Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30928
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የፊደል ታሪክ! HORUS'S GOLDEN ADVICE TO NAGA TUMA: WRITE YOUR LANGUAGE IN FIDEL

Post by Horus » 24 Mar 2024, 15:34

ናጋ ቱማ፣
እኔ የልቤን ልንገርህ? ካንተ ጋራ ፋይዳ ያለው ውይይት ማድረግ አይቻልም ። You have an issue. የቦረና ቋንቋ ምርምር ካማራኛ ወይም ግዕዝ ቋንቋ ጋር የሚደረግ ፉክክር አይደለም፤ መጀመሪያ ከዚህ ያይምሮ ቅርቃር ተገላገልና ነጻ ሆነህ የቦረና ቋንቋ ምንድን ነው? ከየት መጣ? እንዴት አደገ? ከሌልች ተዛማጅ ቋንቋዎች ጋር ምን ዝምድና አለው? እያልክ የቋንቋውን ስረ መሰረት፣ ፊሎሎጂ ወይም ፍትለት፣ የድምጾቹ አከታተፍና አፈታተል፣ የቋንቋውን ስዋስው፣ ፕራግማቲችስ ወይም አጠቃቀም ለመማር፣ ለማወቅ ሞክር ።

በአቋራጭ ምንም ነገር ማድረግ አትችልም ። ከዚያ በተረፈ ትላልቅ ቃላቶችን በዘፈቀድ ምን እንደ ሆኑ በውል ሳትመረምር አትጠቀም ። ለምሳሌ ፊደል ናቹራል ነው ስትል ምን ማለትነው? በድምጽና በቋንቋ መሃል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ እወቅ ። ድምጽ በራሱ ቋንቋ አይደለም ። በድምጽና በመግባባት መሃል ያለው ልዩነት እወቅ ። በተለይ እዚህ እያወራን ያለነው ስለ ፊደል፣ ስለ ጽሁፍ፣ ስለ ምልክት፣ ስለ ቴክኖሎጂ ስለሆነ ደግሜ ላሳስብህ አንድን ቋንቋ በአፍ፣ በቃል መናገርና በምስል በቴክኖሎጂ (ፊደል) መቅረጽ እንደ ሰማይና ምድር የተለያዩ ናቸው ።

እንዳንተ አባባል ቦረናዎች ፊደልን ሊቀርጹ ቀርቶ እስከ ዛሬም አፋን ኦሮሞ ያልተጻፈ ኦራል ወይም የቃፍ ቋንቋ እንጂ የጽሁፍ ቋንቋ አይደለም ። ሰው ሊታዘብ ስለሚችል you need to be conscious of what you are saying.

በአንድ ቃል በአፋን ኦሮሞ ውስጥ የግዕዝ፣ የሴምና የላቲን ቃላት ካሉ እነዚህ ቃላት እንዴት ገቡ ? መቼ? ለምን እያልክ (ሂስቶሪካል ሊጉዊስቲክስ) መመራመር ትችላለህ ። ያ ጥያቄና ፊደል ከየት መጣ፣ ከምን ጀመረ? እንዴት አሁን ያለውን ቅርጽ ያዘ የሚለው ሌላ እራሱን የቻለ ከቦረና ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ጥያቄ በስመ ነጋ ማሰብ አቁም ።

ሶስተኛ አፋን ኦሮሞ በግዕዝ ፊደል መጻፍ ይቻላል ወይ? አሁን ባለው ፊደል ሆሂያት ውስጥ ለማይገለጽ ኦሮሞ ድምጽ እንዴት ተጨማሪ ፊደል ወይም ምልክት መስራት ይቻላል የሚለው ሌላ እራሱን የቻለና ጥሩ ምርምር ሲሆን አንተ እዚያ ብታተኩር ቋንቋህን መርዳት ትችላልህ ።

ላም ባልዋለበት ኩበት አይለቀምም፣ እዚያ ከብቶች ስላልነበሩ ። ቦረና ፊደል ፈጥሮ ቢሆን ኖረ ዛሬ ቁቤ ጋ አንሄድም ነበር። ደሞ አፋን ኦሮሞ በግዕዝ ለመጻፍ ቦረና ግዕዝ ተናጋሪ ነው፣ ፊደልም የፈጠረው ቦረና ማለትን አይጠበቅበትም። ፊደል የመላ ኢትዮጵያ ሃብት ነው የኦርቶዶክስ ሊቃውንት ቢቀርጹትም! ኦርቶዶክስ ለኢትዮጵያ ያበረከተችው ትሩፋት ነው። ይህን ግዙፍ የስልጣኔ ትርፉት ፖሰቲቭሊ ተቀብለህ ሕዝብህና ካልቸርክን ማሳደግ እንጂ ካማራ ጋር የገጠማችሁት ፉክክር ጤነኛም ብልህነትም አይደለም ።

