Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12688
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የትግራይ፥ ጆኖሳይድ፥ መሃንዲስ፥ ዳንኤል፥ ክብረት የሚመራው፥ ማህበር፥ ምን፥ እያለን፥ ነው፤

Post by Fiyameta » 05 Mar 2024, 15:04





ትክክለኛ የመታወቂያ ስሙ ተክላይ አሸብር ሲሆን በተለምዶ (ወዲ አሸብር)እየተባለ ይጠራል፡፡የቀድሞው ብርጋዴር ጀነራል በተለይ በሰራዊቱ የሚታወቀው በጀግንነቱ አልያም በጥሩ አዋጊነቱ ሳይሆን በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የተሳሳተ አመራር በመስጠት 20ኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦርን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ያስደመሰሰ ፣ በዚህም በወታደራዊ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ ሊፈረድበት ሲል ህይወቱ በአንድ ድንገተኛ አጋጣሚ [በሌላ ግዜ እመለስበታለሁ] በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቀጭን ትዕዛዝ የተረፈ ሰው ነው፡፡

ይህ ሰው ባስጨረሳቸው አባላት ሀዘን ቂም በቋጠሩ እና ከእልቂቱ በተረፉ አባላት የመግደል ሙከራ ተደርጎበት የነበረ ሲሆን ከዛን ግዜ ጀምሮ በስጋት የኖረ፣ ከቢሮው ወደ መኪናው ተአምር ቢፈጠር ካለ አጃቢ የማይንቀሳቀስ፣ ድንገት በኮሪደር ላይ ስታገኘው በጥርጣሬ ወደ ኋላ የሚመለስ፣ አከባቢውን የማያምን ድንጉጥ ነበር፡፡

ግለሰቡ አዲስ አበባ ከተማ ጃንሜዳ በሚገኘው በውጊያ ምህንድስና ዋና መምሪያ የጀነራል [በወቅቱ (ሌ/ጄ)] ባጫ ደበሌ ምክትል በመሆን ተመድቦ በጡረታ እስከ ተሰናበተበት ግዜ ድረስ በትንሹ ለ3 ዓመት ያህል አንድ ላይ የሰራን በመሆኑ በደንብ ጠንቅቄ የማወቅ እድሉ ነበረኝ፡፡

በብርጋዲየር ጀነራል ማእረግ የውጊያ ምህንድስና ዋና መምሪያ ም/ አዛዥ በነበረበት ሰአት አንድም ስራ ሰርቶ የማያውቅ ብቻ ሳይሆን በሴራ ጉንጎና እና የራሱን ብሄር ሰዎች በማቧደን በሙስና ሰንሰለት ተቋሙ ላይ እንደ ሀረግ ተጠምጥሞ የነበረ ለመሆኑ አሁን ድረስ ያሉ የተቋሙ አባላት የሚመሰክሩት ሃቅ ነው፡፡ ለዚህ ማረጋገጫው ደግሞ ቦሌ ትምህርት ቤት አጠገብ የሚገኘውና በልጁ ስም የገነባው ብሌን የተሰኘው ግዙፍ ህንፃ ቋሚ ምስክር ነው፡፡

ይህ ሰው በለውጡ አኩርፎ መቐለ ከመሸገ በኋላ በሰሜን ዕዝ ላይ በተደረገው ጭፍጨፋ ዋና ተሳታፊ እና አስተባባሪ የነበረ ሲሆን ዛሬ ላይ ደግሞ የሚያዋጋው ወራሪ ቡድን በጥምር ጦሩ እየተገረፈ መናድ ሲጀምር በመገናኛ ሬዲዬ ሁላችንም ያዳመጥነውን ዘግናኝ ትዕዛዝ ...“በሉዎ ብጥይት!”... “በጥይት በሉት!” እያለ ሲያዝ እንደሰማሁት ነበር የእሱ እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር የቻልኩት፡፡

ይህን ድምፅ ከዘመናት በኋላ ሳደምጠው ወደ አይምሮዬ ቀድሞ የመጣው ጥያቄ በስልጣን ዘመኑ ዞር ብሎ ያላየውን የትግራይ ወጣት በጥይት በሉት እያለ እንዲህ በጭካኔ ሲያዝ የሱን ምቾት እና የሙስና ውጤት የሆነውን ብሌን ህንፃን ለማስመለስ ስንት የትግራይ ወጣትን ያስጨፈጭፍ ይሆን ? የሚለው ብቻ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ወዲ አሸብር ማለት ደካማ እና የአመራር ብቃት የሌለው [ ከአንድ ሀገር ውስጥ ካለ የትምህርት ተቋም ቤቱ ድረስ የሄደለት የሊደርሺፕ ማስተርስን ሳንቆጥር] በብሄሩ ብቻ ከስሙ ፊት ክቡር የሆነው የብ/ጀ ማዕረግ የተቀመጠለት ግለሰብ ብቻ ሳይሆን ለጥቅም እና ምቾቱ ሲል አንድ አይደለም ድፍን የትግራይ ህዝብ እግሩን ቢበላ ደንታም የሌለው ስልጣን እና ሃብት አፍቃሪ ሰው ለመሆኑ ዛሬ ሳይሆን በተቋሙ ውስጥ በነበረበት ግዜ አብረነው የሰራነው ጠንቅቀን የምናውቀው እውነታ ነው፡፡



Axumezana
Senior Member
Posts: 13645
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የትግራይ፥ ጆኖሳይድ፥ መሃንዲስ፥ ዳንኤል፥ ክብረት የሚመራው፥ ማህበር፥ ምን፥ እያለን፥ ነው፤

Post by Axumezana » 05 Mar 2024, 16:12

Ascari boy,

ጀነራል፥ አሸብር፥ ቀበሩኩም፥ እዩ፤ አብ፥ ወርቂ፥ ዲሞ፤ ዋይ፥ ዋይ፤
ውቅኢቱ፥ ስለዘኸመኩም፥ እዩ፥ ዝኹሉ፥ብኽያት፤


Post Reply