Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Semma Adam
Member
Posts: 2
Joined: 01 Sep 2021, 20:01

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Semma Adam » 02 Feb 2024, 07:30

Brother Horus
Your Ethiopian Manifesto post IMHO in it's fundamental logic and highest Ideal and objective is of course laudable since basically stated it points Ethiopians to first of all establish Unity based on the greater Ethiopian Identity rather than their narrow identification with their tribal ethnicity.
I have no doubt that you are pin pointing to the ultimate basic solution for Ethiopia. Actually, your suggested Solution/ Agendas.. does not just apply to Ethiopia's current sad state of affairs of disunity and division among her ethnics but across the board is reflects the sad state of affairs that is inclusive of all humans and their problems who dwell on this planet earth.
That being said,...so.. what am here to share or add to your 'manifesto ?
Well..only this>> For this 'ideal Solution' to be implemented where Peace Justice Equality and Love could reign here on our planet ( not just in Ethiopia and among Ethiopians).it all comes down to the level of Consciousness under which humans will conduct their state of affairs called 'Living Life on Earth in the best way possible'.
So far humans have not been able to achieve this highest of all Consciousness, which is Unity Consciousness that they actually can implement the idea and Live it too.
The real root of the problem is then truly elsewhere:
We know that humans like all nature are under the forces of Evolution. Evolution of Consciousness is still ongoing. Thus Humans are not a finished product. The human brain is still evolving. While in evolutionary terms (time).. we humans did just receive our Neo-cortex, our old Reptilian
( animal/egoic/ selfish survival of 'me' motivated) brain is still with us and very much operative as is evidenced by the fact that we still have WARS and more Wars going on the planet. We humans have not reached the State of Peaceful co-existence among our fellow humans. We as a species have a very very long way to go to reach that lofty State of Unity Consciousness.
Yes Horus..you are absolutely right >> Unity Consciousness states that We are All ONE..All are equal ..and there is actually no substantial difference at all among the races of the world, the original Substance of their makeup being One and the very same and their outer demarcation (individuality) being highly superficial and temporal.
Call this underlying substance God if you like or Universal Field of Unity, the Ground of Being or Existence or whatever is your preferred term for it, perhaps based on your religious conviction/ experience, your education or even your own mind's fancy.

In conclusion..I think..the posters Axumezana and Misrak.. perhaps have a beneficial /similar point as mine to add to your overall suggestion for Ethiopia's / Ethiopians current chaos and state of affairs:
Unity in Diversity maybe the approachable ( doable?) goal for Ethiopians at the current level of Consciousness IMHO. With that in mind then..
There is no doubt in my mind..first things first... Ethiopia needs to get rid of the Apartheid TPLF installed current Constitution which accentuates Division rather than Unity among all ethnics in Ethiopia.
Despite the current chaos and darkness and disunity and PAIN..we Ethiopians are survivors being and ancient dwellers on the planet earth...we don't easily despair and vanish from the face of the earth...we [deleted] our wounds of evolution and keep going..because we have Faith ..we know there is always Light at the end of the dark tunnel. We will Prevail >>>Order out of Chaos as is the universal law.
Thank you Horus for writing this valuable manifesto. It's bright and righteous content actually matches your user name lol.
Horus is the name of the Egyptian Christ = Light!!
Yes,,,I agree with you also:
the visionary among Ethiopians (such as yourself)... should hold this Light Torch high..so that all those who are still in need of Light may find their way out of Darkness to Light.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 06 Feb 2024, 02:29

እነዚህ በአጭሩ ቁልጭ ብለው የተቀመጡ 4ቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፕሮግራሞች ናቸው ። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል የኢትዮጵያ አጀንዳ ምን እንደ ሆነ አንድ ሁለት ብሎ ማስቀመጥ የመጀመሪያ ሃላፊነቱ ነው ። ለምሳሌ አጀንዳ ቁጥር አንድን ተመልከቱ ።

አንድነት የፍጥረት ሁሉ የመጀምሪያ ሕግ ነው ። በዚህ አለም ላይ ያለ የሚኖር ክስተት ሁሉ አንድ ሆኖ ነው ህልው ህያው የሚሆነው ። አንድ ያልሆነ ነገር የማይሰራ ፣ የተሰበረ፣ የጎደለ ፋክሽን የማያደርግ ፉርሽ ፍርስ ነገር ነው ። ተቋም ሁሉ ፣ ቁመና ሁሉ ፣ ድርጅት ሁሉ፣ ስይስተም ሁሉ አንድነት ነው። አንድነት የሌለው አገር አገር አይደለም! አንድነት የሊለው ሕዝብ መንጋ እንጂ አገር አይሆንም ።

ብሄራዊ አንድነት ከሁሉም ቀዳሚው የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው ።

በአንጻሩ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያፈርሱ የኢትዮጵያ ተቀዳሚ ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው ።

ኢትዮጵያ በእውነተኛ ኢትዮጵያዊያን ከተደራጀችና ከተመራች ያላት ብሄራዊ አጀንዳ፣ ያላት ብሄራዊ ፋይዳና ፐርፐዝ በጣም ቀላልና ግልጽ ነው ። ልብ በል ይህ የማንም ጎሳ፣ ቡድን ኃያል ሆነ ደካማ፣ ትንሽ ሆነ ትልቅ ዘውግ ፍላጎትና ህልም አይደለም ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚሽን ማለት ነው ።

1
ኢትዮጵያ የምትባለው ሕዝብና አገር ብሄራዊ አንድነቷ የጸና፣ ጠንካራና የተረጋጋች (እስቴብል) አገር መሆን አለባት፣ መሆን ነው አላማዋ ። ይህ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ቁጥር አንድ ነው ። ከዚህ አጀንዳ ውጭ የሚያስብ ሁሉ ኢትዮጵያዊ አይደለም፣ እራሱን በፈለገው ስምና ቅጽል ቢጠራ ።

2
ኢትዮጵያዊ የተባለው ሕዝብ እንደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ (Political Community) ፍትህ (እኩልነት)፣ ነጻነት እና ዴሞክራሲ መፈለግ ብቻ አይደለም፤ ያለ ፍትህ፣ ነጻነትና ዴሞክራሲ መኖር አይችልም። ሰላም የሚባል ነገር እስከ አለም ፍጻሜ አያገኝም። ስልጣኔም ሆነ እድገት የሚባል ነገር አይኖሩትም ። ስለዚህ 2ኛው የኢትዮጵያ ፋይዳ፣ የኢትዮጵያ አላማ፣ የኢትዮጵያ ፐርፐዝ ዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነትን መወለድና ማሳደግ፣ ማለትም ነጻና ፍትሃዊ ሕዝብ መሆን ነው ። ይህን የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ያልገባቸው ወይም የማይቀበሉ ጸረ ኢትዮጵያ ስብስቦች ናቸው የዚህ ሁሉ መከራና ድቀትት ምክንያቶች ።