እስቲ ዛሬ የስነ ጽሁፉን ገበያና አለም ተመልከት! ኢትዮጵያ ውስጥ ማለት ነው። የአማርኛ ድርሰት ፍንዳታ ነው ያለው ! በየቀኑ እዚም እዛም የመጽሃፍ ምርቃት ነው። አማራኛ እና ግዕዝ በአለም ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ነው! ይህ የሆነው ኢትዮፕያ እንደ ቻይና የአለም ኃያል አገር ስለሆነች አይደልም ። ግዕዝና ፊደል ሃሳብን ለመግለጽ ኃያል ቋንቋዎች ስለሆኑ ነው ።

ለዛሬው ይብቃን

Naga Tuma
Member+
Posts: 5546
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የፊደል ታሪክ! HORUS'S GOLDEN ADVICE TO NAGA TUMA: WRITE YOUR LANGUAGE IN FIDEL

Post by Naga Tuma » 09 Apr 2024, 17:35

Horus wrote:
24 Mar 2024, 15:34
ናጋ ቱማ፣
እኔ የልቤን ልንገርህ? ካንተ ጋራ ፋይዳ ያለው ውይይት ማድረግ አይቻልም ። You have an issue. የቦረና ቋንቋ ምርምር ካማራኛ ወይም ግዕዝ ቋንቋ ጋር የሚደረግ ፉክክር አይደለም፤ መጀመሪያ ከዚህ ያይምሮ ቅርቃር ተገላገልና ነጻ ሆነህ የቦረና ቋንቋ ምንድን ነው? ከየት መጣ? እንዴት አደገ? ከሌልች ተዛማጅ ቋንቋዎች ጋር ምን ዝምድና አለው? እያልክ የቋንቋውን ስረ መሰረት፣ ፊሎሎጂ ወይም ፍትለት፣ የድምጾቹ አከታተፍና አፈታተል፣ የቋንቋውን ስዋስው፣ ፕራግማቲችስ ወይም አጠቃቀም ለመማር፣ ለማወቅ ሞክር ።

በአቋራጭ ምንም ነገር ማድረግ አትችልም ። ከዚያ በተረፈ ትላልቅ ቃላቶችን በዘፈቀድ ምን እንደ ሆኑ በውል ሳትመረምር አትጠቀም ። ለምሳሌ ፊደል ናቹራል ነው ስትል ምን ማለትነው? በድምጽና በቋንቋ መሃል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ እወቅ ። ድምጽ በራሱ ቋንቋ አይደለም ። በድምጽና በመግባባት መሃል ያለው ልዩነት እወቅ ። በተለይ እዚህ እያወራን ያለነው ስለ ፊደል፣ ስለ ጽሁፍ፣ ስለ ምልክት፣ ስለ ቴክኖሎጂ ስለሆነ ደግሜ ላሳስብህ አንድን ቋንቋ በአፍ፣ በቃል መናገርና በምስል በቴክኖሎጂ (ፊደል) መቅረጽ እንደ ሰማይና ምድር የተለያዩ ናቸው ።

እንዳንተ አባባል ቦረናዎች ፊደልን ሊቀርጹ ቀርቶ እስከ ዛሬም አፋን ኦሮሞ ያልተጻፈ ኦራል ወይም የቃፍ ቋንቋ እንጂ የጽሁፍ ቋንቋ አይደለም ። ሰው ሊታዘብ ስለሚችል you need to be conscious of what you are saying.

በአንድ ቃል በአፋን ኦሮሞ ውስጥ የግዕዝ፣ የሴምና የላቲን ቃላት ካሉ እነዚህ ቃላት እንዴት ገቡ ? መቼ? ለምን እያልክ (ሂስቶሪካል ሊጉዊስቲክስ) መመራመር ትችላለህ ። ያ ጥያቄና ፊደል ከየት መጣ፣ ከምን ጀመረ? እንዴት አሁን ያለውን ቅርጽ ያዘ የሚለው ሌላ እራሱን የቻለ ከቦረና ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ጥያቄ በስመ ነጋ ማሰብ አቁም ።

ሶስተኛ አፋን ኦሮሞ በግዕዝ ፊደል መጻፍ ይቻላል ወይ? አሁን ባለው ፊደል ሆሂያት ውስጥ ለማይገለጽ ኦሮሞ ድምጽ እንዴት ተጨማሪ ፊደል ወይም ምልክት መስራት ይቻላል የሚለው ሌላ እራሱን የቻለና ጥሩ ምርምር ሲሆን አንተ እዚያ ብታተኩር ቋንቋህን መርዳት ትችላልህ ።

