Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11715
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

‹‹ደብረ ብርሃን ዓለም-አቀፍ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የፋይናንስ ኤክስፖ›› ከየካቲት 14-20/2013 ዓ.ም ደብረ ብርሃን፣ ኢትዮጵያ

Post by Noble Amhara » 15 Feb 2021, 00:31

Please wait, video is loading...


Debre Berhan the 2nd Addis Ababa of Abysinnia the rising capital of Amhara region
Last edited by Noble Amhara on 15 Feb 2021, 02:34, edited 4 times in total.

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11715
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: ‹‹ደብረ ብርሃን ዓለም-አቀፍ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የፋይናንስ ኤክስፖ›› ከየካቲት 14-20/2013 ዓ.ም ደብረ ብርሃን፣ ኢትዮጵያ

Post by Noble Amhara » 15 Feb 2021, 00:54





የአቡነ ጴጥሮስ 84ኛ ዓመት የሰማዕትነት መታሰቢያ


የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራን በመቃወምና በማውገዝ ለአገራቸው ነፃነትና ክብር የተሰውት ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ በፋሺስት ኢጣሊያ የተገደሉት ከዛሬ 84 ዓመታት በፊት (ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም) ነበር፡፡

ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ (በልጅነት ስማቸው ኃይለማርያም) የተወለዱት በ1875 ዓ.ም ነው፡፡ የልጃቸውን የእውቀት ብልፅግና ለማየት ጉጉት ያደረባቸው ወላጆቻቸው፣ የልጃቸው ዕድሜ ገና ለትምህርት ሳይደርስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ ለጋ አዕምሯቸውን በእውቀት ያንፁላቸው ዘንድ ባህታዊ ተድላ ለሚባሉ መምህር በአደራ ሰጧቸው፡፡ እርሳቸውም በዚያው ገዳም በጥንታዊው የቤተ-ክርስቲያኗ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በሚያስደንቅ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም የቅኔ ትምህርታቸውን ለማበልፀግ ወደ ጎጃም በመሄድ በዋሸራ የቅኔ ትምህርት ቤት ተማሩ፡፡


በውስጣቸው የሰነቁት የመማር ፍላጎት ኃይልና ብርታት ሆኗቸው፣ እንደቅኔው ሁሉ የዜማውንም ትምህርት በሚገባ ለመማር ከቅኔው አውድማ ጎጃም ወዴዜማው ምድር ጎንደር ተሻገሩ፡፡ በዚያም የዜማን ትምህርት ተከታትለው ጨረሱ፡፡ ገና በልጅነታቸው ከደብረ ሊባኖስ ወደ ጎጃም፤ከጎጃም ወደ ጎንደር የወሰዳቸው የትምህርት መንገድ ወሎ አደረሳቸው፡፡ ቦሩ ሜዳ ከተባለው ስፍራ ላይ ወንበር ዘርግተው የመጽሐፍት ትርጓሜ ትምህርቶችን ማለትም መጽሐፈ ብሉያትን፣ ሀዲሳትን፣ ሊቃውንትንና መነኮሳትን በብቃት አስኬዱ፡፡

በ1900 ዓ.ም ልክ እንደርሳቸው ሁሉ እውቀትንና ጥበብን ፍለጋ የገቡትን ደቀ-መዛሙርት ለማስተማር ወሎ ውስጥ ዐማራ ሳይንት በተባለው ቦታ ወደሚገኘው ምስካበ ቅዱሳን ገዳም በመሄድ ወንበር ዘረጉ፡፡ በዚያም ለዘጠኝ ዓመታት ያህል ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ ደብረሊባኖስ በመሄድ ስርዓተ-ምንኩስናን ፈፀሙ፡፡

