Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Naga Tuma
Member+
Posts: 5929
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የቁንዲዶ ተራራ የዱር ፈረሶች!! አስገራሚ ነገር !!!

Post by Naga Tuma » 18 Sep 2024, 17:02

ይህ ለምርምር እጅግ ኣስደናቂ ነዉ።

በኢትዮጵያ ህዳሴ እና ግስጋሴ ዘመን ከዚህ በፊት በጥልቅ ያልተስተዋሉ ተቆጥረዉ የምያልቁ ኣይመስለኝም።

ዕፅ እና እንስሳ ማላመድ የተጀመረዉ የዛሬ አስር ሺህ ዓመታት ገደማ ነዉ ተብሏል።

የዱር ቆቅን የቤት ዶሮ ኣድርጎ ማላመድ፣ የዱር ቀበሮን የቤት ዉሻ ኣድርጎ ማላመድ፣ የዱር አነርን የቤት ድመት ኣድርጎ ማላመድ፣ የዱር ፈረስን የቤት ኣድርጎ ማላመድ ቀላል እንዳልነበሩ እገምታለሁ።

እነዚህ ፈረሶች ከጥንት ጀምሮ የዱር የነበሩ ይሁን ለማዳ የነበሩት ወደ ዱር ተመልሰዉ ይሁን ማወቅ ቁልፍ ምርምር ነዉ የሚሆነዉ።

ዜናዉን ሰምቼ ከፈረሶቹ ባህርይ የገመትኩኝ የፈረሶቹ ስጋት ሰዉ ለማላመድ ያደረገዉ ትግል እና ፈረሶች በሰዉ ቁጥጥር ስር ላለመግባት ያደረጉት ትግል ትዉስታ የምያመለክት ይመስላል። ገርሞኝ ሐረርጌ ዉስጥ ፈረሶችም ሃት ኬኘ ቶኮ፣ ነመቱ አዳን ኑ ባሴ ይላሉ እንዴ ኣልኩኝ።

ከዓመታት በፊት ኣንድ የሐረርጌ ሰዉ ቢጠና ሐረርጌ ዉስጥ ብዙ የጥንት ነገሮች ኣሉ ብሎኝ ነበር።

በአከባቢ ያሉ ቃሉዎች ካሉ በባህል ሲዋረድ ከመጣ አፈታሪክ ዉስጥ ስለ እንስሳ ማላመድ የሚሉት ካለ ሰምቶ ማበጠር ይቻል ይሆናል።

እንስሳ ትዉስታ ወይም ሜሞሪ እንዳለዉ እና ከትዉልዱ ወደሚቀጥለዉ ትዉልድ ማስተላለፍ የሚችል መሆኑ በሳይንስ ተረጋግጦ ይሁን ኣይሁን ኣሁን ኣላስታዉስም።

በጣም ማሰብ እንደሚችል ኣንድ ግዜ ከዝንጀሮ ባህርይ ኣይቻለሁ። ኣንድ ዝንጀሮ ከጫካ ወጥቶ ማሳ ሲገበ ሰዉ ኣይቶ ቤት ገብቶ ጠመንጃ ይዞ ወጥቶ ከርቀት ደገነበት። ዝንጀሮዉ በቅጽበት ነበር ከርቀት ያያዉ። ወድያዉ በፍጥነት ወደ ቀኙ፣ ወደ ግራዉ ተሯሯጠ። የደገነበት እንደደገነበት ቆሞ ኣያዉ። ወደ ጎኖቹ በጣም ከተሯሯጠ በኋላ እግሮቼ ኣዉጪኝ ብሎ ወደ ጫካ በጣም ሮጠ። የነፍስ ነገር ዝንጀሮንም እንደዛ ኣደረገ።

