Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Member+
Posts: 9763
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by DefendTheTruth » 06 Sep 2020, 12:38

Guest1 wrote:
06 Sep 2020, 12:05
Abiy has no the chance to be a dictator. If the Amharas and the southerners pull out their support to his administration, there will no be an Abiy led administration let alone a dictator one. This noise making is about nothing.
ያሻውን መፈጸም ከቻለ፤ በሃይል መቅጣትም ከቻለ ዲክቴተር ካልተባለ ምን ልባል?
ዲክቴተር ስንት ወታደር ያስፈልገዋል? ክክክክክክክክክክክክክ እንቅጠር። የአቢይ ወታደር ስንት ሺ ይደርሳል? 100 000? የኢሳያስ ወታደሮችስ? የአሜሪካንና የአረብ አገር ወታደሮችስ አይረዱትም?

አማራና ደቡብ ቢያፈነግጥ ምን ሊፈጠር? አገር ልትፈርስ? አገር መግዛት ሊያቀተው? ምንም ነገር ኣይመጣም። ሁለቱ ከተስማሙ አዲስ አበባን መያዝ ይችላሉ ምንም ጥርጥር የለውም። ኢሳያስ ወታደሩን ኣይልክም የኣለም ህግ ኣይፈቅድለትም። የኦሮሞያ ጊዜያዊ ትርምስ ይፈጠራል። ከመተላለቅ ብለው ወደ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር የግድ ሁሉም ይገባል።
Trying or wishing to topple the incumbent party from power by a means of violence and then claiming about a democratic transition to follow: What a mix?

But let me ask you one question: is there anybody in Ethiopia today who can be a leader just because that person may wanted to be a leader?

Hope you will give me a honest answer.

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9763
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by DefendTheTruth » 06 Sep 2020, 12:49

Horus wrote:
05 Sep 2020, 16:58

የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?
ዲንቄም ፖልቲካል ሳይንስ። In which kind of a political science is that someone organise himself as an opposition party and then wish himself to be granted a power for himself without any mandate from the electorate in the governing party?

Could you provide any precedence to that anywhere in the world?

"yes, i tried to organise myself as an opposition party but i failed to effect anything through that, now I wish you give me a share of the power of the ruling party as a good will." Horus the doofus!

Doofaa wayi! Yehen inde science ketemark, temerk seihon keserk bebal yeshalal.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 06 Sep 2020, 15:55

አራት፣ ያቢይ አህመድ ቁልፍ ቡድን አባላት እነማን ናቸው? የተጽኖ ቡድን አባላትስ መራጭ አባላትስ? በአጭሩ እንዲ ነው።

ማንኛውም መንግስት ዴሞክራሲም ሆነ ዲክታቶራዊ አራት ረድፎች አሉት ። እንዲያም ትላልቅ ሰፊ አባላት ያላቸው ድርጅቶች ሁሉ ሕግ የገለጻሉ ።

አንደኛድ ረድፍ መሪው ነው ፣ ለምሳሌ አቢይ አህመድ ማለት ነው ። ያንድ መንግስት መሪ በአራተኛው ረድፍ ማለትም በሰፊው መራጮች ተምርጦ ያገሩ ሕግ (ወይም የድርጅቱ ሕግ) በሚያዘው መሰረት የስልጣን ግዜው ሲያበቃ የሚወርድ ከሆነ ዴሞክራታዊ መሪ ይባላል። ይህ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ኖሮ አያቅም ። ከዚህ በተለያዩ ዘዴዎች ስልጣን ላይ ወጥቶ በጉልበትም ሆነ በማጭበርበር እስከ ፈለገና እስከ ቻለ ሚገዛ ዲክታቶር ነው፣ አምባገነን ነው፣ ንጉሰ ነው፣ ያሻችሁትን በሉት ። አቢይ ዲክታቶር ነው ወይስ ዴሞክራቲክ መሪ የሚለው በሚቀጥለው መርጫ ይወሰናል ። አሁን ግዜያዊ መሪ ስለተባለ ።

ሁለተኛ ረድፍ የቁልፍ (ወሳኝ) ደጋፊ ቡድን ይባላሉ ። አቢይ አለ እነዚህ ሰዎች አንድ ቀን በስልጣን አያድርም ። እነዚህ ቁልፍ ረድፍ አባላት እነማን ናቸው ። የቤተ መንግስት ዘብ፣ ሴኩሪቲ፣ የፖሊስ ሌላ ልዩ ሃይል አዛዦች፣ የጦር ሃይል አዛዦች፣ የብልጽግ ና ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች እንደነ ታዬ ደንዳ፣ አዳነች አቤቤ፣ እጅግ የቅርብ አማካሪዎች (ምስጢር ተካፋዮች)፣ በፒፒ ውስጥ በድምጽ የሾሙትና ለማውረድ ሚችለው ጉባኤ ወዘተ ያካትታል።

ስለዚህ ያቢይ እጅግ ተቀዳሚ ስራ ይህን ቁልፍ ረድፍ ማስተባበር፣ ደሞዝ መክፈል፣ መንከባከብ፣ የሚያፈነግተውን ማባረች፣ ሹም ሽር ማድረግ ፣ መገምገም ነው። ከነዚህ በቂ ቁጥር ከክከዱ (እንደ ወሳኘታቸው) ያቢይ ስልጣን አደጋ ላይ ይወድቃል ። የሚሳካ ኩዴታም የሚደረገው በዚህ ረድፍ ነው እንጂ ከመንግስት ውጭ ባሉ የተጽኖ ረድፍ (ምሳሌ እነጃዋር) አይደለም ። ከቁልፍ ረድፍ ውጭ ያሉ ማመጽ እንጂ ኩዴታ ማድረግ አይችሉም።

ስለሆነም እነ አዳነችን፣ ሺመልስን፣ ታዬን ወዘተ ስራዬ ብላችሁ ተከታተሉ ቁልፍ ረድፉ ምን ላይ እንደለ ለማወቅ ። ለማ መገርሳ እንዴት ከቁልፉ ረድፍ እንደ ተወገደ ልብ በሉ ። የቁልፍ ረድፈኛ ስራ ያቢይን ስልጣን መንከባከብ ነው ። ያቢይ ሃላፊነት እነሱን መንከባከብ ነው። ቁልፍ ረድፈኛ የስልጣን ተፎካካሪ ሊሆን ክልክል ነው። ያቢይን ስልጣን፣ ገቢ ምንጭ (ሬቬኑ)፣ የሱን ዝና እና ክብር ሚያበላሽ ባስቸኳይ ይወገዳል፣ ወይም ይከለሳል (ምሳሌ ታከለ)።

