Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Educator
Member
Posts: 2339
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

ዕድገት ከመሰለህ

Post by Educator » 01 Oct 2024, 20:28

ዕድገት ከመሰለህ፦

ሀገር ጫፍ እስክ ጫፍ ተጠብሳ በማዳት፣
አራት ኪሎ አጠገብ ብሽክሊሊት መንዳት፣

ዕድገት ከመሰለህ፦

መሰረትህ ፈርሶ ወደ ሽቅብ መዝለል፣
ሰው እያፈረሱ ድንጋይን መቆለል፣

ዕድገት ከመሰለህ፦

ቤትን አጨልሞ አደባባይ ማፍካት፣
ሞሰበ ሲሚንቶን በለሚ መተካት.....
ከሁለቱ በአንዱ ዕይታህ ተምታቷል፦
ወይ ቡለንህ ላልቷል ፤ወይም ሆድህ ሰፍቷል። (ደረጀ ሀ.)

Educator
Member
Posts: 2339
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: ዕድገት ከመሰለህ

Post by Educator » 01 Oct 2024, 20:37

እቤት ውስጥ መብራት ስለማይኖር ጎዳናዎች ላይ ሲዟዟር አምሽቶ ወደ ቤት የሚገባው ወጣት ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በአራት እጥፍ ማደጉን የብልጽግና ጽህፈት ቤት ያስጠናው አንድ ጥናት አመልክቷል።
" ፍላጎቱን በአግባቡ በማጤንና አደባባዮችን በመብራት በማብለጭለጭ ልዩ ደስታን ስለሰጠነው፤ አብዛኛው የመዲናዋ ወጣት በቤቱ ውስጥ መብራት ባይኖረውም በሚታዬው ፈጣን ዕድገት ደስተኛ መኾኑን ገልጿል" ይላል- ጥናቱ።

Educator
Member
Posts: 2339
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: ዕድገት ከመሰለህ

Post by Educator » 02 Oct 2024, 14:38

ከአብይ አህመድ በላይ በልጽጎና ተደምሮ ወገኑን ሲያሳድድ እና ሲያስገድል የነበረ በሆዱ የወደቀ የብአዴን ሹም ሁሉ፤ እነሆ የመጨረሻው ሰዓት ሲደርስ ፤ጭራውን እየቆላ ባጨበጨበለት ብልጽግና እየታደነ ነው።The Revolution devours its children.
የቀራችሁት ከዚህ እንኳ ትማሩ ይሆን?

Post Reply