Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Fed_Up
Senior Member+
Posts: 20660
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Merkato in 13 minutes

Post by Fed_Up » 07 Apr 2024, 11:01


Fed_Up
Senior Member+
Posts: 20660
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Fed_Up » 07 Apr 2024, 11:45

ይሄ መርካቶ መስሎሽ አዳሜ ቂቂቂቂቂቂቂ
ውስጥን ለቄስ


Horus
Senior Member+
Posts: 30956
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Horus » 07 Apr 2024, 13:52

Fed_up

ይህ የቱርክ ቢጭ ቢጭ ወዲያ ብለህ አንተ ስለ ቀይ ባህር አውራ! የገበያውን ነገር ለጉራጌዎቹ ተውላቸው! አታውቅበትም!!



ሕዝቡ ፍቅር፣ አገሩ የተባረከ፣ ገበያው ጥጋብ፣ the land of plenty~~~

Horus
Senior Member+
Posts: 30956
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Horus » 07 Apr 2024, 14:11

All authentic, organic, fresh !!!


Abere
Senior Member
Posts: 11159
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Abere » 07 Apr 2024, 14:21

ሆረስ፤

የገባያን ነገር ካነሳኸው ገባያ ማለት አገር እንደሆነ የሚያስገነዝብ ህዝባዊ ስንኝ ሰምቼ ነበር። መስዔውም እቴጌ መነን ከዚህ ዓለም እንዳረፉ የወሎ ህዝብ ሀዘኑን ለመግለጽ በአለባበስ እና በአካል እንድገልጽ መኳንቱ እና ባለአባቱ ባላገሩን ይስገድድ ነበር። በተለይ ሴቶቹ ነጠላ አለባበሳቸውን እና እራስ ጸጉር ስሪታቸውን በተለመከተ። ታዲያ አንድት ወጣት በዚህ ትማረራለች - የንጉስ ሚካዔል ትውልድ ስፍራ ከሆነው ደብረ-ዘይት አካባቢ መሆኑ ነበር። ደብረዘይት ትልቁ ገባያ ማሻ የሚባል ከተማ ነው - መቅደላ ወረዳ ውስጥ ይገኛል።

ለአንተም መነን ብትሞት ለእኔም ማሻ ሞተኝ፡
ያለ እናት ያለ አባት - የሚያገለሙተኝ።
አለች የሚል ስነቃል ሰምቸ ነበር - ታላላቅ ሰዎች የገባያን አገር ነት ሲያስረዱ።

መርካቶ ውስጧ ሙቅ ነው። የሁሉ እናት ጓዳ - ሙቀት ድምቀቷ የምዕራቡን ካብ እና ህንጻዋን ያስንቃል።

በነገራችን ላይ ቡታጂራን ለማያውቃት - ቡታጅራ አየሯ እጅግ ድንቅ በአካባቢዋ የሚታዩ የልምላሜ ጋራዎች ማራኪዎች ናቸው። በጣም የምትመች ከተማ ነች - በአንድ አጭር የመስክ ቆይታ ጎብኝቻት አለሁ። ደግሜ የማየት ዕድል እንድኖረኝ እመኛለሁ። ኢትዮጵያ ውበት የታደለች አገር ነች። ሰላም ቢያድላት በአጭር ጊዜ ከምዕራቡ አለም እኩል በዕድገት ትሰለፋለች። ይህ እውነት እንጅ ህልም አይደለም። ምድራዊ ገነት - ኢትዮጵያ። ሰለስቱ ሰይጣናት ወያኔ-ሻዕብያ-ኦነግን እግዜር ብቻ ይገላግላት። እነኝህ የተጣቧት አጋንንት ሲዎጡ -ዕድገት እና ሰላም በምድረ ኢትዮጵያ ይሰፍናል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30956
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Horus » 07 Apr 2024, 15:28

