Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
AbebeB
Member+
Posts: 7694
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

@ESAT: ሀገረ-ሰብ (native) እና ሰፋሪ (settler) ልዩነት ለማታውቁና በደመ-ነፍስ ኦነግንና አብንን (ወይም ሌሎች የአማራ ፓርቲዎችን ከኦሮም ፓርቲዎች) ጋር ለማወዳደር ለምትጥሩ

Post by AbebeB » 12 Jan 2020, 20:37

ሀገረ-ሰብ (native) እና ሰፋሪ (settler) ልዩነት ለማታውቁና በደመ-ነፍስ ኦነግንና አብንን (ወይም ሌሎች የአማራ ፓርቲዎችን ከኦሮም ፓርቲዎች) ጋር ለማወዳደር ለምትጥሩ እነሆ!

በተለይ ፊንፍኔ ውስጥ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እኛ አዳራሽ አጣን (ለምሳሌ፡ አብን፣ ባልዲ ራስ ወዘተ) ግን ኦነግ አንደፈለገ ይሰጠዋል እያሉ የሚጮሁ በቀቀኖችን እሰማለሁ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ቪዲዮ ከታች ያያዝኩት ሞሮንና ሌሎችም (Ethio 360, ESAT etc) ይገኙበታል፡፡

ግን እኮ በቀቀኖቹ ያልገባቸው ኦነግ መስጠት ሲገባው እስከ ጊዜው ተቀባይ የሆነ የሀገሩ ባሌበት (native) ነው፡፡ ሌሎች ለምሳሌ አብን ወይም ባልዲ ራስ የሀገሩን (የፊንፊኔን) ሕግና ሥርዓት ጠብቀው አግልግሉት መጠየቅና ሲፈቀድላቸው የሚያገኙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ እንደ ኦሮሞ የፍንፊኔ መብት በአውስትራሊያ 1st nation ይባላሉ፡፡ በሌሎች ሀገሮችም ይህ አለ፡፡ ተገቢም ነው፡፡

ስለዚህ የሀገረ-ሰብ (native) መብትና ሰፋሪን (settler) መብት ለይቶ ማወቅ ከዚህ ሁሉ አላስፈላጊ ጩኸት ያድናችኃል፡፡




Post Reply