ሶስተኛው ረድፍ የተጽኖ ረድፍ ይባላሉ ። ልክ ስሙ እንደሚለው የዚህ ረድፍ ስራ ተጽኖ መፍጠር ነው። በማ ላይ? በመራጩ ረድፍ (በህዝቡ) ላይ ። የዚህ ረድፍ አባላት አንዳንዶቹ በራሱ በመሪው (ባቢይ) ይመለመላሉ፣ ለምሳሌ ዲያቆን ክብረት ። ብዙዎቹ ግን የሚመለመሉት በቁልፉ ረድፍ ነው። ልብ በሉ ታከለ ኡማ ስንትና ስንቱን በመኪና እና በቤት ጉቦ ተጽኖ ፈጣሪዎችን መመልመያ ያደረገው ጥረት ።

በዛሬቱ ኢትዮጵያ የቁልፉ ረድፍ ምን ያህል መኪና፣ ገንዘብ፣ ቤትና መሬት እንደ ዘረፈ ማንም አያውቅም ። የዚህ ሰሞን ዝርፊያ ባብዛኛው በተጽኖ ረድፉ የተበላ ነው ። አዲሱ የኦሮሞ ተረኛ አገዛዝ ገና የተረጋጋ ሰፊ ተጽኖ ደጋፊ መደብ ስላልፈጠረ ይህ ሁሉ ገሃድ ሌብነት ያንን ሰርቶ ለምርጫው ሕዝቡን የሚያሳምኑ ሰፊ ተጽኖ ፈጣሪ መደብ ለመገንባት ነበር።

የተጽኖ ረድፍ አባላት በቅድሚያ የብልጽ ግ ና አባልት ናቸው። ከዚያም ሚዲያ ውስጥ ያሉ፣ አርቲስቶች፣ ምሁራን ፣ ነጋዴዎች፣ ጎረቤት አገሮች (ኢሳይስ አፈውርቅ) በአንድ ቃል በሕዝቡ ውስጥ አቢያና ብልጽኛ ፓርቲ ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚሰሩት ናቸ። የዝርፊያው መጠንም የሚያጦዙት እነዚህ ናቸው።

አራተኛ ረድፍ መራጩ ሕዝብ ነው። ይህ መደብ በዴሞክራሲ እንኳ በ4 ወይ 5 አመት አንዴ ድምጽ ከመስጠት ያለፈ ሃይል የለውም ። በዴሞክራሲ ውስጥ ይህ መደብ ሰፊ እንዲሆን ይፈለጋል። አንዳንድ አገር ፕሬዚዳንቱን በቀጥታ ቢመርጥም ከላይ ሌላ ምርቻውን ሚያጽድቅ ቡድን ስላለ ባብዛኛው ቦታ የህዝብ ድምጽ ሙሉ በሙሉ ወደ ሃይል አይለወጥም ።

እንደ ኢትዮጵያ ባለ ያንድ ፓርቲ ዲክታቶር እና የጎሳ ሰርዐት የህዝብ ድምጽ ያለው ሃይል ምንም ነው። የፓርቲ አባላት (ተጽኖ ረድፍ) ቁልፍ ረድፍን ይመርጣል። ቁልፍ መደብ መሪውን (አቢይን) ይመርጣል ። ፓርላማ የተባለው ቁልፍ ረድፍ ራሱ ከፓርቲው ተጽኖ ቡድን የተለቀመ ነው። ስለሆነም አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሰራት የሕዝብ ድምጽ ተረት ነው ።

አቢይ አህመድ ዲክታቶር የመሆን እድል አለው ወይ የሚለውን ሌላ ፖስት ላይ እመለስበታለሁ

ይቀጥላል
Last edited by Horus on 07 Sep 2020, 22:25, edited 3 times in total.

sun
Member+
Posts: 9313
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by sun » 06 Sep 2020, 18:51

Horus wrote:
05 Sep 2020, 20:39
sun = Defend The Truth መሆንክን ስለ አመንክ አመሰግናለሁ ።
Dhuubee, 8)

Okay. Now that you have discovered the original and the virgin truth, nothing but the truth, did you smoke and sniff too much to celebrate your new discovery and then start rolling all over the floor, again and again, laughing loud and thanking Sun? :P

sun
Member+
Posts: 9313
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by sun » 06 Sep 2020, 19:36

Guest1 wrote:
06 Sep 2020, 08:47
እውነተኛ ታሪክ
ኣንድ ቀን መንግስቱ ግቢው ውስጥ ሲዘዋዋር እዚያው ያሳሰረውን ጓደኛውን ከእሰር ቤቱ ደጃፍ ቁጭ ብሎ አገኘው። ጓደኛው ደፋር ሰው ነበርና በንዴት “አንተም መሪ ሆነክ’’ አለው።
መንግስቱም ‘ኣንተ ልትሆን ነበር?' ብሎ መለሰለት ይባላል ክክክክክክ
ለመሪነት ኣትበቃም ተባባሉ። መንግስቱ መሪ መሆን የቻለው ብቃት ስለነበረው ኣይደለም?
On the other hand, it is said that nothing is more victorious than victory itself, regardless of what we happen to think about leaders.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 06 Sep 2020, 23:14

አምስት፣ እነዚህ ያቢይ አገዛዝ (ሪጂም) አባላት ከየት ነው ሚመለመሉት? እንዴት እና በምን መለኪያ?

ከላይ እንዳልኩት የአንድ መሪ መሰረታዊ ፍላጎቶች ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ዝና እና ክብር ናቸው። ከነዚህ ሃይልና ገንዘብ እጅግ ቀዳሚ ናቸው። ስለሆነም አንድ መሪ ዙሪያ ቁልፍ ደጋፊዎች ሲመረጡ የሴኩሪቲ፣ ፖሊስና ጦር አለቆች በጣም የቅርብ ጓደኛች፣ እጅግ ሚታመኑ ጓዶች መሆን አለባቸው ። ቀጥሎ እንደ ጉምሩክ ታክስ ባንክ የመሬትና ቤት መስኮች እንዲሁ በቅርብ ዘመድ፣ ጎሳ ወይም ጓደኛ መያዝ አለባቸው። በኢትዮጵያ ገንዘብ ማለት መሬትና የመንግስት ገቢዎች ነው ። እኛ ዘይት ወይ ወርቅ የለንም ። ወደፊት ኤሌክትሪክ የሃብት ምንጭ ይሆናል ።

ስለሆነም መከላከያው፣ ደህንነቱ፣ እነ መሬት፣ መንግስት ገቢዎች የተያዙት በኦሮሞች ነው። በአሃዝ መረጃ ከ100 ስንት % ኦሮሞች ናቸው የሚለውን ምስጢር እስካሁን አይታወቅም ። ሌሎች ላማራ ደበብ፣ ወዘተ ክልል ተዋጽኦ የገቡ ባብዛኛው ቁልፍ ባልሆኑ ሚኒስቴሮች የገቡ አሉ ።