3
3ኛው የኢትዮጵያ አጀንዳ ኢትዮጵያዊያን የሚባሉት ሕዝብን፣ ዜጋዎችን የበለጸጉ፣ ያደጉ፣ የለሙ፣ የተማሩ እና ጤንነታቸው የተጠበቀ ሕዝብ፣ ዚጋ ማድረግ ነው 3ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳና ፋይዳ ። ኢትዮጵያ እንደ አንድ አገር፣ እንደ አንድ ሕዝብ፣ እንደ አንድ ማህበር፣ እንደ አንድ ሲስተም አላማ፣ ፋይዳ አላት ። ይህን ፋይዳ ለመተግበር ነው ህያው ሆነ ምትቀጥለው ። የኢትዮጵያ አጀንዳን አንድ ሁለት ብለው መቁጠር የማይችሉ መሃይም የጎሳ ጥርቃሞዎች ናቸው የዚህ ሁሉ ሰቆቃ ምክንያቶች ።

4
በመጨረሻም 4ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ የሚፈጥር፣ ችግር የሚፈታ፣ የሚራመድ፣ ከከባቢውና ኢኮሎጂው ጋር የታረቀ፣ አፈሩን። ዉሃውን፣ እንሳሳውን፣ እጸዋቱን፣ አየሩን በሃላፊነት የሚንከባከብ ፣ መንፈሳዊ ፣ በፈጣሪ ኃይል የሚያምን በሞራልና ስነ ምግባር ምርሆዎች የተለጎመ ካልቸር መፍጠር፣ መገንባት እና መጠበቅ ነው የመጨረሻው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር ምንድን ነው? ምን መሆን አለበት ብለው መጠየቅ የማይችሉ ቀድሞ ነገር እራሳቸው ካልቸር አልባ የሆኑ ከብቶች ናችው በዚህ ታላቅ ሕዝብና ታላቅ አገር ጫንቃ ላይ ተቀምጠው ያለም ማፈሪያ የሆኑት ። የኢትዮጵያ መፍትሄ ይህ ብቻ ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 06 Feb 2024, 13:49

ይህን ማኒፌስቶ ያወጅኩት ለማንም አይደለም፣ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው ።

አጀንዳ ቁጥር 2፤

ኢትዮጵያዊ የተባለው ሕዝብ እንደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ (Political Community) ፍትህ (እኩልነት)፣ ነጻነት እና ዴሞክራሲ መፈለግ ብቻ አይደለም፤ ያለ ፍትህ፣ ነጻነትና ዴሞክራሲ መኖር አይችልም። ሰላም የሚባል ነገር እስከ አለም ፍጻሜ አያገኝም። ስልጣኔም ሆነ እድገት የሚባል ነገር አይኖሩትም ። ስለዚህ 2ኛው የኢትዮጵያ ፋይዳ፣ የኢትዮጵያ አላማ፣ የኢትዮጵያ ፐርፐዝ ዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነትን መወለድና ማሳደግ፣ ማለትም ነጻና ፍትሃዊ ሕዝብ መሆን ነው ። ይህን የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ያልገባቸው ወይም የማይቀበሉ ጸረ ኢትዮጵያ ስብስቦች ናቸው የዚህ ሁሉ መከራና ድቀትት ምክንያቶች ።

ዛሬ ላይ ትግሬ እስከ አፍንጫው ታጥቋል፤ አማራ እስካፍንጫው ታጥቋል፤ መንግስት እስካፍንጫው ታጥቋል፤ ኦሮሞ እስካፍንጨው ታጥቋል ። ሌሎችም እንዲሁ እንዳቅማችደውና የህዝብ ቁጥራቸው ።

ነገር ግን እነዚህ ከ5 እስከ 10 የሚደርሱ ኃይሎች አንዳቸውም የኢትዮጵያ አጀንዳ፣ የኢትዮጵያ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ራዕይ የላቸውም። ልብ በሉ ኢትዮጵያን ከዳር እስከ ዳር ያጣበቡት የመንግስት፣ የድርጅትና የግል ሚዲያዎች አንዳቸውም አንድም ግዜ የኢትዮጵያ መፍትሄ ምን እንደ ሆነና ምን እንደ ሚመስል ለሕዝብ ማቅረብ አልቻሉም ።

ስለሆነም በመፍረስ ላይ ካለው ብልጽግና ጀምሮ የፖልቲካ ፓርቲ ነኝ ብለው ሱፍ እስከ ለበሱት አንዳቸውም የየራሳቸው ጠባብና ፋይዳ ቢስ ጥቅም ዝርዝር ያለፈ የኢትዮጵያ አላማ ምን እንደ ሆነ ማቅረብ አልቻሉም ።

በአንድ ቃል በኢትዮጵያ ምድር የወታደራዊ ትርምስ እንጂ ፖለቲካ የለም፣ ፖለቲካ ሞቶዋል፣ ፖለቲካ ምን ማለት እንደ ሆነ ተረስቷል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 07 Feb 2024, 01:11

አገር ማለት ዝም ብሎ በስመ ነጋ እንደ መንጋ የተከማችሁ ሕዝቦች የሚኖሩበት ምድር አይደለም። አገርም ፣ መንግስትም ሲስተሞች ናቸው፤ ድርጅቶች ናቸው ። በዚህ በያዝነው የስልጣኔ ዘመን አንድ የነቃ ግለሰብ፣ አንድ በውል የተመራ ቤተሰብ፣ አንድ ማህበር፣ አንድ ድርጅት፣ የንግድ ተቋም፣ መንግስት እና አገር ተመሳሳይ ናቸው ። ተመሳሳይ የሚያደርጋቸው የተፈጠሩለት አላማ፣ ፐርፐዝ ፣ ተግባር ነው። የሕይወት አላማ የሌለው ግለሰብ የጠፋ በግ ነው ። ፐርፐዝ የሌለው አንድ ቤተሰብ ከዱር እንሰሶች ቤተሰብ አይለይም ። አገርም ልክ እንደዚያ ነው ። አገር አላማ አላት፤ ኢትዮጵያ እንደ አንዲት አገር፣ እንደ አንዲት የዜጋዎች ድርጅት ፐርፐዝ አላት፣ አላማ አላት፣ ፋይዳ አላት ።

ሌላው ቀርቶ አንድን ቤተሰብ፣ ድርጅት ወይም አገር አንድ የሚያደርገው፣ በአንድነት አስሮ የሚይዘው ይህ የድርጅት ወይም ያገር አላማ ነው ።

