Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 03 Feb 2020, 23:05

ስለሆነም ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ዛሬ ስለ አለው ሁኔታ የመለሳቸው መልሶች ትክክል ናቸው ። ማለትም በአሁን ሰአት ኢትዮጵያን የሚመሩ ሰዎች ማሰብ ያለባቸው እንዴት አድርገው በቀውስ ውስጥ መምራት እንደሚችሉና ያንንም እምዴት ማወቅ እንዳለባቸው ነው ።

ምሳሌ፤

አንድ፣ የሚቀጥለው ምርጫ የተወሰነ መረጋጋት ቢፈልግም፣ ሙሉ ሰላም እስከሌለ ምርጫ አይደረግ የሚለው የተሳሳተ ግንዛቤ ነው ። በተለይ ሰላም የፈጠሩ ቦታዎች ምርጫ የማድረግ መብታቸው መጠበቅ አለበት ። ሰላም መፍጠር የማይፈልጉና ያልቻሉ እየተማሩ መሄድ አለባቸው ።

ሁለት፣ ለደቡብ ሕዝብ የተሰጠው መልስ እጅግ ትክክል ነው ። በደቡብ መሰረታዊ ልማት፣ የኢኮኖሚ ልማት እና ራስ ገዝነት ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መደራጀት አለባቸው ። ባዶ የክልልነት ሆያ ሆዬ ለደቡብ ሕዝብ አይመጥንም ። በመሰረቱ ሲዳማ ተሳተዋል፣ ሌሎች ያንን ስህተት ቢደግሙ ድድብና ነው።

ሶስት ፣ በእኔ ግምት በኢትዮጵያ ሰላምም ሆነ እድገት የሚያመጡት ግለሰቦችና ትንንሽ ማህበሮች ስለሆኑ ያለው ቀውስ እንዳለ በጥበብ ይዘው ስራቸውን በየመስኩ መትጋት ነው ያለባቸው ። የቀውስ ሆስቴጅ ወይም እስረኛ መሆን የለባቸውም ።

ቀውስ አዲሱ የኢትዮጵያ ሰርዓት ነው ። አዋቂና ብልሆች በዚህ ቀውስ ውስጥ መኖር፣ መስራት፣ መልማት የሚችሉት ናቸው ።

ባንድ ቃል ኢትዮጵያ የተሸጋገረችው ከዎያኔ አምባ ገነንነት ወደ ቀውስ ነው እንጂ ወደ ሙሉ ሰላምና መረጋጋት አይደለም ። ይህን መገንዘብ የዛሬ ፖለቲካ ሃ ሁ ነው ።



TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by TGAA » 03 Feb 2020, 23:56