ባንድ ቃል የመንስቱ ቁልፍ መደብ የሚመለመለው እጅግ በቅድሚያ ለአቢይ ታማኝ ነው ወይስ አይደለም? ተብሎ ነው። ታማኝ ሆኖ ከተገኘ ኦሮሞ ነው ወይስ አይደለም ? ተብሎ ነው። ከዚያም የክልል አስተዋጽኦ ከዚያ ካለፈ አንዳንድ በክህሎት በችሎያ ይመለመላል። ልብ በሉ ታከለ ታማኝ ኦሮሞ ስለሆነ ነው ያዲሳባ ከንቲባ የሆነው ። ችሎታ ስለሌለው ሹም ሽር ተደረገበት። ሁሉም ቦታ እንደዚያ ነው ።

ሹም ሽርና መቅጠር ማባረር በዛ ማለት የሪጂሙ ያገዛዙ ቁልፍ አባላት ብቃትና ክህሎት ዝቅተኛ ወይም አጥጋቢ አለመሆን ማለት ነው ። ዋናው መልኪያ ትማኝነትና ታዛዥነት ስለሆነ ።

ደሞ በኦሮም ፖልቲካ ኤሊቶች መሃል ባለው የስልጣን ሽኩቻ ራሱ አቢይ ቁልፍ ደጋፊ ብሎ የመለመላቸው ኦሮሞች ራሳቸውን ስልጣን፣ ሃብት፣ ዝናና ክብር ሲገነዱ ስለሚገኙ ይባረራሉ ። ጥሩ ምሳሌ ለማ ነው።

እነጃዋር ከመንድስት ውጭ ስለሆኑ አቢይን በሃይል አስወግደው መንግስት መያዝ ነው አላማቸው።

ይቀጥላል

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 07 Sep 2020, 00:39

ስድስት፣ ስለዚህ አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ባህሪ ምንድን ነው? በአሁን ወቅት የራሱ ሪጂም ካራክተር ይልዟል ወይ?

በፖለቲካ አለም አንድ አገዛዝ (ሪጂም) ከፖለቲካዊ ባህሪው የተነሳ የራሱ ጸባይ (ካራክተር) አለው ። አንዱ ሞናርኪ፣ ሌላው አውቶክራሲ፣ ሌላው አውቶሪታሪያን፣ ዲክታቶሪያል፣ ዴሞክራቲክ አገዛዝ ይባላ።

በእኔ ግንዛቤ የ27ቱ ዎያኔ አገዛዝ አውቶሪታሪያን የጎሳ አገዛን (authoritarian ethnocracy) ነበር ። የአቢይ አገዛዝ አሁንም ኤትኖክራቲች (የጎሳ አገዛዝ) ነው። ያቢይ አገዛዝ ልክ እንደ መልስ አውቶሪታሪያን ነው ወይ? አይደለም ። ሪፎርሚስት እና ግዜያዊ (ትራንዚሽናል) ነው። እስከ ሚቀጥለው ምርጫ ድረስ የሽግግር ጎሳዊ አገዛዝ ብዬዋለሁ ።

ያቢይ (ረጂም) አስተዳደር ዴሞክራቲክ አይደለም ። ሙሉ አውቶሪታሪያን ሪጂም አይደለም ። የሽግግር ጎሳዊ አገዛዝ ነው። ኤትኖክራቲች ማለት ልክ ዴሞክራቲክ ሕዝባዊ እንደ ሚባለው ኤትኖክራቲክ ጎሳዊ ማለትም የጎሳ አገዛዝ ነው። ኤትኖክራሲ ማለት ወይ አንድ የጎሳ ቡድን ወይም የተወሰኑ ቅንጅት እንደ ጎሳ አንድ አገር ወይም ያገሩን ዜጎች ሁሉ ሲገዙ ማለት ነው። ፖለቲካና መብት በዜግነት ሳይኖን በጎሰኝነት ላይ ሲመሰረት ማለት ነው።

ለ27 አመት የነበረው ኤትኖክራሲ ቁንጮ የትግሬ ቡድን ሲሆን ዛሬ ያለው ያገዛዙ ቁንጮ የኦሮሞ ቡድን ነው። ይህን አንዱ የኦሮሞ ሄጂሞኒ፣ ሌላው ኦሮሙማ ይለዋል። አቢይ ወደደም ጠላም የዚህ ቡድን አለቃ ነው። እናም ትልቁ ያቢይ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ችግርና ተአማኒነት እያሳታው ያለው የፖለቲካ ቅርቃር ይህ የኦሮሞ ሄጂሞኒነት ነው ።
Last edited by Horus on 07 Sep 2020, 14:18, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 07 Sep 2020, 12:01

ሰባት ፣

አቢይ አህመድ ለስንት ግዜ ይገዛል?
ከስልጣን የሚወርደው እንዴት ነው?
ለምን ይወርዳል?
ማነው ሚተካው?
ለምንድን ነው የሚተካው ቡድን ሊተካው የሚችለው?

በመጀመሪያ የአቢይ መንግስት ለሚቀጥለው አመት ስልጣን ላይ ይቆያል ። በሚቀጥለው ምርጫ ካሸነፈ ሌላ 5 አመት ይቆያል ። ሁለተኛውን ምርጫ ካሸነፈ ሌላ 5 አመት ይገዛል ። ስለዚህ በኩዴታ ወይም በሬቮሉሽን ካልተወገደ በተቀር ያቢይ አገዛዝ ከአንድ እስከ 11 አመት ይቆያል ። አቢያ ዲክታቶር ከሆነ እስከ ሚሸመግል ማለትም ለሚቀጥሉት 30 አመት ሊገዛ ይችላል ። ይህ ከሆነ ግን ሌላ አብዮት ይኖራል ።

አቢይ ከራሱ ጄኔራሎች ጋር ችግር ከገባ በማንኝውም ግዜ በኩዴታ ከስልጣን ይወርዳል ። ከአምስት ወይም አስር አመት በኋላ ዴሞክራሲ ከመጣ በምርጫ ግዜው አልቆ በፈቃዱ ወንበር ይለቅ ይሆናል። እነዝህ ሁለት ቢሆኖች ካልሆኑና የብልጽ ኛ ዲክታቶር መንግስት ከቀጠለ በአዲስ የህዝብ በአዲስ አብዮት ይወርዳል። ከኩዴታ፣ ምርጫ እና አብዮት ወጭ ያቢይ መንግስት የሚወርድበት ሁኔታ አለ፤ እሱም ፍጹም ቀውስ ነው። በቀውስ የሚወርደው መራጩ መደብ ( ሕዝቡ) ስላመጸ አይደለም ። ቁልፍ ደፊዎቹ ከሱ ጋር መቆምን ትተው እሱን ሲቃወሙ ነው። ሕዝቡ ተቃውሞ ግን ቁልፍ ረድፎች ካቢይ ጋር እስከ ቆሙ እናድረስ አቢይ አይወርድም ። ግ ን ቁልፍ ቡድን አቢይ እንዲነሳ ከወሰነ አቢይ ይወርዳል ። ቁልፎች ካቢይ ጋር እስከ ቆሙ አቢይ አይወርድም፣ ያኔ አቢይ ዲክታቶር ይሆናል።