የደገነበትን ለምን ኣልቶከስክበትም ብለዉ ፈገግ ብሎ ማባረር ነዉ የፈለኩኝ ኣለ።

እስከዛሬ ድረስ የሚገርመኝ ዝንጀሮዉ ከርቀት ሆኖ እንዴት በቅጽበት ጠመንጃዉ ዱላ እንዳልሆነ እንደለየ ነዉ።

ምናልባትም ከዛ በፊት ሌላ ዝንጀሮ ተተኩሶበት ኣይቶ ኣልረሳዉም ይሆናል።

ልጅ ሆኜ ያየሁኝ ከጥይት ለማምለጥ ቀጥታ ሳይሆን ዘወርዋራ መሮጥን ጎልማሳ ሆኜ ወታደራዊ ስልጠና ዉስጥ እንዳለ ሰምቻለሁ።

እነዚህ የዱር ፈረሶችም የሰዉ ለማላመድ ጥቃት ትዉስታ ያላቸዉ ከሆነ ይህ አለም አቀፋዊ ምርምር ይሆናል።

ከዓመታት በፊት ሁለት የማዉቃቸዉን ቃላት የጀርመን ቋንቋ ዉስጥ እንዳሉ ኣነበብኩኝ፥ ደንፋ እና ፈርደ። በተለምዶ ደንፋ በአከባቢዉ ስሙ የተፈራ ቃሉ ነበር። ፈርደ ፈረስ ማለት ነዉ።

የቃላቱ ግጥምጥሞሽ ገርሞኝ ዝም ብያለሁ።

በቅርቡ ኣንድ የኢራን ሰዉ በኣጋጣሚ ተገናኝቼ ከየት ነህ፣ ከየት ነህ ስንባባል እሱ ከኢራን መሆኑን እና የሃገሩ ሲም ፋርሲ ይባል ነበር ኣለኝ። ለምን ወደ ኢራን ተቀየረ ብለዉ የኣርያን ሃገር ለማለት ነዉ ኣለኝ።

ገርሞኝ ክህትለር ጋር ምን ኣገናኛች ሁ ኣልኩት፧

ድሮ ሰዎች ከኣፍርካ ወጥተዉ፣ የተወሰኑት ኢረን ሰፈሩ፣ የተወሰኑት ወደ ጀርመን ሄዱ፣ የተወሰኑት ወደ ህንድ ሄዱ ይባላል ኣለኝ። ጨምሮም የሁለተኛዉ አለም ጦርነት ግዜ ኢራን ከጀርመን ጋር ተባባሪ ነበረች ኣለኝ። ኣላዉቅም ነበር።

የነገረኝ ታሪክ ያለዉ ስለ ደንፋ እና ፈርደ ኣስታወሰኝ።

ይህን ምርምር የጀመረዉ ተመራማሪ ዶክተር ከፈና እፋ ለጥናቱ የሚሆን ጃክፖት ላይ ነዉ። ምናልባትም በፍጥረት በር እንኳን ኢትዮጵያዊ፣ ጀርመናዊዉ ደንፋ እያለ ፈርደ ላይ ቁጭ ብሎ ቢመለስ ሌላ ታሪክ ነዉ የሚል ድምዳሜ ላይ ይደርስ ይሆናል።

Fiyameta
Senior Member
Posts: 15470
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የቁንዲዶ ተራራ የዱር ፈረሶች!! አስገራሚ ነገር !!!

Post by Fiyameta » 18 Sep 2024, 19:00

It was the Oromo native of Eritrean origin and a prolific author Tesfaye Gada Gebreab (Rest in Peace) who first discovered the wild horses that live on top of the mountain, and he told their story in his book using it as a very powerful metaphor for lives spent in forced solitude appear to enjoy absolute freedom and the free will to do what is right for themselves without being indentured to others. Once people enjoy the taste of freedom, there is no turning back. The horses become "ተዋጊ" only when their freedom is threatened, otherwise they are very peaceful animals.

Dama
Member
Posts: 2983
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: የቁንዲዶ ተራራ የዱር ፈረሶች!! አስገራሚ ነገር !!!

Post by Dama » 18 Sep 2024, 19:12

Horus wrote:
16 Sep 2024, 22:10
I am Z Sodo
Donkey Horus: Hobyo! Hobyo! Hobyo!



I am Z Sodo
Donkey Horus: Hobyo! Hobyo! Hobyo!



I am Z Sodo
Donkey Horus: Hobyo! Hobyo! Hobyo!


Post Reply