Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4204
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችና በኤርትራ ወታደር የነበረች ስደተኛ ከጓደኛዋ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጣ ከገባች ስድስት ቀን እንደሆናት ተናግራለች። ግን አንመዘግብም አሉን ትላለች

Post by Abaymado » 13 Feb 2020, 10:14

‘’ ቦታውን በግልጽ አላወቃችሁትም፤ሁለታችሁ የምትናገሩት ሠዓት የተለያየ ነው። ስለዚህ አንመዘግብም' አሉን"
………………………………………………………………………………….............
ኤርትራውያን ከሀገራቸው ወጥተው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በድንበር አካባቢ ምዝገባ እንደሚደረግ ይታወቃል። ከዚያ በኋላም ወደ ምዕራብ ትግራይ እንዳ'ባጉና ከተማ ይመጡ ነበር።
እዚህ ስፍራም ስለግለሰቦቹ አስፈላጊው መረጃ ከተጠናቀረ በኋላ ወደ ስደተኞች መጠለያ እንዲገቡ የሚደረግበት አካሄድ ነበር።
ዛላንበሳ ድንበር ፋፂ ከተማ እስካሁን ኤርትራውያን ስደተኞችን እየመዘገቡ ሲያስገቡ የነበሩ የፌደራል መንግሥት የስደተኞችና የስደት ተመላሾች ተቋም ሠራተኞች 'አንመዘግብም' ማለታቸውን ቢቢሲ ከስደተኞቹ መረዳት ችሏል።
ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችና በኤርትራ ወታደር የነበረች ስደተኛ ከጓደኛዋ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጣ ከገባች ስድስት ቀን እንደሆናት ለቢቢሲ ተናግራለች።
ነገር ግን ፋፂ አካባቢ የሚገኙ ስደተኞችን የሚመዘግቡ አካላት ግን ሊመዘግቧቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ታስረዳለች "ወታደሮች እንደነበርንና ለድንበር አሻጋሪ ደላሎች 40 ሺህ ናቅፋ ከፍለን እንደመጣን ነገርናቸው። 'የመጣችሁበትን ቦታ ግልጽ ተናገሩ' አሉን። ምን ያህል ቀን እንደተጓዝን እና ሠንዓፈ ከተማ እንደደረስን አስረዳን። ' ቦታውን በግልጽ አላወቃችሁትም። ሁለታችሁ የምትናገሩት ሠዓት የተለያየ ነው። ስለዚህ አንመዘግብም' አሉን" ብላለች።
ቢቢሲ ከተቋሙ መደበኛ ባልሆነ መልኩ ባገኘው መረጃ መሰረት ከሆነ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ኤርትራውያን ስደተኞችን የመመዝገቢያ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።
ይሁን እንጂ ይህ አሰራር በይፋ ለተገልጋዮች አልተገለጸም።
https://bbc.in/2USXGz9


Fed_Up
Senior Member+
Posts: 20573
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችና በኤርትራ ወታደር የነበረች ስደተኛ ከጓደኛዋ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጣ ከገባች ስድስት ቀን እንደሆናት ተናግራለች። ግን አንመዘግብም አሉን ት

Post by Fed_Up » 13 Feb 2020, 10:30

Gone those days agamewoch claim Eritrean refugees and settle in the West. If you noticed the news say she can’t even identify the geographical location she claimed and her bogus none existent military post. Hehehehe this is what we have been saying for so long that there might be few delusional Eritreans but all the refugees camps are full of your beggars cousins, agamewoch claiming Eritreans. No more!!

Post Reply