አቢይ ለምን ይወርዳል? ይህ ሁኔታ ሰፊና ወስብስብ ቢሆንም፣ ያቢይ መንግስት የሚወርደው የቁልፍ ደጋፊ ረድፍ፣ የተጽኖ ረድፍ፣ የመራጩ ሕዝብ ጥቅምና ህልውና ፍጹም አደጋ ላይ ሲደርስ እና የውጭ አበዳሪና ተጽኖ አድራጊ ሃኢሎች ጥቅም አደጋ ላይ ሲወድ ነው።

የሚተካው ፓርቲ የነዝህን አራት ረድፎችን ጥቅምና ህልውና የሚያረጋጥ መፍትሄ ይዞ ሚመጣው ነው። በአሁን ወቅት ልማታዊ መንግስት የሚባል ዲክታቶራዊ ፕሮግራም አለ። አቢይ መደመራዊ ልማት (ብልጽግ ና) ብሎታል። የዚህ ፕሮግራም ፖለቲካዊ ይዘቱ ገና መፈተን አለበት። በመሰረቱ ዲክታቶራዊ ካፒታሊዝም ማለት ነው። የኢዜማ ሶሺያ ዴሞክራሲ ምን እንደ ሆነ ይታወቃል። ሊብራል ዴሞክራሲ የሚሉ ግ ን ሙሉ ፍኖተ ካርታ የሌላቸ ብዙ ቢሆኑም ከሳሚ ናቸው ።

የቅርብና ልጅም ዘመን የኢትዮጵያ አጀንዳን በሚመለከት እነዚህ ሶስት ርዕዮቶች መሰረታዊ ልዩነት የላቸውም ። ሁሉም አትዮጵያ በ30 አመት ወስጥ አንዱ ያፍሪካ ታላቅ አገር መሆን አለባት በሚለው ይስማማሉ። በዚህ አጀንዳ ማይስማሙ ተገንጣዮች ብቻ ናቸው። እርግጥ ቢያንስ ለሚቀትለው 5 እስከ 10 አመት የሚያወዛግበው ጉዳይ የዘውግና የዜጋ ፍልስፍናዎች እንዴት ይጣጣሙ የሚለው ነው።

በአንድ ቃል የሚቀጥለው ምርጫ ተጀምሮ ብልጽግናና ኢዜማ በሰለጠነ ክርክር አንዱ ከሌላው በምን እና ለምን እንደ ሚሻል ለመዳኘት ጓግተናል።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Guest1 » 07 Sep 2020, 13:55

is there anybody in Ethiopia today who can be a leader just because that person may wanted to be a leader?
እንደተረጎምኩት መሪ መሆን የሚችል ኣለ? ይኖራል። አቢይን የሚያውቅው ሰው ኣልነበረም። በመታወቅ ቢሆን መሪ ለማ ነበር። በአጭሩ ጊዜ መሪን ይፈጥራል። ለወደፊቱ በዲሞክራሲ ኣሰራር አንድ መሪ ሳይሆን የሚኖረው የፓርቲ መሪ ነው።
ዬትኛውም ፓርቲ የብሄርም ሆነ የህብረ ብሄር ፓርቲ ቢመራም ዲክቴተርሺፕ ይኖራል። ዲሞክራሲ ያለ ዲክቴተርሺፕ አናርኪ ማለት ኣይደለም? ዲክቴተሺፕ በሁሉም ስርኣቶች አለ።
ችግሩ እዝህ ላይ መሰለኝ።
ምንም እንኳን የተለያየ ኣመራር ቢኖርም ህብረ ብሄር ፓርቲ ግራ፤ ቀኝ ወይም መሃለኛ ከሶስቱ ኣንዱ እንጂ 3ቱንም መሆን ኣይችልም። በአንድ የብሄር ፓርቲ ውስጥ ግራ፤ ቀኝና መሃለኛ የሆነ ስለሚኖር (በመደብ ስላልተደራጀ) መሪው ግራ፤ ቀኝ ወይም መሃል ሰፋሪ ነው። ከሶስቱ ኣንዱ ነው ሁሉንም መሆን ኣይችልም። (መሃለኛ ግራና ቀኝ ለመርገጥ የሚፈልግ መሆኑ እንዳለ ሆኖ)። ይህ ስለሆነ እንደ ተግባሩ ግራ ክንፍ ቀኝ ወይም መሃለኛ ነው ይባላል። አቢይ ዬትኛው ጉሩብ መሪ እንደሆን ስላልታወቀ ዲክቴተር አያሰኘውም። መሃለኛም ቢባልም በአንድ ፓርቲ ውስጥ መሪ ዲክቴተር ከሆነ ማለት የፈለገውን የሚፈጽም ከሆነ ወዘተ... አገር ብቻ ሳይሆን ፓርቲውም በዲክቴተር እጅ ወደቀ ይባላል። ፓርቲው እንዲቀጥል ከፈለገ ይቆያል። ካልፈለገ ይወገዳል።
ምንድነው የመሪ ዲክቴተርሺፕ? ክክክክክክክክክክ

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9763
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by DefendTheTruth » 07 Sep 2020, 14:26

