22 Aug 2021, 16:36

Horus wrote:
22 Aug 2021, 15:02
ኤደን
የትግሬ ልሂቃን ባህላቸው መዋጋት ስለሆነ አለም ሁሉ ከነሱ ድራማ ጋር እየደነሰ፣ የነሱ ሆስቴጅ አይደለልም ። ያ ደሞ የነሱ ምርጫ ነው። ልብ በል ይትግሬ ሽፍታ ይህን ሁሉ በከንቱ አቧራ እያስነሳ ባለበት ግዜ የቀረው የኢትዮጵያ ስራና ህይወት እንደ ድሮው እየተካሄደ ነው ። የኢትዮጵያ ፓርላማ የ2014 ባጀት እያደረገ ነው ። ያን ነው ፖስት ይደረት ። የትግሬ ጦርነት ቀጠለም፣ አቆመ አንድ ትንሽ የግዜው ግርግር ነው ። ኢትዮጵያ ሙሉ ህይወቷን እየኖረች ነው፣ የዚያ አንዱ ክፍል ባጀት ነው ። ዝሮ ዞሮ ይህ ሁሉ ድራማና ሆያ ሆዬ የሚዘፈነው ከስልጣን፣ ለገንዘብ (ሃብትና መሬት፣ ለዝና እና ለመከበር፣ አንቱ ለመባል ነው ፤ ማለትም ስልጣን ይዞ ባጀት ለመዝረፍ ነው !! ኬር !
Horus,

I don't condone some parts get disadvantaged in the federal arrangement of the country, assuming this is the case. The presenter conveniently tries to present just the income side, the inflow of budgetary allocation without even mentioning about the share of the contribution of the Guraghe Zone in comparison to that of the Sidama Zone or currently Kilil for the federal incomes, which will in turn back to the kilils themselves in the form of budgets. Why is the presenter hiding this part of the story? Something to hide here?

The other flaw in your logical thinking is your claim that the war takes place in the nothern part of the country. Don't kid me please.

A war doesn't happen in a vacum, it is a costly business, with a lot of costly prices, materially and in human lives. Every part of Ethiopia is affected be it today or tomorrow, someone has to bear the cost being incurred on us, as a country. Resources have to be diverted from other vital needs of the communities, like health care, schooling, services of different forms, development initiatives. I just hope the impact will not affect GERD, which would be a very debilitating consequence of this war inflicted on the poor man of Ethiopia, by a cancer that grow among us.

So, your claim "ኢትዮጵያ ሙሉ ህይወቷን እየኖረች ነው" just shows how much you are removed from the reality on the ground.

Ethiopia is bleeding in many different forms, materially and more importantly also in terms of human lives.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Horus » 22 Aug 2021, 18:39

ኤደን
Ethiopia has 120 million people. The Ethiopian state might need 1 million man army to keep local bandits in check. That is called the State< Law, & Order. So, Ethiopia has people whose job is to fight wars. The 119 million people live their lives by doing other things. Ditto. If a Tigray bandits want to live off WFP heat and energy giving biscuits and conduct a permanent war, I say good luck to them. Ethiopia is a fully armed population and one could trick its way into any village any where in Ethiopia and kill any number of peaceful people. Then the bandit will begin to face his own death enmass. War is a double blade sword, it cuts both ways. If you choose to live in peace, you will live and die in peace. If you choose to go around kill, then you will be killed like wise. The choice is yours!

Educator
Member
Posts: 2014
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Educator » 22 Aug 2021, 20:55

300 አማራዎች በአማራነታቸው ምክንያት ተገለውና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት ተቃጥለው አብይ አህመድን ላለማስከፋት ዝምታን መምረጥ የሚደንቅም የሚያሳዝንም ነው::

eden
Member+
Posts: 9269
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by eden » 22 Aug 2021, 21:48

Everything you scribbled on this thread is not new. Your ideas were already in the mind of Mengie and he made no secret but shared the same with
the Ethiopian public numerous times.

