በኦሮሚያ ክልል፣ ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጪ ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተያዙ መኾናቸውን እና የተያዙትን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ መገደዳቸውን፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ሐሙስ፣ ኅዳር 26፣ 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ከኅዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ እና ሻሸመኔ ከተሞች እንዳካሄደ በገለጸው ክትትል እና ምርመራ፣ "የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ" በሚል ሕፃናትንና የአእምሮ ህሙማንን ጨምሮ የክልሉ ነዋሪዎች በግዳጅ መያዛቸውን አመልክቷል።
ኮሚሽኑ በሻሸመኔ ባካሄደው ክትትል እና ምርመራ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መኾናቸውን የገለጹ ሕፃናት፣ ወደ ወታደራዊ ሥልጠና ለሚገቡ ሰዎች በተዘጋጁ የማቆያ አዳራሾች ውስጥ ማግኘቱን ገልጾ፣ በተለይም ሁሩፋ ክፍለ ከተማ፣ ሀሌሉ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ የማቆያ አዳራሽ ውስሽ ውስጥ ካነጋገራቸው 32 ሰዎች መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 ዓመት መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም አንድ የ11 ዓመት ሕፃን ማግኘቱንም አስታውቋል።
ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ ተመልምለው የተያዙ ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከ20 እስከ 100 ሺሕ ብር እንዲከፍሉ እንደሚገደዱ ማረጋገጡን ያመለከተው የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ፣ ቤተሰቦቻቸው የተጠየቁትን ገንዘብ ካልከፈሉ ልጆቻቸው 'ለወታደራዊ ሥልጠና' እንደሚላኩ እንደሚነገራቸውም አብራርቷል።
ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ስመኝሽ የቆየ የኮሚሽኑን ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ወይዘሮ ራኬብ መሰለን አነጋግራለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
https://amharic.voanews.com/amp/ehrc-or ... 88747.html
-
- Senior Member
- Posts: 13983
- Joined: 04 Aug 2018, 13:15
-
- Senior Member
- Posts: 13983
- Joined: 04 Aug 2018, 13:15
Re: ኢሰመኮ - “በኦሮሚያ ክልል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተመለመሉ ነው!”
በኦሮሚያ ክልል ሕጻናትን ጨምሮ በርካቶች “ለመከላከያ ምልመላ” በሚል በግዳጅ መያዛቸው ተገለጸ
የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር አካላት እና የፀጥታ ኃይሎች ሕጻናት እና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ በርካቶችን የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ በሚል በግዳጅ እንደያዙ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ አደረገ።
ከመከላከያ ሚኒስቴር የምልመላ መስፈርት ውጪ በግዳጅ የተያዙ ሕጻናትን እና ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ ጭምር እንዲከፍሉ እነዚሁ ባለሥልጣናት ማስገደዳቸውን ኢሰመኮ ባደረገው ምርመራ እንደደረሰበት ሐሙስ፣ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።
ኢሰመኮ ክትትል እንዳደረገባቸው ከጠቀሳቸው ስፍራዎች አንዷ በሆነችው ሻሸመኔ ዕድሜያቸው ከ18 በታች መሆናቸውን የተናገሩ ታዳጊዎች “ወታደራዊ ሥልጠና ትገባላችሁ” በሚል ማቆያ አዳራሾች መግባታቸውን አረጋግጧል።
በሻሸመኔ ከተማ ሃሌሉ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ማቆያ አዳራሽ ከነበሩ 32 ሰዎች መካከል 14 ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 አንደኛው ደግሞ 11 ዓመት መሆኑን ኢሰመኮ ባናገራቸው ወቅት መግለጻቸው ተጠቅሷል።
ከትምህርት ቤት ሲወጡ ከነዩኒፎርማቸው እዚሁ ማቆያ አዳራሽ እንዲገቡ የተደረጉ ሁለት የ15 ዓመት የ5ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁለት ሳምንት እንዳስቆጠሩ ገልጸዋል።
በዚሁ ማዕከል ውስጥ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ 13 ሰዎች ያለፈቃዳቸው በፖሊስ እና በሚሊሻ አባላት ተይዘው እንደገቡ፣ በማቆያው ከሳምንት በላይ እንደቆዩ እና መውጣት አልቻልንም ማለታቸው ሰፍሯል።
ለልጁ እራት ለመግዛት ሲወጣ በሚሊሻዎች ተይዞ የተወሰደ ግለሰብን ጨምሮ ከሥራ ሲመለሱ የተያዙ ሰዎች እና በተለያዩ ማቆያዎች እንዲገቡ የተደረጉ ምስክርነታቸውን ለኢሰመኮ ሰጥተዋል።
