የፀሃይቱ ነገር!
ይቺ ደግሞ የይልማ መርዳሳ ኮሪደር ነች!
ጸሃዪቱ የተገነባችው አውሮፕላን ብለው ልማታዊ ትንቢታዊ ብልፅግናዊ የኮሪደር ካድሬዎች ለጥፈዋታል!
ጥሩ ሙከራ ነው ግን ለጉራ አትመችም
ጢያራ ኢትዮዽያ ውስጥ ሲሰራ የመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዴ?
ገፅ ግንባታ
ህዝቡ የራበው መች ጢያራ ሆነ!
ማቴዎስ 12:25፤ “ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።”
የብልፅግና ስርአት ማለት ይሄ ነው:: በሃገር ውስጥ ሃገር በመንግስት ውስጥ መንግስት ያለበት ሁኔታ ነው ያለው:: በስላም ወጥቶ መመለስ እንደ ድንቅ የሚቆጠርበት ዘመን:: ኑሮ እንደድንጋይ የከበደበት ሁሉም የመስለውን የሚያደርግበትና ህጋዊ ከለላ ያለው ዝርፍያ የሚካሄድበት ደም የሚፈስበት ዘመን ነው:: ብልጭልጭታውና የካድሬ media ጦርነቱ ቀጥሏል:: ጦፏል:: አወቅን የሚሉ አናማዎች ነን የሚሉ ሳይቀሩ አይናቸው ግንባር ሆኖ 24/7 ይዋሹናል:: ህዝብ ያልደገፈው ከፋፋይና አንካሳ ስርአት የትም አይደርስም:: አዳልጦት ይንከረባበታል እንጂ!
ሪፎርም አሉ? ገና ራሳቸው ሳይታደሱ ሻወር ሳይወስዱ ንስሃ ገብተው በኢትዮዽያዊነት ሳይጠመቁ? እራስን ማታለል ማለት ይሄ ነው::
የተከፋፈለች መንግስት አትፀናም! የህዝብ ጥያቄ ሳይመለስ አገር ወደአንድነት ሳይመጣ የፖልቲካ አመራርና ስርአት ሳይለወጥ ሳይሻሻል የወያኔን የስልጣን በትር ተይዞ ባረጀ አቁማዳ ውስጥ ያረጀ ወይን ይዞ የትም አይዘለቅም! ዝም ብሎ እንደሽሮ መንተክተክ የህዝብ መከራ ማብዛት ነው!!
https://m.youtube.com/shorts/SpJjHdGZtig