Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Member+
Posts: 9765
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Laureate Tsegaye Gebre Medhin's prophecy in year 1990 EC

Post by DefendTheTruth » 15 Sep 2020, 17:34

I just came across the following content in the internet and just started to hate myself for having considered myself also as a fellow human of the same club of the man of such deep knowledge and couldn't stop woundering if this prophecy is real or I am in some kind of illusion.

Please start to read when you have time. ( I myself started to read but had to stop before finishing because of time constraints).

I am not sure, if ጦቢያ መጽሄት can repost the original print of before 20 years.

"
Please wait, video is loading...
ኢትዮጰያዊነት
ኢትዮጰያዊነት ማተብ ነው<> በአካልና መንፈስ ፅናት
በአበው ታሪክ <> አምኖ መኩራት
ኢትዮጰያዊነትን መካድ<>የፍቅር አምላክን ሲሳይ
መርገጥ ነው<> እንደ እኩይ ጠባይ
የአንድነት አድባር ፈንግሎ<>ለመናፈቃዊ ግዳይ
በትውልድ ላይ ሰቆቃ<>የአካል እና መንፈስ ስቃይ
ማንገስ ብቻ ነው ውጤቱ<>በራስም ላይ በህዝብም ላይ
የኢትዮጰያዊነት መስፈርቱ<>ነፃነት ነው ለአንድ ዜጋ
መንፈሳዊ ነው እሴቱ <> የማይዳሽቅ ለስጋ
የማይገብር ለጠመንጃ <>የማይተመን በዋጋ
መንፈሱን ቆርሶ ለመሸጥ <>ሳይሆን እንደ ባዳ መንጋ
ወይ እንደ ትላንቶቹ <>ለዙፍን ባርነት ሳይሆን
ወይ ለጦር መኮንኖች ምርት<>ከማጎብደድ ላንድ ሰሞን።
©©©©©©©
ኢትዮጰያዊነት ክብር ነው<>ለሀያል ክንድ የማይዳር!!
ህዝባዊነት ነው መስፈርቱ<>የህዝብ ወገን የህዝብ አጋር
እንጂ ለዘረኞች ቁማር፣ለአንድ ጎሳ ቡድን ገባር
ሊሆን እንደ ሚጣል እጣ፣አይደለም ሎተሪ ቢጋር።
የየጎሳው ክልል ጣኦት፣እፍ እንዳለበት ጭቃ ጡብ
የሚፍጠረጠር ለቀን እሩብ
ጠዋት ተፈብርኮ ማታ ተገምግሞ እንደ ሚሞት
አይደለም ኢትዮጰያዊነት
የአሻንጉሊትነት ሂወት።
በኢትዮጰያዊነት ፅናቱ፣፣የሀገር ልጅ ሁሉን ቢካንም
የትናንት መነሻውን ሳያጤን በታሪክ አቅም
የነገን መድረሻ ግብ ድንገት መቀየስ አይችልም
መነሻውን ያላወቀ መድረሻውንም አያውቅም።
ስለዚህ ,,,,, ,,
ስለዚህ, ማወቅ ሲጀመር
የሰው ልጅ ልሳኑን በቃል ÷ቃሉን በፊደል ሲቀምር
የአገሩንና የራሱን፣ከወገኑ ስም ሲያጣምር
በማጠናቀር ጀመረ፣፣የሆሄ ልሳናት ድምር።
የኢትዮጰያዊነት ሚስጥሩ¡!!
ወንድምህን መጥላት ሳይሆን÷ራስክን ማወቅ ነው ከስሩ