ላም ባልዋለበት ኩበት አይለቀምም፣ እዚያ ከብቶች ስላልነበሩ ። ቦረና ፊደል ፈጥሮ ቢሆን ኖረ ዛሬ ቁቤ ጋ አንሄድም ነበር። ደሞ አፋን ኦሮሞ በግዕዝ ለመጻፍ ቦረና ግዕዝ ተናጋሪ ነው፣ ፊደልም የፈጠረው ቦረና ማለትን አይጠበቅበትም። ፊደል የመላ ኢትዮጵያ ሃብት ነው የኦርቶዶክስ ሊቃውንት ቢቀርጹትም! ኦርቶዶክስ ለኢትዮጵያ ያበረከተችው ትሩፋት ነው። ይህን ግዙፍ የስልጣኔ ትርፉት ፖሰቲቭሊ ተቀብለህ ሕዝብህና ካልቸርክን ማሳደግ እንጂ ካማራ ጋር የገጠማችሁት ፉክክር ጤነኛም ብልህነትም አይደለም ።

እስቲ ዛሬ የስነ ጽሁፉን ገበያና አለም ተመልከት! ኢትዮጵያ ውስጥ ማለት ነው። የአማርኛ ድርሰት ፍንዳታ ነው ያለው ! በየቀኑ እዚም እዛም የመጽሃፍ ምርቃት ነው። አማራኛ እና ግዕዝ በአለም ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ነው! ይህ የሆነው ኢትዮፕያ እንደ ቻይና የአለም ኃያል አገር ስለሆነች አይደልም ። ግዕዝና ፊደል ሃሳብን ለመግለጽ ኃያል ቋንቋዎች ስለሆኑ ነው ።

ለዛሬው ይብቃን
ሆረስ፥

ይህን ርዕስ ኣሁን ነዉ ተመልሼ ያነበብኩኝ።

ትገርማለህ።

የማታዉቀዉን ለማወቅ ትጋ እንጂ።

ፕሮፌሰር ዶናልድ ኤን ለቪን ተመራምሮ የጻፈዉን ኣንብበህ ኣልገባህም ወይስ ኣላነበብከዉም?

የሎሬት ፀጋዬን ሆሊ ግሬይል የምያስብል ቅርስ ኣልሰማህም ወይስ ሰምተህ ኣልገባህም?

የሃገር ሰዉ፣ ከኣማርኛ ተናጋሪ የበለጠ አማራ ለመሆን ኣትሞክር።

ገና የኣንተን ጽሑፍ ማንበብ እንደጀመርኩኝ ነዉ ሬይኔሳንስ ሰዉ ለመሆን አንኢኒሼይትድ ነዉ ያልኩኝ።

እስከዚህ ግዜ ከዛ ምንም ፎቀቅ ማለት ኣልቻልክም። የምትችል ነዉ ተብሎ ሲታሰብ ኣለመቻልህ ያሳዝናል።

መሠረታዊ ድክመትህ የምታነበዉን ኣዲስ ሀሳብ ወይም ጥያቄ በጥልቀት ሳትመራመር ኣይመስልም ብለህ ማለፍ ነዉ።

በደንብ ኣንብብ። ከአንገትህ በላይ ከምትሸከማት ዉስጥ ካለዉ ዕዉቀት በላይ ሰፊ ዕዉቀት ኣለ። ከቻልክ ቅሰም።

በጣም ቀላል ጥያቄዎችን በቀላሉ መልስ።

ሌላ በጣም ቀላል ጥያቄ። ሙሴ ሰነዓ ተራራ ላይ ሰማሁ ያለዉ፣ ኣንተ የምትለዉ መለኮታዊ፣ እና የቦረና ቃሉ በሚለዉ መካካል ምን ልዩነት ኣለ?

ቀላል ጥያቄ ነዉ። ኣይዴለም? ይህቺን ቀላል ጥያቄ መመለስ ካልቻልክ ምን ትባላለህ?

እኔ የቦረና ቋንቋ እና ባህል የምለዉ ከክርስትና በኋላ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ክርስትናን ሳይቀበል ባህሌ ብሎ የቀረዉን ነዉ። ክርስትና ሽዋ ዉስጥ ሲጀመር ባህሌን ብሎ ወደ ቦረና የተሰደደ አበይ ባቦ ከሸዋ ነዉ።

እንደገና ላስታዉስህ። እኔ ቦረናን መልሼ መላልሼ የማነሳዉ ክርስትናን ለተቀበሉት ኢትዮጵያዊያን እንደ ኮንትሮል ግሩፕ ነዉ።

ተዋህዶ ከዜሮ ኣልጀመረም። ባህል ላይ ነዉ የተመሠረተዉ።

ስለዚህ ሌላ በጣም ቀለል ጥያቄ። የተዋህዶ መሠረትን ከሁሉ በላይ ይዘዉ ያሉት የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች እነማን ናቸዉ?

ሌላ በጣም ቀለል ጥያቄ። ኣዳኙ ተነስቶ እንደ እነዛ ኢትዮጵያዊያን ያልኩኝን ኣሳየኝ ቢልህ የትኛዉ ነዉ ያንን ባህል ይዞ የሰነበተዉ ብለህ የምታሳየዉ?

Post Reply