Everything you put down here came out of his mouth. Not only did your thoughts came out of his mouth decades early, they were put to practice. Guess what? Those ideas failed to prevail.

By the way, you think of Ethiopians minus Tigrayans as one united entity. That's not realistic. If this was the case, Tigrayans, or any people for that matter, would have surrendered. The reality is All of Ethiopia is divided and even individual nations are divided.

This is what is really going on outside of Mengie programmed mind of yours. I think Derg time radio propaganda has penetrated and shackled you for life. Liberate yourself old man. Be brave and read reality the way it really is.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Horus » 22 Aug 2021, 22:41

ኤደን
አንድ ነገር ልምከርህ! ዛሬ ትግሬ የምትፈልገው ብርሃን ነው፤ ትግሬ የሚፈልገው መዋጋት፣ ላይ ታች፣ ከዚህም ከዚያም ጋር መላከፍ ሳይሆን የምትፈልገው ብርሃን ነው ። የታወቀ ፍላጎት የሌለው ሰው ምንም የማያይ፣ በጭለማ ውስጥ ያለ ሰው ነው፤ በጭለማ የሚመላለስ የትም መሄድ የማይችል መንገድ የሌለው ሰው ነው። 120 ኢትዮጵያዊን በግፍና ሌብነት ለመግዛት ተሞከረና እንደ እምቧይ ካብ ፈረሰ ። ትግሬ ማድረግ የሌለበትን ጸያፍ ነው ያደረገው ። አሁንም ትግሬ ከግዙፍ ስህተቱ አልተማረም። ትግሬ ዉጊያዎች እዚህ እዚያ ለህዜው ሊያሸንፉ ችላሉ፤ ጦርነቱን እስከ አለም ፍጻሜ ሊያሸንፉ አይችሉም። ትግሬ ተገነጠለ አልተገነጠለ ግድ ያለው ሰው የለም። ጸረ ኢትዮጵያ አላማ ቢስ ፣ ግቡ የማይታወቅ የዎያኔ የትግሬን ወጣት ሲያስጨፈጭፍ ይሀው 50 አመት ሊሆነው ነው ። ትግሬ ግን ዛሬም የበሰበሰ መች እንደ በቀለ የማይታወቅ ስንዴ ከምዕራብ ለምኖ ነው የሚኖረው ። ምን ማድረግ እንዳለበት የማያውቅ ግትር ግብዝ የትግሬ ልሂቅ ነው!

Lakeshore
Member
Posts: 2627
Joined: 24 Jul 2018, 09:32

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Lakeshore » 23 Aug 2021, 15:05

ሆሩስ
ሙሉ በሙሉ ባልከው ሃሳብ አስማማለሁ። ትግሬ ሁሉም ቦታ ጦረነት የሆነ ነው ይሚመስላቸው ያኔ ገና ኣዲስ ኣበባ ሲመጡም አንድዚሁ ነው ህዝቡን ሲያዮት ተነስቶ ስራ ይሄዳል መርካቶ ሲሄዱማ ተወው ነጋደው ከቁብም ኣልቆጠራቸው ከዛ ሲኒማ ራስ ጋ ኣንዱ ትግሬ ጠመጃውን ወደላይ ትኮሸው ትራምራም ኣደረገው ከዛ ያካባቢው ስዎች አንድምንም ኣረጋግተው ምንደነው ችግሩ ሲሉት ከኪሱ ኣስራ ሁልት ብር ላፍ ኣድርገውትነው ለካ ሰዉን ሁሉ ሊገደል የተናሳው። ከዛ ኣንዱ ሃጂ ሙሳ ሃያ ብር ኣድረገው ሰጡትና ሀደ ማለቴ ለባውም ለብነቱን ኣያቆምም ትግሬ በዋጋ አና ቢያልቅ ማለቴነ።

