Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7994
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

በያየሰው ሽመልስ የተጻፈው "የሴራ እርካብ የደም መንበር" መፅሀፍ ለህዝብ ተለቀቀ!! የሸሌዋ ዝናሽ ታያቸው ጉድ!!

Post by Wedi » 24 Mar 2024, 08:47

በያየሰው ሽመልስ የተጻፈው "የሴራ እርካብ የደም መንበር" ከተጻፈው "የሰውዬው ሚስቶችና ዲግሪዎች" በሚለው እርስ ከተጻፈው የተወሰደ!!

የሸሌዋ ዝናሽ ታያቸው ጉድ!!


የሰውዬው ሚስቶችና ዲግሪዎች

-----------------

ምሽቱን በዚህ ቤት ለማሰለፍ አንዱ ጥግ ላይ ተሰየምሁ። የሥራ ጫና ያዛለውን መንፈሴን ቀዝቀዝ ያለ ቢራ በማዘዝ ላነቃቃው ተቀመጥሁ። በዚህ ሁኔታ እንድ ሰዓት ያልሞላ ጊዜ እንዳሰለፍሁ ስልክ ተደወለልኝ፡፡ ደዋዩዋን አውቃታለሁ፡፡ የፖርላማው የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ ነች።

ሠላምታ ከተለዋወጥን በኋላ «ይቅርታ በዚሀ ምሽት የደወልኩት የነገው ፕሮግራም መሠረዙን ልነግርህ ነው» አለች፡፡ ጥሩ ወዳጅነት ስላለን በቀልድ መልክ «ምነው ተዝረከረካችሁ...? አሁን ድግስ
ጠርታችሁ ሰርዘነዋል ይባላል?!» አልኳት፡፡

«እኛ አይደለንም ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ ነው። ደግሞኮ አልተሰረዘም ወደ ሰኞ ነው የተዘዋወረው፤ ስለዚህ ሰኞ ጠዋት ሁለት ሰዓት ሪፖርተሮችሀን መላክ ትችላለህ። የምትቀይረው ሰው ካለ ነገም ልትነግረኝ ትችላለህ» ስትል አብራራች፡፡ የፓርላማ ዘገበ ለመሥራት የሚሄዱ ሰዎችን የሚዲያ ኃላፊዎች አስቀድመን ማሳወቅ ስላለብን ነው ያንን ማለቷ፡፡ አመስግኜያት ስልኩን ዘጋሁ፡፡

«ይሀንን የሚያህል ነገር፣ የውጪ ሀገር ዲፕሎማቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የሚገኙበት፣ በሀገሪቱ ውስጥ በጉጉት የሚጠበቅን ሥነ-ሥርዓት እንዴት ሊያራዝሙት ይችላሉ?» እያልኩ ለደቂቃዎች ሰስብ ቆየሁና ወደ አንድ የኢሕአዴግ ባለ ሥልጣን ጋር ደወልኩ።

«ለምንድን ነው ሊቀመንበራቸሁን ጠቅላይሚኒስትር ሆኖ የሚመጣበትን ጊዜ የምታራዝሙበት...?» የመጀመሪያ ጥያቄዬ ነበር፡፡

«ምን ተፈጠረ ደግሞ...?» መልሶ ጠየቀኝ፡፡

«ነገ ቃለ መሃላ ፈጽሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆን ፖርላማው ከጠቆመን በኋላ ወደ ሰኞ ተዛውሯል ብለው ደወሉ»

«ይህ የሆነው በምን ምክንያት ነው አሉ ታዲያ?»

«የተጠቀሰ ነገር የለም!»

የለበጣ ሳቁ በስልኩ ውስጥ ተሰማኝ።

«በል ነገ ጠዋት መጽሐፌን ቢሮ ይዘሀልኝ ና» ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡ ንግግሩ ግልጽ ነው። «ቢሮ መጥተሀ እነግርሃለሁ፤ በስልክ አይነገርም» እያለኝ ነው። በርግጥ ከእርሱ የተዋስሁት መጽሐፍ አለ፡፡ የዚሀን ሰው ቀጠሮ አክብሬ ማልጄ መነሳት እንዳለብኝ ስለማውቅ ከሆቴሉ ብዙም ሳልቆይ ወጣሁ።

