Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

የኮሎኔሉ 'ግልፅ ጦርነት!'

Post by Assegid S. » 12 Jan 2020, 22:16

https://www.eaglewingss.com/



የኮሎኔሉ 'ግልፅ ጦርነት!'

የሰው ልጣጭ ነው ያሉት አንድ እናት። ህፃኑ ተቀብሮ የእንግዴ ልጁ (ልጣጩ) ሲያድግ፤ የራስ-ቅል እንዲህ በአንጓል ሳይሆን በአንጀት ይሞላና፥ ሰው ለህሊናው ሳይሆን ለሆዱ ማደር ይጀምራል።

ትዝብቴን በአጭሩ ላስቀምጥ፦

ደቂቃ 0:03:40 – 0:03:55

ሲጀመር፦ ባልደራሱ በSaint Mary College የምርቃት በዓል ጩኽት ተረብሾ ስብሰባውን ማስተላለፍ፥ 'አልረበሽም ' ብሎ ካሰበም በተያዘለት ቀንና ሰዓት ዝግጅቱን መቀጠል በእርሱ (በባልደራሱ) ምቾትና ምርጫ ብቻ የሚወሰን ሆኖ ሳለ፥ 'አንረበሽም እንቀጥላለን' ብለው ሲወስኑ፥ የሆቴሉ መስተዳድር የፀጥታ ሀይል መጥራቱ የሴራውን ጫፍ እንደሚያስይዘን አይገባቸው ይሆን? ለነገሩ አንጀት ማላመጥ እንጂ እንደ አእምሮ ማሰብ የት ይሆንለታልና ይህን ያገናዝቡ?

ደቂቃ 0:07:00 – 0:07:40

ሲቀጥልም፦ ግለሰቡ Saint Mary ኮሌጅ የምረቃ ዝግጅቱን አስቀድሞ እንደያዘ ተናገሩ፥ ለወትሮውም የምረቃ ዝግጅት ሲኖር ..."እንደዚህ ሁኔታ ባለበት ጊዜ ሁልግዜ አንደኛውን አንይዝም ... ብዙ 'ግራጁዌሽኖችን' አድርገናል እኛ " ብለውም ተናዘዙ። ልብ አድርጉ ... 'ከዚህ በፊት ሁለቱንም ኣዳራሽ አናሲዝም፣ እንዲህ አይነት ትልቅ የድምፅ መሳሪያም አይተን አናውቅም ' ብለው ሲገዘቱ፤ ሁልጊዜ፦ ሁለቱንም አዳራሽ ላለማስያዝ ምክንያታቸው የድምፅ መሳሪያው መተለቅና ማነስ ሳይሆን፥ ፕሮግራሙ ’graduation’ መሆኑ ብቻ እንደሆነ በራሳቸው አንደበት እራሳቸው ላይ እየመሰከሩ ነው። ከሰውየው የደቂቃ ስብዕና ትንተና ተነስተን ልናምናቸው ብንቸገርም ... 'ይሁን' ብለን እናዳምጣቸውና ... .

ታዲያ የSaint Mary ኮሌጅ ዝግጅት 'የምረቃ በዓል' መሆኑ እየታወቀና፥ የትምህርት ተቋሙ ኣንደኛውን አዳራሽ ከባልደርሱ በፊት በፊት በፊት ቀድሞ እንዳስያዘ እየመሰከሩ፥ የምረቃ በዓሉ ሊከናወን ኣንድ ቀን ሲቀረው ሁለተኛውን አዳራሽ ለባልደራሱ ለማከራየት ለምን ወሰኑ? ይህም ሌላው የሴራውን ጅማት ጫፍ የሚያስጨብጠን ... ከቀጫጫ አእምሮ የሚወጣ ወፍራም ውሽት ነው።

ጎበዝ ... እኔ ግን ... የከተማው ከንቲባና ጠቅላይ ሚንስትሩ፥ ባልደራሱ የሚመሽግበትን የስብሰባ አዳራሽ ለማወቅ እስከ ምሽቱ ሦስት ሰዓት ድረስ ሲዳክሩ ማምሽታቸው አስገርሞኛል። በዚህና በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ሰፋ አድርጌ እስክመለስ፥ ለኣዲስ አበቤው ኣንድ ጥያቄ አለኝ፦ እስከ መቼ ድረስ ነው ለኮሎኔሉ 'ግልፅ ጦርነት ውስጥ እንገባለን ' ዛቻ አዲስ የምትሆነው? ይልቅ ... ከሰሞኑ እመለሳለሁ።

*video source: Fana Television