Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5625
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: JAWAR: እዚህ ሀገር ሕግን በተግባር ከመጣስ ባልተናነሰ አዛብቶ መተርጎም እየጨመረ መጥቷል። ጀዋር የራሱ ጉዳይ፣ ሕጉን ግን በአግባቡ እንተርጉመው! የሕግ ትንታኔ በግዛው ለገሠ-law

Post by TGAA » 13 Feb 2020, 22:13

የነጀዋር ፖለቲካ ግልጽ ነው ፡ ህግ ወጥነት ተጫውተው የሚያሸንፉበት መንገድ ከተዘጋጀላቸውና ህጉ የማይመለከታቸው ከሆነ ኢ፟ _ ህጋዊ ስራቸውን ይቀጥላሉ ፤ 86 ሰው ገድለው ህጉ እስካልጠየቃቸው ድረስ ህጉ እየሰራ ነው ማለት ነው ፤ ህዝብን አፈናቅለውም ፤ አስፈራርተውም የስልጣን እስከወሰዱ ድረስ ህጉ ይሰራል ማለት ነው ; ነገር ግን ህግ ተከተሉ ሌላው የሚከተለውን ህግ አክብሩ እስከተባሉ ድረስ ግን ፤ ህጉ ይጠየቃል ፤ ስለህጉ ያነሱ ሰዎች ይዘለፋሉ; እንደ መራራ አይነቱ ፊተ ሞኝ ውስጠ ሾክ የሆነ ሰው ደግሞ እያጣቀሰ ለጸረ ኢትዮጵያዊያን መንገድ የሚያስተካክል ጠላት ; ፊቱ ኢትዮጵያዊ ይመስላል እያለ ወንጀሉን እየሰራ እንደገና ደግሞ ቀልደኛ ለምሰል ይሞክራል ፡ አንድአርጋቸው ፤ በስነስርአቱ ከአባልነት ወጥቷል ህጉን ስለሚያውቅ ፤ የውጭ ሰው ማመልከቻ ስላገባሁ ዜግነት ተሰጥቶች የመንግስት ስልጣን ካልተሰጠኝ የሚል ደደብ የኦሮሞ አክራሪ ብቻ ነው፡ ያብሎ ሆያሆሄም ከደደቦች ፋብሪካ የሚመጣ ነው ፡ ለሞኝ ንትርክ የአማራ ስም የያዘ ጠበቃ የጻፈውን ስለለጠፍክ ሀሳቡን ክርፋታ ምንም የሚቀረው ነገር የለም ፡ ይህንን ካሰበ ጀዋር ሁለት አመት ግዜ ነበረው ግን የዜገነቱም የመመለስ ማመልከቻ ያስገባው በጀንዋሪ ነው ፤ አሁን በሁለት ወር አሜረካ በህገመሰረቱ አጣርቶ ነጻ ነህ ብሎ ሳያጽድቅለት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ማሰረጃውን ሳያጸድቅለት ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል ፤ ነገ ደግሞ ፓርላማ ገብቶ የኢትዮጵያዊን ላይ ይወስናል ; እንዴት ነው የሚቀለደው፡፡ አሁን እነጀዋር እየሰሩ ያሉት ምርጫው ውጤቱን አጣጥለው እንደገና እንደለመዱት ህዝብ ለማስተራረድ ነው፡ ተገዳቸሁ አድርጉ ካለዝያ ደግሞ ልክ 86 ሰው እንዳሳረዱት የበለጠ ሰው እናጠፋልን ተጠንቀቁ _ ካለዚያ እንደፈለግነው መሆን አለብን የሚል የውርጋጥ ፤ የሌባ ፤ የማጅራት መጭ የማስፈራርያ ፖለቲካ ነው የያዙት; አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ እነዚህን ሽብር ፈጣሪዎች ህግ ምን እንደሆነ ማስተማር ግን የሀገሪቱን የወደፊት እጣ የሚወስን ነው ፡፡ መደረገ ያለበትም ይህ ብቻ ነው፡፡

Naga Tuma
Member+
Posts: 5536
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: JAWAR: እዚህ ሀገር ሕግን በተግባር ከመጣስ ባልተናነሰ አዛብቶ መተርጎም እየጨመረ መጥቷል። ጀዋር የራሱ ጉዳይ፣ ሕጉን ግን በአግባቡ እንተርጉመው! የሕግ ትንታኔ በግዛው ለገሠ-law

Post by Naga Tuma » 14 Feb 2020, 02:39

TGAA,

ያንተን መልስ ሳላነብ ነበር መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመጠየቅ የተነሳሁኝ። ተመሳሳይ ሃሳብ ቢሆኑም ያሰብኩትን ጸሃፊዉን ልጠይቅ።

፩ኛ) እናት እና ኣባት ኢትዮጵያዊያን ሆነዉ ኣሜሪካ በመወለዳቸዉ ኣሜሪካዊ የሆኑ ልጆች እናት እና ኣባት ኢትዮጵያዊያን ስለሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሊሆኑ ይችላሉ ማለት ነዉ?

፪ኛ) ኣንድ ዜጋ ማክሰኞ ኢትዮጵያዊ የነበረ፣ ረቡእ ኣሜሪካዊ ሆኖ፣ ሃሙስ ወንጀል ፈጽሞ፣ ኣርብ ተመልሶ ኢትዮጵያዊ ልሁን ካለ ጸሃፊዉ ልያስረዳ የሞከረዉ ህግ የሚሰራ ህግ ነዉ ማለት ነዉ? በቴክኒካል መስክ ስዋፕ ሞዴል (swap model) የሚባል ሃሳብ ኣለ። ሁለት መቀላቀል የማይፈለጉ ነገሮችን ከኣንድ ጣሳ ወደ ሌላ ጣሳ ለመቀየር የግድ ሶስተኛ ባዶ ጣሳ ያስፈልጋል። በዚህ ህግ መሰረት መጀመሪያ ሁለተኛ ጣሳ ዉስጥ ያለዉን ሳያጋቡ ኣንድ ጣሳ ዉስጥ የነበረዉን ወደ ሁለተኛዉ ጣሳ ዝም ብሎ መገልበጥ ይቻላል ማለት ነዉ? እኔ የህግ ኣዋቂ ኣይዴለሁም። ሃሳቡን ግን መገንዘብ እፈልጋለሁ።

Post Reply