Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Misraq
Senior Member
Posts: 14189
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

በኦሮምያ ክልል ጠቅላላ ወታደራዊ ምልመላ ትእዛዝ ወጣ - እነ ጥላሁን union ደንግጠዋል

Post by Misraq » 05 Dec 2024, 15:32

.
.
.
ጥሌ እና የቱለማው ሃይል ተሸብሮአል፥፤ ወታደሮቹ አልቀውና ተማርከው የፋኖን ጡንቻ አዳብረዋል፥፥ በዚህ የተደናገጠው የቱለማ ሃይል በስነልቦናም በመከፋፈልም በውትድርናም ክተት ጠርቶ ወደ ስራ ገብቶአል፥፥ ጥላሁን unionም ከርክሩን እያከመ በሳይበር አማራን የሚከፋፍል አጀንዳ እንዲያራግብ የስራ ግዳጅ ተሰጥቶታል



Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4249
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: በኦሮምያ ክልል ጠቅላላ ወታደራዊ ምልመላ ትእዛዝ ወጣ - እነ ጥላሁን union ደንግጠዋል

Post by Za-Ilmaknun » 05 Dec 2024, 15:41

በኦሮሚያ ክልል ሕጻናትን ጨምሮ በርካቶች “ለመከላከያ ምልመላ” በሚል በግዳጅ መያዛቸው ተገለጸ

የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር አካላት እና የፀጥታ ኃይሎች ሕጻናት እና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ በርካቶችን የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ በሚል በግዳጅ እንደያዙ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ አደረገ።

ከመከላከያ ሚኒስቴር የምልመላ መስፈርት ውጪ በግዳጅ የተያዙ ሕጻናትን እና ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ ጭምር እንዲከፍሉ እነዚሁ ባለሥልጣናት ማስገደዳቸውን ኢሰመኮ ባደረገው ምርመራ እንደደረሰበት ሐሙስ፣ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።

ኢሰመኮ ክትትል እንዳደረገባቸው ከጠቀሳቸው ስፍራዎች አንዷ በሆነችው ሻሸመኔ ዕድሜያቸው ከ18 በታች መሆናቸውን የተናገሩ ታዳጊዎች “ወታደራዊ ሥልጠና ትገባላችሁ” በሚል ማቆያ አዳራሾች መግባታቸውን አረጋግጧል።

በሻሸመኔ ከተማ ሃሌሉ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ማቆያ አዳራሽ ከነበሩ 32 ሰዎች መካከል 14 ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 አንደኛው ደግሞ 11 ዓመት መሆኑን ኢሰመኮ ባናገራቸው ወቅት መግለጻቸው ተጠቅሷል።

ከትምህርት ቤት ሲወጡ ከነዩኒፎርማቸው እዚሁ ማቆያ አዳራሽ እንዲገቡ የተደረጉ ሁለት የ15 ዓመት የ5ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁለት ሳምንት እንዳስቆጠሩ ገልጸዋል።

በዚሁ ማዕከል ውስጥ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ 13 ሰዎች ያለፈቃዳቸው በፖሊስ እና በሚሊሻ አባላት ተይዘው እንደገቡ፣ በማቆያው ከሳምንት በላይ እንደቆዩ እና መውጣት አልቻልንም ማለታቸው ሰፍሯል።

ለልጁ እራት ለመግዛት ሲወጣ በሚሊሻዎች ተይዞ የተወሰደ ግለሰብን ጨምሮ ከሥራ ሲመለሱ የተያዙ ሰዎች እና በተለያዩ ማቆያዎች እንዲገቡ የተደረጉ ምስክርነታቸውን ለኢሰመኮ ሰጥተዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c0mvzl0jy1xo

Odie
Member
Posts: 2231
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: በኦሮምያ ክልል ጠቅላላ ወታደራዊ ምልመላ ትእዛዝ ወጣ - እነ ጥላሁን union ደንግጠዋል

Post by Odie » 05 Dec 2024, 15:46

የአምሮ ዝግምት ያለበት ሁሉ ሳይቀር አፈሳ ተጧጥፏል!
ጁሊያና መሲሁ እጭቤ ቀዝነዋል ማለት ነው!

Misraq
Senior Member
Posts: 14189
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: በኦሮምያ ክልል ጠቅላላ ወታደራዊ ምልመላ ትእዛዝ ወጣ - እነ ጥላሁን union ደንግጠዋል

Post by Misraq » 05 Dec 2024, 16:48

Odie wrote:
05 Dec 2024, 15:46
የአምሮ ዝግምት ያለበት ሁሉ ሳይቀር አፈሳ ተጧጥፏል!
ጁሊያና መሲሁ እጭቤ ቀዝነዋል ማለት ነው!
ከበ 2 ሳምንት አማራን ትጥቅ እናስፈታለን ወደ አንድ ሺህ አመት ብትዋጉ አታሸንፉንም የወረደው የጁልያና እና የኮን አርቲስቱ የአብይ ዲስኩር ፍርሃቱን እና በለስ እየቀናው እንዳልሆነ ማሳያው ነበር፥፥ ይባስ ብሎ እብዶችን ሳይቀር ወደ ውትድርና አፈሳ መግባቱ ስልጣኑ እየተነቀነቀና እየተሰነጣጠቀ መሆኑ ሌላው ማሳያ ነው::

እየቀለበና ጸጉራቸውን እያሰራ ሲመግባቸው የነበሩትን ሸኔዎቹን ወደ መዲናዋ ማስገባቱም እንዲጠብቁት እንጂ ለሌላ ለምንም አይደለም

q

Odie
Member
Posts: 2231
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: በኦሮምያ ክልል ጠቅላላ ወታደራዊ ምልመላ ትእዛዝ ወጣ - እነ ጥላሁን union ደንግጠዋል

Post by Odie » 05 Dec 2024, 20:27

Misraq wrote:
05 Dec 2024, 16:48
Odie wrote:
05 Dec 2024, 15:46
የአምሮ ዝግምት ያለበት ሁሉ ሳይቀር አፈሳ ተጧጥፏል!
ጁሊያና መሲሁ እጭቤ ቀዝነዋል ማለት ነው!
ከበ 2 ሳምንት አማራን ትጥቅ እናስፈታለን ወደ አንድ ሺህ አመት ብትዋጉ አታሸንፉንም የወረደው የጁልያና እና የኮን አርቲስቱ የአብይ ዲስኩር ፍርሃቱን እና በለስ እየቀናው እንዳልሆነ ማሳያው ነበር፥፥ ይባስ ብሎ እብዶችን ሳይቀር ወደ ውትድርና አፈሳ መግባቱ ስልጣኑ እየተነቀነቀና እየተሰነጣጠቀ መሆኑ ሌላው ማሳያ ነው::

እየቀለበና ጸጉራቸውን እያሰራ ሲመግባቸው የነበሩትን ሸኔዎቹን ወደ መዲናዋ ማስገባቱም እንዲጠብቁት እንጂ ለሌላ ለምንም አይደለም

q
"ባይቀይ መውት ኮራኮራት" ይላል ጉራጌ

ባማርኛው: "ላይቀር መሞት ማጣጣር" ማለት ነው!
ኮራኮራት ማለት ይሄ ሊሞት ያለ ስው የሚያስማው የጣር ድምፅ ነው!

ብልፅግና/ኦፒዲኦ ማጣጣር ላይ ነች መሞቷ ላይቀር :lol: :lol:

Post Reply