Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5592
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

በኢትዮጵያ ታሪክ ቀጣይ መሪ ቀዳሚ መሪን ኣለማክበር የተጀመረዉ መቼ ነዉ?

Post by Naga Tuma » 10 May 2024, 14:33

እኔ የፖለትካ ሳይንስ ትምህርት ዬለኝም።

ጽንሰ ሀሳብን ማሰላሰል እወዳለሁ።

ሃገር ሉዓላዊ ናት ማለት ከባድ ጽንሰ ሀሳብ ኣይመስለኝም። ሉዓላዊ ሃገር ለሁሉም ዜጎችዋ ከለላ ናት።

በቅርቡ በፊት ሉዓላዊ ማለት ያልቻሉት ሉዓላዊ ማለት ጀመሩ የሚል ርዕስ ኣንብቤ ነበር።

ሁሉም ዜጎች ሉዓላዊ ማለት ከቻሉ፣ በሉዓላዊ ስር እኩላዊ እና “ሎካላዊ” ማለት ከቻሉ፣ ምን የቀረ የፖለትካ ጽንሰ ሀሳብ ይኖራል ብዬ እራሴን ጠየኩኝ። ሎካላዊ ብዙዎች ወደ አዲስ አበባ ከመብረር የራሳቸዉን አዲስ አበባ መፍጠር ይሆናል።

ሁሉም ዜጎች በሉዓላዊነት ከተስማሙ በሃገር ቀጣይነት ይስማማሉ ማለት ነዉ።

ለዚህ ነዉ ዜጋ ሉዓላዊነትን መዳፈር ማለት ሃይማኖተኛ ብላስፈሚ መፈጸም ዐይነት የሚሆነዉ።

ሉዓላዊነት እና የሉዓላዊነት ቀጣይነት ከታወቀ ቀጣይ የሃገር መሪ ቀዳሚ የሃገር መሪን ተገቢዉን ስፍራ ይሰጠዋል ማለት ነዉ።

የኢትዮጵያን የቅርብ ግዜ የፖለትካ ችግር ይህ መቼ እንደተናጋ ማወቅ ግልጽ ኣያደርገዉም?

በኣመዣኙ ይህ መናጋት ከዉጪ በመጣ ተጽዕኖ ነዉ ወይስ ከዉስጥ በተነሳ ቅስቀሳ?