Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

ELICO - Ethio Leather Industry Plc

Post by temari » 25 Mar 2021, 08:51


Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ELICO - Ethio Leather Industry Plc

Post by Ethoash » 27 Mar 2021, 07:25

እንደለመደው አለፍ አለፍ ብዬ ነው ያየሁት ቪድዬውን ። ግን ይህ ነው አስተያየቴ በሁለተኛው ቪድዬ ላይ ከተመለስ አስተያዬቴ መልካም አለበለዚያም እንደምክር ታይቶ የቆዳ ፋብሪካው ቢያስብበት ባይ ነኝ።

የቆዳ ፋብሪካ መጀመሪያ ቆዳውን ከሕዝቡ መስበስብ አለበት ። አስባስቡ በጣም ማዘመን አለብን ትንሽ ማሽኖች ለነዚህ አስባሳቢዎች ስጥተን ቆዳውን የመጀመሪያውን ታኒግ እንዲያረጉ ማስልጠን ምሽኖችንም ማስተዋወቅ ነው። አንድ የቆዳ ስብሳቢ ምን ምን ቢያረግ ነው ቆዳው ጥራቱ የሚጠበቀው ብሎ መስራት ያስፈልጋል ጨውም አጠቃቀም ቢሰለጥኑ። ወይም እንዳልኩት ትንሽ ማሽን የልብስ ማጠብያ የመስለ ነበር አገር ውስጥ ተስርቶላቸው ጨውንና ቆዳውን ታኒግ ለማረግ ማሽኑን በጠቀሙና ማድረቅያ ክፍል ቢኖራቸው ደግሞ ቆዳው ከመጀመሪያው ጥራቱ የተጠበቀ ይሆናል።

ከዚህ ወረድ ስንል ደግሞ ቆዳው ሲገፈፍ እንዳይቀደድ በቄራ ውስጥ ለብዙ ግዜ የስሩትን ስራተኞች ከነልምዳቸው ይህንን ተግባር እንዲያከናውኑ ማረግ እና በቄራ ስራተኞች የተገፈፈ ቆዳ ጥሩ ዋጋ እንደሚያወጣ ከተደረገ ሁሉም ወደ ቄራ አራጁ ይመጣሉ ማለት ነው። በአሁን ግዜ ኮንዶሚኒዎች ስር የበግ ማረጅያ ቦታ ተስርቶ ለነዚህ በቄራ ለስጠኑ አራጆች ቢስጥ ጥሩ ገቢ የገኛሉ ቆዳውንም ወድያው በጨው አርገው የቆዳውን ጥራት መጠበቅ ይችላሉ ። ስውም በፀሀይ ቆዳ ለመሽጥ አይንከራተትም እዛው ቆዳ ገፋፊው ይገዘዋል ማለት ነው።

ከዚህ ወረድ ካልን ደግሞ በጉ፣ በሬው ፣ በአጠቃላይ እንስሳቱ በሕይወት እያለ ጤናው መጠበቅ አለበት። ብዙ ቆዳን የሚያበላሹ በሽታዎች አሉ ታድያ የቆዳ ፋብሪካችን ሁሉም ቢሆኑ ፩ በመቶ ገብያቸውን ለዥህ የቆዳ ጤንነት ጥበቃ ቢያውሉት ትልቅ እምርታ በቆዳ ምርታችን ላይ ይመጣል ማለት ነው። ነገሩን እናዘምነው ካልን በጉዋ ወይም በሬው ከተወለደበት ጀምሮ እስከሚታረድበት ግዜ የተስጠውን መድሀኒቶች በሙሉ በኮሚፒተር ችፕስ በጆሮው ላይ በሚንጠለጠል ቴክኖለጂ ምዝገባ ማረግ ይቻላል። ይህ ቴክኖለጂ ደግሞ በጣም ርካሽ ነው። ከአንድ ዶላርይ ሁለት ዶላር የሚበልጥ አይመስለኝም ለሁለት አመት ለአምስት አመት አገልግሎት የሚስጥ ስራ ይስጠናል በዚህ ላይ በዙ መረጃዎችን ስለሚስጠን በጎደለ ለሞምላት ይረዳናል ማለት ነው።

ለግዜው ይህ ነው። ስለቆዳ አስባስብ።

ሌላው ደግሞ ድርጅቱ ብልጥ ከሆነ ከጥቃቅን የጫማ ስራተኞች ጋራ ተባብሮ መስራት አለበት ። ለምሳሌ በግል የሚስሩት ብዙ ጫማ ስሪዎች በጣም በጣም ጥራት ያለውና ፋሽንን የተከተለ ዲዛይን አውጥተው ይስራሉ ስለዚህ የቆዳ እንዱስትሩ ምንም ሳይደክም የነዚህን ጫማ ስሪዎች ድዛይን ውስደው ቢስሩ ታላቅ እምርታ ያመጣሉ ባይ ነኝ። ለምን ቢባል አሁን በትንሹም ለማየት እንደቻልኩት የድሮ አንበሳ እና ኮስኮ የሚስሩትን ያረጀ ዲዛይን ይመስላል ጫማው ። የወትድርና ጫማው ብቻ ለፋብሪካ ስራተኞች ሁሉ ማገልገል ይችላል ትንሽ ለውጥ በማድረግ ። ፋሽንም ሊሆን ይችላል ጉርድ የወታደር ጫማ ከተደረገ ብዙ ብዙ ጠቀሚታዎች አሉት ለማለት ነው። ደህና ስንብቱ።

temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Re: ELICO - Ethio Leather Industry Plc

Post by temari » 05 Apr 2021, 14:56


temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Re: ELICO - Ethio Leather Industry Plc

Post by temari » 07 Apr 2021, 15:51


Post Reply