በ1910 ዓ.ም ወላይታ ለሚገኘው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም በመምህርነት ተሾሙ፡፡ በዚያም ለስድስት ዓመታ ያህል ካገለገሉ በኋላ በ1916 ዓ.ም ወደ ዝዋይ ተሻግረው የመምህርነት ተግባራቸውን ለሦስት ዓመታት ያህል አከናውነዋል፡፡ በ1919 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርጎ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥት የንጉሰ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የንስሃ አባት ሆኑ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በኢትዮጵያውያን የሐይማኖት አባቶች እንድትመራ ከግብፅ እስክንድርያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ጋር ስምምነት ላይ ሲደረስ በትምህርታቸውና በስነ-ምግባራቸው የተመሰከረላቸው አምስት ኢትዮጵያውያን የሐይማኖት አባቶች ተመርጠው ነበር፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ከነዚህ አባቶች መካከል አንዱ ለመሆን በቁ፡፡ በ1921 ዓ.ም ከግብፅ እስክንድርያ መንበረ ማርቆስ ቤተ-ክርስቲያን መዓረገ-ጵጵስና ተቀብለው ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምስራቀ ኢትዮጵያ ተላዌ አሰሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ›› ተብለው በመንዝና ወሎ ሐገረ ስብከት ተሾሙ፡፡

አቡነ ጴጥሮስ በመንዝና ወሎ ሐገረ ስብከት ከተሾሙ ከሰባት ዓመታት በኋላ፣ በ1928 ዓ.ም፣ ዓድዋ ላይ የተከናነበችውን ሽንፈት ለመበቀል ለአርባ ዓመታት ያህል ስትዘጋጅ የቆየችው ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ አቡነ ጴጥሮስም ወራሪው የኢጣሊያ ጦር በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ ሲመለከቱ ልባቸው በከፍተኛ የሃዘን ጦር ተወጋ፡፡

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን የአቡነ ጴጥሮስ ትካዜና ፀሎት በምናባዊ ህሊናቸው ታይቷቸው በግጥማቸው …

‹‹ … አዬ! ምነው እመ ብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት?
እስከመቼ ድረስ፣ እንዲህ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺ እኮ ማንም የላት… ›› እንዳሉት አቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን መከራ ለሃዘንና ለቁጭት ዳርጓቸው ይህንን ግፍ ዐይተው ማለፍ አልፈለጉም፤ይልቁንም ከአርበኞች ጋር በመሰለፍ አርበኞችን ያበረታቱና ይደግፉ ጀመር፡፡

ንጉሰ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል የሚፈፅመውን ገደብ የለሽ ግፍ ለዓለም መንግሥታት ማኅበር ለማሳወቅ ባህር አቋርጠው ከሄዱ በኋላ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ኃይላቸውን አሰባስበው በአዲስ አበባ የሚገኘውን የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ሰራዊት ለመውጋት በወሰኑበት ወቅት አቡኑ የአርበኞቹን ኅብረት ለመባረክና ሞራላቸውን ለማጠንከር ወደ አዲስ አበባ ሄደው ነበር፡፡

በወቅቱ በነበረው የመረጃ እጥረትና የቅንጅት ጉድለት ምክንያት የታሰበው ጥቃት ባይሳካም ‹‹የመጣሁበትን ሳልፈፅም ወደኋላ አልመለስም፤ ብችል በአዲስ አበባም ጠላት በኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ስላለው ጉዳት ሕዝቡን በማትጋት በጠላት ላይ እንዲነሳ አደርገዋለሁ፤ ካልሆነም እዚሁ እሞታለሁ›› በማለት ሕዝቡ ለፋሺስት እንዳይገዛና አስተዳደሩንም እንዳይቀበል ያስተምሩ ጀመር፡፡
ይሁን እንጂ ጠላት በመላ ከተማው ያሰማራቸው በርካታ ባንዳዎች አወኳቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ጳጳሱ እንዳሰቡት ሊንቀሳቀሱ ባለመቻላቸው በወቅቱ የኢጣሊያ እንደራሴ ለነበሩት ለራስ ኃይሉ እጃቸውን ሰጡ፡፡ ራስ ኃይሉም ለፋሺስቱ አስተዳደር የበላይ ለነበረው ለሮዶልፎ ግራዚያዚ አሳልፈው ሰጧቸውና የፋሺስት ጦር ቤተ መንግሥት ውስጥ አስገብቶ አሰራቸው፡፡