Guest1 wrote:
07 Sep 2020, 13:55
is there anybody in Ethiopia today who can be a leader just because that person may wanted to be a leader?
እንደተረጎምኩት መሪ መሆን የሚችል ኣለ? ይኖራል። አቢይን የሚያውቅው ሰው ኣልነበረም። በመታወቅ ቢሆን መሪ ለማ ነበር። በአጭሩ ጊዜ መሪን ይፈጥራል። ለወደፊቱ በዲሞክራሲ ኣሰራር አንድ መሪ ሳይሆን የሚኖረው የፓርቲ መሪ ነው።
ዬትኛውም ፓርቲ የብሄርም ሆነ የህብረ ብሄር ፓርቲ ቢመራም ዲክቴተርሺፕ ይኖራል። ዲሞክራሲ ያለ ዲክቴተርሺፕ አናርኪ ማለት ኣይደለም? ዲክቴተሺፕ በሁሉም ስርኣቶች አለ።
ችግሩ እዝህ ላይ መሰለኝ።
ምንም እንኳን የተለያየ ኣመራር ቢኖርም ህብረ ብሄር ፓርቲ ግራ፤ ቀኝ ወይም መሃለኛ ከሶስቱ ኣንዱ እንጂ 3ቱንም መሆን ኣይችልም። በአንድ የብሄር ፓርቲ ውስጥ ግራ፤ ቀኝና መሃለኛ የሆነ ስለሚኖር (በመደብ ስላልተደራጀ) መሪው ግራ፤ ቀኝ ወይም መሃል ሰፋሪ ነው። ከሶስቱ ኣንዱ ነው ሁሉንም መሆን ኣይችልም። (መሃለኛ ግራና ቀኝ ለመርገጥ የሚፈልግ መሆኑ እንዳለ ሆኖ)። ይህ ስለሆነ እንደ ተግባሩ ግራ ክንፍ ቀኝ ወይም መሃለኛ ነው ይባላል። አቢይ ዬትኛው ጉሩብ መሪ እንደሆን ስላልታወቀ ዲክቴተር አያሰኘውም። መሃለኛም ቢባልም በአንድ ፓርቲ ውስጥ መሪ ዲክቴተር ከሆነ ማለት የፈለገውን የሚፈጽም ከሆነ ወዘተ... አገር ብቻ ሳይሆን ፓርቲውም በዲክቴተር እጅ ወደቀ ይባላል። ፓርቲው እንዲቀጥል ከፈለገ ይቆያል። ካልፈለገ ይወገዳል።
ምንድነው የመሪ ዲክቴተርሺፕ? ክክክክክክክክክክ
I am not sure if I understood you well when you write so many times about ግራ፤ ቀኝ, ግራ፤ ቀኝ, ግራ፤ ቀኝ as if everything is to be explained by repetition.

Having said that you clarified my question, when you wrote the part highlighted above.

Lemma was removed and Abiy was made to replace him by their party, which means that this is the will of the party but not the will of any individual. Even if there is a will of an individual, then still the will of the party takes precedence over that of an individual's, in what is called a collective decision making.

THis tabtaba ye merkato seqachi is blabbering about Abiy wanted to be a leader which is a fallacy of what you write here.

Guraghe le neged inji le politica ayhonim, lol. Negdum gin tenesh mechbabar keletechemerebat ayhonlachewum. Yaninun mechbarbar izihem mamtat yefelegal.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 07 Sep 2020, 14:47

sun (DDT)
አንተ መሃይም ያስተማርኩህን አልያዝከውም ። አንድ የፖለቲካ መሪ ወደ ስልጣን ለመውጣት የሚፈጥረው ጥምረት (ኮሊሽን) ስልጣን ላይ ለመቆየት አይፈልገውም ። ብዙ ብዙ ግዜ ስልጣን ለመያዝ አብረው የታገሉ ስልጣን እንደ ያዙ ይከፋፈላሉ ብሎም ብዙ የድሮ አጋሮች ይባረራሉ ። ለማ ላይ የሆነው ያ ነው። ለማ ያቢይ ተቀናአኝ ስለሆነ። ስልጣን ላይ ያለ መሪ ታማኝና ታዛዝ ተከታይ እንጂ ወንበሩን ተቀናቃኝ አይፈልግም ። (አንተ መሃይም!)።

ደሞ የፓርቲ ፈቃድ የምትለው ሌላው መሃይምነት ነው። ከላይ ያስተማርኩህን አንብበው። እነዚህ ያንድ አገዛዝ ቁልፍ (ወሳኝ ቡድን) ይባላሉ ። ስይመረጥ ፓርቲ አባል ሆኖ ከተመለመለው ካድሬ ጀምሮ እስከ ፓርቲው ሊቀመንበር ድረስ ሁሉንም የሚገዛው ሕግ ያንድን ግለሰብ የስልጣን፣ ገንዘብ፣ ዚና እና ክብር ፍላጎት ነው ። ይህን ነው እርስበርሳቸው እይተፋገቱ አንድ ላይ አንዱ ተከታይ የሚሆነ፣ አንዱ ተሹሞ አንዱ ሚወርደው ፣ ታከለ ወርዶ አቤቤ ብትሾመው ። (መሃይም)


Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 07 Sep 2020, 15:06

Horus wrote:
05 Sep 2020, 21:08
ሳም እባላለሁ፡

እኔ ምንም አሰምሽን (ቅድመ ውሳኔ) የለኝም ። የፖለቲካ አክቲቪስቶችና ካድሬዎች እንዴት እንደ ሚመለከቱት አላቅም። እኔ የዘረዘርኩት አቢይና አገዛዙን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መተንተን የሚፈልግ ሰውም ቢያንስ መጠየቅ ያለበትን እና ዘዴዎችን ነው የጠቆምኩት ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መረታዊ መሰንጠቂያ መስመር በዘውግ እና ዜጋ ፖለቲካ ላይ መሆኑ እጅግ ትክክል ነው ። ያገሪቱ ቁጥር አንድ የፖለቲካና ሶሺያ ቅርቃር እሱ ነው ።

ስለዚህ የኔ አንዱ ጥያቄ ያቢይ አህመድ አገዛዝ የዘውግ አገዛዝ ነው ወይስ የዜጋ?

ይልቅስ አንተ በግልጽ የመልስከው ነገር አለ፣ ትክክል ሆንክም አልሆንክ ። የዜጋ ፖለቲካው ረድፍ የአቢይ ልብ የት እንዳለ ያውቃሉ ብለሃል ። ይህ ምን ማለት ነው? አቢይ የዜጋ ፖለቲካ አማኝ ከሆነ ያን ድምዳሜ የሚያረጋግጠው ኢምፒሪካል አብነት ምንድብን ነው?

ከላይ ላሉት 7+ ጥያቄዎቼ የዜጋ መልስ አላቸው ወይ?

አቢይ ሞንስተር (ጭራቅ) ነው የሚለው የነጃዋር አቋምና አቢይ ኦኬ ነው የሚለው የዜጋዎቹ አቋም ሁለቱም ሳይንሳዊ ጽንሶች አይደሉም ። አቢይ ዲክታቶር ወይ ዴሞክራት ነው። አቢይ የዘውግ ቡድን ጥቅም ተሟጋች ወይ የዜጋ ጥቅም ተሟጋች ነው ። የሁለቱም ቅይጥ ነው የሚሉ ደሞ ያንን ማሳየት አለባቸው ።

ግ ን ይህ ሁሉ አቢይ አህመድ ለምን ጠ/ሚ መሆን ፈለገ የሚለውን የምቲቭ ጥያቄ አይመልስም ።
ስም

ከላይ ያልኩትን ለማጠናከር፤ ሰሞኑን ኢትዮ360 በፕሮፍ ብርሃኑ ነጋ ንግግር ላይ ያቀረቡትን ትችት ተከታትለህ ከሆነ...