ሳር ቅጠሉ ዕቢይ አሕመድ የተባለን የፖለቲካ ሰው በማስተዋወቅ ላይ ተጠምዷል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ቅዳሜ ማለዳ ይዘውት በወጡት ሕትመት ይሀንን ሰው የሚገልጹበት አማርኛ ቸግሯቸው ታዩ፡፡ እንደ መለኮትም እንደ መላዕክትም አድርገው፣ እንደ ሙሴም እንደ ኢየሱስም ስም አውጥተውለት አዲስ አበባን አጥለቅልቀዋታል። ስለማያውቁት ሰው ይሀንን ያህል ድፍረት አግኝተው መፃፋቸው እያስገረመኝ ወደቀጠረኝ የኢሕአዴግ ባለ ሥልጣን ቢሮ አመራሁ። በዚህ ሁሉ የገጽታ ግንባታ ሥራ ላይ ኦሮማራ እንደተሰማራ ግን አላጠሁትም።

ወደ ኢሕአዴጉ ወዳጄ ቢሮ ስዘልቅ አንድም ደቂቃ አላረፈድሁም፤ የትናንቱን ጥያቄዬን ሰቀርብም ፋታ
«ሊቀመንበራችሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ለማድረግ ምነው ዘገያችሁ...? ለምንስ ፕሮግራማችሁን
“እኛ አላዘገየንም፤ እኛም አልሰረዘነውም» መለሰልኝ። "እና ማነው?..

«ለምን ቢባል...? እንደምሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ለመበል በጣም ቸኩሏል!»

«እኮ ለምን..?»

ይቺን ጥያቄ በሰፊው አብራርቶልኛል። የዚህን ሰው ምላሽ በራሴ ቃላትና ትረካ እንደሚከተለው ልውጣ

ዐቢይ ከሚስቱ ዝናሽ ታያቸው ጋር ከተለያየ ስምንት ዓመት አልፎታል፡፡ በርግጥ ተፋታ ማለት አይቻልም፡፡ ቀድሞ ነገር ሕጋዊ ጋብቻ አልመሠረቱም፡፡ እርሱ የሬዲዮ ኦፕሬተር እርሷ ደግሞ የመከላከያ ዘፋኝና ተወዛዋዥ ሆነው ነበር በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ የተዋወቁት። በርግጥ እርሷ ከዚያ በፊት የብዙ መኮንኖች ቀሚስና የአይን ማረፊያ ነበረች። ከጥቂቶቹ ጋርም በአልጋ ደረስ ግንኙነቷ የምትታወቅ ናት፡፡ በኋላ ግን የመቶ አለቃ ዐቢይ ሚስት ሆና ልጆች ወለዱ፡፡ ሆኖም ከዓመታት በኋላ ተጣሉ፡፡ እርሱ ማገጠ። ቤቱን ትቶ ውጪ ውጪውን ማለት አበዛ፡፡ እርሷ በዚህ መሀል ጴንጤ ሆና ነበር፡፡ ከዚያ ከአንድ የኢቫንጀሊካል ቸርች ጋር በተደረገ ግንኙነትና በአንድ ባለ ሥልጣን እገዛ፣ በአንድ ባለሃብትም ድጋፍ ወደ አሜሪካ ሄደች። ከዚያ በኋላ እርሱ የአባዱላን ሚስት (ራሔል) እህት አግብቶ መኖር ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም ነፍሰ ጡር እያለች የጤና እክል አጋጥሟት ጽንሱ ተቋረጠ፡፡ ለዚህ የእርሱ እጅ አለበት፡፡ በኋላ ላይ ከእርሷም ጋር ተለያየ፡፡ በዚህ ምክንያት የአባዱላ ሚስት ዐቢይን ማየት አትፈልግም።

የሆነው ሆኖ ከዚያ በኋላም ሌሎች ሴቶችን ለማግባት ሞክሮ ነበር፡፡ ትዳር እንደ ሰልባጅ ልብስ አይበረክትለትም። ያገባል፤ ይፋታል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ትልቅ ኃላፊነት አናቱ ላይ ወደቀበት። ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። በዚህ ወግ አጥባቂ ማሀበረሰብ ውስጥ ልጅ ወይም ትዳር ሳይኖርህ አለያም ፈት ሆነህ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ስትበቃ፣ ተቀባይነትሀ እምብዛም ይሆናልና ሚስትሀን መልሰህ አምጣ› ብለው እነ አባዱላ እማከሩት፡፡ ከዚያም ሽማግሌዎች ላከ። መጀመሪያ የሄዱት አባዱላና ሲሳይ የሚባል ባለሃብት ናቸው፡፡ ሲሳይ በአንድ ወገን የጎንደር ተወላጅ በመሆኑ ነው የተመረጠው። የዝናሽ ታያቸው የሀገር ልጅ መሆኑ ነው።