ከላይ ስጀምር ከጠቀስኳቸው 4 የኢትዮጵያ አጀንዳዎች አንዱ ይህ ነው ።

"3ኛው የኢትዮጵያ አጀንዳ ኢትዮጵያዊያን የሚባሉት ሕዝብን፣ ዜጋዎችን የበለጸጉ፣ ያደጉ፣ የለሙ፣ የተማሩ እና ጤንነታቸው የተጠበቀ ሕዝብ፣ ዚጋ ማድረግ ነው 3ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳና ፋይዳ ። ኢትዮጵያ እንደ አንድ አገር፣ እንደ አንድ ሕዝብ፣ እንደ አንድ ማህበር፣ እንደ አንድ ሲስተም አላማ፣ ፋይዳ አላት ። ይህን ፋይዳ ለመተግበር ነው ህያው ሆነ ምትቀጥለው ። የኢትዮጵያ አጀንዳን አንድ ሁለት ብለው መቁጠር የማይችሉ መሃይም የጎሳ ጥርቃሞዎች ናቸው የዚህ ሁሉ ሰቆቃ ምክንያቶች ።'

ለምሳሌ የአለም ግለሰቦች ወደ አሜሪካ የሚጎርፉት አሜሪካኖች የነሱ ዘር፣ ጎሳ ወይም ብሄር ስለሆኑ አይደለም ። አሜሪካ እጅግ ገናና እንደ አለት የጸና አላማ ፣ ፐርፐዝ ያላት አገር ስለሆነች ነው ። አሜሪካ በየእለቱ ከምታራምዳቸው አላማዎች፣ አጀጅንዳዎች ዋነኛው የግለሰቦችን፣ የዜጋዎችን እድገት፣ ብልጽግና ፣ ትምህርት እና ጤንነት ያለ ማቋረጥ ስለምታሟላ ነው ።

አገር ማለት ሕዝብ ማለት ነው ። ሕዝብ ማለት ግለሰብ ማለት ነው ። ያገር ብልጽግና ማለት የግለሰቦች መበልጸግ፣ ሃብት ማፍራት ማለት ነው። ያልተማረ አገር በዚህ ዘመን አገር ሊባል አይችላም ። የተማረ አገር ማለት የተማሩ ግለሰቦች ማለት ነው። ግላሰብቹን የማያስተምር አገር የደንቆሮዎች በረት ነው ።

ያልተማረ ሰው፣ ያልተማረ ሕዝብ ጤንነቱን መጠበቅ አይችልም፣ አያውቅበትም ። ስለዚህ የተማረ ሕዝብ ማለት ጤናማ ሰዎች የሚንሩበት አገር ማለት ነው ።

ይህ ብቻ አይደለል። በቁጥር 2 የተቀመጠው የዲሞክራሲ፣ ነጻነትና ፍትህ አላማ ሊሳካ የሚችለው በተማሩ ሰዎች ውስጥ ነው ። ያልተማረ ሕዝብ ዴሞክራሲን መተግበር አይችልም፣ ለነጻነቱ አይታገልም፣ ነጻነቱን አያስከብርም፤ ለፍትሃና እኩልነት አይቆምም።

ይህን 3ኛ አጀንዳ ማለትም የሕዝብ ባለጸጋነት፣ ትምህርት (እውቀት) እና ጤንነት እውን ማድረግ አንዱ ታላቁ የኢትዮጵያ ፋይዳ ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 07 Feb 2024, 15:01

አጀንዳ ቁጥር 4

የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

(ይህ ሃተታ በ9/2/1995 ለER መጽሄት ልልከው ከጻፍኩት በኋላ ተረስቶ ዛሬ እንዳጋጣሚ ሳነበው አሁንም ያለውን ሁኔታ ስለሚያሳይ ምንም ሳልቀይር እነሆ ከ29 አመታት በኋላ። ሃተታው ረጅም ስለሆነ ለመደምደምያው ታገሱ)

የጽሁፉ መቋጫ ፤ የቀድሞ ኢትዮጵያም የቀድሞ ጎሳዎችም ወደ ዘመናዊነት በሚደረገው አድካሚ ጉዞ ይለወጣሉ፤ አሁን የምናየው ሁሉ ግዜያዊ ነው። በዚህ የሽግግር ውጥንቅጥ መሪና አሸናፊዎቹ እጅግ አዲስና ያልታየ መፍትሄ ማመንጨት የሚችሉት ፈላስፎች፣ ነዳፊዎች፣ ሃሳቢዎችና የኪነት ፈጣሪዎች ናቸው ።
ኢትዮጵያ መሰረታዊ የውድመትና የድቀት አደጋ አለባት እላለሁ ። ይህን ስል ምን ማለቴ ነው?

አንደኛ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአካል አይወድሙም፤ አይጠፉም። እንዲያውም በሚቀጥሉት ሰላሳ አምስት አመታት ወስጥ የሕዝባችን ቁጥር ከ55 ሚሊዮን ወደ 140 ሚሊዮን ያድጋል። የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ ስርዓታት ተሽካሚዎችና አንቀሳቃሾች ይህ ሕዝብ ነው። ሆኖም አሁን ካለው ሕዝብ የተወሰኑት በሽግግሩ ወቅት ይጠፋሉ። ሽግግር ስል ግዙፉን ወደ ዘመናዊነት የሚደረገው አስቸጋሪና ዝብርቅርቅ ሽግግር ማለቴ ነው ። በሽሽግሩ የሚወድሙት ግን ከፊሉ ብቻ ናቸው።

በኢትዮጵያ ካሉት ብዙ ጎሳዎች አኳያ ወደ ዘመናዊነት በሚደረገው ሽግግር ወቅት የሚወድሙት ማህበረ ሰቦች የተኞቹ ናቸው? ከወድመት የሚድኑት ከመጥፋት የሚተርፉት በምን በምን ምክንያቶች ነው? በመሰረለቱ ከውድመት የሚድኑት ሕዝብ ሆኑ ጎሳዎች አሁን ከሚያምኑበት የጥፋትና የቀውስ ባህል እየከዱ ወደ አዲስ አስተሳሰብና ባህል የሚዞሩት ናችው። ይህን መሰል እውቀትና ችሎታ የሌላቸው ግለሰቦች፣ ጎሳዎችና ቡድኖች ወዳሚዎች ናቸው። ስለዚህ የዘመኑ ቀውስና ብሶት የሚጠይቀውን ለውጥ ለማድረግ ችሎታ ያላቸው ክፍሎች ግዙፉን ሽግግር ያልፋሉ፤ ያልቻሉት ይወድማሉ። አሁን ያለው ሞራሉ የላሸቀው ሰው አዲስ ነገር አይፈጥርም።