ሁለት ነገሮችን ነው ማየት ያለብን፡ ቀውሱን ስርአተ ህግን ተጠቅመን መቆጣጠር የምንችለው ነው ፤ ወይስ ከቁጥጥር ውጭ የሚሆን ቀውስ እየሆነ ይመጣል? አብይ ፖለቲካዊ ህግና ስርአት አጠባበቅ ፍጽሞ መውጣት አለበት ፤ ባጠቃላይ ይህግና የጽጥታ መዋቅሩም ከፖለቲካ መሳሪያነት ውጥቶ ለህዝቡ ህግን የሚያከበር መንግስታዊ መዋቅር መሆኑን ማሳየትና የህዝቡን አመኔታ ማግኝት መቻል አለበት፡ ከጥቅላይ አቃቢው አንስቶ ስለጀዋር መሀመድ የሰጡት ፖለቲካዊ መግለጫዎች ህግ አስከባሪዎች ከማንኛውም ነጻ የሆኑ በእውነት ወንጀለኛውን ፈልገው ለመቅጣት የህግ ተቋማት መሪ ሳይሆኑ አጀንዳ አራማጅ የፖለቲካ አቀንቃኝ መሆናቸውን በግልጽ አሳይተዋል ፡፡ 86 ሰው በቀን ሲታረድ እያየ ፤ ብጥብጡ የተነሳው እኛ ኦሮሞዎችን ለመከፋፈል ነው ብሎ መግለጫ ሲሰጥ ፤ የኦሮምያ ፖሊስ ኮሚሽነር ደግሞ ጀዋር ያይናቸን ብሌን ነው ብሎ ሲለፈልፍ ይታያል ፡ እንዲህ አይነት የህግ መዛባት ያለበት ሀገር በጭራሽ ልትረጋጋ አትችልም ፡ የአብይ የህግ ተቋማት የፖለቲካ ማራመጃ እንጂ የፍትህ ገለልተኛ ሆነው አልታዩም ፡፡ የህግ ተቋቅማትን ከፖለቲካ አግልሎ ቢመ ራ ኖሮ ፤ ህዝቡ ወንጀሎችን በወንጀላቸው እንጂ ፖለቲካ ማራመጃ፤ መሳሪያ ነው ብሎ አያስብም ነበር፡፡ በቅርቡ የኦሮምያ ፖሊስ ባለስልጣን የታገቱትን ሲቶች ምንም ማስረጃ ሳይኖረው አውቀው እራሳቸም ለፖለቲካ ፍጆታ ሰውረው ይሆናል ብሎ ሲናገር ፤ ፖለቲካዊ ንግግር እንዲሁም ወገናዊ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ቀውሱ መቼ እንደሚያልቅ የለም ብሎ ድምዳሜ ቢሰጥ እንኳን ህጉ እንዲት ይህንን እንደሚቆጣጠረው ፤ ማስረዳት ነበረበት፡፡
ሌላው ችግር ደግሞ በአሁኑ ሰአት ይብዛም ይነስ የተወሰነ ህዝባዊ እምነት በአብይ ላይ አለ፡፡ ነገር ግን ሀገሪቷ መረጋጋት ላይ ሳትደርስ እግዚያብሄር አይበለውና አብይ ቢሞት እህንን እንደወንፊት የተበተነ ህብረተሰብ እንደገና መልሶ አብሮ ለማድረግ የግዴታ በደም መፍሰስ መሆን አለበት ማለት ነው፡ ስለዚህ በአፋጣን በራሳቸው ቆመው የሚሰሩ ህጋዊ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ በጣም ወሳኝ ነው ፡፡

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 04 Feb 2020, 00:15

TGAA
አሁንኮ አንተ ጥሩ አድርገህ የምትዘረዘው ራሱ ቀውሱን ንው! ያ ነውኮ ወደፊትም የሚቀጥለው ቅውስ ። የቀውሱኮ አንደኛ ምክንያት ራሱ መንግስቱ ነው ። ቀጥሎ ራሱ ገዢው ፓርቲ ነው ። የዚያ ሁሉ ግንዱ የጎሳ ፖለቲካ፣ ክልልና የጎሳ ፌዴሬሽን ናቸው ። ችግሩኮ አንድ ማህበረሰብ ከፋም ለማም ያለ መንግስት አንድ ቀን ሊያድር አለመቻሉ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ያላት ሰራት ይህ ነው በቃ ። አቢይና ሌሎች ቀስ በቀስ ወደ ህግ ግዛትና ሰላም ይወስዱታል ወስይ ፈስትሞ ወደ ሱማሌ ኔዳለን የሚለው ነው ጥያቄው ። በዚህ ቀውስ ተጠቅሞ ራሱ ብልጽ ኛ ወደ ፍጹም አምባገነን ፓርቲነት ሁሉ ሊሄድ ይችላል ። ስለዚህ በጉቦ ሚነዳው የሲቪል ህግ ካልሆነ በቀር ሌላው ህግ ከንቱ ነው። እንዲያውን አቢይ እየሰበረው ሻል ያለ ነገር ቢያረግበት ነው ጥሩ። አንድ አፍ ቀውስ ማለት ይህ ነው !