Abere wrote:
07 Apr 2024, 14:21
ሆረስ፤

የገባያን ነገር ካነሳኸው ገባያ ማለት አገር እንደሆነ የሚያስገነዝብ ህዝባዊ ስንኝ ሰምቼ ነበር። መስዔውም እቴጌ መነን ከዚህ ዓለም እንዳረፉ የወሎ ህዝብ ሀዘኑን ለመግለጽ በአለባበስ እና በአካል እንድገልጽ መኳንቱ እና ባለአባቱ ባላገሩን ይስገድድ ነበር። በተለይ ሴቶቹ ነጠላ አለባበሳቸውን እና እራስ ጸጉር ስሪታቸውን በተለመከተ። ታዲያ አንድት ወጣት በዚህ ትማረራለች - የንጉስ ሚካዔል ትውልድ ስፍራ ከሆነው ደብረ-ዘይት አካባቢ መሆኑ ነበር። ደብረዘይት ትልቁ ገባያ ማሻ የሚባል ከተማ ነው - መቅደላ ወረዳ ውስጥ ይገኛል።

ለአንተም መነን ብትሞት ለእኔም ማሻ ሞተኝ፡
ያለ እናት ያለ አባት - የሚያገለሙተኝ።
አለች የሚል ስነቃል ሰምቸ ነበር - ታላላቅ ሰዎች የገባያን አገር ነት ሲያስረዱ።

መርካቶ ውስጧ ሙቅ ነው። የሁሉ እናት ጓዳ - ሙቀት ድምቀቷ የምዕራቡን ካብ እና ህንጻዋን ያስንቃል።

በነገራችን ላይ ቡታጂራን ለማያውቃት - ቡታጅራ አየሯ እጅግ ድንቅ በአካባቢዋ የሚታዩ የልምላሜ ጋራዎች ማራኪዎች ናቸው። በጣም የምትመች ከተማ ነች - በአንድ አጭር የመስክ ቆይታ ጎብኝቻት አለሁ። ደግሜ የማየት ዕድል እንድኖረኝ እመኛለሁ። ኢትዮጵያ ውበት የታደለች አገር ነች። ሰላም ቢያድላት በአጭር ጊዜ ከምዕራቡ አለም እኩል በዕድገት ትሰለፋለች። ይህ እውነት እንጅ ህልም አይደለም። ምድራዊ ገነት - ኢትዮጵያ። ሰለስቱ ሰይጣናት ወያኔ-ሻዕብያ-ኦነግን እግዜር ብቻ ይገላግላት። እነኝህ የተጣቧት አጋንንት ሲዎጡ -ዕድገት እና ብእሰላም በምድረ ኢትዮጵያ ይሰፍናል።
አበረ፣
ምን ጥያቄ አለው?!!! ሕብረ ቀለሟ ኢትዮጵያን ፣ እነዚህ ሁላ ደማቅ ከተሞች በገበያ ነው የተሰሩት ። የጦር ሰፈር ሆነው የተጀመሩትም ቢሆን ሰራዊቱን ለማስተናገድ የተጀመረው ጉሊት ነው ከተማ የሆነው። ገነያ እናት ናት! የትም ተወለድ መርካቶ እደግ! መርካቶ የሁሉን እናት ምትባለው ለዚያ እኮ ነው!፣

ይህው እዚህ እንደ ምታየው አንዲት ሴት አንድ እራስ ሰላጣ በ$10 ትገዛለች፤ ይህም ማለት 10 ያሜሪካን ሳንቲም ማለት ነው። ደሞ ይህ የዋጋ ግሽበት መውረዱ አይቀሬ ነው ።

ቡታጀራን አውቀሃታል! ውብ ቦታ ነው! እዚያ የስላምና ክርስቲያኑ ፍቅር እኛ እዚያው የተወለድነውን ያስገርመናል! ፍጹም የፍቅር ምድር ነው። አሁን እዚም እዛም ስላም ስልጠፋ ወሎዬ ምሹሮች እዚያ ድል ባለ ዘፈን ሲጋቡ አይቻለሁ ።

እነዚህ ባለግዜ ኦሮሞች ከበረደላቸው (ደሞም ይበርድላቸዋል) አገራችን ገና ታብባለች!