ሁለተኛ፣ ስለ ኢትዮጵያ ወድመት በሚጠቀስበት ወቅት ሌላው ግልጽ ነገር ኢትዮጵያዊያን እስከ ዛሬ የፈጠሯቸው ቁሳዊ ባህላት፣ ቁሳዊ ግንባታዎች ሁሉ አይደመሰሱም። የፈጠሩት ሳይንስ ሆነ ቴክኒክ ሁሉ አይወድምም። ሆኖም ከቁሳዊ ባህላችን፣ ከልማት ውጤቶች ከፊሉ በሽግግሩ ጦርነት፣ አብዮት፣ አናርኪና ሁከት ይወድማሉ። ከውድመት የሚድኑት ቁሳዊ (ለምሳሌ ቤቶች፣ መንገዶች፣ መኪናዎች) ከእሴታዊ ምንነት ጋር ብዙም የተቋለፉ አይደሉም። ለምሳሌ ለዘውድ አገዛዝ የታነጸው ቤተ መንግስት ለኮሚኒስት ፓርቲና ለወያኔ መሰብሰቢያ ያገለግላል። ፈንጂ ለጥፋትም ለማእድንም ያገለግላል። ስለዚህ ቀደም ሲል ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ የተፈጠሩት ቁሳዊ ባህላት ሆነ ተቋማት አሁን ለጎሳ ስርዓት ግንባታ መገልገያ ተደርገዋል።

ምንነትና እሴት እና የነሱ ተሸካሚ የሆነው ቁሳዊ መሳሪያ ያላቸው አንድነት እጅግ የላላ ነው። ቴሌቪዝን ሃይማኖትም ሌብነትም የሰበክበታል። እነዚህ ቁሳዊ መሳሪያዎች የአዲሱ ስርወ እሴት አገልጋይ ይሆናሉ።

ሶስተኛ፣ ከዚህ ቀደም በፌውዳሉ ስርዓት ስር ተዋቅሮ የነበረው የነበረው የመላ ኢትዮጵያ ስርወ እሴት መዝቀጥና መፍረስ የሁሉም ባህልና ማህበራዊነት መፍረስ ወይም መበታተን አይደለም። ቀድሞ ያልተዋሃደ ነገር ሊበተን አይችልም። ስለዚህ የዘመኑ የጎሳ ስርወ እሴት ድሮ የነበረውን የጎሳዎች ልዩነት አጽድቋል፣ አጠናክሯል፤ እስከ ተወሰነ ድረስ እያደጉ የነበሩ የመላ ኢትዮጵያ እሴቶችን ሰባብሯል። ሆኖም ተጽዕኖው የተወሰነ እንጂ ጠቅላላ መበታተንና ዝቅጠት ሊሆን አይችልም። ጠበብ ብሎ በሴምና ባማራው ዙሪያ ያደገው ባህል ስሜታዊ ሆነ ሳይንሳዊ እስከ ተወሰነ ድረስ ተለውጦ ስፋት እያገኘ ነው። ግን ይህ ምን አይነት ባህል ነው?

አራተኛ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እሴትና ምንነት ወይም ማንነት በጎሳ እሴትና ማንነት እየተተካ ሲሄድ ወይም መሄድ ማህበረሰባዊና ባህላዊ ፈጠራን ማለትም ስልጣኔን ቀጥ አቁሟል፤ ያቆማልም። የተፈጥሮ ስይንቲስቶች እና ቁሳዊ ፈጣሪዎች የሚሰሩለት አገራዊ ፋይዳ ሆነ ትርጉም ከጠፋ ወዲህ ስራ አቁመዋል። በመንቀሳቀስ ላይ ያለው የጎሳ ባህል፣ ተረት፣ ታሪክና አፈታሪክ የሚቆፍረው ጠባቡ የሶሻል ሳይንስ ምሁር ብቻ ነው። በአንጻሩም ለኢትዮጵያዊነት የሚሟገተው የሶሻል ሳይንስ ምሁር ፖለቲካዊና ታሪካዊ ክርክር ያደርጋል። ክዚህ ውጭ የጎሳ ሳይንስ ወይም ቴክኖሎጂ የሚባል ነገር ስለሌለ ሳይንሳዊ ፈጠራ ከእሴትና ምንነት እጦት የተነሳ ወድቋል። ይህ መቼም ትልቁ ቀውስ ነው። ይህም ሆኖ በተፈጥሮ ሳይንስ ዙሪያ እያቆጠቆጠ የነበረው ምሁር ሲበተን ጠንካራ ብሄራዊ ምሁራን በሃይማኖት፣ በፍልስፍና በስነ ፖለቲካ ዙሪያ ተነስተው ብሄራዊ ፈጠራ ሊያደርጉ አልቻሉም።

ይህ ሁለገብ ዝቅጠት እጅግ አሳሳቢው ቀውስ ነው። በኢትዮጵያ ወስጥ ለብዙ ግዜ ብሄራዊ ሳይንሳዊ የፈጠራ እንቅስቃሴ ሊኖር አይችልም፤ አገራዊ እሴትና አለኝታ ጠፍቷልና። በማህበራዊ ፍልስፍና መስክም ተመሳሳይ ቀጥ የማለት አደጋ አለ ። በአጠቃላይ አገራዊ የሆኑት የፍልስፍና መሰረቶች ማለትም የግለሰቡ ሰብአዊነት፣ እና መደባዊ ህብርዊነት በዘር ጽንስ ስለተሻሩ ጎሳ በተሰኘው የቡድን ጽንስ ዙሪያ አንድም የረባ ፍልስፍና ሊነሳ አይችልም ። የጎሳ ጽንስ ቅድመ ፍልስፍና ስለሆነ፣ ቅድመ ሰብአዊነት ስለሆነ። ስለሆነም ሶሺያ ፊሎሶፊም ከፍተኛ ዝቅጠት ወስጥ ይግኛል። ሌላው ቀርቶ መንፈሳዊ ፍልስፍና እንኳን ሊያቆጠቁጥ አልቻለም።

አምስተኛ፣ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሳይንስ ቀውስ አለ። የጎሳ ጽንሰ ሃሳብም ሆነ የጎሳ እንቅስቃሴ ማህበራዊ ወይም ሶሺያል ሳይንስ የለውም። ይህ አዲስ ተብዬ ፖለቲካም በጭለማ ውስጥ የሚደረግ ሙከራ ነው። ጠባብ የፖለቲካ መሃንዲሶች የሚያጨማልቁት ሙከራ ነው። ብሄራዊ ሶሺያል ሳይንሱ ስረው መሰረቱን በደንብ ለውጦና ግልጽ አድርጎ የፈጠራ ንቅናቄ ማድረግ ተስኖት ቆሟል። የሶሺያ ሳይንስ ቀውሱ የጀመረው በሃይለ ስላሴ ዘመን ነበር። የዘውድ አገዛዝን ዘመናዊ ለማድረግና ለምዕራብ ተቀባይነት ለመስጠት ሲሞከር የተፈጠረ ውዥንብር ነበር። ስለዚህ በዘውድ አስተሳሰብና በሊብራል ዴሞክራሲ መካከል የተነሳው ቀውስና ውዥንብር እልባት ሳያገኝ የአብዮቱ ዘመን መጥቶ ሁለቱም (የመለኮታዊም ሆነ የሕዝባዊ ሃይል አስተሳሰብ) ከመድረክ አስወገዳቸው።