ግን ሆሩስ ኣንድ ልጨምረው ይምፈልገው ነገር ባንተ ቶፒክ ላይ ብይጀቱን በተመለከተ በፌዴራልና በደቡብ ክልል የሚደርስበትን ግፍ ስትል በፊት ምን ብዬህ ነበር ጉራጌ በኦርሞ ክልል ወስጥ ነው ጉራጌ ዞነ ብሎ ነገር የለም አና ኦሮሞን ነው መጠየቅ ያለብህ። ያኔ ኦሮሙማ ስራውን አየሰራ ነው ይክልል መስፋፋት ስልህ ኣሁን የጦረነት ጊዜ ነው ኣልክ ኣሁን ደግሞ ጦረነቱ ሰሜን ብቻ ነው ትላለህ አና አርሳህን አይተቃወምክ ነው ያለከው። ያብይ ምንግስት ኣውቆም ይሁን ሳያውቅ ከጦረነቱ ጀርባ ዮርሙማን ኣጀንዳ ነው አያስፈጸመ ያለው። የተኩስ ኣቁሙ ለዚህ ተብሎ ተፎካካሪውን ኣምራን ልማዳከም አና በጦአረነት ሲወጠር የንድዚህ ያለ ይብጀት አና ሌላ ነገሮችን ማስፍጸም ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Horus » 23 Aug 2021, 16:29

Lakeshore,

በኢትዮጵያ ጎሳዎች የስልጣንና የሃብት (መሬት) ትግልና ፉክቻ ላይ የአለኝ አቋም በድንብ የምታውቀው ይምሰለኛል። የዘር ፖሊቲካ እስትራክቸራሊ እስከ ሚለወጥ ማለትም የጎሳ ክልሎች፣ የጎሳ ባጀትና ቢሮ ክፍፍል እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ በህወት የምትኖረው በሃይል ሚዛን መሰረት ነው። ጎሳዎች በተለይ ትላልቆቹ ያለ ማቋረጥ መፎካከራቸው ፣ መፏከታቸው ወደ ፊትም ይቀጥላል ። የጎሳ ሳይኮሎጂ እኔ ከሌላው እሻላለሁ፣ እበልጣለሁ የሚል ስለሆነ። ለምሳሌ አሁን በትግሬ ላይ ያለው የሁሉም ጎሳዎች አንድነት ቅዋሜ አስተውል! ትግሬ እኔ ከሁሉም ጎሳ በላይ ጦር አለኝ ገንዘብ አለኝ ብሎ ተነሳ። ይሀው የሱን ሃይል በዕጥፍ የሚበልጥ አገር አቀፍ ህብረት ተነሳበት ። ነገም የሚሆነው ያ ነው ። እኔ አንድም ቀን ኦሮሞ ስልጣን ፣ ሚሊታሪ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እያካበቱ እንደ ሆነ ክጄ አላቅም ። አማራ የኦሮሞ ተመጣጣኝ ተፎካካሪ ስለሆነ አማራ ኦሮሞን በቅርብ አይነ ቁራኛ መጠበቁ ናቹራልና የሚጠበቅ ነው ። ግን አትርሳ ኦሮሞም አሁን በመንግስት ውስጥ ያለውን ቦታ አቢዩዝ ካደረገ በሱም ላይ አገር አቀፍ አንድነት ይነሳበታል ። ሕዝቡን ማመን አለብህ ። ተራው ሕዝብ ከኛ በላይ የቅራኔዎች ቅደም ተከተል፣ የቱ መጀመሪያ፣ የቱ ቀጥሎ በማለት ያውቃቸዋል ። ትግሬ የ30 አመት ሬኮርድ አለው የማይረባ፤ አላዋቂ ስግብግብና ግፈኛ ሃይል እንደ ሆነ። የዚህ ሃይል መነቀል ፍጹም ተቀዳሚ ብሄራዊ ተግባር ነው ። ነገ በሚዋቀረው የጎሳ መንግስት ማን ምን ያገኛል የሚለው እንደርስበታለን ። ችግር የሚፈታው ተራ በትራና አንድ ባንድ ነው ። አሁን ትግሬን ተመልከት! በምን ሎጂክ ነው ከአማራ፣ ከኦሮሞ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከአፋር ጋር ተዋግቶ በጉልበት አዲስ አበባ ስልጣም የሚመለሰው?! ስለጉራጌ በጀት ግፍ መለስ በጉራጌ ላይ የተከለው ነገር ነው ። ጉራጌ በቁጥር ከትግሬ ለማሳነስ መጀምሪያ ስልጤን አታልሎ ለሁለት ከፈለን። ቀጥሎ ከዱብ ጋር አደባልቆ ታልቁ ጉራጌን ኢትዮጵያን ለዘመንት የገነባው ጉራጌን አንዲት ዞን አድርጎ ያለ ንጽሁ ዉሃ 30 አመት አፈረሰን ። ያ ግፍ ነው ዛሬም ያልተመለሰው ። ግ ን አንድ ነገር ልንገርህ የጎሳ ፖለቲካን ከኢትዮጵያ ምድር ሳናጠፋ አናርፍም ።

