Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Ejersa
Member
Posts: 3141
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ሕወሓት ስልጣን ካጣ በኋላ 'የጸጥታ ኃይል መምሪያ' የሚል ዘርፍ አደራጅቶ ለሽብር ሲንቀሳቀስ ቆይቷል - ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

Post by Ejersa » 10 May 2021, 16:19

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራት (ሕወሓት) በማዕከላዊ መንግስቱ ያለውን ስልጣን ካጣ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል በመሄድ 2011 ዓ.ም 'የጸጥታ ኃይል መምሪያ' የሚል ዘርፍ አድራጅቶ ለሽብር ተግባር ሲዘጋጅ መቆየቱን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገለጸ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ 'ሕወሓት እና ሽኔ' ሽብርተኛ ያስባላቸውን ምክንያትና በአክሱም ከተማ ስለተፈጸመው ግድያ መግለጫ ሰጥቷል።

ባለፈው ሚያዚያ 28 ቀን ሁለቱ ድርጅቶች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት መሰየሙ ይታወቃል።

መግለጫውን የሰጡት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ፍቃዱ ጸጋ ሁለቱ ድርጅቶች ሽብርተኛ ስለተባሉበት ሁኔታ ዛሬ ዝርዝር መግለጫ ሰጥተዋል።

"በዋናነትም ሁለቱ ድርጅቶች ሽብርተኛ የተባሉት ሰላማዊ ሕዝብን ከጥቃት ለመከላከል፣ የሕግ ማስከበር ስራውም እንዲጠናከርና ተባባሪዎቹን ለመቆጣጠር እንዲረዳ ነው" ብለዋል።

ሁለቱ ድርጅቶች በሽብርተኝነት ሕጉ መሰረት ሽብርን ዓላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ፣ ድርጊታቸው የሽብር መገለጫ በመሆኑና የድርጅቶቹ ውሳኔ ሰጪ አካላት ሽብርተኝነትን በመቀበላቸው ነው ይላሉ።

በተለይ ደግሞ ሕወሓት ከስልጣን ሲወገድ ጀምሮ የተለያዩ ችግሮችን ሲፈጥር ቢቆይም ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የተጠናከረ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

"በዚሁ መሰረት የጸጥታ ኃይል መምሪያ የሚል ዘርፍ በማደራጀት፤ መምሪያውንም ከመከላከያ የወጡ መኮንኖች እንዲመሩት አድርጓል" ይላሉ አቶ ፍቃዱ።

ይህንንም በማድረግ ከሚሊሻ ጀምሮ ለሁሉም የጸጥታ አካላት ሰፋፊ ስልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱንም አንስተዋል።

ለአብነትም ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ከ37 ሺህ በላይ ሚሊሻ ማሰልጠኑን ገልጸዋል።

በቀደመው ጊዜ በዓመት ከ500 በላይ ልዩ ኃይል የማያሰለጥነው ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በዓመት 5 ሺህ ልዩ ኃይሎችን ሲያሰለጥን መቆየቱንም ነው ያስታወሱት።

የክልሉን ሕዝብ በጦርነት ለማሳተፍም ከአርሶ አደር እስከ መንግስት ሠራተኛ ሰፋፊ ስልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱንም ነው ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የተናገሩት።

በተጨማሪም ህወሓት ሕገ ወጥ ምርጫ ማድረግ፣ በሦስት ወር ውስጥ የፌዴራል መንግስቱን መቆጣጠር የሚያስችል እቅድ ማውጣትና ግጭቶችን በገንዘብ ሲደገፍ መቆየቱ ተረጋግጧል ብለዋል።

"በዚህም በአፋር፣ በአማራ፣ በጋምቤላና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ግጭቶች እንዲባበሱ ማድረጉና ሌሎች የድርጅቱ ተግባራት በሽብር የሚያሰይሙት ናችው" ነው ያሉት።

ይህ ብቻ ሳይሆን ጥቅምት 19 ቀን 'ቀድሞ ማጥቃት' በሚል ዝግጅት ጀምሮ ጥቅምት 24 የሰሜን እዝ አባላት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የአገር መከላከያ ሠራዊቱን ማዋረዱም ሌለኛው ድርጅቱን ሽብርተኛ ያስባለ ተግባር ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ 'ሸኔ' የተባለው ድርጅትም በምዕራብ ኦሮሚያና በደቡብ ኦሮሚያ 'አባ ቶርቤ' የተባለ ቡድን በማደረጀት የጸጥታ አካላትና አመራሮችን ሲገድል ቆይቷል ብለዋል።

ሸኔ የተባለው ድርጅት ንጹሃን ዜጎችን ከመግደል ባለፈ የመንግስት መዋቅርን የማፍረስ ድርጊት ሲፈጽም ቆይቷል ይላሉ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ።

እሳቸው እንዳሉት ቡድኑ በ2013 ዓ.ም ብቻ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ 463 ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ከነዚህም መካከል 112 ፖሊስ፣ 57 ሚሊሻ እና 18 በተለያዩ ደረጃ ያሉ አመራሮችን ገድሏል።

"በተጨማሪም በአክሱም ከተማ ስለተደረገው ግድያም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሁለት መንገድ ወንጀሉን እየመረመረ ይገኛል" ነው ያሉት።

ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ፍቃዱ በክልሉ በሴቶች መደፈር ጋር ተያይዞም የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ጨምረው ገልዋል።

Abdisa
Member
Posts: 4282
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: ሕወሓት ስልጣን ካጣ በኋላ 'የጸጥታ ኃይል መምሪያ' የሚል ዘርፍ አደራጅቶ ለሽብር ሲንቀሳቀስ ቆይቷል - ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

Post by Abdisa » 10 May 2021, 20:11

The Ethiopian government's 2-month investigation into allegations of atrocities committed against civilians in Tigray is replete with damning details that it debunks a series of false claims made by the terrorist junta and its enablers. The overthrow of the Tigray terrorist junta, and subsequent annihilation of its terrorist leaders and fighters, will go down in Ethiopian history as a dawn of true independence and freedom from outside control. Gone are the days when foreign NGOs, the so-called human rights organization, and the western media, thought Ethiopia was the devil's playground they can impose their will on the people.

Post Reply