ሶሺያሊዝም እየተባለ ይታወቅ የነበረው የተሳሳተ ወታደራዊ አገዛዝ በአንድ ቃል የፖለቲካ ሃተታ ወይም ትንተና ከህብረተሰቡ እንዲጠፋ አደረገ። ወታደራዊ የቡድን አገዛዝ ከሶሻሊዝም ጋር እንደ ተምታታ ሁሉ ዛሬ ደግሞ የጎሳ አስተሳሰብና ርዕዮት ከዴሞክራሲ ጋር እየተምታታ ቀርቧል። ስለሆነም በጎሳ አስተሳሰብ መግነን ሳቢያ አዲሱ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ትልቅ ቀውስ እንዲወድቅ ተደርጓል። ዘመናዊ ዴሞክራሲና ጎሰኝነት እስካልተለያዩና ዴሞክራሲ ከጎሰኘነት እስካልጸዳ ድረስ በኢትዮጵያ የሶሺያል ሳይንስ ቀውስ አያበቃም።

ሌላው ትልቁ የኢትዮጵያ ቀውስ የስነ ጥበብ ውድቀት ነው። እነሱም ስዕል፣ ጠረባ፣ ሙዚቃ፣ ስነጽሁፍ፣ ውዝዋዜ፣ ቲያትር፣ ሲኒማ፣ ዚቅ፣ አርኪቴክቸር ወዘተ ። ቀደም ሲል የነበሩት ጠቢባን እያለቁ ነው። አዲስ የሚፈጠሩት አብዛኞቹ ዋጋ ቢስ ናቸው፤ ጥልቀትና ንቃት የላቸውም። ብሄራዊ ራዕይና ስረው እሴት ላይ የተመሰረተ ፈጠራ ሳይሆን ከዚህም ከዚያ የተለቃቀመ፣ ከምዕራብ የተገለበተ የተቀዳ ስራ ነው ።

የቀረው ከጎሳዎች ግላዊ ባህል፣ ሙዚቃ ወዘተ ጋር የተያያዘ ነው ። የኪነትና የስነት መስክ በውራጅ ፈጠራ ተጥለቅልቋል ። እዚህ ላይ ተደጋግሞ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ኪነትና የኢትዮጵያ ስነ ጥበብ የሚባል ነገር አለ ወይ የሚለው ነው? ወይስ የ90 ብሄረ ሰቦች ስብስብ ጥርቅም ስነ ጥበብ? ይህ ያልተመለሰውና አወዛጋቢው ጥያቄ ነው።
ሌላው ትልቁ የኢትዮጵያ ቀውስ ሕግና ስነምግባር (ኤቲክስ) የተመለከተ ነው። በአንደኛ ደረጃ ዘመናዊ ወይም በተዋሃደ መልኩ የኢትዮጵያን ሕግና ስነምግባር የምንላቸው በምዕራቡ ግፊት የገባው እጅግ አለማዊና አምባገነን ባህል ሳቢያ ለብዙ አመታት የተከሰተ ኢሕጋዊነት ወይም የሕገወጥነት ክስተት አለ። ይህ የሕገወጥነትና የስነ ምግባር (ሞራል) ብልሹነት በአገሪቱ ለዴሞክራሲ አለመኖር ብቻ ሳይሆን በታሪክ ውስጥ በብሄረሰቦች መካከል የነበረውን ግንኙነት የመነጨም ነው። በተለይ ስነምግባር በተመለከተ የ90ቹ ጎሳዎች ግላዊ ኤቲክስ አለመዋሃዱና አንድ ብሄራዊ የኢትዮጵያ ስነምግባር አለመፈጠሩን ያመለክታል።

በዚህ መስክ ያለው ቀውስ እጅግ አሳሳቢ የሚሆነው የተለያዩ የብሄረ ሰብ ሴራዎችና ስነምግባራት መኖራቸው ብቻ አይደለም። የሕግ አለመከበር፣ የሃይል መግነን፣ በስልጣን መባለግና ፍርደገምድልነት፣ እኔባይነት ሌሎችን ማፈን በሃይል ሌሎችህን ማንበርከክ የዛሬን ጥቅም ባይነት ብቻ (ሄደኒዝም) እና አፍራሽነት የደምሳሽነት አመለካከት (ኒሂሊዝም) የመሳሰሉት የሁሉንም ብሄረሰብ አኗኗር ስለሚያቃውሱ አደገኛነታቸው ህብረባህል ከመሆን የባሰ ነው።

ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ቀውሶችን እናስተውላለን። አንደኛው የመላ ኢትዮጵያ አንድ ወጥ ስርዓት፣ እሴት፣ ባህል፣ ለማስተባበር ለማዋሃድ የሚሞክረው አዝማሚያ ነው። ይህ አዝማሚያ የተበተነና አቅጣጫ የለሽ መሆኑ ነው። ሁለትኛው የእያንዳንዱ ጎሳ እሴትና ባህል ቁንጽል ብቸኛ መሆንና በሌሎች ተቀባይነትን ማጣት እንዲሁም በዘመናዊነት መመታቱ ነው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ እሴት የላትም፤ ያለውም በምዕራብ ዘመናዊነት ተቃውሷል። የጎሳው እሴት አንዱም ለብሄራዊነት ብቃት ማጣቱ ብቻ ሳይሆን እሱም በዘመናዊነት ተቃውሷል። በሶስተኛ ድረጃ በኢትዮጵያ እሴትና (ካለ ማለት ነው) በጎሳው እሴት መሃል ያልተቋለጠ ግጭት ይካሄዳል። እነዚህ ሶስት ክስተቶች ሕግን፣ ስነምግባርን፣ ዴሞክራሲን፣ አስተዳደርን፣ አደረጃጀትን፣ ወዘተ ሁሉ ያካልላሉ። ለዚህ ደግሞ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ የለንም።

በሌላ ደረጃ እየተከሰተ ያለ መሰረታዊ ችግር አለ። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ ብሔራዊ እሴትና ባህል አለመፍጠሯ፣ በ90 ብሄረሰብ ባህሎችና በብዙ ሃይማኖቶች መከፋፈሏ ብቻ ሳይበቃ በተለይ ከምዕራቡ ዘመናዊነት ጋር የተቃመሱት የጎሳ ባህላትም የስሜታዊነት ጥራዝነጠቅነት ብልሽት ደርሶባቸዋል። ያጭር ግዜ ድል፣ ደስታ፣ ተንኮልና አፍራሽነት በሁሉም ባህላት ዘንድ እሴቶች ሆነዋል። ስለዚህ ስርወ እሴት ያጣው የኢትዮጵያዊነት ባህል (ካልቸር) ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ጎሳም ተመሳሳይ ቀውስ አጋጥሞታል። ከዚህ ሁለገብ የሆነ ቀውስ ለመውጣት ሰዎች ግዙፍ የሆኑ የእምነት፣ የአንድነት፣ የትብብር፣ የፍቅር እሴቶችን ከመሻት ይልቅ በግላዊና ቡድናዊ የታሪክና የህላዌ ምርምር ወይም ቁፋሮ ላይ ስለተጠመዱ እጅግ ቅጥ ያጣ የአመለካከት ጥበትና ውዥንብር በህብረተሰቡ ሰፍኗል። ስለሆነም ኢትዮጵያ የረዥም ግዜና መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችላት ብሩህ አመለካከት፣ ብሩህ ራዕይ የላትም፤ በምሁሮችዋ ማለት ነው።