ሰው በወንድሙ ሲሳለቅ ፣÷፣ያው በራሱ እንደ መሳለቅ
ነውና ከቅድመ ታሪክ ÷አስቀድመህ ራስክን እወቅ
መባሉ በጥላቻ ዚቅ ታውረህ ÷ወንድምህን ስትንቅ
ያው ራስክን ነው የናቅከው÷ከራስህ ጋር ነው ትንቅንቅ
የዘረኝነት በሽታ÷ መልሶ ራስክን ስለሚያንቅ
መነሻውን ያላወቀ ÷መድረሻ ግቡንም እማያውቅ
ኢት ስራ ቃል እውነት ማለት÷ ኦጰ የበላይ ቢያ ሀገር
ኢትዮጰያ ሲዘረዘር በአይግሮፊክ የፊደል ዘር
ከስድስት ሺ አመት በፊት÷ በካም አበው አፍ ሲነገር
የላይኛው እውነት ሀገር÷ እንደ ማለት ያህል ነበር።
ከአራቱም የአፍሪካ ዘር ግንድ ÷ከቻድ ከባርቤር ከባንቱ
ነገደ ካም ነው ታላቁ ÷ የስልጣኔው አባቱ።
የነገደ ካም ግንድ ነው ÷ ኢትዮጰያዊ መሰረቱ።
ማ ትክክል ማለት ሲሆን፣ካ ማለት የእግዚያብሄር ስም ነው
የእግዚያብሄር ትክክል ወገን፣ካማ ወይም የካም ሰው
ነበረ ጥንት የሚባለው።
ስደትና ጦርነቶች በየዘመኑ ሲራቡ
የካም አበው ወገኖችም፣ከየመጣው ዘር ሲጋቡ
ከ,ባእድ ሀይማኖቶች ጋር፣ባእድ ልሳኖች ተሳቡ።
ከመነሻው ግን ካም ቃሉ ፣ሆዋላም ፣ለአዳም ስም አዶም
አራት ባህሪይ ይዞ ነው ÷ጥቁር ፣እሳት፣ ፀሀይ ፣ሰላም
አፍሪካዊ መሰረቱን፣÷፣ ጥቁር ለሚያሰኝው ሚስጢር
ቃሉን እያወራረሰ ፣÷፣ ከካም ወይም ከካማ ስር
ኦርኦሞ፣አምሀራ ስሙን ፣÷፣አግአሜ አማሴን ጭምር
ካማ ግንዱን አለቀቀም ፣የአንድ እናት ልጅ ክሩን ጥምር።
የእሳትነት ባህሉንም በችቦ እያቀጣጠሉ
ኢካም እሳት ነን እያሉ፣÷፣ አራት ሺ አመት ሙሉ
ፈርኦኖችም ሲምሉ
የካም አበው ስርአት ፣÷፣ ሳይለወጥ ኖረ ቃሉ።
ግሪክ የተቃጠለ ገፅ፣÷፣ ያለው ነበልባልነቱ
ላቲን ኮም ዌል ካም ብሎ፣÷፣ ያለው ሰላማዊነቱ
ኢብራኢስጥ ኩሽ እያለ ፣÷፣የካም ልጅ እሳትነቱ
ያበሰሩት በውርስ ነው ፣÷፣ ሳያዛቡ መሰረቱን
ኦሪትም ወደ ካም ምድር ፣÷፣አፍሪካ መግባት ሳይጀምር
በፀሀይ አምላክ ነበረ፣÷፣ የካም ሀይማኖት እምነቱ
እግዚያብሄርን ያመለከው ፣÷፣በኦራ ብርሀን ድምቀቱ።
እግዚያብሄርን ያመለከው።
ስለዚህም ነው ካም አበው
የኢትዮጰያዊነቱን ምስጥር ፣÷፣ከዘ ፍጥረት ሲቀምረው
ጥቁር፣እሳት፣ፀሀይ፣ሰላም መሰረቱን እያሰኝው
ከአራት ባህሪይ በአንድ አካል፣÷፣ በሊቅ እያዋሀደ ነው፣
ማንነቱን የገለፀው።
የካም አበው ኦራ ፀሀይ፣÷፣የመጀመርያው የበላይ
የጮራ ፆላት ታቦቱ ፣÷፣ጥቁር ካቢያ ድንጊያ ቅርፁ
በሜሮና በጥቁር ግብፅ ፣÷፣አስቀድሞ መታነፁ
ከዛም አዱሊስ መጠራዋ፣÷፣ አዳ አዱኛ እየበራ
ቀጥሎም አክሱም ሲደራ
የአፋር፣ አፈር፣ አፍሪካ ዘር ፣÷፣የፊርአዎን አብነቱን
የጥቁር ደም አሻራውን፣÷፣ የካም ወገን ቅርስነቱን
የኢትዮጰያ ስር አንጡራ ውርስ ፣፣የአበው አፅም ርስትነቱን
አልካደም የማንነቱን፣አለቀቀም መሰረቱን።
ስለዚህ በአይሮግሊፊክ ፣÷፣ሳባን የመንፈስ ልጅ ብለው
ካባን በስረ ቃላቸው ፣በእግዚያብሄር መንፈስ ሰይመው
ካባሳ ወይም ሀበሻ፣÷፣ ሆዋላም ሀባሻ አሰኝተው
ሀባ፣ ጃማ ፣ሀባ ካማ ፣÷፣በካባ ክቡር ስም መዝገብ
በቋንቋ ሳይንስ አምጥቀው ፣በጥንቃቄ ነድፈው ነው
ኢትዮጰያዊነታችንን ከጥንት ያወረሱን አበው።