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by TGAA » 04 Feb 2020, 01:02

Horus, ቀውስ እንደሚኖር የማይቀር ነው ከመንግስትም ይሁን በጎሳ ፖለቲካ ልክ እንደ ፋፋ የህጻናት ምግብ ሲመገብ ለከረመ ሰው አይቀሬ ነው ፡ የኔ ትኩረት የምናልፍበትን ጉዞ ሳይሆን የት ነው መድረሻቸን የሚለው ነው፡፡ አሁን ፖለቲካዊና ህጉ ለይቶ እንኳን ማየት አይቻልም ህጉ ያለው በፖለቲካው ስር ነው ፤ ፖለቲካው ደግሞ አድሏዊና ጎሰኛ ነው ስለሆነም ለፖለቲካው መገዛት የሚፈልግ ሰው አይኖሩም ፤ ፖለቲካው አድሏዊም ስለሆነ ህዝባዊ ቅቡልነት የለውም መጨረሻውም ወደ ግጭት ነው የሚያመራው፤ ነገር ግን በራሱ የቆመ ህጋዊ ተቋምና ህግ አስፈጻሚው ልክ እንደ ብሄራዊው ሰራዊት ለሁሉም በተግባር ያለአደሎ እኩል የሚያገለግል መሆኑን በተግባር ቢያሳይ ቀስ በቀስ የህዝብ አመኔታ እያገኘ በመሀከል ላይ የሚከሰቱት ቀውሶች ከመንግስትም ይሁን ከህዝብ ይመንጩ ለብቻው የቆመ ፤ፍጹም እንኳን ባይሆን አሳማኝ አድላዊ ያልሆነ ውሳኔ ለህዝቡ በመወሰን እምነትን ካገኘ ቀስ በቀስ ቀውሱ በህግ እየተገዛ እየሰከነ ይመጣል ፡፡ አሁን ግን የዘር ፖለቲካና ህግ እየተነካካ ፖለቲካው አድሏዊነቱን በህግ ሽፋር የሚያራምድ ከሆነ ቀውሱ ይባስ ብሎ እንደውም የህብረተሰቡን መሰራት እየሸረሸረ አብረን የሚያስተሳስረን ነገር እንኳን ላይኖር እንዳችሉ ሊያደርግ ይችላል፡ ለዚህ ነው ህጉ በቀውስ ስርአት ውስጥ፣ ቀስ በቀስ እየተጠናከረ መምጣት ያለበት የምለው ፤ ያ ብቻ ነው ተስፋ ሊስጠን የሚችለው፤ የፖለቲካውና የፖለቲከኞች በመንገድ ወደ ገነት ሳይሆን ሲኦል ነው የሚወሰደን _ በሌላም ምክንያት ሳይሆነ አርቀው ማየት የማችሉ በስሜት እንደ ተልባ የሚንጫጩ ደደቦች ስለሆኑ ፡ እራሳቸውንም ሀገሪቷንም በእውር ድንብር ገደል ነው የሚከቷት ፡፡

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 04 Feb 2020, 01:52

TGAA ,
እኔኮ የንተን ፍርሃትህም፣ ተስፋህም፣ ምኞትህም እጋራለሁ ፤ ግን ያ የኛ ምኞት ነው። ልክ እንዳልከው ዛሬ በኣኢትዮጵያ ፖልቲካና ሕግ ባንድ ገመድ መታሰራቸው ብቻ ሳይሆን ያለው ያ ሰራዓት ነው። ፓርላማ ተብዬ ሀግ አውጪ ወይም መወሰኛ የዘመናችን ቀልድ ነው። የህግ ክንፉ የብልጽኛ ካድሬ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያ ያለው አንድ ፓርቲና የሱ መንግስት ነው። ሌላ ትንተና እንኳንስ ኢዜማ አቢይም አላቀረበም ። ጥያቄው አማራጩ ምንድን ነው ?