ስለዚህ ግዙፉ የኢትዮጵያ ሽግግር ከየት ወዴት የሚሄድ ሽግግር ነው? የሚለው በፍጹም ግልጽ አይደለም። ከአንድነት ወደ መበተን ወይስ ከመበተን ወደ አንድነት? ወደ አለማዊነት ወይስ ወደ መንፈሳዊነት? ከእምነት ወደ ሳይንስ ወይስ ከሳይንስ ወደ እምነት? ከጎሳዊነት ወደ ዜግነት ወይስ ወደ ባሰ ዘረኝነት? ከኢሰባዊነት ወደ ሰባዊነት ወይስ ሌላ?

ይህን ግዙፍ ሽግግር ለምፍጠር በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፊሎሶፊ፣ በሶሺያል ሳይንስ በተለይ በፕለቲካ ሳይንስ፣ በስነ ጥበብ፣ በሕግና ስነምግባር መስኮች ሊመሩ የሚችሉ የሃይማኖት፣ የሳይንስ፣ የስነት፣ የስነ ህብረተሰብ መሪዎች ኢትዮጵያ የሏትም። መፈጠር ያለበትና ሊፈጠር የሚታሰበው እምነትና ንድፈ ሃሳብ መብላላት አልጀመረም፤ ሲብላላ አይታይም።

ከላይ የቀረበው ሃተታ የሚያመለክተው ጉዳይ ቀደም ሲል በትንሹም ቢሆን በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትና በአማርኛ ቋንቋ ዙሪያ ተገንብቶ የነበረው የባህልና እሴት መለኪያ (ደረጃው) እጅግ መዝቀጡን ነው። የብሄረሰቦች ፉክክር ከሰፈነ ወዲህ አገሪቱ ባህላዊና እሴታዊ ህብረተሰብ መሆኗ ጠፍቶ የምዕራብና የምስራቅ ሸቀጣ ሸቀጣዊ ባህል በገፍ የሚራገፍባት ገበያ ሆናለች። በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እንጂ አገር መሪዎች የሉም። የዜጋዎች ደህንነት ባገር አቀፍ ድህነት ማለትም የእምነት ድህነት፣ የፍልስፍና ድህነት፣ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና የፈጠራ ድህነት፣ የሶሻልና ፖለተካ ሳይንስ ድህነት፣ ተዉጧል። በስነ ጥበብ ማለትም በስዕል፣ ጠረባ፣ ሙዚቃ፣ ስነጽሁፍ፣ ቲያትር፣ ውዝዋዜ፣ ስነሲኒማ፣ ስነፎቶ ሁሉ ድህነት፤ በሕግና ስነምግባር ድህነት ጭምር የታጠረ ሁኖዋል። ህብረተሰቡ በጥቂት ያልተማሩ ሃብታሞችና በብዙሃን ያልተማሩ ድሆች ተከፋፍሏል። ከላይ የተዘረዘሩትን መስኮች ሊፈጥር የሚችለው ምሁር ወይም ተሰዷል፣ አለያም ፈጽሞ የለም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን በአይምሮዋቸው የሚሰሩ ሕዝቦች ሳይሆኑ መደባዊ ክፍፍሉ በሚበሉና በሚራቡ ሰዋዊ እንስሶች መካከል ነው። ይህ ሰቆቃ (ትራጀዲ) እንጂ ሽግግር አይደለም።

ከዚህ መቀመቅ እንዴት እንደሚውጣ የሚያሳይ ብርሃን አለን? ለኢትዮጵያ ወድቀትና ወድመት ምክንያት አገሩ ቀውስ መሆኑ ብቻ ኣይደለም። ከፍተኛ ያስተሳሰብና የመመራመር ድርቀት አለ። ከፍተኛ የፈጠራ አልባነት ጭለማ ሰፍኗል። ትልቁ ችግር የድንቁርና መስፈን ነው። በዚህ ጭለማ ወስጥ ከምዕራብ በሚመጣ ውራጅ ሸቀጥና ባህል አንድም ፋይዳ ለመፈየድ አይቻልም።

ስለሆነም አዲስ ቅድመ መርህ (አዲስ ፓራዳይም) አዲስ መርሃ እሴት (ቫልዩ ፕሪንሲፕል) መፈልሰፍ አለበት ። ይህን መሰል የሃሳብና የፈጠራ ብርሃን በኢትዮጵያ ምሁራን ሁሉ ይሞከራል ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ነው። የጎሳ ፖለቲካ የምሁራንን አንድነት አፍርሷል። ተያይዞም ብሄራዊ (አገራዊ) የሃሳብ አንድነት ፈርሷል። በመሆኑም ሙሉ ባህል ወይም አሞሌ ካልቸር፣ የኢትዮጵያ ምልአተ ባህል ሊፈጥሩ አይችሉም፤ እንዳይፈጠር አድርገዋል። የኢትዮጵያ እጅግ መሰረታዊና ወሳኝ ቀውስ (ችግር) መከፋፈል፣ መበታተን ነው። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ብትንና የቅውስ (ኬዎስ) ስርዓት ነው። ከሃይማኖት እስከ ተራ ሕይወት ሁሉም ብትን ስርዓት ነው።

ኢትዮጵያ ብትን ስርዓት እስከ ሆነች ድረስ ምልአተ ባህል፣ እሴተ ተዋህዶ ያለው ብሄራዊ ሴራ መፍጠር አለመቻል ብቻ ሳይሆን የተበታተኑት ክፍሎች እርስበርሳቸው ይጋጫሉ፣ ይጣላሉ፣ ይወድማሉ። ከላይ የተዘረዘሩት የባልና የፈጠራ መስኮች የሚንቀሳቀሱት በሰዎች፣ በቡድኖች፣ በሕዝብ ነው። እነዚህ የባህል ተሸካሚዎች እስከተበጣበጡ ድረስ አንድ ወጥ ነገር ለመፍጠር አለመቻል ብቻ ሳይሆን ምንም ነገር ሊፈጥሩ አይችሉም፤ አንዱ ሌላውን ስለሚያፈርሰው። ኢትዮጵያ ብትን ስርዓት ብቻ ሳትሆን የግጭት ስርዓት ነች ። የእርስበርስ መጠፋፋት፣ መዋደም፣ የእልቂት ስርዓት ንች ። ይህን መሰል ህብረተሰብ ወደ ታች እንጂ ወደ ላይ አይሸጋገርም። ለዚህ ሁሉ መሰረቱ ኢትዮጵያዊያን ማንም ይሁኑ ከየትም ይወለዱ፣ በአንድ ፈጣሪ የሚያምን፣ በሰው ልጅ ሰባዊነትና ልዕልና የሚያምን፣ በኢዮጵያዊያን ሁሉ ወንድማማችነት የሚያምን አንድ ሕዝብ አለመሆናቸው ነው። ይህን መሰረት፣ ይህን ቅድመ መርህ፣ ይህን ፓራዳይም እውን የሚያደርገው ትውልድ ገና የለም።