ከዚያም ጳጳሱ የኢጣሊያን ገናናነት አምነው እንዲሁም የንጉሥ ኢማኑኤልንና የቤኒቶ ሙሶሎኒን ገዢነት ተቀብለው በሐይማኖታዊ ተልዕኳቸው እንዲሰብኩ ተጠየቁ፡፡ ጥቂት ኢትዮጵያውን አገራቸውን ከድተው በአድርባይነትና በጥቅም ለግፈኛው ጠላት ድጋፍ እንደሰጡ ሁሉ ጳጳሱም ጣሊያኖች የነገሯቸውን ተግባራዊ ቢያደርጉ የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን መሪነትንና ለስብከት ማስፋፊያ የሚሆን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና የተንጣለለ መኖሪያ እንደሚሰጣቸው የሚያረጋግጥ መደለያ ተንቆረቆረላቸው፡፡ ለጥቅም ያደሩ የእምነት አባቶችም ኢጣሊያውያን የሰጧቸውን እድል እንዲጠቀሙ ጳጳሱን ይማፀኑ ጀመር፡፡
አቡኑም ‹‹ለመሆኑ የኢጣሊያን ገናናነት እንዳምን፣ የኢማኑኤልንና የሙሶሎኒን ገዢነት እንድቀበል ነው የፈለጋችሁት?›› ብለው መስቀላቸውን ጠበቅ ላላ እያደረጉ ጠየቁ፡፡ ‹‹በትክክል!›› አሉ ጣሊያኖች፡፡ ‹‹ማመን ብቻ በቂ ነው፤ ከዚያ ስልጣኑ፣ ገንዘ…›› አላስጨረሷቸውም፡፡

ይህን ጊዜ ጳጳሱ ገሰጿቸው፡፡ ‹‹በቃችሁ! በቃችሁ! ይህቺ ክብሯን የደፈራችኋት አገር ለመሆኑ ‹መኳንንት ከግብፅ ይወጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪ ትዘረጋለች› የተባለላት ቅድስት አገር መሆኗን ታውቃላችሁ? ይህቺ የቆማችሁባት ምድር ለእብሪተኞች ረመጥ፣ እንደ እሳት የምታቃጥል መሆኗን ብታውቁ ኖሮ ምን ያህል ጥርሳችሁ በሃዘን እየተፋጨ በተንገጫገጨ ነበር፡፡ ግን ግብዝ ሆናችኋል፤ በኃይላችሁ ተማምናችኋል፡፡ እኔ የምፈራው የሰው ሰይፍ አይደለም፡፡ የእናንተ እብሪት፣ የእናንተ ጉልበት ትንሽ ጉም ነው፤ ነፋስ የሚበትነው፡፡ እና የፋሺስት ኢጣሊያን የበላይነት ከምቀበል ሞቴን እመርጣለሁ፡፡ ወደ እግዚአብሔር እጆቿን የዘረጋችውን ቅድስት አገሬን እብሪተኛ ሲደቀድቃት እንዲኖር አልፈቅድም፤ እምነቴም በፍፁም አይፈቅድልኝም!›› አሉ ጳጳሱ አምርረው፡፡ ቀጥለውም ‹‹የኢጣሊያን ገዢነት የተቀበላችሁ ሁሉ አወግዛችኋለሁ! የኢጣሊያን ገዢነት ከተቀበለ እንኳን ሰው ምድሯ የተረገመች ትሁን!›› አሉ ጣታቸውን ወደላይ ቀስረው ሰማይ ሰማይ ዕየተመለከቱ፡፡

እንዲፈፅሙ የተጠየቁትን ፍርጥም ብለው ‹‹እምቢ!›› ያሉት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድም የተሰየሙት ዳኞች ሦስት ነበሩ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ የቀረበባቸው ወንጀል ‹‹ሕዝብ ቀስቅሰዋል፤ ራሳቸውም አምፀዋል፤ ሌሎችም እንዲያምፁ አድርገዋል›› የሚል ነበር፡፡
ፋሺስቱ ዳኛም ‹‹ካህናቱም ሆኑ የቤተ-ክህነት ባለስልጣኖች እንዲሁም ሊቀ-ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የኢጣሊያን መንግሥት ገዢነት አምነው ‹አሜን› ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን አመፁ? ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ አቡነ ጴጥሮስም እንዲህ ብለው መልስ ሰጡ፡፡ ‹‹አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፤ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ … እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፤ ተከታዮቼን ግን አትንኩ! …›› አሉ፡፡ ዳኞቹም ጳጳሱ በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ፈረዱ፡፡