ብዙ ኢትዮጵያዊያን ጎሳ ና ክልል ቅዠታቸውን ትተው ህዝቡን በኢጎሳዊ ድርጅት ቢሰበስቡ አንድ ቀን ይህ ነገር ይቆም ነበር። ግ ን አዳሜ ራሱን በጎሳ እያሰባሰበ በኢትዮጵያ ስም ፕሮፓጋንዳ ቢነፋ ሰሚ የለውም።

የጎሳ ሳይኮሎጂ፣ የጎሳ ሚዲያ፣ የጎሳ መሰባሰብ፣ የጎሳ ክልል፣ የጎሳ ጦር፣ ወዘተ እስከ ቀጠለ አይደለም ያሁኑ የበፊቱ ይብሳል ። ስለዚህ የቀውሱ ሁሉ መሰረት፣ የቀውሱ ሁሉ ፈጣሪ በጎሳ ስም የሚንፋው ድንቁርና ነው። በለፈው 2 አመት እምኳን የጎሳ ፌዴሬሽን እንዲፈርስ፣ የጎሳ ድሪጅቶች፣ የጎሳ ሚዲያ እንዲፈርሱ ብንታገል ዛሬ ማጆሪቲ እንሆን ነበር።

ማን ም ጎሳ ራሱን በጎሳ እያደራጀ የሚያመጣው ፋይዳ የለም ። ልብ በል አማራ በግፍ የተጠለፉ ሴቶችን ማስፈታት አልቻለም ! ለምን ቢባል ማን ከማን ጋር ነው ጦር የሚዋጋ !! የጎሳ ደንፊዎች የስይኮሎጂ እርካታ እንጂ ፋይዳ ቢስ ናቸው ። መፍትሄው የጎሳ ድራማ ሁሉ ከመድረክ በማውረድ ለረጅም ኢትዮጵያዊ መዋቅሮች መስራት ነው ። እስከዚያ በጉልበተኛ የጎሳ አለቃ ስር የቀውስ ሰለባ መሆናችንን መካድ ዉሸተኛ ያስብለናል። ህግና ፖለቲካ እንዲለዩ ከፈለን ፖለቲካና ጎሳን መለየት ግድ ይለናል !

Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Dawi » 04 Feb 2020, 01:56

Horus wrote:
04 Feb 2020, 00:15
TGAA
አሁንኮ አንተ ጥሩ አድርገህ የምትዘረዘው ራሱ ቀውሱን ንው! ያ ነውኮ ወደፊትም የሚቀጥለው ቅውስ ። የቀውሱኮ አንደኛ ምክንያት ራሱ መንግስቱ ነው ። ቀጥሎ ራሱ ገዢው ፓርቲ ነው ። የዚያ ሁሉ ግንዱ የጎሳ ፖለቲካ፣ ክልልና የጎሳ ፌዴሬሽን ናቸው ። ችግሩኮ አንድ ማህበረሰብ ከፋም ለማም ያለ መንግስት አንድ ቀን ሊያድር አለመቻሉ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ያላት ሰራት ይህ ነው በቃ ። አቢይና ሌሎች ቀስ በቀስ ወደ ህግ ግዛትና ሰላም ይወስዱታል ወስይ ፈስትሞ ወደ ሱማሌ ኔዳለን የሚለው ነው ጥያቄው ። በዚህ ቀውስ ተጠቅሞ ራሱ ብልጽ ኛ ወደ ፍጹም አምባገነን ፓርቲነት ሁሉ ሊሄድ ይችላል ። ስለዚህ በጉቦ ሚነዳው የሲቪል ህግ ካልሆነ በቀር ሌላው ህግ ከንቱ ነው። እንዲያውን አቢይ እየሰበረው ሻል ያለ ነገር ቢያረግበት ነው ጥሩ። አንድ አፍ ቀውስ ማለት ይህ ነው !
Horus,

p2 won't have a choice in our case; if TPLF & Jawe & assoc. force election, Abiy right after the fake election should move to "Dictatorships" to manage the coming crisis situations.

