ኢሰመኮ - “በኦሮሚያ ክልል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተመለመሉ ነው!”
Posted: 06 Dec 2024, 07:42
በኦሮሚያ ክልል፣ ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጪ ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተያዙ መኾናቸውን እና የተያዙትን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ መገደዳቸውን፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ሐሙስ፣ ኅዳር 26፣ 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ከኅዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ እና ሻሸመኔ ከተሞች እንዳካሄደ በገለጸው ክትትል እና ምርመራ፣ "የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ" በሚል ሕፃናትንና የአእምሮ ህሙማንን ጨምሮ የክልሉ ነዋሪዎች በግዳጅ መያዛቸውን አመልክቷል።
ኮሚሽኑ በሻሸመኔ ባካሄደው ክትትል እና ምርመራ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መኾናቸውን የገለጹ ሕፃናት፣ ወደ ወታደራዊ ሥልጠና ለሚገቡ ሰዎች በተዘጋጁ የማቆያ አዳራሾች ውስጥ ማግኘቱን ገልጾ፣ በተለይም ሁሩፋ ክፍለ ከተማ፣ ሀሌሉ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ የማቆያ አዳራሽ ውስሽ ውስጥ ካነጋገራቸው 32 ሰዎች መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 ዓመት መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም አንድ የ11 ዓመት ሕፃን ማግኘቱንም አስታውቋል።
ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ ተመልምለው የተያዙ ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከ20 እስከ 100 ሺሕ ብር እንዲከፍሉ እንደሚገደዱ ማረጋገጡን ያመለከተው የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ፣ ቤተሰቦቻቸው የተጠየቁትን ገንዘብ ካልከፈሉ ልጆቻቸው 'ለወታደራዊ ሥልጠና' እንደሚላኩ እንደሚነገራቸውም አብራርቷል።
ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ስመኝሽ የቆየ የኮሚሽኑን ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ወይዘሮ ራኬብ መሰለን አነጋግራለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
https://amharic.voanews.com/amp/ehrc-or ... 88747.html