Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: የጉራጌ ምሁራን ተነሱ !! የጉራጌ ክልልነት የዘገየ ጉዳይ ነው

Post by simbe11 » 17 Oct 2020, 01:59

በመጀመሪያ ደረጃ የብሄር ክልል መጥፋት አለበት::
ጉራጌ ክልል መመስረት የሚገባው
በደቡብ አላባ ከምባታና ጠምባሮ እንዲሁም ሃድያንና ስልጤን ጨምሮ
(አላባ ቁሊቶ/ ዱራሜ / ሺንሺቾ / ሆሳእና / ቅበት እንዲሁም አብያታና ሻላን ይዞ)
በምሥራቅ እስከ ዝዋይ ሃይቅ ተሻግሮ ዛይ/ላቂዎችን መስቃንና ማረቆን ይዞ::
ወልቂጤ ዙሪያ ያሉትን ቀቤናዎች ይዞ::
በውሸት የወያኔ ሪፍረንደም ወደ ኦሮሞ የገቡትን የሶዶ ወረዳዎች አጠቃሎ (ሶዶ ጅዳን)::
በሰሜን ምእራብ በኩል እስከ ወንጪ ሃይቅ ያሉትን ወሊሶንና ዳርያን ጨምሮ (ጨቦና ጉራጌ የሚባለው ማለት ነው):: በመሃልአምባ ያሉትን ወለኔዎች አካቶ::
ወደጅማ መንገድ እስከ ጊቤ በረሃ ያሉትን (ባብዛኛው የወላይታ ተወላጆች ያሉበት) ጦላይን አካቶ መሆን ይገባዋል::

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጉራጌ ምሁራን ተነሱ !! የጉራጌ ክልልነት የዘገየ ጉዳይ ነው

Post by Horus » 17 Oct 2020, 03:35

Simbe
አንድ ነገር ልንገርህ ። እነዎያኔ፣ እነሲዳማ እኛው አልምተናቸው በኛ ላይ ለተነሱ ሁሉ መልስ እንሰጣለን ። በታሪክ ና በሳይንስ ጉራጌ የሆኑት እነዛይ፣ ኡርባረግ፣ አዝርነጥ ስልጤ ተመልሰው ከታላቁ ከክቡሩ ጉራጌ ዘራችው ጋር መዋሃድ ከፍቅዱ ቤተጉራ ምን ግዜም እጁ ክፍት ነው ።
ሌሎች እንደ ከምባታ ያሉ የምናክብራቸው ህዝቦች ምን እንደ ሚፈልጉ የነሱ ነው ። እኛ ጉራጌ ግን የራሳችን አገር ይዘን ይህን ሁሉ ሃብትና እውቀታችንን የምናሳይበት ዘመን ደርስናል። ዞሮ ዞሮ ኢትዮጵያ ጉራጌን ነው የምትመስለው። ወላይታ የራሱን ጉዳይ ይፈታል ። ሃጊያም፣ ከምባታም ። ጉራጌ ጉራጌ ነው ። ጉራጌ ሁለት ነገር ነው ፣ ኢትዮጵያና ጉራጌ ። አበቃ !!

ጉራጌ ክላስትር ምናምን የሚባል የካድሬዎች ምናንባና ሽውዳ ለጉራጌ ስድብ ነው !!


Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ክላስተር የጉራጌን ዘር ለማጥፋት የታቀድ መርዝ ነው !! ጉራጌ ራሱን የሚገዛ (አጉራ ጠነ) ነጻ ሕዝብ ነው !!

Post by Guest1 » 17 Oct 2020, 04:47

በቅሚያ ሁሉም የኢትዮ ዜጋ ነው። አገር ማለት ደግሞ የተወለድክበት ቦታ ዬትም ይሁን፤ ያደግክበት ቦታ፤ የኣያትህ የወላጆችህ እትብት የተቀበረበት ቦታ አገርህ ነው አራት ነጥብ።
ክልል ይሁን በዞን ሆነ በወረዳ መዋቀር ድሮም ነበር። ስጋት የፈጠረው የአስተዳደር ክልል ሳይሆን እንደ ደቡብ አፍሪካ ባንቱስታናይዜሽን የሚባለው በብሄር የሚከልል ስርኣት አቢይም እንደገለጸው (ሚልኪ ዌይ ጋላክሲ ሶላር ስስተም ክክክክክክክክክክ ምናልባት ይህን ማለቱ ላይሆን ይችላል ክክክክክክክክክ) ለመፍጠር ታቅዷል የሚለው ነው።

የጉራጌ ህዝብ ክልል የጠየቀው ለአስተዳደር አመቺ ስለሆነ፤ መግባባት ስለጠፋ፤ ሌብነትም ስለበዛና ምናልባትም የስልጤ ጉራጌ አንድነትን ስለፈለገም ይሆናል። ትክክለኛ ጥያቄ ነው። ይቅናቸው። አንተ እንዳቀረብከው ከደቡብ ህዝብም ሆነ ከጎረቤቱ ጋር ተለይቶ የብሄር ክልል የመፍጠር ፍላጎት አይደለም።



Post Reply