አንዳንድ የክልሉ የሚሊሻ አባላት ወጣቶችን ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት ምልመላ በሚል ከያዙ በኋላ ለመልቀቅ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ መሆኑን ኢሰመኮ አረጋግጫለሁ ብሏል።
ገንዘብ የማስከፈል ድርጊቱ በተለይ በአዳማ እና በአካባቢው በተስፋፋ ሁኔታ ሲፈጸም እንደነበር ተቋሙ መረዳቱን አትቷል።
በአዳማ ከተማ አንጋቱ ወረዳ በእህል መጋዘን ውስጥ በሚሊሻዎች ተይዘው ከነበሩ አብዛኞቹ ከ20 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቤተሰቦቻቸው እንዲከፍሉ መጠያቃቸውን የ15 ዓመት ሕጻን የተያዘባቸው እናት ለኢሰመኮ ገልጸዋል።
“ሕጻናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የክልሉ መንግሥት የአስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል” ሲል ኢሰመኮ በዛሬው ሪፖርቱ አጽንኦት ሰጥቷል።
ኢሰመኮ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ለመከላከያ ሠራዊት ምልመላ እናካሂዳለን በሚል ሕጻናትን ጨምሮ ሰዎችን በግዳጅ እንደያዙ እንዲሁም የተያዙትን ለመልቀቅ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስገደዳቸውን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ወደ ምርመራ ገብቻለሁ ብሏል።
ተቋሙ ከኅዳር 4 እስከ ኅዳር 20/2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ ምልምል የመከላከያ ሠራዊት አባላት ማቆያዎችን መጎብኘቱን አመላክቷል።
በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን፣ ቤተሰቦችን እንዲሁም የሚሊሻ እና የፖሊስ ተቋማትን ጨምሮ ከክልል እስከ ቀበሌ መዋቅር ያሉ የመንግሥት ኃላፊዎችን በማወያየት ሪፖርቱን ማጠናቀሩ ተገልጿል።
የክልሉ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ እንዲሁም በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ችግሩን ማመናቸውን ኢሰመኮ ያናገራቸው ባለሥልጣናትን ዋቢ አድርጎ በሪፖርቱ አካቷል።
እነዚህ ባለሥልጣናት የማቆያ ስፍራዎችን በመፈተሽ የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን እና ድርጊቱን በፈጸሙ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የሚሊሻ አባላት ላይ እርምጃ እንወስዳለን ማለታቸው ተጠቅሷል።
ኢሰመኮ ክትትል ባደረገባቸው አንዳንድ አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ በሚል ተይዘው የነበሩ ሕጻናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ በግዳጅ የተያዙ በርካቶችን ከክልሉ አመራሮች ጋር በመሆን ለማስለቀቅ መቻሉም በዚሁ ሪፖርት ሰፍሯል።
በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች ከመንግሥት አመራሮች ጋር በተደረጉ ውይይቶች ከሕግ እና ከሠራዊቱ መስፈርቶች ውጪ የተያዙ 8 ሕፃናት እና 1 የአእምሮ ህመምተኛን ጨምሮ ከ36 በላይ ሰዎች እንዲለቀቁ ለማድረግ መቻሉን ኢሰመኮ በሪፖርቱ ጠቅሷል።
በአንዳንድ አካቢዎች የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ከመስፈርት ውጪ የተደረገ ምልመላ መሆኑን በመግለጽ በክልሉ የፀጥታ አካላት የተያዙ ሰዎች ከማቆያ ስፍራዎች እንዲለቀቁ ያደረጉ መሆኑን መገነዘቡን ኢሰመኮ አመልክቷል።
ኢሰመኮ “የመከላከያ ሠራዊት አባላት ምልመላ” በሚል ሕፃናትን ጨምሮ በግዳጅ የተያዙ ሰዎችን የመከላከያ ሠራዊት በምልምል ወታደርነት ያለመቀበሉን ካሰባሰባቸው መረጃዎች ማግኘቱን ገልጿል።
እነዚህ ሕጻናት በዋናነት በግዳጅ ምልመላ (conscription) ሳይሆን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 17 መሠረት በነጻነት መብት ማዕቀፍ እንዲሁም የሕገወጥ እና የዘፈቀደ እስራት ክልከላን በሚመለከቱ ድንጋጌዎች መሠረት እንደሚታይ ጠቅሷል።
ሆኖም “እነዚህ ተግባራት በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች እና በሕገ መንግሥቱ ጥበቃ የተደረገለትን የነጻነት መብት የሚጥሱ የሕገወጥ እና የዘፈቀደ እስራት ናቸው” ብሏል።
“በኦሮሚያ ክልልም ሆነ በሌሎች ክልሎች የሚካሔዱ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ምልመላ ሠራዊቱ ባስቀመጠው አሠራር እና መስፈርት መሠረት በፈቃደኛነት ላይ ብቻ ተመሥርተው መከናወናቸውን ሊያረጋገጥ ይገባል” ሲሉ የኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ መናገራቸው በሪፖርቱ ተካቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0mvzl0jy1xo.amp

- Posts: 12718
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Re: ኢሰመኮ - “በኦሮሚያ ክልል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተመለመሉ ነው!”
አዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ ህንጻ እና ቤት ለእናንተ ተሰርቶላችኋል ሂዳችሁ ትሰጣላችሁ ተብለው ይሆናል። እንደ ልጅ በከረሜላ በማታለል ይባላል እኮ።ስንዴ በልተው ጠግበው ጨርሰዋል አሁን ባለቀለም ግንብ እና ጨረቃ የመሰለ መንገድ መንፈላሰስ ነው የሚፈልጉት።