ከፍርዱ በኋላም ተመልሰው ወደእስር ቤት ተወሰዱና ተዘጋባቸው፡፡ ሌሊትም ዶፍ ዝናብ ሲዘንብ፣ ጎርፉ ሲጋልብና ነጎድጓዱ ብልጭ ድርግም ሲል በግፍ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አቡነ ጴጥሮስ ‹‹ሰዓሊለነ ቅድስት ኢትዮጵያን ጠብቂያት እመብርሃን … ሕዝበ ኢትዮጵያን ጠብቅ …›› እያሉ ፀሎታቸውን ያደርሳሉ፡፡


ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ጥሩምባ ተነፍቶ ሕዝቡ ግድያው ከሚፈፀምበት ቦታ አራዳ፣ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን በታች ከአትክልት ተራ ፊት ካለው ቦታ ላይ ተሰበሰበ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በፋሺስት ወታደሮች ታጅበው መጡ፡፡ ሞት አይፈሬው የነፃነት አርበኛም ‹‹ዓይንዎን በጥቁር ጨርቅ እንዲሸፈኑ ይፈልጋሉ?›› ተብለው ተጠየቁ፡፡ ‹‹እናንተ እንደፈለጋችሁ አድርጉት፤ እንደ እኔ ምርጫ ግን የወራሪን፣ የእብሪተኛን ሞት ፊት ለፊት ገጥሜ ድል አድርጌ መሞት ስለምፈልግ ባትሸፍኑኝ ደስ ይለኛል፤ ሞቴ አያሳፍረኝም፡፡ የምሞተው ለአገርና ለትልቅ ሕዝብ ነው›› በማለት የዓይናቸውን መሸፈን ተከላከሉ፡፡

ጳጳሱም ፊታቸውን ወደ ምዕራብ እንዳዞሩ ስምንት ወታደሮች የመሳሪያቸውን አፈ-ሙዝ አነጣጠሩባቸው፡፡ ሕዝቡና ሰማዩ እኩል አጉረመረሙ፡፡ ኮማንደሩ ‹‹ተኩስ›› የሚል ትዕዛዝ የሚሰጥ የግፍ ቃታዎች ተሳቡ፡፡ ‹‹ስልጡን ነን፤ ሰብኣውያን ነን›› የሚሉት ነጮች አረመኔያዊ ድርጊት ፈፀሙ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በስምንት ጥይቶች ተደበደቡ፤ ከአንገታቸው በታች ሰውነታቸው ቢበሳሳም ነፍሳቸው አልወጣችም ነበር፡፡ ኮማንደሩ ሽጉጡን ከክሳዱ በመምዘዝ በሦስት ጥይቶች ጭንቅላቸውን ሲመታቸው ሕይወታቸው አለፈች፡፡ በሚወዱት የኢትዮጵያ አፈር ላይ ወደቁ፡፡ የኢትዮጵያ መወረር የእሳት አሎሎ ሆኖ ሲቃጠል የነበረው አንጀታቸው ተሰብስቦ ተኛ፡፡

አቡነ ጴጥሮስ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ክብርና ነፃነት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፡፡ ያን ዕለት ኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ ጮኸች፡፡ የአዲስ አበባ ሰማይ በግፍ ደመና ተዋጠ፡፡ እንቅልፍ ከነዋሪዎቿ ርቃ ወደ ምድረ-በዳ ተሰደደች፤ ኡኡታ ከጋራ ጋራ አስተጋባ፡፡ ሞታቸውን በዓይኑ ያየው ሰው ሁሉ ወሬውን ሰምቶ ከሚከተለው እየቀደመ መንገድ አሳብሮ የአርበኞችን ፈለግ ተከትሎ ወጣ፡፡ መርዶው መርዶ ሆኖ አርበኞችን እንዲያኮሰምን ሳይሆን ቁጭት ለኳሽ ሆኖ በዱር በገደሉ ተናኘ፡፡

‹‹ኮርየር ደላሴራ (Corriere Della Sera) የተባለው ጋዜጣ ወኪል የነበረው ኢጣሊያዊ ጋዜጠኛ ቺሮ ፖጃሌ አቡነ ጴጥሮስ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ እስከተገደሉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሂደት ባሰፈረው ጽሑፍ ካካተተው ሃሳብ ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል፡፡