ሁለቱም አሜሪካ ሲሄዱ ሰውዬው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኗል ለልጆቻችሁም ሆነ ለአንቺ ትልቅ ዕድል ነውና ተመለሺ› አሏት። እርሷም መጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሳ በዝሙት ምክንያት መለያየቷ በእግዚአብሔርም የተፈቀደ ነው ብላ አሻፈረኝ አለች፡፡ አልሳካ ብሏቸው ተመለሱ። የታወቁ የፐሮቴስታንት ሃይማኖት ፓስተሮችም በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገቡ። «የጌታ ሰው ወደ መንበሩ መጥቷልና ሚስት ሆነሽ ተመለሺ » ብለው

በዚህ መሀል የአሜሪካ የደኅንነት ተቋማት የኢትዮጵያ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስትና ልጆች በዜግነት አሜሪካዊ ሆነው በእነርሱ ሀገር እንደሚኖሩ አወቂ፡፡ ከዚያም ወደ እንድ ደሀንነታቸው ወደሚጠበቅበት ቦታ አዘዋወሯቸው። ከዚያ በኋላ ማይክ ሬይነር ወደ አዲስ አበባ መጣ። ማይክ የተዋጣለት የጎዳና ላይ ነውጥ አቀጣጣይና ቀራጭ ነው። የሲአይኤም ኤጀንት ነው። በተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት አምባሳደር ተደርጎ በሠራባቸው ወቅቶች አሜሪካኖች የማይፈልጉትን መንግሥት በአመጽ እንዲወድቅ የሚያስችል ተልዕኮ ይዞ ከውኗል፡፡ ቤኒን ለዚህ ምሳሌ ነች፡፡ ሆኖም ትራምፕ ከመጣ በኋላ በሀገሪቱ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ተራ የሰው ኃይል አስተዳደር ሠራተኛ ተደርጎ ተመድቦ ነበር። ስላልተመቸው ትቶት ወጣ።

በመጨረሻ ግን የኢትዮጵያ ጉዳይ እየሞቀ ሲመጠ ሲ.አይ.ኤ. አንድ ሁነኛ ሰው በአምባሳደርነት መሰየም ሲፈልግ ማይክ ሬይነርን አገኘ፡፡ ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከዐቢይ ጋር ተገናኘ፡ በዚህ ወቅት እርሱ ጠቅላይሚኒስትር የመሆኑ ነገር እርግጥ ስለነበር በዚህ ላይ የሚያግዘው ነገር እንደሌለ ያውቃል፡፡ ዋናው የዐቢይ ችግር አሜሪካዊቷ ሚስቱ ወደ ኢትዮጵያ አልመለስም, ማለቷ መሆኑን ግን ሊደብቀው አልፈለገም፡ ማይክ <ነገሩን በኔ ጣለው› አለ፡፡ (የትዳርሀን ጉዳይ አሜሪካ ትይዘዋለች, እያለው ነበር፡፡

ከዚህ በኋላ ዐቢይ ከማይክ ሬይነር ጋር የወቅቱን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁን፣ መደበ። ከዚያም ወደ አሜሪካ ጉዞ ሆነ፡፡ ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው «ዳግመኛስ የዐቢይ ሚስት ሆኜ አልኖርም፤ እኔ ትዳሬም ኑሮዬም ኢየሱስ ነው» ብላ አሻፈረኝ ስትል ብትከርምም በአሜሪካ መንግሥት እና በኢትዮጵያ መንግሥት ሚስትነትሽ ይመለስ› የሚል ምልጃ ሲቀርብላት የምትሰጠው ምላሽ ተጠባቂ ሆኖ ሰነበተ። በመጨረሻም በዕለተ አርብ መጋቢት 21/2010 ዓ.ም. በቅድመ ሁኔታ ተስማማች፡፡ «ለሕዝብ ቀዳማዊት ዕመቤት ሆኜ እንደምኖር ቢገለጽ ችግር የለብኝም፤ በቤቴ ውስጥ ግን ከዐቢይ ጋር አልጋ የሚያጋራ ትዳር አይኖረንም» አለች፡ በዚሀ ስምምነት መሠረትም ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ለማድረግ ተወሰነ፡፡

