Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30991
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የበቀለ ሞላ ላንጋኖ ሪዞርት ልክ እንዳለ ነው!

Post by Horus » 05 Apr 2024, 21:17

ብዙ ግዜ የከተምኩባት የዋኝሁባት ላንግዬ ላንጋኖ ይገርማል እንዳለ ነው ። እዚያ መጨረሻ ክሊፉ አጠገብ ያለው ቤት የግሮሰሪ ሱቅ የነበረው ነው! ዳቦና ቪኖ የምንገዛበት! ምግብ ቤቱ ፣ ሲሊማ ቤቱና መኝታ ቤቶቹ እንዳሉ ነው ። የቢቹ አሸዋ ተበላሽቷል ። ጠጠር በዝቶበታል ። ውሃው ትንሽ ዝቅ ብሏል። የቢቹ ምዕራብ ጫፍ ድሮ ሰዎች መሬቱን ተከራተው የራሳቸው ድንኳን የሚተክሉበት ነበር ። $15 ወይም $30 ይከፈል ነበር ። እነዚህ የታደሱት ሁሉ መኝታ ቤቶች ነበሩ


Horus
Senior Member+
Posts: 30991
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የበቀለ ሞላ ላንጋኖ ሪዞርት ልክ እንዳለ ነው!

Post by Horus » 05 Apr 2024, 21:32

ላንጋኖ በዝናብ ውሃ ስለሚሞላ አረንጓዴ ሳይሆን ቢጫ አፈራማ ውሃ ነው። አንድ ሳምንት በየቀኑ የዋኘ ሰው ጸጉሩ ሁሉ ቀለም ይለውጣል ። እኛ ቆዳችን ሁሉ አሸዋ ይሆን ነበር ። ሁለት ሂፖዎች ነበሩ ።ማታ ማታ ሳር ሊበሉ ይወጡ ነበር ። ሂፖ የሚያዩት ባጭር ስለሆነ በድንገት ሰው አጠገባቸው ከተገኘ ይገድላሉ ። አሁን ይህቺ ሴት ስትዋኝ በጣም ርቃ መሄዷ ስህተት ነበር ። የሞተር ጀልባዎቹ የሉም ።

በኢትዮጵያ ሰላም ከመጣ መጀመሪያ የምሄደው ላንጋኖ፣ ሻላና አቢያታ ነው!

Post Reply