በአማራ ክልል ራያ አላማጣ ዛታ እና ኦፍላን ጨምሮ አወዛጋቢ አካባቢዎች ባሉ አማራ ማኅበረሰብ ላይ እየደሰ ያለው ግፍ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ገለጹ
Posted: 03 May 2024, 13:38
በአማራ ክልል ራያ አላማጣ ዛታ እና ኦፍላን ጨምሮ አወዛጋቢ በሆኑት አካባቢዎች ባሉ አማራ ማኅበረሰብ ላይ በትግራይ የታጠቁ ኃይሎች እየደሰ ያለው ግፍ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሐማት ገለጹ።
የአማራ እና የትግራይ ክልሎች በይገባኛል በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የታጠቁ ኃይሎች እየገቡ መሆናቸውን በመግለጽ ነዋሪዎች እየሸሹ መሆናቸው መዘገቡ ይታወቃል።
ለሁለት ዓመት የቆየውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማስቆም ያስቻለውን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ከአወዛጋቢዎቹ አካባቢዎች ከፌደራል መንግሥቱ ኃይሎች ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ለቀው እንደሚወጡ የተገለጸ ሲሆን፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተለያዩ መረጃዎች ከአካባቢዎቹ ነዋሪዎች እየወጡ ነው።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እና የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት እንደሚሉት በከተሞች አካባቢ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት መሠማራታቸውን፣ ከከተሞች ውጪ ባሉ ቦታዎች ላይ ደግሞ የህወሓት ታጣቂዎች እንደሚታዩ ገልጸዋል።
ይህንንም ተከትሎ በምሥራቅ በኩል በሚገኙት አወዛጋቢ ቦታዎቹ ይገኙ የነበሩ ነዋሪዎች በተፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት መኖሪያቸውን ለቀው ወደ አጎራባች የአማራ ክልል አካባቢዎች መፈናቀላቸው ተነግሯል።
በዚህም ሳቢያ ከአላማጣ ከተማ፣ ዛታ እና ኦፍላ የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ከቀናት በፊት አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx9wxyxkpxeo