Jawar Mohammed
@Jawar_Mohammed
የሶሪያው ግልገል አምባገነን በሺር አል አሳድ ዛሬ ተገረሰሰ። ሥልጣን ከአባቱ በመውርሱ ሀገሪቷ የቤተሰብ ርስት ስለመሰለቸው፣ ፕሬዝደንትነቱን የሙጥኝ ብሎ ሶሪያን ወደ አስከፊ የእርስበርስ ጦርነት ከተታት። ለ13 ዓመታት የዘለቀው ጦርነትም ሶሪያን የተለያዩ የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች መፋለሚያ አውድማ በማድረግ አደቀቃት፣ ሕዝቦቿም በሺዎች ሞተው፣ በሚሊዮኖች ደግሞ ተሰደው አለም ላይ ተበተኑ።
በውጪ ኃይላት ድጋፍ ሥልጣኑን ተንጠልጥሎ ቢቆይም፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ነገሮች በቅጽበት ተቀያይረው አማጺያኑ ገስግሰው ደማስቆ ሲደርሱ “ሶሪያ ወይም ሞት” እያለ ሲፎክር የነበረው አሳድም እንደማንኛውም አምባገነን ፈረጠጠ።
ለመሆኑ ለዓመታት ተከፈፍለው እና ተዳክመው የነበሩት የሶሪያ አማጺያን እንዴት በዚህ ፍጥነት ሥርዓቱን ሊገረስሱ ቻሉ?
ለ13 ዓመታት የቆየው የእርስበርስ ጦርነት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ አላሸቀው፤ የመንግስት አስተዳደራዊ መዋቅርን አወላለቀው። ሠራዊቱ እና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች በውጪ መገዝገዝ እና ለውስጣዊ ክፍፍል በመዳረግ አቅማቸውን አሽመደመደው። አማጺያኑ የተከፋፈሉ ቢሆንም እንኳ፣ የተራዘመው የእርስበርስ ጦርነት የመንግስትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ የሥልጣን ምሰሶዎች ቀስ በቀስ በመገዝገዝ ሰባበራቸው። በሌላ አባባል አሳድ ፕሬዝደንትነቱን ተቆናጥጦ መቆየት ቢችልም፣ የሶሪያ ሀገረ-መንግስት አቅም ከቀን ወደ ቀን እየሞተ ነበር።
አሳድ ግን አማጺያኑ የተከፋፈሉ በመሆናቸው እና ከውጪ ኃይሎች በሚያገኘው ድጋፍ በመተማመን፣ የሥልጣን ምሰሶውን መሽመድመድ አልተገነዘበም ነበርና እውነታን ተቀብሎ አቅሙን መልሶ ለመገንባት ከመሞከር ይልቅ እየተኮፈሰ ቀጠለ። በቅርቡ ግን ነፍስ አባት ሆነው ያቆዩት ኃይሎች በራሳቸው ጦርነት ተጠምደው ድጋፋቸውን መቀነሳቸውን የተረዱት አማጺያን የተቀናጀ ዘመቻ ሲከፍቱበት፤ የተሽመደመዱት የሥልጣን ምሰሶዎች በቅፅበት ወዳደቁ። አሳድ ከተጠናወተው አምባገነናዊ መኮፈስ ሲነቃ፣ እግሩ የወላለቀ የሥልጣን ወንበር ላይ መቀመጡ ታየው። ምንም ማድረግ አልቻለም።
የሀገሪቷን የፖለቲካ ችግሮች በድርድር እና ውይይት ለመፍታት ሲቀርብለት የነበረውን ጥሪ ሁሉ በእብሪት እምቢ ብሎ፣ በሰላማዊ ሰልፍ መብቱን የጠየቀን ሕዝብ ላይ በጄት ቦምብ አዝንቦ፣ የእርስበርስ ጦርነትን አስነስቶ፣ ያቺን ስመጥር ታሪካዊ ሀገር በታትኖ በውርደት ፈረጠጠ። የሶሪያ ዜጎች በአሳድ መገርሰስ ቢደሰቱም፣ የፈራረሰችውን ሀገራቸውን መልሶ መገንባት ቀላል አይሆንላቸውም።
ሀገሮቻቸውን በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ዘፈቀው በውጪ ህይሎች ነብስ አባትነት ስልጣን ላይ ተንጣልጥለው ያሉ ሌሎች ግልገል አምባገነኖች ከአሳድ ተምረው ሳይዘገይ ይታረሙ ይሆን? አይመስለኝም። አምባገነኖችን ከሚያመሳስላቸው ባህሪያት ውስጥ ዋነኛው፣ አንዱ ከሌላው አለመማር ነውና!
