ቁልፍ ቃላት
(1) መደብ
(2) ጉሊት
(3) ተራ
(4) አዳራሽ
(5) ማዕከል
(6) ፎቅ
መደብ በጣም ትንሹ የምርት ወይም የሸቀጥ መደርደሪያ ነው ። መደብ ብዙውን ግዜ በክፍት ገበያ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚለው የአደራደር አይነት ነው ።
ጉሊት የገበያ አይነት ነው ። ብዙውን ግዜ በመኖሪያ ሰፈር ለተወሰኑ ሰዓታት ብቻ የሚቀመጥና ከ5 እስከ 20 ነጋዴዎች ብቻ የሚገኙበት ገበያ ሲሆን ጉሊት መጎለቻ መቀመጫ ማለት ነው ። ጉሊት ጉልቻ ማለት ነው። ጎለት በጉራጌ ለብቻው ለሙሽሪት መቀመጫ የሚሰራ የቤት ክፍል ነው ።
ተራ እጅግ ትልቁ የገበያ አደረጃጀት ሴራ ነው። መርካቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ የምርትና ሸቀጥ ተራዎች አሉ ። በአንድ ቃል መላው መርካቶ የተከፋፈለውና የተደራጀው በተራ ነው ። ከሎሚ ተራ እስከ ጫማ ተራ፣ ከዘይት ተራ እስከ ቅቤ ተራ ህሉ ነገር ተራ አለው ። ንግድ የሚማሩ ተማሪዎች ምርምር አድርገው መርካቶ ውስጥ ስንት ተራዎች እንዳሉ ቢጽፉበት እንዴት መልካም ነበር!
አዳራሽ ክፍት ገበያ ህንጻ ውስጥ መግባት የጀመረበት ሴራ ነው ። የገበያ አዳራሽ የጀመረው ከአረብ ሱቅ ነው ። ሱቅ በውስጥ ብዙ አይነት ምርትና ሸቀጥ ሲኖሩት በመደብ ወይም መደርደሪያ ይደራጃል ።
የገበያ አዳራሽ በወስጡ ብዙ ሱቆችና መደቦች ያሉት የገበያ ሴራ ነው ። በገበያ አዳራሽ ውስጥም የተራ ሴራ አለ። አንዱ ሱቅ ወይም አንዱ መደብ አንድ አይነት ምርት ወይም ሸቀጥ ብቻ ያስተናግዳል። ትለቅ ያሉት ሱቆች እንደ ባለብዙ ምርትና ሸቀጥ ናቸው ፤ በምዕራብ ጄኔራል እስቶር እንደ ሚባሉት ማለት ነው ።
የገበያ ማዕከል ከገበያ አዳራሽ የተለቀ ከ3 እስከ 5 ወለል ያለው በምዕራብ ዲፓርትመንት እስቶር ወይም ሱፐር ማርኬት የሚለው ሲሆን ይህም በውስጡ ልክ እንደ ተራ አደረጃጀት ሰፋፊ የምርትና ሸቀጥ ገበያ ፍሎች አሉት ። ይህ በምዕራብ ሱፐር ማርኬት እንደ ሚባለው ነው ። ዛሬ መርካቶ ባብዛኛው በገበያ ማዕከሎች እየተደራጀ ነው ።
የመጨረሻው ዘመናዊ ባለ ኤሊቬተርና ኤስኬለተር የገበያ ፎቅ ነው። ይህ በአይነቱም በጥራቱም የተራቀቀ ምርትና ሸቀጥ መገበያያ የሾፒንግ ሴንተር ስርዓት ነው ።
መላው መርካቶ በዚህ መልክ እየተለወጠ ሲሄድ መደበኛ የመኪና ትራፊክ የተከለከለበት እጹብ ድንቅ ያፍሪካ ቁጥር አንድ ግዙፉ ማርሼ መርካቶ ይሆናል !
የመርኬ መፈክር፤ የትም ተወለድ መርካቶ እደግ !!!