«ዐቢይ ወርቅነህ ገበየሁ ትዳሩን እንደገና ለመመለስ እንዳገዘው ባይናገርም በ2010 ክረምት ወደ አሜሪካ በተጓዘ ጊዜ ግን «ወርቅነህ የቲም ለማ አባል ነው ፤ የውጪ ጉዳይ ኃላፊና አማካሪም ነው» በማለት ገልጹዋል። በሌላ መድረክ ደግሞ «ወርቅነህ ባይኖር ልጆቼ መማር አይችሉም ነበር፤ ትሣል ላይ ስለነበርን ወደ አሜሪካ የመጡትን ልጆቹን ያስተማሩልኝ ከአሜሪካ መንግሥት ቀጥሎ እነ ወርቅነህ ናቸው፤ መስረቅ ስለማንቸል ልጆቻችንን ማስተማር አልቻልንም ነበር» ብሏል፡፡ እርሱም ሆነ ወርቅነሀ ሚኒስትርና የመንግሥት ባለ ሥልጣን ናቸው። ታዲያ ወርቅነህ hoቢይ የተሻለ ኢኮኖሚያዊ አቅም ኖሮት እንዴት ልጆቹን ሊያስተምርለትና ከግዙፉ የአሜሪካ መንግሥች ቀጥሎ የአብራኩን ክፋዮች ሊንከባከብለት ቻለ የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ ግን በወቅቱ እንደ ብሔራዊ ሐጢአት ይቆጠር ነበር።


ከዚያ በፊት ግን የኦሮማራ ቡድን የዐቢይን በዓለ ሲመት ለማከናወን ለዕለተ ቅዳሜ መጋቢት 22/2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዞ ደፋ ቀና እያለ ነው፡፡ መገናኛ ብዙሃንን እየጠራ፣ እምባሳደሮችን እየጋበዘ፣ ቢሮ እየተረካከበ ነው። ዐቢይም ሚስቱ የማትስማማ መስሎት በተቆረጠው ቀን ቃለ መሃላውን ሊፈጽም ንግግሩን ጽፎ ጨርሷል፡፡ በአማርኛና በኦሮምኛ ንግግር አቀርባለሁ ብሎ በነ አባዱላ ተግሳጽ ነው፤ የተወው። ያኔ አባዱላ አፈ-ጉባኤም የኦሕዴድ ነፍስ አባትም ነበር፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ግን ዐቢይና ኦሮማራዎቹ ከአሜሪካ የብሥራት ዜና ሰሙ። «ዝናሽ ሚስት ትሆን ዘንድ በመርሀ ደረጃ ተስማምታለች፤ ግን ቅድመ ሁኔታ አላት› ተባለ፡፡ ዐቢይም «ብቻ እሺ ትበል እንጂ ለሁሉም ቅድመ ሁኔታ ዝግጁ ነኝ፡፡ ሲል ማለ፡፡ ግን ለበዓለ ሲመቱ አትደርስም፡፡ ከ13 ሰዓታት በላይ የሚፈጀው በረራ ቅዳሜ ጠዋት ለሚካሄደው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ድግስ ላይ አያደርሳትም። እናም በአሜሪካ መንግሥት ተማጽኖ ቀዳማዊት ዕመቤት ለመሆን ለተስማማቸው ለዝናሽ ታያቸው ሲባል፣ ቅዳሜ ዕለት ሊካሄድ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመትም ወደ ሰኞ መጋቢት 24-2010 ዓ.ም. ተራዘመ፡፡

የአሜሪካ መንግሥት በመሪዎቻችን የትዳር ጉዳይ ሳይቀር የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እያስገረመኝ የወዳጄን ቢሮ ለቅቄ ወጣሁ፡፡ በዚሁ አላበቃሁም። የኢሕአዴጉ ወዳጄ የሰጠኝን መረጃ ይዤ እርሱ በውይይታችን ወቅት ያነሳቸውን ሰዎች ተከትዬ ወደማጣራት ገባሁ። ነገሩ በትክክል የተፈፀመ ነው። ይባስ ብሎ የእርሱን ትዳር ለመመለስና ዝናሽን ሚስቱ ለማድረግ ከሚቴ ተቋቁሞ እንደነበርም ሰማሁ።


በያየሰው ሽመልስ የተጻፈው "የሴራ እርካብ የደም መንበር" በሚል ር ዕስ የተጻፈው ሙሉውን መፅሀፍ በPDF ከዚህ ላይ አውርዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ!!