ይህ ኢቬንት በድምበር የሚጋጩት ምስራቅ መስቃንና ማረቆ እርቅ ያደረጉ እለት የነበረ ደስታ ነው!

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12701
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Fiyameta » 07 Apr 2024, 15:50

ጣልያኖች መርካቶ የሚለውን ቃል ከኢትዮጵያ የኮረጁት ነው። በጥንት ዘመን ትግራይ ባህርን ተሻግራ እስከ ኢጣልያ ድረስ ትገዛ፣ ታስተዳድር፣ ትመራ የነበረች ሀገር እንደነበረች የወያኔ ሊቃውንት ይጠቅሳሉ። :P :P

Last edited by Fiyameta on 07 Apr 2024, 15:55, edited 1 time in total.

Fed_Up
Senior Member+
Posts: 20660
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Fed_Up » 07 Apr 2024, 15:54

Fiyameta wrote:
07 Apr 2024, 15:50
ጣልያኖች መርካቶ የሚለውን ቃል ከኢትዮጵያ የኮረጁት ነው። :P :P

:lol: :lol: :lol:
እቺ ብጣሻም አገር እሚኮረጂ የላትም... ካለም ሞራላቸው ሳይነካ ይሄ አለን ይበሉን እስኪ?

ethiopianunity
Member+
Posts: 9128
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: Merkato in 13 minutes

Post by ethiopianunity » 07 Apr 2024, 16:09

talking about merkato, i have suggestion, conscioncious community, people and government must come together to make every market area organized, by building designed Medeb, that means I bet, the government might charge them or small annual fee and all community must make the area clean setting up system of good sewerage. One should check out how other Markets are built. I think around near Gojam Berenda, the [deleted] sale area is ideal but that is even inside, it should be open market with good Medeb. Especially where fresh foods are sold such as vegetable can turn the area really dirty

Horus
Senior Member+
Posts: 30956
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Horus » 07 Apr 2024, 21:29

ethiopianunity,
ይህ ቦታው ስላልሆነ ብዙ ዝርዝር ውስጥ መግባት ባልፈልግም ጥቂት ነገር መርካቶ ስለሚለው ቃል ልንገርህ ። ይህ ቃል ላቲን ውስጥ ገብቶ መርካቶ፣ ሜርካዶ፣ ማርኬት፣ ሜርካሪ፣ ሜርኩሪ፣ መርቸንት፣ መርቸንዳይዝ ከመባሉ በፊት ከጥንታዊ ግብጽ ቃል 'ኧርክ' ከዚያም ወደ ግዕዝና የቀሩት ኢቲዮፒክ ቋንቋዎች ዘልቆ ዛሬ ላይ 'አራዳ' ፣ 'ገበያ' ፣ 'አደባባይ' ፣ 'ቸርቻሪ' መደብር፣ ወዘተ የምንለው ቃል ነው ። ሲጀመር መሰብሰቢያ፣ መከማቻ፣ መከመሪያ ፣ መደመሪያ ቦታ ማለት ነበር።

አራዳ የሚለውና አዳባባይ (አደባባሊ ቦታ፣ መደበሊያ ቦታ) የሚሉት ቃላት አሁንም ድረስ መከማቻ ቦታ ማለት ነው። መደበልያ ከሚለው መደበሪያ (መቀመጫ) የሚለውና መደብር የሚሉት ጽንሶች ሰጥቶናል ፣ በረንዳ የሚለው የህንድ ቃል በቀጥታ መደብር ማለት ነው ።

አደባባይ ማለት አገባባይ ማለት ነው ። ገበያ ፣መገበያየት ማለት ነው ። ላቲኖች ከኢትዮፕያና ቅርብ ምስራቅ መገበያየት ከጀመሩ በኋላ ነው 'ኧርክ' 'አራዳ/አራካ' የሚለው ቃል ወደ ላቲን ቋንቋ ገብቶ 'መርክ' የተባለው ።