የማንነት አርማችንን፣÷፣ ከዘ ፍጥረት ሲቀምሩት
በልሳንና በፊደል፣ ከመሰረቱ ሲቀርፁት
በማያሻማ ቋንቋ ነው አበክረው የገለፁት።
**$**
ታድያ ዛሬ በእውር እግር<>ማንነታችንን መክዳት
የአለም ስልጣኔ ቁንጮ<፣>በኩሮዋችንን ለማስቀማት
መነሻችንን እንዳናውቅ<፣>ታሪካችንን በመግፍት
የአንጋፍችንን ክብር ፅላታችንን ለማጥፍት
ኢትዮጰያዊነታችንን ለማጨለም ይሀው ዛሬ
ታሪክ ፍቀን፣ ቅስፈት ጠርተን ፣በዘረኝነት ካድሬ
በጎሳ ፕሮፖጋንዳ በከፍፉለህ ግዛው ወሬ
በጥላቻ ፖለቲካ በደናቁሩት ፍካሬ
ገባን እንጂ ወደ ሲኦል፣ወደ መጠፍፍት አለም
ሁላችን አንድ የካም ልጆች፣በዘር በአጥንትና በደም
በታሪክ ማንነታችን፣እኛን ከኛ ሚለይ የለም።
በቅድመ ታሪክም ድርሻ በአርኪዮሎጂ ፈለጎዋ
የአለም ሙዝየም እናት ነው የኢትዮጰያ ኢትዮጰያዊነቷ።
ኢትዮጰያዊነት ፈለግ ነው የቅድመ ሰው ዘር መገኛ
ፍና ነው የአሻራው ህትመት ቀደምት የአንቀልባው መተኛ።
*** ***
የእፅዋትና የበቀልት የአና ምርትና ነገያት
የዘ ፍጥረታቱ ቋት ነው የአራዊት እና የእንስሳት።
ጥንት ማለት ኢትዮጰያ ናት ለጥንታዊነትም መንፈስ
አብርሀም ልጅን ሊሰዋ፣ገና ሀሞራ ጫፍ ሳይደርስ
ኢትዮጰያ በስልጣኔ ቀድማ መጥቃ ስለነበር
የካም ነገድ ገባር ሆኖ ይኖር ነበር የአብርሀም ዘር።
ከአራት ሺህ አመት በፊት፣፣ኢትዮጰያ ግሪክን ወግታ
በጦርነት አስገብራ፣፣ህዝቡን በባርነት ገዝታ
የበላይነትን ጥበብ፣፣፣ቀድማ ይዛ መቆየትዋ
ታሪክ የመሰከረው ነው የስልጣኔዋን ዋልታ።
ከብዙ ሺህ አመት ሆላም ፣ ሙሴ ከአብ ምድር ሲወለድ
ኑሮው በባርነት ነበር ለፈርኦን የካም ነገድ
ከዛም ቦሀላም መሀመድ ኢትዮጰያዊ ሚስቱን ያጨው
በዘር ከካም መቀላቀል ክብር ስለነበረ ነው።
የፍልስፍናዎች ሁሉ መሪ ፍልስፍና በአለም
አስቀድመህ ራስክን እወቅ መባሉ ለዋዛ አይደለም።
ታሪካችንም ካስካደን ኢትዮጰያዊነትም አይተርፍም።
ማንነታችን በግልፅ ካወቅን ግን አንሞትም።
***$***
በሳይንሳዊ ምሰሶ ፣÷፣ በሀቅ ላይ ተንተርሶ
በጋራ ታሪክ አቅመርስት ፣÷፣ካም አበው ባወረሱን ቅርስ
ማንሰራራት እንጂ በህብር፣ በአኩሪ ስልጣኔያችን ውርስ
ማንነታችንን ስተን<^>በጎሳ ብንፈራርስ
ኢትዮጰያዊነት አማራጭ<፣>ስለሚያጣ ፅኑ ሂወት
ወይ በመተባበር መትረፍ<> ወይ ተነጣጥሎ መሞት።
ብቻ ነውና መንገዱ<> በስተቀር ስርየት የለም
በዘረኝነት ተናቁሮ <>ታፍኖ በጥላቻ አለም።
መንግስት እንደ ቁማር አኪር<> በተገለባበጠ ወቅት
በየጎሳው ቡድን አድማ<> ከምንነዳ እንደ ከብት
ከትላንትናው ማንነት<> የነገው አዲስ ክስተት
በዲሞክራሲ እኩልነት<> ካልቀየስነው በህብር ሂደት
በሚገነጥለን ሳይሆን<> በምንዋሀድበት ፅንፍ
የሚለያየንን ሳይሆን<> የሚያመሳስለንን ቁልፍ
በታሪክ ፈለግ ውርሳችን<> ይበልጥ ለመተሳሰብ
የአንድ ስልጣኔ ወራሽ<> መሆናችንን ማስነበብ
የአንድ ነገድ እናት ልጆች<> መሆናችንን ማስገንዘብ
ሊያስተቃቅፈን ይገባል<> በጎሳ ከመተናነቅ።
ኢትዮጰያዊነታችንን <>በመንፈስ ኩራት ለማፅደቅ
በታሪክ ላይ ተመስርተን <>ማንነታችንን ማወቅ