ፐርስፔክቲቨ (መመልከቻ ቦታችን) ምን ያህል አንድን ነገር ለያይተን እንደ ምናይና ፋክት የምንለውን ነገር እንደ ሚወስን ማሳያ ምስሌ ነው። ያቢይ መንግስት በሚመለከት ኢትዮ360 ብርጭቆው ግማሽ ጎደሎ ነው ይላሉ ። ኢዜማዎች ብርጭቆው ግማሽ ሞልቷል ይላሉ ። ይህንን ሃቅ ነው እንደ ትልቅ የስርዓት ደረጃ በማውጣት ሚዲያው ሚቶዘው። አንዳቸውም በኢትዮጵያ ኤትኖክራሲ የሚባል የጎሳ አገዛዝ ስርዓት መኖሩን ተቀብለው አንድ ሕብረተ ሰብ ከኤትኖክራሲ ወደ ዴሞክርሲ እንዴት ሊለወጥ እንደ ሚችል ያቀረቡት ሞዴል የለም ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 07 Sep 2020, 22:10

እኔ እዚህ ቪዲዮ ውስጥ ኤርሚያስ በሚለው ሁሉም አልስማማም ግ ን ከዚህ በላይ ያቢይ ቁልፍ ደጋፊ ረድፍ ያልኳቸውን ሰዎች ያነሳል ። ብሎም ጥቂት ስለመሆናቸው ያነሳል ። አንድ መሪ የሚያምናቸው ቁልፍ ደጋፊዎች ሲያንሱና ዴሞክራቲክ መሰረት ከሌለው ሁል ግዜ የሚከቡት ቁልፍ ሰዎች በጣም ጥቂት ይሆናሉ ። ይህ የፖለቲካ ሳይንሱን ትክክለኛነት ያረጋግጣል። እነዚህ እጅግ ትቂት ቁልፍ ታማኞችን በማጥናት ያገዛዙ ባህሪ ምን እንደ ሆነ ለማወቅ ይቻላል።


Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 08 Sep 2020, 02:59

እኔ ብንያም ተወልደ በአውሎ ሚዲያ ላይ ስለ አቢይ አህመድ የሰጠውን ሳይኮሎጂያዊ ፕሮፋይል ዛሬ ነው ያየሁት ። እኔ ከሳይኮ ሜትሪክስ ሳይሆን ከዲስክሪፕቲቭ ሳይኮሎሎጂ ተነስቼ ስለአቢይ ባህሪ የደረስኩባቸው ግህንቶች አሉኝ ። እኔ ዝም ብዬ ሜዳ ላይ አልዘራቸውም ። ግ ን ተወልደ እኔግራም በሚባለው ሳይኮሜትር (እንደ ብሪግስ ማየር ያልው ነው) መሰረት አቢይን ከሚገፉት ሞቲቬሽን ውስጥ ለዝና ያለው ፍላጎት ነው ብሏል ። ከዚህ ባለፈ አቢይ ለገጽታ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ፣ ፓርኮች እንደ ሚሰራ ገልጿል ።

አቢይ አጭበርባሪ ነው የሚለው ያቢይ ፕራግማቲክ እና ፕራክቲካል ባህሪን ማለቱ ነው። ስለዚህ አንዳንድ እኔ ለብዙ ግዜ ማውቃቸው ባህሪያትን ተናግሯል ። እነዚህ ሳይኮሎጂያዊ ተፈጥሮዎቹ እና ባህሪዎቹ እንዴት ወደ ፖለቲካ አስተሳሰቡ ሄዱ፣ እንዴት ከመሪነቱ ጋር ተያያዙ በሚለው ትወልደ ምንም አያቅም ። አኔግራም ላይ ያሉትን ጸባያትን ነው ሚዘረዝረው ። ለምሳሌ አቢይ በኦሮሞ ብሄር ጥያቄ ላይ ምን አመለካከት አለው? ካለውስ የትኛው ሳይኮ ፕሮፋይል ነው ያንን የሚነግረን? ወዘተ! ተወልደ ምንም አያቅም ። ዎያኔ ስለ አቢይ ማንነት፣ ምን እንደ ሚፈልግ እና እንዴት ነገሮች እንደ ሚስራ ካወቀ እንዴ ባቢይ ተሸነፈ? ስለዚህ ኢንሳ ውስጥ እንደ መጻፍ ቅዱስ የታመነበት አኔግራም ሰው ሰራሽ እስታቲስቲካል ፊክሽን ወይም ልብ ወለድ እንደ ሆነ ዎያኔ አያቅም።

የዘመኑ ኒውሮ ሳይንስ የደረሰበት የውቀት ደረጃ እንዲህ ነው። በአንጎላችን ወስጥ የተቀመጠ ቁሳዊ ባህሪ የለም ። አይምሮ ስጋና ደም ፊዚካል ነገር ነው። ሃሳብ 90% በመቶ ከንቃት በታች ያለ ድብቅ ነገር ነው ። ጽንሰ ነገር ወይም ክንሴፕት ሜታፎር ወይም ምሳሌ ነው። የሰው ባህሪ በየቀኑ ራስችን ምንሰራው ክንስትራክት ነው። በቃ ። ስለዚህ ከመጻፍ ሚቀዳ ሞዴል ፊክሽን ነው። ሰው ዝና እና ክብር መፈለጉ የሁሉም ሰው ባህሪ ነው። ቁም ነገሩ ያንድ ሰው የፖለቲካ እና የመሪነት ባህሪ ለማወቅ መቻል ነው ። ተወልደ ይህን አያደርግም ። እኔ ግን ስለአቢይ ይበልጥ ትክክለኛ ባህሪ የማውቀን አልገልጽም ። አቢይ አጭበርባሪ ሳይሆን ፍጹም ፕራግማቲክ ሰው ነው ። ትርጉሙ ለሚገባችሁ !


Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Guest1 » 08 Sep 2020, 06:29

I am not sure if I understood you well when you write so many times about ግራ፤ ቀኝ, ግራ፤ ቀኝ, ግራ፤ ቀኝ as if everything is to be explained by repetition.
በእውነት ይሄ በጣም ኣስቆኛል። ክክክክክክክክክክ

ብሄር በመደብ የተከፋፈለ ነው። ሃብታምና ደሃ ኣለው። ከተማ በተለይ ምናልባት ገጠርም። የህዝብ ወገን ግራ ክንፍ፤ ቀኝ ክንፍ ኩላክ ያስፈልገናል ባይ የሃብታም ወገን ክክክክ መሃለኛ የመደቦች ኣስታራቂ ለመሆን የሚሞክር ነው። በየትኛውም ፓርቲ ይህ ክፍፍል ኣለ። በአገራችን ብሄር ብሄር፤ በደፈናው ጽንፈኛና ጠባብ ይደጋገማል እንጂ የመደብ ጀርባውን ክክክክ የሚያውቅ የለም ወይም ሆን ተብሎ ኣይነገርም።

ግራ ቀኝ መሃለኛ መደጋገም ያስፈለገው የማትፈልገው ስለሆነ ነው። አንተ ራስህ ሴንተሪስት ሳትሆን ኣትቀርም። ሃብታምና ደሃ ተስማምቶ ይኑር ባይ። የዜጋ ወይስ የብሄር ስላልክም ኣታመልጥም። ያው ነው ክክክክክ

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9763
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by DefendTheTruth » 08 Sep 2020, 11:27

Guest1 wrote:
08 Sep 2020, 06:29
I am not sure if I understood you well when you write so many times about ግራ፤ ቀኝ, ግራ፤ ቀኝ, ግራ፤ ቀኝ as if everything is to be explained by repetition.
በእውነት ይሄ በጣም ኣስቆኛል። ክክክክክክክክክክ

ብሄር በመደብ የተከፋፈለ ነው። ሃብታምና ደሃ ኣለው። ከተማ በተለይ ምናልባት ገጠርም። የህዝብ ወገን ግራ ክንፍ፤ ቀኝ ክንፍ ኩላክ ያስፈልገናል ባይ የሃብታም ወገን ክክክክ መሃለኛ የመደቦች ኣስታራቂ ለመሆን የሚሞክር ነው። በየትኛውም ፓርቲ ይህ ክፍፍል ኣለ። በአገራችን ብሄር ብሄር፤ በደፈናው ጽንፈኛና ጠባብ ይደጋገማል እንጂ የመደብ ጀርባውን ክክክክ የሚያውቅ የለም ወይም ሆን ተብሎ ኣይነገርም።

ግራ ቀኝ መሃለኛ መደጋገም ያስፈለገው የማትፈልገው ስለሆነ ነው። አንተ ራስህ ሴንተሪስት ሳትሆን ኣትቀርም። ሃብታምና ደሃ ተስማምቶ ይኑር ባይ። የዜጋ ወይስ የብሄር ስላልክም ኣታመልጥም። ያው ነው ክክክክክ
Taking the middle road could be more safe at the end, as far as that is not about አድር ባይነት ።

Any how is this ግራ፤ ቀኝ also what others call liberalists and conservativists?

In that case there is also a difference between the terms depending in which context you are using the words, if I am not mistaken. These could be፣ for example, in the social arena, or also in the economic arena. (Social conservatives, econcomic conservatives and their counterparts in the liberalists field).

In that case፣ is Dr. Abiy a conservative or a liberal, in which of the arenas?

ይህ የመርካቶ ወያለ ሆሩስ ዝም ብሎ ነው የምቀባጥረው።

He filled two full pages of the thread that he himself started but in all of this he has not even bothered himself to take any emprical example from around the world in order to substantiate his claims, a complete failure.

In my view a collective decision is more rational and has the power of overriding that of an individual decision.
In a party politics there can't be a room for a dictatorial one person rule or will, it has to be based on the will of the majority in the party.

A recent example from around the world:

Dr. Angela Merkel of Germany is/was a very much liked politician across the broader political spectrum of her country. But there was a "mistake" (at least according to her distractors) that she committed in the year 2015 in her executive decision of allowing in millions of refugees from many parts of the world and declared "wir schaffen es" (we can overcome it) but many of her own party compatriots were no more ready to take that step with her and said "no, Dr. Merkel, we are no more ready to stand behind you anymore". That misstep costed her ambition to remain as uncontested party leader and with that also a leader of her country. Now she is waiting just to finish her current term and her political career is nearing its end with that.

ይህ የመርካቶ ወያለው has no explanation for his claim of an individual wants to be a leader and becomes (remains) a leader according to his/her individual will on this example.

Gallo
Member
Posts: 278
Joined: 29 Feb 2020, 04:08

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Gallo » 08 Sep 2020, 11:53

አብይ አህመድ ራሱ ስለ እራሱ ሳይኮሜተሪክ ስትራክቸር የነገረን!!

“ሰዎች ራስ ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው። የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደ ምትፈልገው ስፍራ ውሰዳቸውና ጣላቸው!!” ዶር አብይ አህመድ


ዶር አብይ አህመድ በታህሳስ 2009 ዓም አካባቢ አንዲት ወደ 173 ገጽ የምትሆን “እርካብና መንበር” የሚል የመጽሃፍ ርዕስ ያላት መጽሃፍ ጽፎ ነበር፡፡ ዶር አብይ በጻፈው መጽሃፉ በገጽ 38 ላይ እንዲህ ይላል፡-
“ሰዎች ራስ ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው። የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደ ምትፈልገው ስፍራ ውሰዳቸውና ጣላቸው። ከዚያም “በሬ ሆይ! ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ የሚለውን ተረት ተርትባቸው። ይህን መሰሉ ለዘብተኛ የኃይል አጠቃቀም ዘዴ ሰላም ሳይበጠበጥ ህዝብም ሳያጉረመርም የተደላደለ ስልጣን ባለቤት ለመሆን ያግዛል።”

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 08 Sep 2020, 16:52

ተወልደ የሚባለው ሰላይ ያደረገው ስህተት ያ ነው። አቢይ ይህን ከነ ሱን ዙ ዘመን ጀምሮ ያለ የፖለቲካ ትግልና የውጊያ ታክቲክ ወይም እስትራታጀም ሪቻርድ ግሪን 48ቱ የፖወር ሕጎች ከሚለው መጻፉ የተገለበጠ እንጂ ከኢኔግራም ሳይኮሜትሪክስ ጋር አይገናኝም ። እነዚህ የስትራተጂና ታክቲክ ክህሎቶች፣ ዘዴዎች በየቀኑ ነጋዴው፣ ባለባንኩ፣ ጦር ት/ቤት ፣የፖለቲካ እስትራተጂ አማካሪዎች ሚሰሩት ጉዳይ ነው። የአቢይን ባህሪ የሚመራው ፕሪንሲፕል ፕራግማቲዝም ይባላል። ፕራግማቲኮች አንድ የፈለጉትን ነገር ለማግኘት እንደ ሁኔታው ፣ እንደ ሲቱዋሽኑ እርምጃቸውን፣ ዘዴአቸውን ሚቀያይሩ ማለት ነው ። ይህ ደሞ አጭበርባሪነት አይደለም ። በጥቅም ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ጨዋታ ስልት ነው።

