Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Revelations
Senior Member+
Posts: 33813
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: በአዲስ አበባ ቅርጫ ለሰላም ስጋት ነው በሚል ፍርሃት ምክንያት ተከልክሏል

Post by Revelations » 02 May 2024, 17:28

ፒን ያስደነበረው የቅርጫ ስርአት! "አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም!" ብለው ቢያውጁ መልካም ነበር::





የኢትዮጵያውያንን በዓላት ከሚያደምቁ ሁነቶች መካከል ቅርጫ መከፋፈል ይገኝበታል፡፡ የቅርጫ ሥጋ መከፋፈል ከበፊት ጀምሮ የመጣ ባህል ሲሆን፣ አንድ ማኅበር ወይም ቡድን፣ ጎረቤታሞች፣ ዘመዳሞች፣ ጓደኛሞች አንዳንዴም የማይተዋወቁ ሰዎች ለስድስት አሊያም ለስምንት በመሆን ከብት አርደው ለመቀራጨት በሌሊት ወይም በቀን የሚሰባሰቡበትም ነው፡፡ ድባቡም በሥራ፣ በቀልድና በጨዋታ የታጀበ ነው፡፡

የቅርጫ ክፍፍሉ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ሁሉም ሰው በየፊናው በተሰጠው ኃላፊነት ደፋ ቀና ይላል፡፡ የከብት ግዢና ዕርዱም ከተከናወነ በኋላ በቅርጫው የሚሳተፉት በአንዳንድ ቦታ ደግሞ እናቶች ጭምር ከሥጋው እንዲሁም ከጉበት የሚቀመስ ነገር በማዘጋጀት በጋራ ተሰብስበው ይበላሉ፡፡ የአበሻ አረቄን ጨምሮ የተለያዩ መጠጦችም የቅርጫ ዝግጅት ማድመቂያዎች ናቸው፡፡


Post Reply