ወንድይራድ ሀይለገብርኤል
እንዄን ለመመረጥ ለመምረጥም መታገድ የሚገባቸው አያቶቻችን!!!
ሀሳቡን ለመግለፅ ከባድ ነው። ቢሆንም ልሞክር።
----
ትንሽ ቆየት ብሏል። የህግ ትምህርትቤት ውስጥ እያለው "Legal Analysis and Problem Solving" በተባለ አንድ ዩኒት ውስጥ የምርጫ ህግ ፍተሻ የተሰኘ ኢፒሶድ ነበር።
ግብሩ ወይንም ምርምሩ የምርጫ ህጉን ፈትሾ ሊሻሻሉ/ሊጣሉ/ሊጠቃለሉ ወይንም ሊታደጉ (amended /repealed /consolidated or revived) የሚገባቸው ህጉች ካሉ ዲያጎኖሲስ ሰርቶ ፕሮፖዛል ማቅረብ ነው።
የኔ ሪኮመንዴሽን የሚከተለው የምርጫ ማስፈፀሚያ ደንብ ላይ ያተኮረ ነበር። ደንቡ የዕድሜ ገደብ ተቀምጦለት amended ሊደረግ ይገባል ነው ያልኩት። የዕድሜ ገደቡም ከ 18 - 65 አመት ሊደረግ የተገባ ነው ነበር ያልኩት።
የፌደራል መንግስቱ የምርጫ ማስፈፀሚያ ህግ 1918 አንቀፅ 245 ቁጥር 1 እንዲህ ተመልክቷል ""ከ 18 አመት በላይ ለሆናቸው ዜጎች በሙሉ መምረጥ ግዴታ ነው it shall be the duty of ---- compulsory to all citizens over the age of 18 to enroll and vote""
መከራከሪያየን ያስቀመጥኩት ባጭሩ እንደሚከተለው ነበር፡ --
*** ዕውነታ አንድ: የሴቶች ዕድሜ ዘመን life expectancy በአማካኝ 84 አመት ሲሆን የወንዶቹ ደግሞ 80 አመት ነው። እስካሁን ድረስ 4250 ዜጎች መቶ አመት ደፍነዋል። 110 አመት ሞልቷቸውም እስካሁን ያላለፉ በርካታ ዜጎች አሉ። እንግዲህ መምረጥ የሚችሉትና መምረጥ ግዴታቸው የሆኑ እነዚህ ሁሉ አዛውንቶች ናቸው። ግዴታ ስለሆነ አብዛኛዎቹ የሚመርጡት አልጋ ላይ እንደተኙ ነው።
*** ዕውነታ ሁለት፡ ከ 24 ሚሊዮን የሀገሪቱ ጠቅላላ ህዝብ እድሜው 65 እና በላይ ያለው የሽማግሌና ጡረተኛ ቁጥር 30 በመቶ ነው።
*** ዕውነታ ሶስት፡ 16 ሚሊዮን ከሚሆነው ለመምረጥ የደረሰ Eligible to vote ማለትም 18 እና ከዚያ በላይ ከሆነው የህዝብ ቁጥር መካከል 50 በመቶ የሚሆነው ጡረተኛና የሽምግልና ዘመኑን በአዛውንቶች ማቆያ ስፍራ ተቀምጦ በአማካኝ በቀን እስከ 12 የደረሱ የተለያዩ መድሀኒቶችን በመውሰድ ቀኑን እየገፋ ያለ ነው።
ያቀረብኩት የማስተካከያ amendment ሀሳብ በከፊልና ባጭሩ፡ --
*የምርጫ ማስፈፀሚያ ህጉ 1918 s245 ተሻሽሎ የመራጭነት ግዴታው የዕድሜ ገደብ ሊጣልበት ይገባል። ገደቡም ከ 18 -65 ቢሆን መልካም ነው። 65 የጡረታ መውጫ ዕድሜ ነው።
*ሰው ጡረታ ከወጣ በሗላ ህይወቱን የሚገፋው ስራላይ በነበረበት ግዜ ባጠራቀመው የሱፐርአኑየሽን እና ከሰራተኛው ሀይል በግብር አግባብ በተሰበሰበ የመንግስት ፔንሽን ፈንድ ነው።
*ለጡረተኞች ነፃ ህክምና በፖለቲካል ፓርቲዥያን የማይናወጥ የዜጎች መብት በመሆኑ ጡረተኛው ከሰራተኛው ሀይል በሚሰበሰብ ግብር ተንቀላጦ መኖር አልበቃው ብሎ የወጣቱንና የሰራተኛውን ህይወት ሊያናጋ በሚችል የፖለቲካ ምርጫ ላይ እየተሳተፈ የወጣቱንና የሰራተኛ ሀይሉን እጣ ፋንታ ሊወስን አይገባም።
*ስለማይኖርበት የስራና የትምህርት ፖሊሲ ምርጫ ላይ መሳተፍ የለበትም። የወጣቱ የወደፊት ዕጣ ፋንታ የራሳቸውን ኑሮ አጣጥመው ባበቁ የመቶ አመት አዛውንቶችና ጡረተኞች political determination ሊሰጠው አይገባም። ዛሬ ላይ የጡረታ መውጫውን እድሜ ከፍ አድርገውታል።
እኒህንና ተያያዥነት ያላቸውን 27 ነጥቦች በማንሳት ደንቡ ሊሻሻል ይገባል የሚል ፕሮፖዛል ነበር ያቀረብኩት። ባቀረብኩት ፕሮፖዛል ቢገረሙም የወደዱት ግን አልመሰለኝም። የዲሞክራሲ ፅንሰሀሳብን ይንዳል የሚል ትችትም ሰጥተውበታል። ሊንድ ይችላል። የአንፃራዊነት ባህሪው የዚሁ መገለጫ ነው።
ለኢትዮጵያ ፖለቲካም መፍትሄ የምለው ይህንኑ ነው። የተከበሩ አባቶቻችን እነጋሽ በየነ ጴጥሮስ፡ አረጋዊ በርሄ፡ መራራ ጉዲና እንዃንስ ሊመረጡ ሊመርጡም ሊፈቀድላቸው አይገባም። they have had their time and chances አልተጠቀሙበትም። ለማያባራ መከራ ነው የዳረጉን። የሌላ አለም ሰዎች ናቸው። አካላቸው እንጅ አስተሳሰባቸው ከዚህ ትውልድ ጋር ቁርኝት የለውም። ሀገሪቱ አቅም ካላት ለነዚህ አዛውንቶች ማድረግ የምትችለው ሰብሰብ አድርጋ የዕድሜ ጠገብ ማዕከላት ውስጥ በማስገባት መጠወርና የቀን ክኒናቸውን ሳታጓድል ማቅረብ ነው።
ስለማይኖሩበት አለም የወጣቶቻችንና የሀገራችን የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ ጭቃ እንዲያቦኩ ሊፈቀድላቸው የተገባ አይደለም። በአፄ ሀይለስላሴ ዘመን የደነቆረ ጀሮ በአብይ ዘመን ሊሰማ አይችልም። they all expired! ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናት። በወጣቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ልትገነባ የግድ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩን የገጠማቸው ፈተና ከባድ ነው። ከእኒህ old geared mentalities ጋር እንዴት ተሁኖ ነው መደመርስ መለወጥስ የሚቻለው?
እኒህ ሰዎች የመምረጥም የመመረጥም መብታቸው በሲቪል አክሽን ሊታይ ይገባል። ማህበረሰባዊና ሀገራዊ ደህንነት ከዲሞክራሲያዊ ፅንሰሀሳብ በላይ ነው።
ከባድ ነው!!!