በቋንቋ፣በዘር፣በሀይማኖት <>በመጣመር ከሌሎች ጋር
ኢትዮጰያዊነት ህብር ሆኖዋል<> ባለ ብዙ ቀለም አውታር።
ካማ ከሳባ ሲዋለድ<> አረብ ከአፍሪካ ተጋባ
የሰው ዘር ነገድ ተራባ።
ከሳባ ሰለሞን በፊት <>የሙሴ ዘር በባርነት
ሲያገለግል ካም አበው ቤት
ከዚያም ቀደም ፣በጦር ፣በንግድ ከሜሶፖታሚያ ጋራ
በሜዴቴርያ ባህር<> ከግሪክ ደምብ ወራራ
ካም አበው በመርከብ ውግያ
አሰልጥነው ሲዋኙበት<> በቅድመ ታሪክ ጦቢያ
የካም ቤት ክብርዋን ሳትለቅ <>ስትማጥቅ ከሌሎች ጋር
ኢትዮጰያዊነት ህብር ሆነ <>ባለ ብዙ ቀለም አውታር።
ካም በህዋው ጠረፍ ዳሱ <>በ,ቅድመ አለም አድማሱ
ኦሮሞም አማራም ትግሬም<> በኢትዮጰያዊ ኩሩ ቅርሱ
ፅኑ ማተብ ነው መንፈሱ <>መልኮስኮስ አይፈቅድም ነፍሱ።
ኢትዮጰያዊነት ረቂቅ ነው <>በመናፍቅ የቀን እርካብ
ሊደርሱበት የማይቻል<> በትምክህተኝነት ህዛብ
ወይ በጎሳ የበላይነት<> በጎጠኝነት ልበ እባብ
የማይሞከር እሴት ነው<> በዘረኛና በጠባብ
ኢትዮጰያዊነት ምጡቅ ናት<> በጎጥ አድማ አትደመምም
ሰንደቅ አላማ ማተብዋ <>በጠመንጃም አትነጠቅም።
በፍቅር እንጂ በጉልበት<> በእብሪት አትንበረከክም።
ሊያወድሞት የተነሱትን <>በቅፅበት የምታጨልም።
በመለኮት የፅናች ናት <>አጥፊዋን የምታከስም።
ጥራቱ እንደ ምንጭ ውሀ <>ድብብቆሽ ያልከለለው
ብሩህ እንደ ሜሮን ፀበል<> ኢትዮጰያዊነት ግልፅ ነው።
ይሄ ተለጉሞ መዳህ ~ተጨቁኖ መረጋጋት
አጎብድዶ ለአምባገነን ~እነደ መጋጃ መነዳት
ኢትዮጰያዊነት አይደለም!!
ይሄ ሆድ አምላኩ ግሳት
አጉል ማቀርሻት እንደ አራስ
እንደ ተኮላሸ ጥጃ የአምባገነንን መዳፍ መላስ
ኢትዮጰያዊነት አይደለም!!
ይህ ፈርጥጦ ሩቅ ሆኖ ~ከስደት ኬላ ማላገጥ
ከህዝብ ሰቆቃ ሸሽቶ~ ኢትዮጰያን ከጣር ማፍጠጥ
ፅዋውን አብረው ሳይቀምሱ ~ትውልዱን ከሞት ማጋፈጥ
ራስን ከሀቅ ደብቆ ~በስደት ዋሻ ማሽቃበጥ
ነገ በስልጣን ኮርቻ እንደ ታቦት ለመቀመጥ
ቀቢፀ ተስፍን ማቁነጥነጥ
ኢትዮጰያዊነት አይደለም!!
ይሄ በቁም ተደናብሮ
በመገነጣጠል ሮሮ
ጤና እንደሌለው አእምሮ
በጎሰኝነት ተሳክሮ
ወደ ሲኦል መሽቀዳደም በዘር ጥላቻ ታውሮ
ኢትዮጰያዊነት አይደለም!!
ግን ያለውድ በግዳጅ <>ተገፍትሮ ለነባርነት
እምቢኝ ማለት ለነፃነት
ከኢትዮጰያዊነት አላማ <>በየጎጥ ሳንዘናጋ
ለኩልነት መዋደቁ <>ፅዋን መቀበል በፀጋ
የመንፈስ ኩራት አብነት <>የማይተመን በዋጋ
አበው በደም ያወረሱን <>አፅመርስት ነው የዜጋ።
በጎሰኝነት ትምክት <>ጀርባው ጎጥ ያልቀደደው
አንድነታችን ከብረት <>እንዲጠነክር እንደ አበው
በኢትዮጰያዊ ማተባችን<> እንድንተምም እንደ ንብ
ደሞችን የኢትዮጰያ ልብ<> ግባችን የህዝባችን ግብ
አገራችን:ሰንደቃችን:ዜጋችን የኢትዮጰያ ህዝብ
ሲሆን ብቻ ነው ዘላለም <>ኢትዮጰያዊነታችን የሚያብብ።
አድባር ኢትዮጰያ ልደታ
የአት እናት የባህታ
ወደ እግዚያብሄር ልጆችዋን <>ለእርቀ ሰላምዋ ዘርግታ
በነቀዝተኞች ብትደቅም√
በዘረኞች ብትዳሽም√
በጎሰኞች ብትቆሽሽም√
በመናፍቃን ብታድፍም√
