Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12620
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must Watch: ኃይለማርያም ደሣለኝ ኢትዮጵያ በዓብይ አመራር እንደዚህ ዓይነት አዘቅት ውስጥ እንደምትገባ ተንብዬ ነበር አለ

Post by Thomas H » 04 Apr 2024, 08:42

Source: Bewketu Seyoum

ብሶት
እኛ ቤት መብራት ከጠፋ ሁለተኛ ቀኑን ያዘ፤ በዚህ ክረምትማ ፥ የራስጌ መብራት ብቻ ሳይሆነ የግርጌ መብራት ይኖረኛል እያልሁ ስፎክር ጉድ ሰሩኝ ፤ ለነገሩ ህዳሴ ግድብን አሳ ማርቢያ ሲያረጉት ነው ተስፋ የቆረጥኩት፤ አምስተኛው ተርባይን ተገጠመ ምናምን የሚል ዜና ስጠብቅ አምስት ኪሎ እሚመዝን አሳ ተመረተ እያሉ ይዘግቡልኛል ፤ ለዚህ ነው ከፈርኦኖቸ ጋራ ደም የተቃባነው? ለዚህ ነው ቦንድ የገዛነው?
መብራት ለምን ተቋረጠ ብየ በጠየቅሁ ቁጥር ደሞ መልሳቸው አንድ ነው” ፖል ወድቆ ነው” ይሉኛል፤ እኛ ሰፈር ያለው የመብራት ፖልማ ጭንቅ አይችልም፤ ቦርጫም ርግብ ሲያርፍበት ራሱ ፍንግል ይላል!
ስሙኝማ! ባለፈው ምኡዝ ካንዲት ቀዘባ ጋራ ሲጀናጀን “ለመሆኑ እድሜህ ስንት ነው?” አለችው ፤ በቀጥታ በመናገር ፋንታ “ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከተቆጠረ አራት መንግስታትን ያየሁ ሰው ነኝ ‘ ብሎ መለሰላት፤ ንድድ አለኝ፤ ጅንጀናው ጋብ ካለ በሁዋላ ወረድሁበት ” ሀይለማርያም ደሳለኝ ባንተ አፍ የሚጠራ ሰው አይደለም ! ሀይለማርያም ደሳለኝኮ ‘ የተከበራችሁ የጎዳና ተዳዳሪዎች” በማለት የኢትዮጵያን ህዝብ መጭ እድል መተንበይ የቻለ መሪ ነው፤ “ በማለት ወቀስኩት፤ ምኡዝም እንባ ባቀረረ አይን ወደ የካ ተራራ እየተመለከተ እንዲህ አለ ፤ "አይ ሀይልሻ! ሳናውቅህ ወቀስንህ! ስናውቅህ አጣንህ!"
ሀይልሽ ግን የት ደረሰ? በቅርቡ የሆነ ቸርች ላይ እንደ እንደ እንደ ሀመር ጎረምሳ፥ እግሩን ገጥሞ እየዘለለ ሲሰብክ አይቼው ነበር፤ የስብከት አገልግሎቱን በፈቃዱ በመልቀቅ የመጀመርያውም የመጨረሻውም ሰባኪ ይመስለኛል ፤



Thomas H
Senior Member
Posts: 12620
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Re: Must Watch: ኃይለማርያም ደሣለኝ ኢትዮጵያ በዓብይ አመራር እንደዚህ ዓይነት አዘቅት ውስጥ እንደምትገባ ተንብዬ ነበር አለ

Post by Thomas H » 04 Apr 2024, 09:07


ኃይለማርያም ደሣለኝ የዓብይ እና የብርሃኑ ጁላ ጦር እንደዚህ መጫወቻ እንደሚሆንም ተንብዮ ነበር
Please wait, video is loading...

Post Reply