‹‹ … ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸው ጠየም ያለ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር። በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ … እኝህ ጳጳስ ሐቀኛ ነበሩ። ነገር ግን ለኢጣልያ ለጋስዮን ታዝዞ የመጣው አስተርጓሚ ዳኞች የሚሉትን ብቻ ከማስተርጐም በቀር ጳጳሱ የሚናገሩትን ሐቀኛ ንግግር አላስተረጐመም። እኔ እንኳን የሰማሁት በአዲስ አበባ ለሠላሳ ዓመታት የኖረው የእቴጌ ሆቴል ኃላፊ የነበረው የግሪክ ዜጋ ማንድራኮስ አጠገቤ ተቀምጦ ስለነበር የተናገሩትን ሁሉ ስለገለጠልኝ ነው። እኔ እንደ ሰማሁት ፍርዱን ለመስማት በብዛት የተሰበሰቡት ጣልያኖችና ታዝዞ የወጣው የአዲስ አበባ ሕዝብ ሐቀኛ የሆነውን ንግግራቸውን ቢሰሙ ኖሮ ልባቸው ይነካ ነበር …››

በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ «አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?» ሲል ሙሴ ፓይላክን ጠይቋቸው እርሳቸውም የሚከተለውን ተናግረዋል። «አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ። መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም የያዙትን መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ። የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት። ወዲያው ወታደሮች በእሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው። ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ …››


አቡነ ጴጥሮስ በፅናትና በጀግንነታቸው ዓይኖቻቸውን በጠላቶቻቸው ዓይን ላይ ተክለው የአረመኔዎችን ህሊና በረጋግደው እውነቱን እንዲያይ አደረጉት፡፡ የነፃነት መቅረዙ ላይ ራሳቸውን ሻማ አድርገው መቅረዙን ለኮሱት፡፡ እርሳቸው ግን በእውነት አደባባይ ላይ በተከሉት ሐውልት ለዘላለም በፅናት ቆሙ፡፡ የእርሳቸው መስዋዕትነት የኢትዮጵያውያን ጀግኖችን እልህ አፋፍሞ እንደቋያ እሳት ይበልጥ እያንቀለቀለ በየቦታው እንዲስፋፋ አደረገው፡፡ የኢጣሊያውንን ጭካኔ ያዩት የኢትዮጵያ ጀግኖች ውርደትንና ስቃይን ከእንግዲህ ዓናይም ብለው ‹‹ኧረ ጥራኝ ጫካው›› በማለት ቤታቸውን እየዘጉ፣ ቀያቸውን እየለቀቁ ‹‹ዱር ቤቴ …. መደፈር ህመሜ ….. ነፃነት ገዳሜ›› አሉ፡፡ በፅኑ ትግላቸውም ፋሺስትን አንበርክከው የኢትዮጵያን ነፃነት አስመለሱ፡፡

@AbenePetros
@Ethiopia
@Abysinnia
@Semien Shewa

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11715
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: ‹‹ደብረ ብርሃን ዓለም-አቀፍ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የፋይናንስ ኤክስፖ›› ከየካቲት 14-20/2013 ዓ.ም ደብረ ብርሃን፣ ኢትዮጵያ

Post by Noble Amhara » 15 Feb 2021, 01:27



Abysinnia 💪




የልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል 168ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ

የገናናው የሸዋ ንጉሥ የንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ የልጅ ልጅ፣ የታላቁ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ የአክስት ልጅ እንዲሁም የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ አባት የሆኑት ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የተወለዱት ከዛሬ 168 ዓመታት በፊት (ግንቦት 1 ቀን 1844 ዓ.ም) ነበር፡፡

🔯🔯🔯

ስመ ጥሩ የሸዋ ንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ ልዕልት ተናኘወርቅን ይወልዳሉ፤ ልዕልት ተናኘወርቅ ደግሞ ወልደሚካኤል ወልደመለኮትን አግብተው ልዑል ራስ መኮንንን ይወልዳሉ፡፡ ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የተወለዱት ሸዋ ውስጥ ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ነው፡፡