ኢትዮጰያ የፀሀየም ኩራብ<> የአዲስ ትውልድ ብሩህ ህልም
አውዳሚዎችዋን አውድማ<> ትነሳለች እንጂ አትሞትም።
የካም ፀዳል ጀግኖች እናት
ቅድመ አለም ፍኖት እሳት
የዘላለም ችቦ ብርሀን<> የማትሻር ህያውነት
ራእይ ናት ኢትዮጰያዊነት።
የአንድነት ደመራ ድምር
የህብረታችን ግብ ሚስጥር
የመቻቻል ረቂቅ ጥምር
የዘላለም ህብረት ሸማ
ዘረኝነትን አውድማ
የምትወጣ ከጨለማ
ኢትዮጰያዊነት ብርሀን ናት<> በአዲስ ዲሞክራሲ ፍና
በአዲስ ችቦ በአዲስ ጮራ<> የምታብብ እንደገና
የአለም ጥቁር ህዝቦች ቤዛ
እናት ፀሀይ እናት ሰላም
ኢትዮጰያዊነት ፍቅር ናት <>የአፍሪካ ዘላለም ገዳም
ያጠፍዋትን እያጠፍች<> ታበራለች እንጂ አጠፍም።
ኢትዮጰያ ዘላለም ሰላም<> ዘላለም ፀሀይ ብስራት
ለአለም ስልጣኔ ቁንጮ <>ለአለም የጥቁር ዘር ኩራት
ለወዳጆቿ ብርሀን <>ለጠላቶቿ ግን እሳት
እጅዎችዋን ወደ እግዜያብሄር<> ዛሬም እንደዘረጋች ናት።
ኢትዮጰያዊነት ጥበብ ናት<>የአለም ባህል ምንጭ ድባብ
የፈሪሀ እግዜያብሄር ምኩራብ
አለምን በጉዲፈቻ<> የምትታደግ ከረሀብ
ታናሹ ያቆብ በችጋር <>በወንድሞቹ ታፍኖ
በጦርነት ለካም ንጉስ<>ተሽጦ ቀርቦ ለመኖ
ንጉሱ ግን በአበው ባህል<>በኢትዮጰያዊነት አርአያ
በጉዲፈቻ አሳደገው<>እስራኤል እንዳትሆን ባርያ።
ሙሴም በአገልግል አንቀልባ<>አባይ ዳር በአራስነቱ
ተጥሎ አይታ የቅን ባህል<>የካም ዙፍን ልእልቲቱ
ሂወቱን ከሞት አድና><አሳድጋ ለአለም ዝና
አበቃችው እንዲያበቃ<>እስራኤልን ለቡኩርና።
ጌታ መድሀኒታችንም><በህፃንነት ክርስቶስ
እንዳይታረድ አምልጦ<>በአረመኔው ንጉስ ሄሮድስ
በአለም ቤዛነቱ ምግባር<> በተልኮው ሊያገለግል
ተወለደና ካበተ<> በካም ምድር በአበው ባህል።
የነብዮ መሀመድም ቤተሰብ<> በስደት ማአበል
ወደ ካም ቤት ሸሽተው መተው<> ከቋርያ ሸከፍ በቀል
በኢትዮጰያዊነት ባህል ስር <>ተረፉለት በመጠለል
ብሩህ እንጂ ምጡቅ ጥበብ <>ኢትዮጰያዊነት መች በልክ የሚካኑበት ቅጥፈት ነው<> በዘረኝነት ንትርክ።
የኢትዮጰያዊነት ጥበቡ<> መደናበር ሳይሆን ግቡ
በሆድ አምላክ ከመታወር <>በደም ጭቃ ከመነከር
ለንቅዘት ጣኦት ከመስገድ <>ተፈቃቅዶ መከበር
መቻቻል ነው በሀገር ህብረት
በአርቆ ማስተዋል ሚስጥር >< አንድነት በካበተበት።
ለነገ ትውልድ ተስፍ >< አዲስ ጎህ እንዲታይበት
የልእልና መክሊት ነው ><ራእይ ነው ኢትዮጰያዊነት።
በአለም ሀይማኖቶች ፅንሰት>< ግዙፍ ታላቅነት ያለው
ኢትዮጰያዊነት ጥልቅ ነው።
ዘንድሮ ግን ሰይጥነናል>< ኢትዮጰያዊነት ንቀት
እንደ ሱሜር አምላክ ከድተን
እንደ ሳጥናኤል በቲቢት>< ያለኔ እግዜር የለም ብለን
እንደ ባቢሎን በቋንቋ>< ተገማግመን ተደናቁረን
የምንኳኳበት እንጂ>< የምንግባባበት አተን
ህሊናችንን ከርችመን ><ወደ ሲኦል ብንጋጋም
ኢትዮጰያዊነት ርቱ ነው ><በትብትብ ልብ አይረታም
ስማችን ዛሬ ቢበዛም ><ማሞካሻችም ቢንዛዛም
አንዳንዴም በነፍጠኝነት√
አአንዳንዴም በውሾች ጩሀት√
አንዳንዴም በሀድጊ ጭነት √
አንዳንዴም በጨርቅ ዝቅጠት√
መንፈሳችንን ለማቁሰል ><ያለ ለከት ብንጠራም
ኢትዮጰያዊነት ርቱ ነው ><በነቀዝ አፍ አይፈታም።
ምክንያቱም ከመሰረቱ ><ኢትዮጰያዊነት እምነቱ
ህዝብን ነፃ ማውጣትና<^> ነፃነት መንጠቅ አይነቱ
የተለየ ነው ስርአቱ።
ለህዝብ ነፃነት ገድል <^>ሂወቱን መስዋት አርጎ
እንደገና ነፃነቱን <^> ከህዝቡ እጅ ሰንጎ
በጠመንጃ ጉልበት ነጥቆ<^> የአለም ዲሞክራሲን ሸማ
የሀፍረት ማቅ አከናንቦ <^>ኢትዮጰያዊነቱን አርማ
በአንድ አናሳ ጎሳ ቡድን <^>, በዘረኝነት ግፍ አድማ
በአደባባይ እያደማ
ነፃ አውጪ ነኝ ማለት ደሞ
ለእብሪተኝነት እንጂ <^> መች ለነፃነት ቆሞ
ኢትዮጰያዊነት ምጡቅ ነው <^>ለእኩይ ስንዝር አይሞላም
በጠባብ ክንድ አይለካም
የዘረኝነት መቀነት <^>ለሽንጧ ቁመት አይበቃም።
ስለዚህ,,,,,,,,,,, ሰለዚህ
ኢትዮጰያዊነት <>አስቀድሞ ራስን አውቆ
የካም አበው መነሻውን<> ማንነቱንም ጠንቅቆ
በአንድ እናት አገር ልጅነት <¢>የብረት ሸማ ተላብሶ
በአለም ስልጣኔ መስራች<¢> ሳይሳዊነት ምሰሶ
በስልጣኔያችን ታሪክ <¢>ከፅንፍ ፅንፍ ታድሶ
እያስተጋቡ በርእቱ<¢> ለነገ ትውልድ ሰንደቅ
ከህዝብ፣ለህዝብ፣በህዝብ <¢>ዲሞክራሲን ማንፀባረቅ
ነውና ኢትዮጰያዊነት<¢> ጥቁር እሳት ፀሀይ ሰላም
ኢትዮጰያ የካም ግንድ ናት <¢>ኢትዮጰያ የአፍሪካ ገዳም
ያጠፍዋትን እያጠፍች <¢>ታበራለች እንጂ አትጠፍም።
ጥራቱ እንደ ምንጭ ውሀ<¢> ድብብቆሽ ያልከለለው
ብሩህ እንደ ሜሮን ፀበል <¢>ኢትዮጰያዊነት ግልፅ ነው።
ይሄ ተለጉሞ መዳህ <^> ተጨቁኖ መረጋጋት÷
አጎብድዶ ለአምባገነን <^> እንደ መጋጃ መነዳት
ኢትዮጰያዊነት አይደለም¡¡!!
ይህ ፈርጥጦ ሩቅ ሆኖ <^> ከስደት ኬላ ማላገጥ
ከህዝብ ሰቆቃ ሸሽቶ <^> ኢትዮጰያን ከጣር ማጣፈጥ
ፅዋውን አብረው ሳይቀምሱ <>ትውልዱን ከሞት ማጋፈጥ
ራስን ከሀቅ ደብቆ <>በስደት ዋሻ ማሽቃበጥ
ነገ በስልጣን ኮርቻ<> እንደ ታቦት ለመቀመጥ
ቀቢፀ ተስፍን ማቁነጥነጥ
ኢትዮጰያዊነት አይደለም!!
ይሄ በቁም ተደናብሮ
በመገነጣጠል ኑሮ
ጤና እንደሌለው አእምሮ
በጎሰኝነት ተሳክሮ
ወደ ሲኦል መሽቀዳደም <¶> በዘር ጥላቻ ታውሮ
ኢትዮጰያዊነት አይደለም¡!!
ይሄ በቅዥት ተናውጦ <^>ማስረከብ ሰብአዊ ክብርን
እንደ አጋሰስ ሞኮር ኮዳ<^> ሳይንተራሱ ክንድን
ኢትዮጰያዊነት አይደለም!!
ግን ያለውድ በግዳጅ <^>ተገፍትሮ ለነባርነት
እምቢኝ ማለት ለነፃነት
ከኢትዮጰያዊነት አላማ <^> በየጎጥ ሳንዘናጋ
ለኩልነት መዋደቁ ፅዋን <^>መቀበል በፀጋ
የመንፈስ ኩራት አብነት<^> የማይተመን በዋጋ
አበው በደም ያወረሱን<^> አፅመርስት ነው የዜጋ።
በጎሰኝነት ትምክት <^>ጀርባው ጎጥ ያልቀደደው
አንድነታችን ከብረት <^>እንዲጠነክር እንደ አበው
በኢትዮጰያዊ ማተባችን <^>እንድንተምም እንደ ንብ
ደሞችን የኢትዮጰያ ልብ<^> ግባችን የህዝባችን ግብ
አገራችን:ሰንደቃችን:ዜጋችን<^> የኢትዮጰያ ህዝብ
ሲሆን ብቻ ነው ዘላለም<^> ኢትዮጰያዊነት የሚያብብ።
ሎሬት ፅጋዬ ገብረ መድህን
ጦቢያ መፅሄት
ቅፅ 5 ቁጥር 10
1990 ኢቲ





TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: Laureate Tsegaye Gebre Medhin's prophecy in year 1990 EC

Post by TGAA » 15 Sep 2020, 18:18

Thank you, DTT, UPLIFTING. Tsegaye Gebre Medhin is to Ethiopians as Alexander Pushkin is to Russians. Eternal.

EthioRedSea
Member
Posts: 4089
Joined: 31 Aug 2019, 11:55

Re: Laureate Tsegaye Gebre Medhin's prophecy in year 1990 EC

Post by EthioRedSea » 15 Sep 2020, 18:30

That is what the writer thought. But in reality Ethiopia is savage and primitive, killing and attacking non-Amharas. ETHiopia is the wrecth of the earth. Most of the history Tsegaye wrote is about Aksumite Ethiopia and not about the Ethiopia at the time of Menelik and there after.

gagi
Member
Posts: 618
Joined: 16 Jun 2013, 16:34

Re: Laureate Tsegaye Gebre Medhin's prophecy in year 1990 EC

Post by gagi » 15 Sep 2020, 19:29


“የኢትዮጰያዊነት ሚስጥሩ!
ወንድምህን መጥላት ሳይሆን÷
ራስክን ማወቅ ነው ከስሩ“


ይድረስ በጎጠኝነት ለታወሩ

What a masterpiece! It just transports one who reads and understands to an extraordinary height, to a different universe!

Thank you for sharing!

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: Laureate Tsegaye Gebre Medhin's prophecy in year 1990 EC

Post by TGAA » 15 Sep 2020, 19:45

Ethiored

ኢትዮጰያዊነት ምጡቅ ነው <^>ለእኩይ ስንዝር አይሞላም
በጠባብ ክንድ አይለካም
የዘረኝነት መቀነት <^>ለሽንጧ ቁመት አይበቃም።

Is your pea brain wide enough to contain this .

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9765
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: Laureate Tsegaye Gebre Medhin's prophecy in year 1990 EC

Post by DefendTheTruth » 16 Sep 2020, 14:29

TAGA, gagi and others,

I just felt that his words were purely prophetic considering at least the time when he wrote the piece and the current real situation on the ground.

