Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አሁን የሌባን ገንዘብ መውረሻ ዘመን ነው! ኢትዮጵያችን በርግጥ ትንሳኤዋን ጀምራለች፤ ለምን በሉ?

Post by Horus » 15 Sep 2020, 22:48


ዝም ብላችሁ በራንደም የኢትዮጵያ ዜና ስታገላብጡ ምንድን ነው የምተሰሙት ነገር?

አንዱ ታላቁ ወሬ አባይ ነው ። አባይ የዘመናችህን የኢትዮጵያ ልዑልነትና ያገራችህን የዉሃ አብዮት ጅማሮ አዋጅ ነው ። ይህ ታሪካዊ የሆነ ያገር ትንሳኤ ምልክት ነው ።

ሌላው የአረንጓዴ ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ኢኮሎጂ አብዮት ነው ። ያግራችህን አረንጓዴ መሆን በኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይኮሎጂ ላይ፣ ካልቸር ላይ፣ ኢኮኖሚና ማሀራዊ ሕይወት ላይ እጅግ ግዙፍ ዘላለማዊ ለውጥ ያመጣል ። ይህ ሌላው ታሪካዊ ያገር ትንሳኤ ነው ።

የትላንትናው ፕሮጀችት ኤክስና ገንዘብ በመለወጥ የተጀመረው ሌብነት የማጥፋት ዘመቻ፣ የመሬት ወረራና የቤት ዘረፋን ጨምሮ በዚህ ከቀጠለ አንዱ ሌላው ያገር ትንሳኤ ይሆናል። አንዱ ትልቁ የኢትዮጵያ ሞራል ውድቀት ማረጋገጫ ያገሪቱ የሞራል ውድቀት፣ አገሩ የሰራተኛ ሳይሆን የሌቦች አገር መሆኑ ነው። ልክ አባይ የኢትዮጵያ ልዕልና እንደ ሆነ ሁሉ አትዮጵያን ከሌቦች ማጽዳት እጅግ ግዙፉ የማህበራዊ ፍትህ አብዮት ነው ። ኢትዮጵያ ከሌብነት ካልቸር ነጻ ሳትሆን ነጻ ሕዝብና ፍትሃዊ ማሀበረሰብ አትሆንም።

በእኔ ግምት ፕሮጀችት ዋይ (Project Y) የሚባል አሸባሪዎችና አገር አውዳሚዎችን የማጽዳት ዘመቻ ያለ ይመስለኛል ። ይህም የሕግ የበላይነት ወይም የሰላም ዘመቻ በዚህ ከቀጠለ ሌላው ያገር ትንሳኤ መሆኑ አይቀርም ።

አሁን የተጀመረው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እድገት (Political Development) የፓርቲዎች ስራ ጠንክሮ ባመት ውስጥ ሰላማዊ ምርጫ ከተደረገ ሌላው ታልቅ ያገር ትንሳኤ እንደ ሚሆን አያጠራጥርም ።

ሳይንሳን ቴክኖሎጂ የራሱ አብዮት ይዟል።

ዲጂታል ትራንስፎርማኤሽን ስትራተጂ የራሱ አለው።

አገር በቀል የኢኮኖሚ ረፎርም እንዲሁ ።

የሲቪልና የምሁራን ስብስብ ስለ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ራዕይና አገር ግንባታ ይመራመራሉ ።

መንግስት የ10 እና 20 አመት የኢትዮጵያ ራዕይ ቀርጽ ይንቀሳቀሳል ።

በአንድ ቃል ኢትዮጵያ መውደቅ የምትችለውን ርቀት ወርዳ ወደ ላይ ያለውን መሰላል መውጣት ጀምራለች የሚል ስሜትና ግምት አለኝ !!!

የፍጹም ደስታ መስቀል ለኢትዮጵያ !!! ኬር ዬሁን :!: :!:

Last edited by Horus on 16 Sep 2020, 11:34, edited 4 times in total.


Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እኔ ሆረስ ነኝ፣ መስቀል ደርሶብኛል ! ኢትዮጵያችን ግን በርግጥ ትንሳኤዋን ጀምራለች፤ ለምን በሉ?

Post by Horus » 16 Sep 2020, 01:04

እኔ እዚህ ፎረም ላይ ለ15 አመት እያወጅኩት ያለውን የኢትዮጵያ አጀንዳ እስቲ ልድገመውና አሁን ካለው ሂደት ጋር ላስተያየው ። የኢትዮጵያ አጀንዳ ምን ሁኒታ ላይ ይገኛል?

የኢትዮጵያ አጀንዳ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ አላማ ምንድን ነው?

አንድ፣
ኢትዮጵያን አንድነቷ የጸና፣ የተረጋጋች፣ ጠንካራ አገርና መንግስት መሆን ነው ። ይህ ዎያኔ ከገባ ጀምሮ ሲጠቃ የነበረ አጀንዳ አሁን ቀስቱ ወደ አንድነት፣ መረጋጋት እና ወደ ጠንካራ አገርነት ዞሮዋል ። ከዚህ በኋላ ይህ ቀስት ወደ ተቃራኔው አቅጣጫ አይዞርም። ለምን ብትሉ ያባይ በለስ ፕሮጀችት ነው ።

ሁለት፣
ኢትዮጵያን ዴሞክራሳዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ሕብረተ ሰብ ማድረግ ነው። ይህ ገና በትንሽ ጅማሮ ያለ ሲሆን እስከ ሚቀጥለው ምርጫ ድረስ በዴሞክራታይዜሽን፣ በግለሰቦ ነጻነት (ሊበርቲ) ላይና ፍትህ ዙሪያ ምን እንደ ሚመጣ ይታያል ። ግን ጥሩ ጅማሮ አለ።

ሶስት፣
የኢትዮጵያን ሕዝብ የበለጸጉ፣ የተማሩና ጤነኛ ዜጎች ማድረግ ነው። እዚህ ላይ በጂዲፒ ደረጃ እድገት ቢኖርም ሰፌው ሕዝብ ድሃ ነው ፣ ትምህርት ወድቋል፣ ጤናውም ገና ዋስትና ያለው ሕዝብ አይደለም ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ IQ 69 መሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ እውቀት ማን ያህል ዘቅጦ እንዳለ ለመገመት አያቅትም።

አራት፣
በኢትዮጵያ ፈጣሪ፣ ኢኮሎጂያዊ፣ እና መንፈሳዊ ብሄራዊ ካልቸር መገንባት ነው። እዚህ አጀንዳ ውስት በጣም አመርቂው የኢትዮጵያ አረንጓዴው አሻራ ነው ። ፈጠራም በተለይ ሙዚቃ፣ ቲያትር፣ ሲኒማ ፣ ስነጽሁፍ ደህና ነው። የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፍልስፍና እና የቲኦሪ ፈጠራ ገና ነው ። መንፈሳዊነት በስፋት ያለ ቢሆንም አሁንም ችገር አለበት ።

ስለዚህ እስከነ ችግርና ድክመቱ የኢትዮጵያ አጀንዳ ወደ ፊት እያዘገመ ነው ። ከዎያኔ ዘመን ወድቀቱ ተነስቷል ። ኬር !


Post Reply