ያልኳቸውን ነገሮች በትንሹ ለመድገም፣ ኢትዮጵያ በማንኛውም መስክ ብትለካ ማለትም በሃይማኖት፣ በፍልስፊና፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሶሺያል ሳይንስ፣ በስነ ጥበብ፣ በሕግና በስነ ምግባር በሁሉም መስክ ቁርጭራጭ ስርዓት ነው። እነዚህ እጅግ ብዙ ቁርጭራጮች በግለ ህልውናቸው ፋይዳቢስ ሲሆኑ በህብረ ህልውናቸው ተጻራሪ፣ ተዋዳሚ፣ ተፋላሚና የግጭት መነሾዎች ናቸው። ስለዚህ ለየብቻም በህበረትም ዋጋቢሶች ናቸው። በግል ለድህነትና ለድንቁርና ተጋልጠዋል፤ ከተባበሩ ይተላለቃሉ ። መውጫ የለሽ ዙሪያ ጥምትም ማለት ነው።

ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች በኢትዮጵያ ግለሰቦች እና ቡድኖች አይምሮ ላይ ወይም አስተሳሰብ ዘንድ የሚያስከትሉት ተጽዕኖዎች አሉ። የግለሰቦች፣ ብሄረሰቦችና ቡድኖችን የማንነት ትርጉም ለውጠዋል፣ አናግተዋል። እነዚህ የምንነትና የማንነት ትርጉሞች ተበታትነዋል፣ ተፍረክርከዋል፣ ተቃውሰዋል፣ ተዘባርቀዋልም። ተያይዞም እነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች ያሏቸው፣ የነበራቸው እሴቶች ወይም ሰርዓተ እሴቶች፣ አስተሳሰብ፣ መርሆችና እምነቶች ተበታትነዋል፣ ተፍረክርከዋል፣ ተቃውሰዋል። የሞራል ስነስርዓታቸው ላሽቋል፣ ወድቋል። ማለትም ደግና ክፉ፣ ጥሩና መጥፎ፣ ትክክልና ስህተት፣ ፍትህና ግፍ፣ ጠቃሚና ጎጂ፣ ገምቢና አፍራሽ፣ እድገትና ወድቀት፣ ልማትና ወድመት፣ ነጻነትና ባርነት፣ ትልቅነትና ትንሽነት፣ ክብርና ውርደት፣ ራዕይና መታወር፣ ብርሃንና ጭለማ፣ ፍቅርና ጥላቻ፣ የሰላምና ሽብር፣ ስርዓትና ቀውስ በአንድ ቃል ደህንነትና ድህነትን የሚለይ የግምትና የህሊና ተቋማቸው ወይም ችሎታቸው ተቃውሷል። ከላይ የተጠቀሰው መበታተንና መጋጨት የግለሰቦችን አስተሳሰብና ሰነምግባር በመበታተን ላይምሮና የሞራል አናርኪ ዳርጓቸዋል። ማሀበራዊ አናርኪና ያስተሳሰብ ምስቅልቅልነት አይነጣጠሉም። አንዱ ሌላውን ይወልዳል፤ እንዲያውም ያስተሳሰብና የሞራል ስርዓት ሳይኖር ማህበራዊ ስርዓት ሊኖር አይችልም። ብትን ሃይማኖት፣ ብትን ፍልስፍና፣ ብትን እሴት፣ ብትን ፖለቲካ፣ ብትን ስነት፣ ወዘተ የሚፈጥሩት ብትን ህብረተሰብን ነው።

ያስተሳሰብ፣ የህሊናና የሞራል ቀውስ ወይም አናርኪ ውጤቱ የተፋፋመ ቅራኔ ፣ ግጭት፣ ሁከትና ጦርነት ነው። በኢትዮጵያ የሃይልና የጉልበተኝነት ሚና እየገነነ ይሄዳል። ጦርነት፣ አብዮት፣ አመጽ፣ ወንጀል፣ ሕግ አልባነት በአገሪቱ ይስፋፋሉ። በሰው ሕይወት ላይ እልቂት ይከተላል። የሕዝቦች ቁሳዊ መደላደል (አኗኗር) ይፈርሳል። ያገሪቱ ቁሳዊ ሃብት ይወድማል። ይህ የመጨረሻ ወድመትና ጥፋት ከሚከተሉ ሶስት አዝማሚያዎች አንዱን ሊወድ ይችላል።

አንደኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በብትንትንነቱና በቀውሱ ለረጅም ዘመን ሊቀጥል ይችላል። ይህም ማለት አገሪቱ ምንም አይነት መሰረታዊ መፍትሄ ሳታገኝ በሞትና በህይወት መካከል አሳዛኝ የሆነው ህልውናዋ እንደ ተንጠለጠለ ሊቀጥል ይችላል።

ሁለተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በተወሰኑ ሰፋፊ መሬቶች ፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ግዛቶች፣ ተከፋፍሎ በአዲስ ፌዴራላዊ ወይም ኮንፌዴራላዊ ስብስብ ሊቀጥሉ ይችላሉ። ኢትዮጵያ በብዙ አገሮች የምትከፋፈለቅ ይህ አዝማሚያ እውን ከሆነ ነው።

ሶስተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ መሰረታዊ ያስተሳሰብና የእስትራተጂ ለውጥ አድርጎ ስርወ እሴታችን የአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ የሰው ልጅ ልዕልናና የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ሆኖ አገሪቱ ከውድቀት ልትድን ትችላለች ።

ከነዚህ ሶስት አዝማሚያዎች የትኛው እውን እንደሚሆን የሚወሰነው በኢትዮጵያ ምሁራን መካከል ባለው የሃይል ሚዛንና የማሰብ ችሎታ ነው። ለምሳሌ ያንድነትም ሆነ የብሄረሰብ ምሁራን ከደከሙና አዲስ መፍትሄ ማቅረብ ካልቻሉ ወይም አንዱ ከለላው በልጦ ማሸነፍ ካልቻለ አንደኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

የብሄረሰብ ምሁራን የበላይነት ይዘው የጎሳ ክፍፍል አሁን ባለው ቀጥሎ ካደገና ካሸነፈ ሁለተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል። የኢትዮጵያ አንድነት ምሁራን ከጠነክሩ ሶስተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