He will do the El-Sisi type; a "friendly" dictator per Trump. Most of the modern societies, even liberal democratic systems have states of emergency, states of siege, or martial law to deal with catastrophes, crisis and threats. As is, our is like that.

The American South during the early stages of Reconstruction, France 2005 civil unrest and again in 2005? in the US state of Louisiana due to hurricane Katrina. This special states are very similar to "dictatorships", but they are justified because, these are the largest threats to the well-being of their citizens, and swift decisions have to be made to solve them.

For a developing nations like ours, more than anything else lack of development (poverty) is a very big threat to the well-being of our citizens, and so swift decision making is crucial to solve this as well. All the countries that have it have resolved crisis with that.

deja vu! Meles!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 04 Feb 2020, 02:13

Dawi,
አንተ ያልከው አንዱ ሊሆኑ ከሚሽሉት ሴኒሮች ነው ። ይሆናል ማለት ግን አትችልም። ባገራችህን እርስበርስ የሚሳሳቡት፣ የሚገታቱት ህይሎች ብዙ ናቸው። በኢትዮጵያ ያሻህን ፕላን ማድረግ ትችላለህ ግ ን አንተን ለመግታት የሚችሉ እልፍ ናቸው። የኝ ችግር ሌላውን ማስቆም አይደለም ። ራሳችህን ወደ ፊት መገስገስ አለመቻል ነው። ስለዚህ አቢይ እጅግ ከገፉት አምባገነን እንዲሆን ህዝቡ ራሱ የሚጠይቅ ይመስለኛል፣ ለዚህ ነው ደደብ የጎሳ ፓርቲዎች መረን መልቀቅ የሌለባቸው። ግ ን አቢይ ራሱ አምባ ገነን በመሆን መሞት የሚፈልግ ሰው አይደለም ። ማለትም የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሻማ ገና አልጥፋችም ።

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by TGAA » 04 Feb 2020, 02:22

በጣም ጥሩ አድርገህ አስቀምጠህዋል ፡፡ አንተ የምትለው መሰረታዊ ፖለቲካ ቀዶ ጥገና አድርገን የመፈወሱን ግዜ እናቅርበው ፤ ሁሏችንም ጥፍንጎ በሽተኛ ያደረገን ጎሰኝነት ስለሆነ፡ የጎሳውን ፖለቲካ ካመከነው ሌላው በሽታን መፈወስ ቀላል ነው ፡ ህጉንም ሆነ ኢኮኖሚውን፡ እስማማለሁ፡፡ካንተ ትንሽ የምለየው
የጎሳው ፖለቲካ ኢትዮጵያን በጣም ጎድቷቷል ፡ ህዝቡም ልክ በቪይረስ እንደተበከለ ሁሉ አስተሳሰቡ ዞሮ ዞሮ ወደዚያው ጎሳ ሀይቅ ውስጥ ዘሎ ይዘፈቃል፡፡ በተለይ ደግሞ በጎሳ ፖለቲካ የደለቡ ጥቅማቸው እንዳይቀርባቸው ለመዋጋ ዝግጁ የሆኑ በአብይ መንግስትም ስር ይሁን በተቃዋሚ ነን የሚሉ ጎሰኞች ከፍተኛ እየቀሰቀሱ ነው ፤ በእንደዚህ ባለ ሁኔታ ላይ የአጭርና የረጅም ግዜ ተግባራዊ ውጥን ያስፈልጋል ፡ ህጉን በሁሉም ደረጃ ካጠናከርነውና ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ቀስ በቀስ መብት ምን እንደሆነ ፤ ህጉም ህገመንግስቱ ላይ ያለው እንደሚያስከብርላቸው በተባር ማሳየት ከተቻለ ለነጻነት ፤ ሀሳብን በነጻ ለመግለጽ መብቶች ተግባራዊ ሲሆኑ ሰው ወደ አንድ ካምፕ እየተሰበሰበ ፤ ጉሰኝነትም እየመነመነ ይሄዳል; ከዚያ በኋላ አንተ እላይ የዘረዘርካቸው መልካም ሀሳቦች የለማ አፈር ላይ በቀላሉ መብቀል ይችላሉ ፤ ምንም እንኳን ደምዳሜ ሀሳብህን 100/100 ብስማማበትም እዚያ ላይ እንዴት እንደምንደርስ ግን ግልጽ ያደረክ አይመስለኝም ፡

