Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የትግራይ የመከላከያ ሰራዊት ሕዝባዊ ሰራዊት ነው፤ ከዓፋር ከአማራም ሆነ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ወገናዊነት እንጂ፤ እንደ ሕዝብ ጠብ ወይም ጠላትነት የለዉም!

Post by sarcasm » 22 Jul 2021, 05:20

የትግራይ የመከላከያ ሰራዊት ሕዝባዊ ሰራዊት ነው፤ ለትግራይ ሕዝብ ህልውናና ደሕንነት የቆመ ሰራዊት!

የሕዝባዊነቱ መገለጫም፤ ስለ ትግራይ ሕዝብ ህልውናና ደሕንነት ለመስዋእትነት ዝግጁ ሆኖ፤ በተግባር ያረጋገጠ፤ በስነስርዓት የታነፀ ሃላፊነት የሚሰማው ሰራዊት መሆኑ ላይ ነው::

የትግራይ የመከላከያ ሰራዊት ሙሉ ቁመናና ስብዕና፤ ሕዝባዊነት እስከሆነ ድረስ፤ ሕዝብ ከሕዝብ አይለይም:: ከዓፋር ከአማራም ሆነ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ወገናዊነት እንጂ፤ እንደ ሕዝብ ጠብ ወይም ጠላትነት የለዉም! ዋናው አንኳር መገለጫውም ይህ ሕዝባዊነቱ፤ የሕዝብ ወገንተኛነቱና ለሕዝብ የሚሰዋ መሆኑ ላይ ነው::

የትግራይ ሕዝብ ላይ ወረራ ያካሄዱና እጅግ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ ሃይሎችን ግን እያሳደደ፤ ከትግራይም አልፎ በአጎራባች ክልሎች ዘልቆ እየቀጣቸው በመገስገስ ላይ ይገኛል::

በትግራይ ውስጥም ሆነ ከትግራይ ውጭ በሚያካሂዳቸው ወታደራዊ ዘመቻዎች፤ የሰራዊቱ ሕዝባዊነት አንዳችም መዋዠቅ አይታይበትም አይኖረውምም:: ለትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ያለው ተቆርቋሪነትና አሳቢነት፤ ለሌሎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦችም አለው::

ጠቡ ከግፈኛ ገዢዎች፣ የግዛት ተስፋፊ ሕልመኞችና ከባዕዳን ወራሪ አጋሮቻቸው ጋር እንጂ፤ እነዚህ የጦር ወንጀለኞች ከወጡበት ሕዝብ ጋር አይደለም:: እነዚህ የጦር ወንጀለኞች፤ የወጡበትን ብሄር ብሄረሰብና ሕዝቦች ወይም አገር ስለማይወክሉ!

ጠቡ የትግራይ እናቶችንና ህፃናት እህቶቻችንን ካልደፈሩ፤ የትግራይ ወላጆችንና ወጣቶችን ካልጨፈጨፉ፤ ኣብያተክርስትያናትና መስጊዶችን ከአገልጋዮቻቸው ጋር ካላወደሙ፤ የትግራይን መሰረት ልማቶችና የማሕበራዊ ተቋማትን ካላፈረሱ፤ ... ዕንቅልፍ ከማይወስዳቸው ከነአብይ ደመቀ ተመስገንና ጋሻጃግሬዎቻቸው ጋር ነው።
የትግራይ የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብን በጠላትነት ሊፈርጅ አይደለም፤ ከየአቅጣጫው ትግራይን ለመውጋት በመዝመት ላይ ካሉት የክልል ሚሊሽያዎችም ጋር ጠብ የለውም:: ለዚህም ነው በብዙ ሺዎች የአማራና የኦሮሞ ሚሊሽያዎች እንዲበተኑና ወደቀያቸው እንዲመለሱ እየሰራ ያለው!

ከዚህም አልፎ፤ እየተዋጋው ካለው የመከላከያ ሰራዊትም ሆነ የክልሎች ልዩ ሃይሎች ጋር ሳይቀር ጠብ የለውም! ለዚህም ነው በውዴታ ይሁን በግዴታ፤ ወይም በጥቅም ተታሎ የዘመተውንና የተዋጋውን፤ የጠላት ወታደር በሽዎች ማርኮ ተንከባክቦ፤ ወደየመጡበት ክልላቸው በሰላም የሚሸኛቸው::

የትግራይ የመከላከይ ሰራዊት በሚደርስባቸው የዓፋር የአማራና ሌሎች አካባቢዎች ሁሉ እያሳየ ያለው ሕዝባዊነት፤ ከዚህ በፊትም የነበረ ለወደፊቱም የማይቀየር፤ መገለጫው ወጥ ቁመናው ነው! ከአፈጣጠሩ ለሕዝብ ህልውናና ደሕንነት በፅናት የቆመ ሕዝባዊ ሰራዊት ስለሆነ! ጠቡ የሕዝብ ጠላት ከሆኑና የሕዝቦችን ዕልቂት ካዘዙና ካስፈፀሙ ቁንጮ የጦር ወንጀለኞች ጋር ብቻ ነው::


ስለዚህ የትግራይ መከላከያ ሰራዊት በሚደርስባቸው የዓፋር የአማራና የሌሎች ክልሎች አካባቢዎች ሁሉ የሚገኝ ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል፤ ምንም ዓይነት ስጋት ሳይገባው፤ ተረጋግቶ የራሱን የቤተሰቡንና የአካባቢውን ደሕንነት በማስጠበቅ፤ የዕለት ተዕለት ኑሮውን እንዲያስቀጥል ይመከራል!

እነ አብይ ደመቀ ተመስገንና ጋሻጃግሬዎቻቸው፤ ለእነሱ የጥቂቶች ፍላጎት ማርኪያ አገር ለማፍረስ የድሃውን ልጅ ለማስጨረስ እንጂ፤ በቋሚ የተደራጀ የአገራት የመከላከያ ሰራዊት ያላንበረከኩትን የትግራይን የመከላከያ ሰራዊት ግስጋሴ በሚሊሽያና በፖሊስ ሊያስቆሙት እንደማይችሉ በደንብ ያውቁታል! ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ዓላማ የሌለው የጥፋት ሞት ልጆችህን ወገኖችህን አድን!

ትግራይ ትስዕር! ካሳ ሃይለማርያም

https://www.facebook.com/kassa.hailemar ... 1358620473

Tog Wajale E.R.
Member+
Posts: 9893
Joined: 31 Oct 2019, 15:07

Re: የትግራይ የመከላከያ ሰራዊት ሕዝባዊ ሰራዊት ነው፤ ከዓፋር ከአማራም ሆነ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ወገናዊነት እንጂ፤ እንደ ሕዝብ ጠብ ወይም ጠላትነት የለዉም!

Post by Tog Wajale E.R. » 22 Jul 2021, 05:47

Bissbiss Shettattam Agga*me Too Late Now. The Only Way With Dedebit Woorgach Tigrayian Agga*me Is ☆ The Languages Of Destroying Exterminating The Rest Juntas Terrorist ☆ Short Of That, There Will Be No Business Or Relationship With Dedebit Woorgach Tigrayian Agga*me At All.

Post Reply