ወደፊት በሰፊው የቃሉ ኢቲሞሎጂና ሞርፎሎጂ ላይ እጽፍበታለሁ ።

Abaymado
Member
Posts: 4217
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Abaymado » 07 Apr 2024, 21:45

This is Istanbul, Turkey

Horus
Senior Member+
Posts: 30956
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Horus » 07 Apr 2024, 21:55

Abaymado wrote:
07 Apr 2024, 21:45
This is Istanbul, Turkey
ኧረ በተሰቀለው :lol: :lol: :lol: ይህማ እስከነ ዳገቱ ዶሮ ማነቂያ አይደል እንዴ :lol: :lol:

Naga Tuma
Member+
Posts: 5549
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Naga Tuma » 08 Apr 2024, 06:18

Fed_Up wrote:
07 Apr 2024, 15:54
Fiyameta wrote:
07 Apr 2024, 15:50
ጣልያኖች መርካቶ የሚለውን ቃል ከኢትዮጵያ የኮረጁት ነው። :P :P

:lol: :lol: :lol:
እቺ ብጣሻም አገር እሚኮረጂ የላትም... ካለም ሞራላቸው ሳይነካ ይሄ አለን ይበሉን እስኪ?
እኔ የድሮ ክፍለ ሃገር የዘንድሮ ጎረቤት ሃገር ወንድሞች እና እህቶች እንጂ ኣንተ ኤኤምሲኢ ኣልልም። ዛሬ ኣሳስተሀኝ ኣልኩኝ።

እኔ እንደመሰለኝ ፍያማታ ማለት የፈለገዉ ስለ ስሙ ሳይሆን ስለ ፊደሎቹ ነዉ። መ፣ ረ፣ ቶን ኣይቶ። መረቶ? መርካቶ? ብሎ ለማንበብ ሲሞክር ግራ ተጋብቶ።

እንዲገባዉ የምያዉቃትን ሀ ሁ ኣስታወሰ።

ሀ ግዕዝ፣ ሁ ካዕብ፣ ሂ ሳልስ፣ ሃ ራብዕ፣ ሄ ሃምስ፣ ሂ ሳድስ፣ ሆ ሳብዕ እያለ ስያስታዉስ የበለጠ ግራ ተጋባ።

ራብዕ? ያ ራባ፣ ያ ረብ፣ ራብዕ ምን ማለት ነዉ እያለ ግራ ገባዉ።

ሃምስ? ሐሙስ? ከምሲ? አምስተኛዉ ቀን?

ሳድስ? ስድስት? ሰዲ? እያለ የበለጠ ግራ ተጋባ።

ስለ ፊደሎቹ ኣይዴለም የለጠፍኩኝ ካለ ይሄዉ መድረኩ። ያብራራ።

ሆረስማ የጉልት ዘመን የለፋሁበት ሱቅ ኣለኝ ከመርካቶ ዘመናዊ ብሉ ፕርንት ብላችሁ እንዳትጠጉኝ የሚል ይመስላል።

Abere
Senior Member
Posts: 11159
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Abere » 08 Apr 2024, 11:36

ሆረስ፥

የገባያ እናት እንደሆነ ( ሁሉን የሚያቀርብ) ከጥንት ጀምሮ ያለ ነባር እውነት ነው። እንደህ እንደ አሁኑ ዘመን አጨብጫቢዎች ይህን እውነት በመዘንጋት ነበር በንጉሱ ዘመን እቴጌ መነን በማረፋቸው ምክንያት የአካባቢው ትልቅ ገባያ እንድዘጋ እንድከለከል በመሆኑ ያች ጋለሞታ ወጣት ብሶቷን በስነ-ቃል የቋጨችው።