https://x.com/Jawar_Mohammed/status/1865735080636739625
-
- Senior Member
- Posts: 10729
- Joined: 23 Feb 2013, 20:08
-
- Member
- Posts: 202
- Joined: 15 Jul 2023, 13:21
Re: ሀገሮቻቸውን በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ዘፈቀው በውጪ ሃይሎች ነብስ አባትነት ስልጣን ላይ ተንጣልጥለው ያሉ ግልገል አምባገነኖች ከአሳድ ተምረው ሳይዘገይ ይታረሙ ይሆን? ጃዋር
Ayatollah ወደ ፓለቲካው የመመለስ አሳብ አለው ልበል። እነዚህ አምባገነኖች አይማሩም ያላቸው ስም የላቸውም። ምነው አንድ ስም እንኳ ቢጠራ።
-
- Senior Member
- Posts: 10729
- Joined: 23 Feb 2013, 20:08
Re: ሀገሮቻቸውን በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ዘፈቀው በውጪ ሃይሎች ነብስ አባትነት ስልጣን ላይ ተንጣልጥለው ያሉ ግልገል አምባገነኖች ከአሳድ ተምረው ሳይዘገይ ይታረሙ ይሆን? ጃዋር
ግልገል አምባገነኖች gave it away. ስለ የአሕመድ ዓሊ ልጅ እያሰበ ነው።
-
- Senior Member
- Posts: 10729
- Joined: 23 Feb 2013, 20:08
Re: ሀገሮቻቸውን በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ዘፈቀው በውጪ ሃይሎች ነብስ አባትነት ስልጣን ላይ ተንጣልጥለው ያሉ ግልገል አምባገነኖች ከአሳድ ተምረው ሳይዘገይ ይታረሙ ይሆን? ጃዋር
"ግልገል አምባገነን" is a nickname given to Abiy by ሴኩቱሬ. Jawar needs to respect copy right.
-
- Senior Member
- Posts: 12718
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Re: ሀገሮቻቸውን በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ዘፈቀው በውጪ ሃይሎች ነብስ አባትነት ስልጣን ላይ ተንጣልጥለው ያሉ ግልገል አምባገነኖች ከአሳድ ተምረው ሳይዘገይ ይታረሙ ይሆን? ጃዋር
ጁሃር ስጋት የሆነበት የአብይ አህመድ ግልገል አምባገነንነት ሳይሆን፤ ፋኖ የአብይ ኦሮሙማ መንግስትን ይጥልብኛል ጭንቀት ነው። እውነቱ ግን የፈሩት ይደርሳል፤ የጠሉት ይወርሳል ነው። አዲስ አበባ እንደ ደማስቆስ በደስታ ሲቃ የምትጨፍርበት፤ የምድር ቤት እስር ቤቶች በር የሚከፈትበት ቀን አይቀሬ ነው። እንኳን እንድህ እንደ ኦሮሙማ ተጨመላልቆ ሽቅብ ቀዝኖ አይደለም ተግቶ እና ሰርቶ ማስተዳደር እንኳን ብዙ ሳካ የገጥመዋል።
ጁሃር የተጠቀመው "ግልገል አምባገነን" እጅግ ደካማ እና የተለሳለሰ ቃል ነው። የኦሮሙማ ስርዐት እንሰሳዊ ደመ-ነፍስ ሳይሰራ ያየውን ሁሉ የእኔ ነው የሚል፤ አራዊት ነው። የአራዊት ስብስብ ውስጥ አምባገነን የሚባል ነገር የለም። መንጋ ነው የሚባለው።
ጁሃር የተጠቀመው "ግልገል አምባገነን" እጅግ ደካማ እና የተለሳለሰ ቃል ነው። የኦሮሙማ ስርዐት እንሰሳዊ ደመ-ነፍስ ሳይሰራ ያየውን ሁሉ የእኔ ነው የሚል፤ አራዊት ነው። የአራዊት ስብስብ ውስጥ አምባገነን የሚባል ነገር የለም። መንጋ ነው የሚባለው።