Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ሰሞንኛ ኤርትራዊ ግጥም፡ በጦቢያ በአብይና በአባይ ዙርያ!

Post by Meleket » 04 Jul 2020, 03:34

ማነህ አንተ፣ ንሳ’ማ ተቀበልልኝ!

ቢሞላ ባይሞላ አባይ፣
መሻገሪያው አብይ።

ቢሞላ ባይሞላ አባይ፣
አሻጋሪው ዐብይ። :mrgreen:

አባይ ሙላ ብለው ጀምረህ ከሃምሌ፣
ህዳሴን ሙላ ብል ጀምረህ ከሃምሌ፣
'ቦለቲከኛ ነኝ' ባይ ባንዳና ባተሌ፣
ተልእኮ አንግቦ ተወዲያ ተመቀሌ፣
ሥራ ሊያደናቅፍ ተቀብሎ አሞሌ፣
ሲሽሎኮሎክ አየን የማንም ጩሉሌ፣
ሲልከሰከስ አየን የማንም ኮልኮሌ። :lol:

አገር ሊያተራምስ አጀንዳ ሊያስቀይር፡
ሰላም ሊያደፈርስ አንገት ሊያስቀረቅር፡
በብልጥግናው ላይ ዘመቻ ጀምሮ፣
እንዳምና ታቻምናው አምባጎሮ ፈጥሮ፣
በጥበቡ ሰው ላይ መሳሪያ ወድሮ፣
የሴራ ተልእኮውን እንደክርቢት ጭሮ፣
ሃጫሉን ነጠቀን በባዕድ ተቀጥሮ፣
ባንዳ የባንዳዘር ለየከርሱ አድሮ። :mrgreen:

እርማችሁን አውጡ ባንዶች በሙሉ፣
ወሬ በማንመንዠኽ ልኂቃን ምትመስሉ፣
የስልጣን ጥመኞች እዚ እዛ ምትፈሉ፣
ሰላም ለማደፍረስ የምትማማሉ፣
ህዝብን ለማጫረስ ካራ የምትስሉ፣
በባዕድ እርጥባን ከርሳችሁን ምትሞሉ፣
እንደ የቀን ጅቦች ምትጎማለሉ፣
አንዳች ሳትሰሩ ታታሪን ምትጠሉ፣
አገር ለመበጥበጥ ምትፈለፈሉ፣
ቁምነገረቢሶች ንጹሐን ምትገድሉ፣
አሁንስ ይበቃል እስቲ ገለል በሉ። :lol:

አባይና ህዝቧ የሚናበቡባት፣
ሰላሚቱ ጦቢያ የብዙዎች እናት፣
በፍቅር ትህትና በተስፋና ትእግስት፣
እምነቷን አጥብቃ በአላማ ጽናት፣
በንጹሃን ጥረት በልጆቿ እውቀት፣
የሰላሙ ጀግና አብይ እየመራት፣
ገና ትወጣለች በብልጽግና አናት። :mrgreen:

ግሩም ይሆን ዘንድም መዋእል ዘመኗ፣
እኛም ኤርትራዉያን ሁሌም ነን ከጎኗ፣
አንድባንድ እስኪጠፋ ቁንጫ ትኇኗ። :mrgreen:

የማንም ጤባና የማንም ገሪባ፣
ስልጣን ሊፈናጠጥ በንጹሃን እምባ፣
ጥላቻን ሲዘራ ቆሞ ባደባባይ፣
እፍረት ማይሰማው ጣድቅ መስሎ ሊታይ፣
ይህ በምን ይለያል ከደደቢት ብቃይ! :lol:

ጂራ ጂራ ጂራ፣ ጂራ ጂራ ጂራ፣
በገነት ላይ ያለው ሃጫሉ ሲጣራ፣
በዙፋኑ ያለው በጥበብ ሲያጠራ፣
ጸረ ሰላሞችን በድምር በጣምራ፣
አደብ ስናስገዛ በኅብረት ስንገራ፣
ለሰላም ለፍትህ በጋራ ስንሰራ፣
እጅግ ደስ ብሎናል ጦቢያና ኤርትራ።
:mrgreen: :lol: :mrgreen: