Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
AbebeB
Member+
Posts: 7694
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

Breaking Analysis: የኮ/ል አብይ ግራንድ ፕላንና ህዳሴ ግድብ ዕውኔታ::

Post by AbebeB » 31 Jul 2020, 12:31

ኮ/ል አብይ ህዳሴ ግድቡን አሳልፎ ሰጥቶአል፡፡ አመናችሁም አላመናችሁም ይህ የማይታበል ሀቅ ነው፡፡ አመክኖውም እንዲህ ነው፡፡
1. ኢሰያይስ አፈወርቂ (ታርካዊው የኢትዮጵያ ጠላት) በሱዳን፣ ግብፅና ኢትዮጵያ መካከል ተመላልሶ ሸር ሰርቶአል፡፡ ዓላማውም ኮ/ል አብይን ለማሻገርና በአብይ በኩል ኢትዮጵያን መበዝብዝ ነው፡፡ ባድሜን እርሱት፡፡ አብይ እንዳያፈገፍግ ደግሞ ሠራዊቱን ኢትዮጵያ ውስጥና አራት ኪል አስማርቶአል፡፡
2. በኢሰያይስ አፈወርቂ ሽምግልናም አብይና ግብፅ ተስማምተዋል፡፡
3. ግድቡ በዚህ ክረምት በመሞላቱ ግብፅም ይሁን ሱዳን (ለዚያው ሲዳን ውሀ መቀነሱን በኦፊሴል ሪፓርት እያደረገች) ያለ ወትሮአቸው ዝም ነው ያሉት፡፡ ይሁንታ ሰጡ ማለት ነው፡፡
4. የደቡብ አፍሪካው መሪና አደራዳሪው (አፍርካ ህብረት) በሰጠው የስምምነት ሂደት ፍንጭ ላይ ግብፅ ፍጹም ደስተኛ መሆኑዋን ለመታዘብ ችለናል፡፡ ደስታው ከምን ተገኝ? እንዴት ሊሆን ቻለ?
5. የኮ/ል አብይ ሚዲያዎች ውሀው ተሞላ እንጂ ወደ ሀይል ማመንጨት (operation) የምንገባው ሰኔ ላይ ነው ብለውናል፡፡ ለምን? እንዲህ ከሆነ እልህ ተጋብተን ውሀ ለመሙለት መጣደፍን ምን አመጣው? የተሞላው ውሀ በጋ ላይ እንዲተን ነው? መጪው ሰኔ እኮ ለሁለኛ ዙር ውሀ ሙሌትና ለተጨማሪ ሀይል ማመንጫ የሚከድበት ጊዜ ነው፡፡
6. በዚህ በኩል ደግሞ፤ አብይ የሕዝብ ድጋፍ ያላቸውን ዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስሮ ከዶሴ ፓርቲዎች ጋር ስለ ምርጫ ምክክር ጀምሮአል፡፡ በዘጠኝና አስር ወራት ውስጥም ምርጫ እንደሚካሄድ ነግሮናል፡፡ ይህ ደግሞ ግንቦት ወይም ሰኔ አካባቢ ማለት ነው፡፡
7. የጊዜው ቀመር የአባይ ግድብ ሥራ (operation) ይጀምራል የተባለበት ጊዜ መሆኑ ነው፡፡
8. ስለዚህ እስከ መጪው ምርጫ በኤርትራ ጦር ታግዞና ተቃዋሚዎችን አፍኖ ምርጫ በማካሄድ ተመረጥኩ ሊለን ነው፡፡
9. ከዚያ እኔ ሕጋዊ መንግስት ስለሆንኩ የኢትዮጵያ ጦር ጠራዊት ሕገ-መንግስቱንና ሥርዓቱን ጠብቅ ለማለት ድፍረት ያገኛል፡፡ እምቢ የሚል አዛዥ ካለም የኤርትራ ጦር ይላክበታል፡፡
10. በዚህ ሲረጋጋ፣ ወደ ሕዝቡ ይመለስና ግድቡ ከኢትዮጵያ ስለማይበልጥ ሀገራችንን ለማትረፍ ሲባል አሳዛኝ ውሳኔ ወስነናል ይለናል፡፡ ወደ ፊት እእእህህህህ እያለ ደግሞ ማጭበርበርያ ተስፋ ይሰጠናል፡፡ ያኔ መርዶአችንን እናወጣና እንዲህ፣ እንዲያ ባደርግ ኖሮ ማለት እንጀምራለን ማለት ነው፡፡ ጅብ ካለፈ በኃላ ውሻ ይጮሀል አይደል ተረቱ?
11. ኮ/ል አብይ ደግሞ በሬ ሖይ ይለናል ማለት ነው›፡፡
12. የጊዜው ሰው ካደረገን እንገማገማለንና ለታሪክ ይመዝገብ፡፡