ይህ ጉዳይ አሁን በዚህ ዘመን እየተደገመ ስናይ እጅግ አሳፋሪ ነው። ዛሬ የኦሮሙማ ተረኛ ታላቁን የአፍሪካ ገባያ የሆነውን መርካቶ መዝጋት ሳይሆን እያፈራረሰ ይገኛል። ይህ ኦሮሙማ ቱባ ቱባ ጀኔራሎቹ በጦር ሜዳ ሲገደሉ በንደት ድሃ ጠግቦ የሚያድርበትን የገባያ ቦታ ያፈርሳል። ቤት እና የገባያ አዳራሽ ማፍረስ የአብይ አህመድ የሀዘን መውጫ መሆኑ ነው። እንደ ኦሮሙማ ህልም ታላቁን መርካቶ በማፍረስ የኦሮሙ የገባያ አዳራሽ በኦሮሞዎች መፍጠር ነው። ይህ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ መንጋ እንሰሳ ያለ አስተሳሰብ ነው። የተሰራን ከማፍረስ ያልተሰራ ሰርቶ ማሳየት ለምን ተሳናቸው? ኦሮሙማዎች መንጠቅ እንጅ መስራት ስለማይችሉ ነው። እንኳን የማይሰራው ተረኛ በመንጋ የሚያስበው ኦሮሙማ አይደለም ሰርተው እና አገር ወዳድ ሁነው እንኳን አገር ማስተዳደር ፈታኝ ነው። The end of OLF-PP is very obvious - it will soon k!ss goodbye.

Naga Tuma
Member+
Posts: 5549
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: Merkato in 13 minutes

Post by Naga Tuma » 09 Apr 2024, 15:47

ኣንድ ሀሳብ ሌላ ሀሳብ ያመጣል።

ከሁሉም በላይ ራብዕ የሚለዉን ቃል ኣስታዉሼ ልረሳዉ ኣልቻልኩም።

ምን ማለት ነዉ?

እናቶች ረቡዕ ቀን ቡና በማፍላት እንደ በዓል ቀን ያስታዉሱ ነበረ። ስለምን እንደሆነ የምያዉቅ ኣለ? ወይም ጠይቆ መገንዘብ ይቻላል?

ረቡዕ በኦሮምኛ ሮቢ ነዉ። ሮበ ማለት ዝናብ ማለት ነዉ። ካልተሳሳትኩ ራቡ ማለት ትንቢት መናገር እንደማለት ነዉ።

ዮሴፍ ህልም ሰምቶ ስለ ድርቅ እና ዝናብ ዓመታት እንደተነበየዉ።

ራበ ዶሪ ማን ነበረ? ትንቢት በመናገር የታወቀ ነዉ?

ነቢ ማን ነበር? ነቢ እና ነብይ ልዩነት ኣላቸዉ?

ነቢም ከፋሲካ በኋላ የሚከበር ባህላዊ በዓል ነዉ። ጠጅ ተጠምቆ።

ሀ ግዕዝ፣ ሁ ካዕብ፣ ሂ ሳልስ፣ ሃ ራዕብ፣ ሄ ሓምስ፣ ሂ ሳድስ፣ ሆ ሳብዕ ሲቆጠሩ ሰባት ናቸዉ።

የሳምንት ቀናት ሰባት ናቸዉ።

ከኣሁን በፊት ኣስተዉዬ በጣም የገረመኝ በኦሮምኛ ሰባቱም ቀናት ልዩ መለያ ኣላቸዉ። ዼንገደ ዱበ፣ ዼንገደ፣ ከሌሰ፣ ሀርዸ፣ ቦሩ፣ እፍታን፣ እፍታን ዱበ ተብለዉ።

እንደዚህ ሰባቱም ቀናት ልዩ መለያ ያላዉ ሌላ ቋንቋ እስከ ኣሁን ኣልሰማሁም።

ለተመራማሪዎች መልካም ጥያቄዎች ናቸዉ። ኣይዴሉም?

Post Reply