[‹‹የራስ መኮንን አባት ስማቸው ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ ነው›› የሚሉም አሉ፤ ይሁን እንጂ ልጃቸው ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የራስ መኮንን አባት ወልደሚካኤል ወልደመለኮት የተባሉ የዶባ/መንዝ ባላባት እንደሆኑ ጽፈዋል]


🔯🔯🔯

14 ዓመት እስኪሆናቸው ድረስ ከአባታቸው ጋር ከተቀመጡ በኋላ ወደ ምኒልክ ቤተ-መንግሥት ሄደው ከአጎታቸው ልጅ ከንጉሥ ምኒልክ (በኋላ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ) ጋር ተዋወቁ፡፡ የምኒልክ ባለሟል ሆነውም የተሰጣቸውን ስራ ሁሉ በጥንቃቄና በብቃት እያከናወኑ ለመንግሥት ስራ ታማኝና ትጉህ መሆናቸውን አስመሰከሩ፡፡

🔯🔯🔯

በፀባያቸውም ታጋሽና አስተዋይ ስለነበሩ ከንጉሥ ምኒልክ ጋር ጠንካራ ወዳጆች በመሆን እንደ አባትና ልጅ ይተያዩ ጀመር፡፡ በ1868 ዓ.ም፣ በ24 ዓመታቸው የ"ባላምባራስ"ነት ማዕረግን ተሾሙ፡፡ በዚህ ወቅትም ሕጋዊ ሚስታቸውን ወይዘሮ የሺእመቤት አሊን አገቡ፡፡ ምኒልክና መኮንን ቤተሰባዊ ዝምድናቸውን አጸኑ፡፡

🔯🔯🔯

የሐረርጌን ግዛት በማቅናትና በሚገባ በማስተዳደር ለንጉሥ ምኒልክ ሀገር የማቅናት ተግባር ብርቱ አጋዥ ሆኑ፡፡ ከቤተ መንግሥት ባለሟልነት ተነስተው በዘመኑ ከንጉሥ በመቀጠል ከፍተኛ ለሆነው የ‹‹ራስ›› ማዕረግም በቁ፡፡

🔯🔯🔯

ልዑል ራስ መኮንን የአጼ ምኒልክ ተወካይ በመሆን ሁለት ጊዜ ወደ አውሮፓ ሀገራት ተጉዘዋል። ወደ ኢጣሊያ በሄዱ ጊዜም የኢጣሊያ ጋዜጦች የውጫሌ ውልን ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ በኢጣሊያ መንግሥት ጥገኝነት ስር እንዳለች አድርገው የሚጽፉትን ጽሑፍ በመመልከታቸው ራስ መኮንን ተቃውሟቸውን ለኢጣሊያ መንግሥት ከነገሩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የውሉን መበላሸት ለአጼ ምኒልክም አሳውቀዋል።

🔯🔯🔯

የውጫሌ ውል ያስከተለው የትርጉም ለውጥ መፍትሄው ጦርነት ሲሆንም ልዑል ራስ መኮንን ሰራዊታቸውን ይዘው ከአምባላጌ እስከ እስከ አድዋ በተደረጉት ውጊያዎች ላይ በመሳተፍ ጀግንነታቸውን አስመስክረዋል፡፡

🔯🔯🔯

ልዑል ራስ መኮንን ከቤተ መንግሥት ባለሟልነት ጀምረው በወታደርነት፣ በጦር መሪነት፣ በግዛት አስተዳዳሪነትና በዲፕሎማትነት በፈጸሟቸው አኩሪ ተግባራት ምክንያት ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዙፋናቸው ወራሽ ሊያደርጓቸው ያስቡ ነበር፡፡ ነገር ግን እምዬ ያሰቡት ሳይሆን ቀረና ልዑል ራስ መኮንን መጋቢት 13 ቀን 1898 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

🔯🔯🔯

ሞታቸው በንጉሰ ነገሥቱ ቤተ መንግሥት (አዲስ አበባ) በተሰማ ጊዜም ከፍተኛ ሀዘን ሆነ፡፡ ታላቁ ንጉሥ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክም አምርረው አለቀሱ፡፡ በወቅቱም ይህንን የተመለከቱ ሰዎች እንዲህ ብለው ገጠሙ …

