ምነው ንገሩን አላቹሳ?
4 ኪሎ ቤተመንግስት በሻዕብያ ኮማንዶዎች ለተከታታይ 4 ዓመታት የተጠበቀው በሽንታሙ የእናተው የህወሓት መንግስት ዘመን ነው።
መቼም ክህደት እና ውሸት ባህላቹህ ሆነ እና ታሪክን ትጠመዝዛለቹ እንጅ፤ የሻብዕያ ሰራዊት ቤተ መንግስትን ጨምሮ በአዲስ አበባ፣ ባህርዳር እና መቀሌ ከተሞች እስከ 1995/1987 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበሩ ይታወቃል።
*እግረመንገዴን መለስ ዜናዊ ባይፈርም ንሮ የ1993 የኤርትራ ሪፈረንደም እውን አይሆንም ለምትሉ ሁሉ። የፈራሚው ሰውየ መኝታ ቤት ጭምር ይጠበቅ የነበረው በሻብዕያ ኮማንዶዎች እንደነበረ ላስታውሳችሁ እወዳለው።
("ወደሽ ነው ቆማጢት ንጉስ ትመርቂ" ነው ነገሩ ለማለት ነው።)
ለማንኛውም የፕ.ኢሳያስን ንግግር ትርጉም እዚህም ጭምር ላስቀምጥላቹህ።
ጥያቄው-ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነ አካባቢው ላይ ተፈጠረ ለምትለው ማንኛውም ነገር ለምንድነው ኤርትራን የምትከሰው ?
ፕ. ኢሳያስ አፈወርቂ - "ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ዝምድና ለማራራቅ ኤርትራ እንደዚህ አደረገች፣ ሻቢያ እንዲህ አደረገች፣ ሻቢያ ይህን ፈጠረች፣ ኢትዮጵያ ላይ ይህን አደረገች፣ በአካባቢው ላይ እንደዚህ አደረገች......
እንዴ ! ያኔ አዲስ አበባ ታንኮቻችን እና መድፎቻችን ይዘን
የገባነው እኮ ለጉራ አይደለም፤ ለዝና አይደለም የገባነው። ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ መጻኢ እድል ብለን ነው። እኛ ጎበዞች ነን እናተ ሰነፎች ናቹህ የምንለው ጉዳይ አይደለም፤ በጋራ የሰራንበት ነው። ታዲያ ለምን ይህን ሁሉ ድካምና ኪሳራ ከሰርን? አሁንስ አዲስ ፈጠራ አለን? በፍጹም አዲስ ፈጠራ የሚባል ነገር የለም። የኢትዮጵያ ህዝብም አዲስ ፈጠራ የለውም። እኛ በኤርትራ ህዝብ እና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ለሚኖረው ዝምድና አዲስ ዓላማ (ፈጠራ) የለንም። መጻኢ እድላችን እንዴት ይሆናል፣ እንዴት ነው የምንተጋገዘው፣ ወዴት ነው የምንጓዘው ለሚለው፤ ለማንም ሰው ግልጽ ነው....."
ጥር 2018