Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11132
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ምዕራባዊያን የቀኝህን ጠጣ ካሉህ- የግራህን ጠጣ።ዐብይ አህመድ ከኤርትራ ጋር ላደረገው ስምምነት የኖቤል ሽልማት ያሰጡት የሴራ ህልማቸው የተሳካ መስሏቸው -ኢትዮጵያን የሚጓዳ ሁኖ ስላገኙት።

Post by Abere » 17 Mar 2024, 10:00

ዐብይ አህመድ ከኤርትራው ክፍለ ሀገር ኢሳይያስ አፈወርቅ ጋር ላደረገው ስምምነት የኖቤል ሽልማት ያሰጡበት ምክንያት ምስጢሩ ግልጽ ነው። በኤርትራ በኩል የነበረው የሴራ ህልማቸው የተሳካ ስለመሰላቸው ። ኢትዮጵያን የሚጓዳ ሁኖ ስላገኙት ነው።

ምዕራባዊያን ኤርትራ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ የመልክዐ ምድር እና የፓለቲካ ክፍል መሆኗን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በማንኛውም በተጭበረበረ መንገድ ይችን ቀጭን የመሬት ወሽጥ ምንም እንኳን እራሷን ችላ አገር መሆን የማትችል መሆኗን መቶ በመቶ ቢያውቁትም የተገነጠለች የችግር ደሴት እንድትሆን ይፈልጋሉ። በቀንደኛ የምዕራባዊ መሳሪያ በነበረው ወያኔ ላይ የተደረገው 27 አመታት ትግል ውጤት ኤርትራ ክፍለ ሀገር ጋር ስለተደረገ የጓዳ ምስጢር ውል ሳይሆን ( to free Ethiopian from ethnic apartheid kilil) ቅድምያ የአለም እና የምዕራባዊያን አትኩሮት መሆን የነበረበት አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የዜጎች እስር ቤት የሆነውን የጎሳ ክልል አፈረሰ ወይ ዜጎች በአገራቸው እንደ ዜጋ እየኖሩ ነወይ ነበር። የምዕራባዊያን ፍራቻ ግን ኢትዮጵያ ወያኔ ከደመሰሰች ፤ ህዝቧ በአንድነት በአንድ አገር ከቆመ ሳይወደድ በግድ በምዕራባዊያን ተጽኖ በህገ-ወጥ መንገድ ሌላ እስር ቤት የገባቸው ኤርትራ ወደ እናት አገሯ ኢትዮጵያ ትመለሳለች ነበር። ይህን ተፈጥሮዊ ሂደት ለማስጨንገፍ ህጻኑ አብይ አህመድ ላይ በአንገቱ ሽልማት በማጥለቅ በህገ-ወጥ እርምጃ ለተገነጠለችው ኤርትራ እንድተባበራቸው የተዘየደ ሴራ ነበር። ሴራው ሴራ ስለነበረ ውሎ አድሮ ግን በመክሸፍ ላይ ይገኛል። ኤርትራም የችግር ደሴት ሁና ቀጥላለች፤ የኢትዮጵያ ዜጎችም የዜጋ እስር ቤት የ100 አመት የቤት ስራ የሆነው የጎሳ ክልል እየመዘዙ በማፍረስ ላይ ናቸው።

A priory clash between the West and Ordinary Ethiopians after the fall of TPLF/Woyane: West dream to get a foot hold in Africa by creating fake country called Eritrea; Ordinary Ethiopians 27 years of fight, to bull doze and ban ethnic apartheid region and restore sovereign Ethiopia.