‹‹ዋ አጤ ምኒልክ እግዚአብሔር ያጥናዎ፣
በየበሩ ቋሚ ከልካይ ሞተብዎ፡፡
ሲታሰር አየነው ብረቱ ሲመታ፣
ምን ዋስ አገኘና ሐረርጌ ተፈታ፡፡
ጃንሆይ ምኒልክ ጠጉራቸው ሳሳና በራ ገለጣቸው፣
እንግዲህ ንጉሡ ምን ራስ አላቸው፡፡››

🔯🔯🔯

ከአልቃሾቹ መካከል አንደኛው ደግሞ የልዑል ራስ መኮንንን ደግነት ለማስታወስ እንዲህ ብሎ ሙሾ አወረደ …
«ስልከኛው ሲያረዳ ነገር ተሳሳተው፣
መኮንን አይደለም ድሀ ነው የሞተው፡፡»

🔯🔯🔯

(ምንጭ ፡ ልዩ ልዩ)



Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11715
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: ‹‹ደብረ ብርሃን ዓለም-አቀፍ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የፋይናንስ ኤክስፖ›› ከየካቲት 14-20/2013 ዓ.ም ደብረ ብርሃን፣ ኢትዮጵያ

Post by Noble Amhara » 15 Feb 2021, 02:07




የአቡኑ ከተማ ሰላ ድንጋይ
******************************
የአቡኑ ከተማ ሰላድንጋይ ከደብረብርሃን በስተሰሜን 72 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ለ38
አመታት የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ የነበሩት ግብፃዊው አቡነ ማቴዎስ መንበረ ጵጵስናቸው
በዚችው በሰላ ድንጋይ ነበር፡፡ በ1875 ዓ.ም በአቡነ ማቴዎስ የተሰራው የሰላድንጋይ
ማርቆስ ቤተክርስቲያን በ25 አመቱ በመብረቅ ቢፈርስም እንደገና በ1900 ዓ.ም በአጼ
ምኒሊክ ልዩ ትእዛዝ ተሰርቶ ሚያዚያ 30 ንጉሱ ባሉበት በአቡኑ ተባርኳል፡፡ የቤተክርስቲያኑ
ህንፃ የውስጥ አሰራር ውበት አይንን የሚማርክና የዘመኑን የህንፃ ሥራ ልዩ ችሎታ
የሚመሰከር ነው፡፡ በውስጡም ከግብጽ ሀገር የመጣውን የአቡነ ማቴዎስ መቀመጫ
ጨምሮ በርካታ የታሪክና የባህል ቅርሶች ይገኙበታል፡፡ ሰላድንጋይ የንጉስ ሳህለ ስላሴ
የትውልድ ሥፍራም ናት፡፡ በእናታቸው በወይዘሮ ዘነበወርቅ እንደተሰራችና በስማቸውም
የምትጠራው ሰገነት ከተሰራች 150 አመት አስቆጥራለች፡፡ ስላድንጋይ የአብዛኛዎቹ የሸዋ
ነገስታት ሚስቶችና እቁባቶች መቀመጫ ስለነበረች የወይዘሮዎች ከተማ በመባልም
ትታወቃለች፡፡
ከሰላድንጋይ አቅራቢ ከ1433 /1434/ ዓ/ም በአጼ ዘርአያቆብ የተተከለችው
ደብረምጥማቅ ቤተክርስቲያንና ብዙ መነኮሳት የሚገኙባት የፃድቃኔ ማረያም ከፊል ዋሻ
ደብር ይገኛል፡፡



kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ‹‹ደብረ ብርሃን ዓለም-አቀፍ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የፋይናንስ ኤክስፖ›› ከየካቲት 14-20/2013 ዓ.ም ደብረ ብርሃን፣ ኢትዮጵያ

Post by kibramlak » 18 Feb 2021, 02:52

Do you have the source of this information, for more details? it's worth visiting this event
Noble Amhara wrote:
15 Feb 2021, 00:31
‹‹ደብረ ብርሃን ዓለም-አቀፍ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የፋይናንስ ኤክስፖ››

ከየካቲት 14-20/2013 ዓ.ም

ደብረ ብርሃን፣ ኢትዮጵያ

Post Reply