Lakeshore
Member
Posts: 2627
Joined: 24 Jul 2018, 09:32

Re: ጉራጌ ላይ የሚፈፀመው የበጀት ሸፍጥ!

Post by Lakeshore » 23 Aug 2021, 18:37

በጣም ትክክል ነህ ( ይሄ ቀልድ ነው ዛሬ ኪኒንዋን ውጠሃል ማለት ነው) ዋናው የችግሩ መሰረቱ የጎሳ ፕሊቲካ ነው። አና ኣንተ አንዳልከው ትግሬ ዋጋውን ካገኘ ብሁዋላ አደገና ወደ ጦረንት ልንገባ ነው ማለት ነው ከኦሮሞ ጁንታ ጋር ካሁኑ ጦረነቱ አይተካሄደ አንድገና የርምት አርምጃ መወሰድ ኣለበት ባይ ነኝ ግን ኣብይ ይሄንን ስያደርግ ኣይታይም በሃሳብ ደረጃ አንኳን። ወይ በኦርሙማዎች አጁ ተጠምዝ ዞዋል ውይም እሱ ራሱ የመጣበት መንገድ ስለሆነ ከዛ መላቀቅ ችግር ሆኖበታል ባይ ነኝ። ለምሳሌ የትግሬን ጦረነት ስናይ እነ ኣሜሪካን ኣማራ ከትግራይ ይውጣ ሲሉ ቀላሉ መንገድ አስከ ጊዜውም ቢሆን በፓራላማ ወልቃይትን አና ሁመራን ያምሃራ ክልል አንዲያስተዳደረው ማድረግ ልክ ላፋር ኣንድ ቀበሌ አንድመለሱት ያማራው ይማይመለሰው ለምንድን ነው ብልህ ብትጠይቅ ኦርሞ ክልል ብዙ ብሃይል የጠቀለላቸው ህዝቦች ኣሉ ለምሳሌ ጉራጌ ኣዘርነት በርበሬ ጁንታው ጉራጌ ኣይደሉም አንዳለው አና አንሱ ጥያቄ ያነሳሉ። ሌላው ደግሞ መከላከያው ከመቀሌ ሲወጣ ካምሃራ ሚሊሺያ ጀርባ ሆኖ ነው ትኩስ ኣቁም ላ ነኝ ያለው ያማላት ማራውን ለግዛጥ ትዋጋ ማንም ኣያግዝ ህም አንደማለት ነው መከላከያ ውስጥ አንደጁንታው ጊዜ ሰባ ፐርቸንቱ ኦሮሙማ ነው። አና ባጠቃላይ ትግሬ አስኪሸነፍ ስንል ሆን በለው አያራዘሙት ነው ምክኛቱም ኦርሚያ ውስጥ ኣይደለም ጦረነቱ የሚል ደካማ ኣስተሳሰብ ኣላቸው ግን ይህዝቡ መነሳት መጣም ነው ትምህርት የሰጣቸው

Post Reply