Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የክስታኔ ጉራጌ ታሪክ

Post by Horus » 14 Feb 2020, 04:18

ከዚህ በታችህ የምጸሙትን ቪዲዮ በተመለከተ ያሉኝን እርማች መጥቀስ እፈልጋለሁ ።

አንድ፣ አይመለል ማለት በክስታኔኛ አይማለል ከሚለው ጋር አይያያዝም ። ወማለል ማለት ማፈር ማለት ነው። ያ አይደለም አይመለል። በሴም ቋንቋ ስረ ቃል ወይም ኤቲሞሎጂ አይመለል አማኝ ማለት ነው። አይመናን በድሮ አባባል አማኛን አማኞች ማለት ነው። በእብራይስጥ የአማኞች ህብረት ወይም ኮሚኒቲ ማለት ነው እንደ ማለትም ይቻላል።

ስለሆነም አይመለል የትግርናኛ ቃል አይደለም ። ቃሉ ከጥንትዊ ግብጽ እና ከግዕዝ ጋር የመጣ አሙን፣ አመነ ከሚለው የተቀዳ ነው።

ሁለት፣ ሶዶ በትክክል የቦታ ስም ነው እንጂ ከህዝብ ጎሳ ጋር አንድም ግንኙነት የለውም ። በክስታኔኛ ቋንቋ ሳድ፣ ሳዳ ፣ ሳዶ ማለት ክፍል፣ ክፍለ ቦታ፣ ክፍለ አገር ማለት ነው። ሳደ ማለት ከፋፈለ አከፋፈለ ማለት ነው።

ስለዚህ ሶዶ በፍጹም ለክስታኔ ጉራጌ መጠሪያ መዋል የለበትም። አገር፣ መንደር፣ ቀበሌ ማለት ነው። ለዚህ ነው ዎላሞ ሶዶ፣ ጉራጌ ሶዶ ሚባለው።

ሶስት፣ የጉራጌን ጉዳይ ከግራኝ ዘመን መጀመር ፍጹም ስህተት ነው ። ለዚህ ዋና ምስክር የአምደ ጽዮን ጦርነቶች ዝርዝር ውስጥ በአማዊቴዎች ላይ ስላገኘው ድል የተጻፈውን ገድል መርምሩ ። ይህም 1330ች ማለት ነው። የዚያን ዘመን ጉራጌ የዳሞት አካል ሆኖ በንጉስ ሞታልሜ (በእኔ ግምት የዮዲት ልጅ ልጅ ) ስር የነበረ አገር ነው። ጉራጌን መጀመሪያ የወሰደው አምደ ጽዮን ነው በ1333 ዓ/ም።

አራት፣ እንዲሁም ካምደ ጽዮን ቀድሞ ተክለ ሃይማኖት 1300ቹ እና በ1440ቹ ግብጻዊው አቡነ ገብረ መንፈስ በምድረ ክስታኔ ያዳረጉትን እንቅስቃሴ መጥቀስ ግዴታ ነው። ለምሳሌ ተልከ ሃይማኖት የሚያነጋግሯቸው የገላን ጎሳ የጥንት ኦሪት እምነት ተከታይ የጉራጌና ጋፋት አባቶች ነበሩ ።

ስለዚህ በሙሉ ምርምር ያልተደገፈ መደምደሚያ መወርወር ትክልል አይሆንም ።

የታሪክ እውነት መውጣቱ ስለማይቀር የችኮላ ስህተት መወርወር አስፈላጊ አይደለም ።

Last edited by Horus on 14 Feb 2020, 04:56, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የክስታኔ ጉራጌ ታሪክ

Post by Horus » 14 Feb 2020, 04:49

ሌላ የዚህ ቪዲዮ አዘጋጅ ብዙ ጥሩ ነገሮችን የያዘ ሲሆን ስህተቱ ያለ ምርምር እና አብነት መደምደሚያ ይደርሳል ። እነ ባህሩ እነ ብርሃኑ ለምን የጉራጌ ብሄረተኛ አልሆናችሁም ማለት ለምን ጉራጌ እንደሌሎች ጎሳ ፖለቲካ ገብቶ ሆያሆዬ አይልም እንደ ማለት ነው ።

ጉራጌ በራሱ ግዜና ውሳኔ ታሪኩን መርምሮ ያረጋግጣል ፣ እንደገቱንም እንዲሁ !!! የጉራጌ ሰውን በስሜት መቀስቀ ማስነሳት መሞከር ስህተት ነው።

ጉራጌ በምርምር እና በእውቀት መመራት ነው ያለበት ። ታሪክ አልፏል ። ነገ በ21ኛ ዘመን ክህሎት ነው ሚመራ !!!

Post Reply