Just consider the following part.
በሳይንሳዊ ምሰሶ ፣÷፣ በሀቅ ላይ ተንተርሶ
በጋራ ታሪክ አቅመርስት ፣÷፣ካም አበው ባወረሱን ቅርስ
ማንሰራራት እንጂ በህብር፣ በአኩሪ ስልጣኔያችን ውርስ
ማንነታችንን ስተን<^>በጎሳ ብንፈራርስ
ኢትዮጰያዊነት አማራጭ<፣>ስለሚያጣ ፅኑ ሂወት
ወይ በመተባበር መትረፍ<> ወይ ተነጣጥሎ መሞት።
ብቻ ነውና መንገዱ<> በስተቀር ስርየት የለም
በዘረኝነት ተናቁሮ <>ታፍኖ በጥላቻ አለም።
መንግስት እንደ ቁማር አኪር<> በተገለባበጠ ወቅት
በየጎሳው ቡድን አድማ<> ከምንነዳ እንደ ከብት
ከትላንትናው ማንነት<> የነገው አዲስ ክስተት
በዲሞክራሲ እኩልነት<> ካልቀየስነው በህብር ሂደት
በሚገነጥለን ሳይሆን<> በምንዋሀድበት ፅንፍ
የሚለያየንን ሳይሆን<> የሚያመሳስለንን ቁልፍ
በታሪክ ፈለግ ውርሳችን<> ይበልጥ ለመተሳሰብ
የአንድ ስልጣኔ ወራሽ<> መሆናችንን ማስነበብ
የአንድ ነገድ እናት ልጆች<> መሆናችንን ማስገንዘብ
ሊያስተቃቅፈን ይገባል<> በጎሳ ከመተናነቅ።
ኢትዮጰያዊነታችንን <>በመንፈስ ኩራት ለማፅደቅ
በታሪክ ላይ ተመስርተን <>ማንነታችንን ማወቅ
በቋንቋ፣በዘር፣በሀይማኖት <>በመጣመር ከሌሎች ጋር
ኢትዮጰያዊነት ህብር ሆኖዋል<> ባለ ብዙ ቀለም አውታር።
ካማ ከሳባ ሲዋለድ<> አረብ ከአፍሪካ ተጋባ
የሰው ዘር ነገድ ተራባ።
ከሳባ ሰለሞን በፊት <>የሙሴ ዘር በባርነት
ሲያገለግል ካም አበው ቤት
ከዚያም ቀደም ፣በጦር ፣በንግድ ከሜሶፖታሚያ ጋራ
በሜዴቴርያ ባህር<> ከግሪክ ደምብ ወራራ
ካም አበው በመርከብ ውግያ
አሰልጥነው ሲዋኙበት<> በቅድመ ታሪክ ጦቢያ
የካም ቤት ክብርዋን ሳትለቅ <>ስትማጥቅ ከሌሎች ጋር
ኢትዮጰያዊነት ህብር ሆነ <>ባለ ብዙ ቀለም አውታር።
ካም በህዋው ጠረፍ ዳሱ <>በ,ቅድመ አለም አድማሱ
ኦሮሞም አማራም ትግሬም<> በኢትዮጰያዊ ኩሩ ቅርሱ
ፅኑ ማተብ ነው መንፈሱ <>መልኮስኮስ አይፈቅድም ነፍሱ።
ኢትዮጰያዊነት ረቂቅ ነው <>በመናፍቅ የቀን እርካብ
ሊደርሱበት የማይቻል<> በትምክህተኝነት ህዛብ
ወይ በጎሳ የበላይነት<> በጎጠኝነት ልበ እባብ
የማይሞከር እሴት ነው<> በዘረኛና በጠባብ
ኢትዮጰያዊነት ምጡቅ ናት<> በጎጥ አድማ አትደመምም
ሰንደቅ አላማ ማተብዋ <>በጠመንጃም አትነጠቅም።
በፍቅር እንጂ በጉልበት<> በእብሪት አትንበረከክም።
ሊያወድሞት የተነሱትን <>በቅፅበት የምታጨልም።
በመለኮት የፅናች ናት <>አጥፊዋን የምታከስም።
ጥራቱ እንደ ምንጭ ውሀ <>ድብብቆሽ ያልከለለው
ብሩህ እንደ ሜሮን ፀበል<> ኢትዮጰያዊነት ግልፅ ነው።
ይሄ ተለጉሞ መዳህ ~ተጨቁኖ መረጋጋት
አጎብድዶ ለአምባገነን ~እነደ መጋጃ መነዳት
ኢትዮጰያዊነት አይደለም!!
ይሄ ሆድ አምላኩ ግሳት
This message was at that time primarily, I think, for those in power during those days and who considered themselves the ultimate force in the country who would going to shape the course and destiny of the nation of Ethiopia, by mere power of gun. They had at the time in fact all the power it takes to keep everybody under serveillance and remove anybody they deemed a hinderance to the course they themselves envisaged for Ethiopia. The good Poet himself was under their close surveillance but still he dared to tell them in unmistakable words to first know where they came from before trying to chart or envisage their future. But they ignored the message and pursued their own course.

Today the good Poet Laureate is no more with us but those who were so narcissist and consumed just about their power are also on the retreat and holding for a while at their last strong hold, which we are not yet sure for how long they could hold on there.

But we can say with all certainity that the people of Tigray are not the right choice to negotiate about their Ethiopianism, they know where they come from and as such understand where they should head to in the future, except the manga part of the society which is already on the retreat.

The manga politics is today on the retreat!

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: Laureate Tsegaye Gebre Medhin's prophecy in year 1990 EC

Post by TGAA » 16 Sep 2020, 15:06

You encapsulated the Laureate Tsegaye Genre Medhn's Ethiopia. He is the northern star for all lost souls of Ethiopia.what a gift he was?

gagi
Member
Posts: 618
Joined: 16 Jun 2013, 16:34

Re: Laureate Tsegaye Gebre Medhin's prophecy in year 1990 EC

Post by gagi » 16 Sep 2020, 17:53

Tsegaye was not just a renowned poet; he was a philosopher. His multicultural and multi-faith background of Christian God and Oromo Waka allowed him to have keen, observant and deep thinking mind! Such duality served him as inspiration for him to deeply search for the identity and fabric of Ethiopians. He was a philosopher who understood the complex array or web of identities that formed Ethiopia!

Post Reply