Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የትግራይ ህዝብ እና ህወሓት! ክፍል 3

Post by Hameddibewoyane » 13 Feb 2020, 06:52

አቶ ከሊፋ ኩሪ ይባላሉ፣ ነዋሪነታቸው ወረዳ አድያቦ ነው፣ አቶ ከሊፋ ሶስት ልጆቻቸው በህወሓት ትግል መስዋእትነት ከፍለዋል።

አመተ ከሊፋ
ግርማይ ከሊፋ
ገብረመስቀል ከሊፋ

አቶ ከሊፋ በእርሻ ይኖራሉ፣ ሰዎቱም ልጆቻቸው በህወሓት ትግል ስለ ተሰዉባቸው መሬታቸው የሚያርስላቸው የለም፣ ስለሆነም መሬታቸ ከሚያገኘው ምርት ተካፍለው ያሳርሱታል። አቶ ከሊፍ ምግብ ካገኙ ይበላሉ ካጡ ደግሞ ፆማቸው ያድራሉ። ባለቤታቸው በሂወት ስለሌሉም ከሚበሉበት የማይበሉበት ቀን እና ሳአት ይበዛል። አቶ ከሊፋ ልጆቻቸውን ባሳደጉባት ደሳሳ ጎጆ ይኖራሉ። የህወሓት አመራሮች በአዲስ አበባ እና መቀሌ ያሰሩት ፎቅ ቤቱ ይቁጠረው። አቶ ከሊፋ ባለቤታቸውም ስለሞቱባቸው መራብ እና መጠማት እንደ ፀሃይ መውጣት እና መጥለቅ ተያይዘውታል። እኝህ የሰማእታት አባት እየተራቡ እና እየተጠሙ ህወሓቶች እና የትግራይ ዳያስፖራዎች የካቲት ፩፩ን፣ በጭፈራ እና በመጠጥ ሊያሳልፉት ነው።

ህወሓት ለየካቲት የምታወጣውን ሁለት መቶ ሃምሳ ሚልዮን ብር ስንት የሰማእታት ቤተሰብ የኑሮ ሁኔታ ይቀይር ነበር! አሁን የሚኖሩበት ጎጆ እንካንስ ሰው እንስሳም እንዲኖርበት የምትመኘው ጎጆ አይደለም።ተጋዳላይ ባመጣው ድል እምበር ተጋዳላይ መዝፈን ጀግንነት ያደረጉት የትግራይ ሙሁራን እና የትግራይ ዳያስፖራዎች፣ በየሜዳው እና በየተራራው ልጆቻቸው ያጡ የሰማእታት ወላጆች ምን ላይ እንዳሉ እንኳን ለአንድ ቀን ማሰብ አልቻሉም። ድል ለትግራይ ህዝብ ሞት ለህወሓት አመራሮች!!!


Abdelaziz
Senior Member
Posts: 11365
Joined: 29 May 2013, 22:00

Re: የትግራይ ህዝብ እና ህወሓት! ክፍል 3

Post by Abdelaziz » 13 Feb 2020, 06:55

JISS TEALE ATA CHENAWI MEAKORU TEREWAEE HAMAENAY LOOTIEEW, THIS IS ETHIOPIA, I DO NOT KNOW WHY YOU KEEP ON COMIG HERE DAY IN AN DAY OUT. YIRDAEKA, ATA DIRBAY, BOOSHTIEW HAMASENAY.

Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

Re: የትግራይ ህዝብ እና ህወሓት! ክፍል 3

Post by Hameddibewoyane » 13 Feb 2020, 06:56

እኝህ አባት አሕፈሮም በተባለ ወረዳ ከባለቤታቸው አደይ ለተማርያም አብርሃ ጋር አብረው ይኖራሉ፣ በትግሉ ጊዜ ሶስት ልጆቻቸው
መብሪሂት
ፀጋይ
ሃይለ
የተባሉ አጥተዋል። ከድል ቦሃላ ህወሓት ስልጣን ስትይዝ፣ እኝህ የሰማእታት ቤተሰብ እንደማንኛው የትግራይ የሰማእታት ቤተሰብ ተረስተዋል። የህወሓት አመራሮች የሰማእታት ደም ወደ ዊስኪ፣ የሰማእታት ስጋ ወደ ቁርጥ ቀይረው ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት በትግራይ ህዝብ ስም መላው የኢትዮጲያ ህዝብ ሲጨቁኑ ከርመዋል። እኝህ የሰማእታት ቤተሰብ መስማት እና ማየት ካቆሙ አስር አመታት አልፎባቸዋል፣ ከአልጋ መነሳት አይችሉም፣ ሽንትቤት የሚወስዳቸው ልጃቸው ነው፣ ሲሪባቸው እና ሰውነታቸው ሲያማቸው ጎረቤት እስኪሰማ ድረስ ይጮሃሉ። በህክምና እና በንፅህና ጉድለት ሰውነታቸው በቁስል ተወረዋል። የህወሓት ልጆች አሜሪካ እና አውሮፓ ይማራሉ ይኖራሉ ይመላለሳሉ።የህወሓት ባለስልጣንት ግን አሁንም ድረስ በትግራይ ህዝብ ስም ባቋቋሙት ድርጅት(ኢፈርት)በሆቴል ውስጥ ይኖራሉ፣ ይበላሉ ይጠጣሉ። የሰማእታት ቤተሰቦች በደህንነት እየኖሩም፣ የካቲት 11 ለማክበር ህወሓቶች ሁለት መቶ ሃምሳ ሚልዮን መድበዋል፣ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ህዝብ በተራበበት ወቅት ለጭፈራ እና ለመጠጥ ያባክናሉ። የዛሬ ሃያ አመት የተቋቋመው የሰማእታት ቤተሰቦች ድርጅት በስብሓት ነጋ መሪነት ፈርሰዋል፣ ያኔ የተዋጣው ገንዘብም የህወሓት አመራሮች በልተዉታል። በዳያስፖራ የሚኖሩ ተጋሩም፣ እኝህ አባት እና እናት በተራቡበት፣በተጠሙበት ጊዜ የካቲት አስራ አንድ ለማክበር እና ለመጨፈረ ወስነዋል። ድል ለትግራይ ህዝብ ሞት ለህወሓት አመራሮች።

Post Reply