አንድ ሃኪም ፣ አንድ ቄስ፣ አንድ ዳኛ፣ አንድ አስተማሪ፣ ምሁር፣ አካዳሚ የሚመራው ባብዛኛው በሞራል ወይም ኤቲካል ወይም ሃይማኖታዊ ፕሪንሲፕለ ነው። ግ ን ፖለቲካ የስልጣን፣ የገንዘብ የዝና፣ ወይም የክብር ትግል ነው ። ለምሳሌ አንድ የጎሳ ፖለቲከኛ ሚታገለው ለክብር ነው። በዚህ ትግለ ወይም ጨዋታ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት አቢይ የሚጠቀመው ስልት ፕራግማቲዝም ወይም ፕራክቲካሊቲ ይባላል ።

ብዙ ሰዎች የሚምታታባቸው ይህን መሰል የመሪነት ስልትና መሪው ለመምራት ካገርና ከሕዝብ ድጋፍ ለማግኘት የሚፈጽማቸው ፓፕሊክ ፕሮጀክቶች ማያያዝ ስለማይችሉ ነው። አንድ መሪ ሃይል፣ ሃብት፣ ዝና፣ እና ክብር የሚያገኘው መንገድ በማሰራጥ ዉሃ በማስገባት፣ ፓርክ በመጥረግ ፣ ክንዶ በመገንባት ነው፣ ለምሳሌ።




Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 08 Sep 2020, 21:22

ከላይ እንዳሳየሁት ኤኔግራም የሚባለው ጥንቆላ ማለትም ሰው በ9 አይነት ፐርሰናሊቲ ይከፈላል የሚለው መላምት በሳይሳዊ ስይኮሎጂ አለም ወድቅ የሆነ ሆኖ ሳለ ተወልደ ሚባለው ሰላይ በአውሎ ላይ ስንት ቀባተረበት ። የዎያኔ ዉሸት ፕሮፓጋንዳ ! ይህን ተመልከቱ
https://en.wikipedia.org/wiki/Enneagram

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፖለቲካ ሳይንስ፣ አቢይ አህመድ ጠ/ሚ መሆን የፈለገው ለምንድን ነው?

Post by Horus » 08 Sep 2020, 22:09

ጠ/ሚ የሌለና የተሳሳተ ጽንሰ ነገር ለምን እንደ ሊጠቀም አይገባኝም ። በዛሬው ያዲስ አመት ቃለ መጠይቅ አቢይ አራቱ ምሰሶዎች የሚላቸውን እንደ ገና ተጠቅሟቸዋል ። ምንድን ናቸው እነሱ? የአቢይ አህመድ ባለ 4 ምሰሶ ያገር ማቆሚያ ሞዴል የሚከተለው ነው ።

ምሰሶ 1 አልትራ እስትራክቸር፣ የእምነት፣ የሲቪል፣ የሚዲያ፣ የካልቸር ተቋማት
ምሰሶ 2 ሱፐር እስትራክቸር፣ መደመርና የብልጽግና ፓርቲ
ምሰሶ 3 ኢንትራ እስትራክቸር፣ የመንግስት መዋቅሮች፣ አውታሮች፣ ተቋሞች (እስቴት አፓራተስ ና ኢንስቲቲውሽን)
ምሰሶ 4 ኢንፍራ እስትራክቸር ፣ መንገድ፣ የሃይል ፣ የኮሚኒኬሽን ወዘተ ሲስተሞችና ዝርጋታዎች

በመሰረቱ ይህ ሞዴል ስህተት ነው ። ቀድሞ ነገር እስትራክቸር የሚለው ቃል የአንድ ሲስተም ክፍል ስለሆነ ዝም ብለው ለብቻው መወርወር ትርጉም አልባ ነው። አንድ ሲስተም እስትራክቸር፣ ፕሮሴስና ፉክሽን አለው። ስህተቶቹ፤

አንደኛ፣ አልትራእስትራክቸር የሚባል ጽንሰ ሃሳብ በሶሺያል ሳይንስ ውስጥ የለም ። በባዮሎጂ ውስጥ እጅግ ረቂቅ ሆነው በኤሌክቶ ማይክሮእስኮፕ ብቻ የሚታዩ ሴሎች ናቸው አልትራእስትራክቸር ሚባሉት ። ብዙዎቹ አቢይ አልትራ የሚላቸው በማርክሲዝም ሱፐር እስትራክቸር ሚባሉት ናቸው ።

ሁለተኛ አቢይ ሱፐር እስትራክቸር ያለው ብልጽግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ባገሪቱ እኮኖሚኢክ ሲስተም ላይ የበከሉት ሲስተሞች ሁሉ ነው ሱፐረስትራክቸር ሚባሉት ።

ሶስተኛ አቢይ ኢንትራ እስትራክቸር የሚለው ጽንሰ ነገር በፍጹም የሌለ የተሳሳተ ሃሳብ ነው። ቀድም ነገር ቃሉም የለም ። አቢይ በኢንትራ እስትራክቸር ሰር ያሰራቸው የመንግስት አውታሮች (እስቴት አፓራተስ) የታወቀ ሳይንሳዊ ምደባ አላቸው ። እነሱ ደምበኛ የሱፐር እስራክቸር ምሳሌዎች ናቸው። ስለዚህ ኢንትራ እስትራክቸር የተሳሳተ ኮንሴፕት ነው ። ኢንተርናል እስትራክቸር (ውስታዊ መዋቅር) ለማለት ተፈልጎ ከሆነ የምን ሲስተም ውስታዊ መዋቅር እንደ ሆነ መገለጽ አለበት ።

እኔ በዚህ ፖስት ውስጥ አንድ መሪ የመንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ የሚቀጥለው ስራው እስቴት አፓራተስ መቆጣጠር እንደ ሆነ ጠቅሻለሁ ። አቢይ ያን አድርጓል፣ እሱም የመንግስት አውታሮችን መቆጣጠር ወይም መገንባት የሚባለው ነው ። ኢንትራእስትራክቸር ሚባለ ነገር የለም ።

አራተኛ ኢንፍራእስትራክቸር ትክክል ነው ፣ መንገድ፣ ኤሊክትሪክ ግሪድ፣ ወዘተ ማለት ነው ።

መደመር የሚባለውም ግልጽ የሆነ የመቀናጆ ወይም ኮሊሽን ጽንሰ ሃሳብ አላግባብ ተለጥጦ ብዙ ቀለም ፈሰሰበት ። መደምር የሚባል ፍልስፍና ወይም ቲኦሪ የለም ። መደመር የአንድ ፓርቲ ፕሮግራም መተግበሪያ እስትራእጅ ነው።


Post Reply