Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

አቶ አገኘሁ ተሻገር ኣደረጉት ስለተባለው የስልክ ንግግር፤ እሳቸው ወይም ታማኝ በየነ ይሄን ነገር አስተባባሉ ወይ? ጠበቃ አንዱኣለም ቡከቶ ገዳ

Post by sarcasm » 20 Jul 2021, 20:06

አቶ አገኘሁ ተሻገር (የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር) አደረጉት ስለተባለው የስልክ ንግግር ሰማሁ፡፡የራሳቸው ንግግር ሊሆንም ይችላል ወይም ቅንብር ሊሆን ይችላል፡፡ዋናው ነጥቤ እሱ አይደለም፡፡

ግን እሳቸው ወይም የክልሉ ኮሚኒኬሽን ይሄን ነገር አስተባባሉ ወይ?

መልእክቱ የተላለፈለት የተባለው አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነስ ስለዚህ ጉዳይ ምን አለ?

ከዚህ ቀደም ዶ/ር አብይ በድብቅ የተቀረጹት ነው በሚል የወጣውን ድምጽ ለማስተባበል መንግስት የሄደበት ፍጥነት እጅግ አስገራሚ ነበር ፡፡
አሁንስ?


ምናልባት እኔ ያልሰማሁት ማስተባበያ ካለ እስቲ አሳዩኝ፡፡

እራሳቸው ኢንቮልቭድ የሆኑ ሰዎች ማስተባበያ ካልሰጡበት ሌሎች የእነሱን ጉዳይ ለማስተባበል የሚጋጋጡበት ምክንያትስ ምንድን ነው? ባለጉዳዩ ካስተባበለ በኋላ በደጋፊነት ወይም በአጋዥነት መቀጠል ..shouldn’t this be the minimum moral standard on social media?

ለትንሹም ለትልቁም ወደ ሶሻል ሚዲያ የሚሮጡት በለስልጣናትስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ብለዋል?

መረጃ ያላችሁ በመረጃ ፡ሙግት የምትችሉ እና እውቀት ያላችሁ በሙግት ሁለቱም የሌላችሁ በስድብ መሳተፍ ትችላላችሁ!
Please wait, video is loading...