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 04 Feb 2020, 02:36

ቲጂኤኤ፣
እኒኮ ነገርኩህ በማህበራዊ ሳይንስ ውስጥ ትንበያ የሚባል ነገር የለም፤ እኔ አንድ ነገር ሳደርግ፣ አንተ አንድ ነገር ታደርጋለህ ። ልክ አሁን ለዚህ ሃሳቤ ምን እንደ ምትመልስ መተንበይ እንደማልችል ማለት ነው። የት እንደ ምንደርስና እንዴት የምንወስነው እኛ ራሳችን በምናደርገው ስራ ነው። አቢይ አምባገነን እንዳይሆን ከፈለን ማድረግ እንችላለን፣ እንዲህ ያለውን የስትራተጂና ታክቲክ ነገር ተግባር ሜዳ ላሉት ይቅር ። ዋና ቁም ነገሩ ግን የነገን ምጽአት ምንወስነው እኛ ነን፣ በስራችህን ማለት ነው። We can't predict the future, but we can choose it, we can create it.


Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 04 Feb 2020, 02:52

TGAA wrote:
04 Feb 2020, 02:48
I agree with you completely.
ሰላም ዋል፣ ኬር !

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 04 Feb 2020, 03:21

ይቤሎ፣
አንተ መሃይም ! በቀውሱ ምትታመስ አንተው ነህ፣ ገንፎ በሳት ይሳቅ ወይስ አመድ በሳት ይሳቅ?? አንተና ያንተ ድራማኮ እለታዊ መሳለቂያችን ነው !!! አየሃት ያቺ የዎያኔ አሮጊት የተጻፈላትን ማንበብ አቅቷት?!!! ደሞስ በጂማ ያለው የኦሮሞ ጎሰኞች ድራማ እንዴት አየሀው ማፈሪያ !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 04 Feb 2020, 04:28

ያቤሎ
አንተኮ የምታስገርም ሰው ነህ !!! ኦሮሞ ማእትኮ ኦሮሞኞ ቋንቋ ሚናገር ልዩ ልዩ ጎሳ ማለት ነው ። በኦሮሞ ወረራና መስፋፋት የጠፉትን ጋፋት ሳንቆጥር፣ ገላን፣ ያዮ፣ ጨቦ፣ ዛይ፣ አዘርነት፣ ጂዳ (ለለጌ) ። እንደ ገብጣን ፣ ማረቆ (ማለቆ) ወዘተ ሁሉ በደም ጉራጌ ዛሬ ኦሮሞፋ ተናጋሪ ህዝባችህን ናቸው !! አንተም ዬኔ ኦሮሞፋ ተናጋሪ ኮንታ ትሆናለህ!! ፈታ በል ከጉራጌ የተጠጋ ክቡር ነው ሚሆን !!!!


TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by TGAA » 04 Feb 2020, 09:47

Yabllo Arrarsa is an individual who have been ravaged with self induced chronic inferiority complex. No cure insight. The only solution is let him wallow in self pity whenever Ethiopians raise above and beyond his tribal utopian that never were. I enjoy the pain in his blabber when Abiy kick his balls and makes the Babylon tower he disparately want to build out of reach and out of sight. Hi Arrarsa how your buddy Ayatola is holding up? He doesn't seem to please you no more..just like the Babylon time a communication problems are spinning in? The so called activist calling you a radical dose bite a little bit. Hold on tight .

