Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Abaymado
Member
Posts: 2903
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ያስገኘው ዋና ለውጥ ምንድነው? እንደታሰበው አይደለም

Post by Abaymado » 06 May 2021, 21:33

ይህንን ሥራ በየግዜው እከታተለው ነበር እና ብዙ ጠብቄ ነበር ግን እንዳሰብኩት አይደለም:: ይህ የቢልዮን ብር ፕሮጀክት ነው ለማለት ይከብደኛል::

ሰው የሚቀመጠው ድንጋይ ላይ ነው? ከዛ ሳር አለ ግን ይህ ሳር ወደ ጭቃነት እንዳይቀየር ያስፈራል:: ይህ ከሚሆን ለምን ሲሚንቶ አልሆነም?

ሁለት በጣም የጠበኩት ዛፍ ይተከላል ብዬ ነበር:: ግን ወፍ የለም:: የተተከለው ዛፍ በእንስራ በሚመስል መልኩ የመጡ ናቸው:: አንዳንዶቹም ደርቀዋል:: ይህ በጣም ደባሪ ነው:: ትላልቅ ዛፎች መተከል ነበረባቸው:: ፀሀይ በጣም ኃይለኛ በመሆኑ ማለት ነው:: ዛፍ ያልተተከለበት ምክንያት የመኪና ማቆምያ ምድር ስለተሰራለት ነው::


ይህ ፕሮጀክት ዋና ስራዬ ብሎ ያሰበበት የመኪና ማቆምያ ግንባታ ብቻ ነው:: ይህ የአብዛኛው ሕዝብ ጥያቄ አይደለም:: የመስቀል አደባባይ ጥያቄ ችግር የመኪና ማቆምያ ችግር ሳይሆን ጥርት ያለ ደረጃውን የጠበቀ እና ዛፎች ያሉት ቢሆን ነበር:: በዛ ላይ ሕዝብ የሚያስተናግደው ደረጃዎች ለመኪና ማቆምያ ተብሎ ሳይቀንስ አልቀረም::

መስቀል አደባባይ ዋና ስራው ሚልዮኖችን ማስተናገድ ነው እንጂ አንድ ሺ ለማይሞላ ባለመኪናዎች አይደለም:: ፕሮጀረክቱ የምልዮኞችን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገና ለእይታ የሚያምር መሆን ነበረበት::

እንደእኔ ለወደፊት ፕሮጀክት ሲሰራ በጥልቅ ቢጠና ጥሩ ነው::Post Reply