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by TGAA » 04 Feb 2020, 22:06

After years of scrabbling "about the prison of national and nationalities the Ethiopian empire bla bla bla " what failed to sink in your vicious skull is that being whatever nationality you are and being a proud Ethiopian never been mutually exclusive concept. It has been demonstrated time and time again that Bing an Ethiopian is the crown of all Ethiopian nationalities. Who the hell make you to represent Oromos -- except the pseudo speakership you assigned to yourself. All your writing evolves around Amhara this Amhara that -- there is a deep psychological wound that never seems to heal. You gloat whenever you hear the Amharas are divided, you cry like a baby when you see the strength of Ethiopian nationalism both within Amhara and without, all your collection of items of news and pictures geared to toward a poor assumption that the demise of Ethiopia is near. You have no clue the potent of Ethiopian nationalism if you want to dismantle, you have to be really prepared to pay in blood and limbs more than the Ethiopian nationalist are willing to pay. If you win, you can have your fiefdom for your selected posterity. I guarantee you though you phonies will disappear like a speck of dust in the wind when push comes to shove. By the way the beautiful Agew girls you posted as proof are wearing Ethiopian Green, Yello, Red flag hand band and head ribbon. The last time I checked all Ethiopians and particularly Amharas love for the Ethiopian flag is unparalleled. Do you see the irony? But again I don't have confidence in your ability to read this kind of Ethiopian social cues. You wouldn't have provided evidence that contradicts your own statements. Do you think these monkeys are welcoming and hospitable to "newcomers? Their facial expression says otherwise, but Do I have to guess where you will end up with your mob glorification tendencies? You be the judge if you have a clue what it is.
enjoy:
https://i.pinimg.com/originals/b5/bb/48 ... 05bc96.jpg

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by TGAA » 05 Feb 2020, 01:25

Though some of the pictures have an entertaining value, such as the guy with " I am a kemant committee sign on his mule forehead, all the rest is just fluff. The problem with tribalist nuts such as you is that by default you mistake the fluff for substance.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 05 Feb 2020, 01:46

በእኔ እምነት ሰዎች ለእቀታቸውም ለድንቁራንቸውም ተጠያቂዎቹ ራሳቸው ናቸው ። በኢትዮጵያ ለ30 አመት ሰፍኖ ያለው የጎሳ ስርዓት ነው ። ስለዚህ የእኔ ምኞትና መሻት የጎሳ አገዛዝ እና የጎሳ ሴራ መቃወስ፣ መታመስ፣ መፈራረስን ማየት ነው። ይህን እያየን ነው። የዘር ፖለቲካ የትም ቦታ እየሰራ አይደለም ። ይህን ነው አቢይ የመሰክረው ። አሁን የዚህ ፎረም የጎሳ መሃይሞች ለደቂቃ እንኳን ማሰብ አይችሉም።

ኢትዮጵያ በቀውስ ውስጥ ነች ሲባልኮ የጎሳ ነጋዴዎች ማለት ነው ። ሕዝቡማ በጎሳ ሌቦች ሴራ ከሚረገጡና ከሚዘረፉ በጎሳው ቀውስ መዝናናት ሺ ግዜ ይመርጣሉ !!!

ይህን ምስጢር የጎሳ ደንቆሮ ሊይዘው አይችልም !!!

The people prefer the crisis and chaos of tribalism over the order and stability of tribalism !!!


Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 05 Feb 2020, 02:05

:!: :!: :!: የጎሳ ፖለቲካ እስከሚጠፋ ቀውሱ ይቀጥላል ። የጎሳ ተሰላፊም በረሃብ እየተቆላ ጎሳ ማለት ስህተት እንደ ሆነ ይቅመስ ። ትምህርትም ይቁም የጎሳው መንገድ ዘጊም በመሃይምነት ኑሮን ይሞክረው ። ምክር የማያስተምረውን ቀውስ ያስተምረዋል !!!

tlel
Member
Posts: 1559
Joined: 28 Dec 2019, 14:24

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by tlel » 05 Feb 2020, 02:26

yaballo wrote:
04 Feb 2020, 04:05
ሆረስ፣

የጅማ ቀውስ ብሎ ነገር የለም። ያ የኦፒዲኦ ካድሬዎች ሼር አካል ነው። ለማንኛውም ጅማ አባ ጅፋር በራሱ ንጉስ ሲገዛ የነበረ የኦሮሞ ህዝብ መሆኑን አትርሳ። ያ ደሞ ከላይ የገለፅኩትን ነጥብ የሚያጠናክር ክስተት ነው። በነገራችን ላይ፣ ብዙ የወንድም ጉራጌ ጎሳዎች የሃበሾችን/የነፍጠኞችን ካምፖ እየጣሉ አጋርነታቸውን ለወንድም የኦሮሞና የሲዳማ ህዝቦች እየገለፁ የገኛሉ። ያንተ ጎሳ በቻ ነው የቀረው። :oops: :oops: - ለጊዜው!!። ይህ ክሊፕ የማረቆ-ጉራጌ ጎሳ አባላት ለጃዋርና ለኦፌኮ ፓርቲ አባላት ባህላዊ አልባሳት ሲሸልሙ ያሳያል። How are you feeling about it? .. Bit angry? Bit resigned to the fate that ethnic self-rule is the future & only saviour of emama Ethiopia?? Poor man .. feel a bit sorry for your predicament. :oops: Oh, well ...



VIDEO: <<Greatful to Maaraqoo ( corrected with apology). Community of Baatu town for gracing us with their traditional attire = Jawar>>
Please wait, video is loading...


Yabello,

You were quickly to judge H/selassie and Minilik, can you take responsibilities of the Pakistani Jimma Aba Jiffar who sold thousands of Oromos, Gurages, Kemabata to Arab countries? You evil, it is YOU Arab lovers trying to impose on the rest of Ethiopians not H/selassie or Minilik.

It is funny, the so called Horus, Tgaa are trying to discuss with the likes of Jawar, Yabello etc... Yabellos job here is trying to turn Ethiopia to Islamic nation no doubt about it that is why these people under the opportunity they have today the chaos is giving them ample opportunity like Aba Jiffar to sell off Ethiopia, that is why they need chaos and trying to bring back the era of Aba Jiffar. That is why i don't trust the likes of Aby, what is our proof this Aby guy is any different. Even if he is not, with what is going on with global situation, when he is made dictator, it is not just about selling of your resources but also selling Ethiopians off as it had already started during the era of Tplf they just call it today gong for labor.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ስርዓት ለሚቀጥሉት 6 አመታት የቀውስ ስርዓት ሆኖ ይቀጥላል

Post by Horus » 05 Feb 2020, 02:40

ተለል፣
ምንድን ነው ምታወራው? ቀድሞ ነገር አባ ጅፋር ኦሮሞ አይደለም ። ሁለተኛ ጉርጌና አባጅፋር የሚያገናኛቸውም ነገር የለም ። አባ ጅፋር ባሪያ ሲሸጥ ታላቁ ምኒሊክ ቁርጥ ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል ። ጉራጌ በማንም በባሪያነት ተሽጦ አያቅም ። የኦቶማን ቱርክ የሃረም ግሞች ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን ስለሚሰብስቡ ከብት የሚጠብቁ ቆንጆ ልጃገረዶች እያሰረቁ ካደሬም፣ ካማራም፣ ከጉራጌም ይሰርቁ ነበር እጅግ እጅግ ጥቂት ። ብዙ የወሰዱት አርመኖችን ነው ። ስለዚህ ስለማታቀው ነገር አትቀባጥር ። አባ ጂፋር ኦሮምኛ ተናጋሪ ባሪያ ነጋዴ ነው በቃ ! ሌላ ምን አረገ !! አትቀባጥር !!!

Post Reply