ለምሳሌ ሶስተኛው አዝማሚያ ሃይማኖትን በተመለከተ የኢትዮጵያዊያን እምነት ሆነ አምልኮ መሆን ያለበት እግዚአብሄር፣ ክርስቶስ፣ አላህ፣ ያዌ፣ ጂሆቫ፣ ዋቃ፣ ሌላም ሌላም በሚል መናቆር ሳይሆን በአንድ ፈጣሪ ማመን ነው። ቤተ እምነት ሆነ ቤተ አምልኮ ሁሉ የአንድ ፈጣሪ ቤተመቅደስ ሆኖ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የአንድ እምነት አማኝ አንድ ሕዝብ መሆናቸውን መቀብለና ያንን ማስተማር አለበት ። የኢትዮጵያ ብሄረሰብ ግለሰቦች ሁሉ ማለትም ኢትዮጵያዊ ሰው ሁሉ የአንድ ፈጣሪ ፍጡራን እንደ ሆኑ። እነሱም አንድ ኢትዮጵያዊ ብሄር እንደሆኑ ተቀብሎ የኢትዮጵያ ጎሳ እንደሆኑ ማመንና ማስተማር አለበት ። በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አንድ ቤተሰብ ፣ ወንድማማች እንደሆኑ ማመንና ማስተማር አለበት ።

በእነዚህ ሶስት ስረወ እሴቶች መሰረት የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣ የፍልስፍና፣ የስነ ጥበብ፣ የማህበራዊ ሳይንስ፣ የሕግና የስነ ምግባር ውህደቶችን የሚያንጸባርቅ ባህል፣ ፈጠራ፣ ንድፈ ሃሳብ መቀመር ግድ ይላል። የኢትዮጵያ አንድነት ምሁራን ይህን ማድረግ ካልቻሉ የጎሳ ምሁራን አሁን በጀመሩት አጀንዳ ቀጥለው ሕዝቡን በብዙ አማልክት በብዙ ጎሳዎች፣ በብዙ ቋንቋዎች፣ በብዙ ባህሎች በመከፋፈል ይህም ውሎ አድሮ ወይ ኢትዮጵያ መከፋፈል ወይም ወደ ኢትዮጵያ ወድመት ማምራቱ አይቀሬ ነው።

ይህን ያልኩት የዛሬ 29 አመት ነበር

አንድ ጽንሰ ነገር ተቀርጾ፣ ተተክሎ፣ ለምቶ እስኪያብብ በድጋሚ በድጋሚ እንክብካቤ ይሻል። ስለ ኢትዮጵያ ማህበረ ሰብ፣ ስለ ኢትዮጵያ ፍጥረ ግብር ወይም ካልቸር ስናስብ ያለው ሃቅ ተመሳሳይ ነው።

እንደ ገና ልድገመው፤ ሁላችንም የምታኮራ፣ ተወዳጅ ኢትዮጵያ ላይ ለመስማማት ሶስት ስርወ እሴቶች ወይም ኮር ቢሊፍስ ላይ እንስማማ። ሁላችንም በአንድ ፈጣሪ እንመን ። ያ አንድ ፈጣሪ በተለያዩ ስሞች መጥራታችንን ተቀብለን በስም ልዩ በይዘት አንድ እምነት እንዳለን እንቀበል። ከዚያም ይህ አንድ ፈጣሪ የፈጠረውን የሰው ልጅ ማለትም አንድ ግለ ሰብ ፍጹም ልኡል፣ ፍጹም ነጻ የሆነ ሰብአዊነቱም ከፈጣሪው ያገኘው መሆኑ ላይ እንስማማ። ይህም ስለሆነ ኢትዮጵያዊያን ሰው በመሆናቸው ብቻ ወድማማች በመሆናቸው እንስማማ። ይህ ነው ያንድ ትልቅ ካልቸር ወይም ፍጥረ ግብር መሰረቱ። በዚህ መሰረት አንድ ኢትዮጵያዊ ካልቸር (ፍጥረ ግብር) ይፋፋል።

ከዚያ በኋላ በኢትዮጵያ አጀንዳ ላይ መጣላታችን ያበቃል። ያኔ ከላይ በዚህ ሃረግ መክፈቻ ላይ ያሉት አራት የኢትዮጵያ ፋይዳዎች ሌላው የአንድነታችን ምሰሶ ይሆናሉ ። አላማ አንድ የሚያደርግ ምሰሶ ነው ። በነዚያ አራት የኢትዮጵያ ፋያዎች ላይ ለመስማማት ግን እነዚህ ሶስት የኢትዮጵያ ካልቸር መቆሚያ ምሰሶዎች ላይ መስማማት አለብን ማለትም በአንድ ፈጣሪ እንመን፣ በግለሰብ ለዕልና እነመን፣ ኢትዮጵያዊያን የአንድ ፈጣሪ ልጆች ወንድማማቾች እንደ ሆኑ እንመን ። ከዚያም በ4ቱ የ ኢትዮጵያ ፐርፐዝ ላይ እንስማማ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 08 Feb 2024, 16:21

በሰው ልጆች አለም ውስጥ ያሉት ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው፤ አንድ ፍጥረት ነው፣ ሌላው ካልቸር ነው ። አንዱ ፍጥረት የሰራቸው ነገሮች ናቸው፣ ሌላው የሰው ልጅ የሰራቸው ካልቸሮች ናቸው።

ካልቸር የሰው እጅ ከገነባቸው ቁሳዊ የሚዳሰሱ ፈጠራዎች እስከ ምናባዊ የሰው ሃሳቦች ያሉትን ሰው ሰራሽ ነገሮችን ይጠቀልላል። በኢትዮጵያ አጀንዳ ቁጥር አራት የተጠቀሰው የሚፈጥር፣ ከተፈጥሮ ጋር ስምም የሆነ እና መንፈሳዊ ካልቸር ማለት ያ ነው። ከዚህ እጅግ ግዙፍ የሰው ስራ ውስጥ አንዱ ቁልፍ የሆነው የካልቸር አይነት የኑሮ ዘዴ የሚባለው ነው ። የኑሮ ዘዴ ወይም የሰው ባህሪ አንድ ማህበረሰብ ህልውናውን በተግባር የሚገልጸበት፣ የሰው ልጅ ግላዊም ሆነ ማህበራዊ ሕይወቱ የሚተገብርባቸው ክስተቶች ናቸው ። አንድ ሕዝብ ምን ያክል ሰለጠነ፣ አደገ፣ አሰበ፣ አወቀ ፣ ፍለሰፈ፣ አመነ፣ ተራቀቀ ፣ ክነየ፣ ተወነ ... የምንለው በነዚህ የካልቸሩ ፈጠራን ምርቶች አማካይነት ነው ። በአንድ ቃል አንድ ሕዝብ ሆነ አገር ፕርፐዙ ምንድን ነው? አገራዊ አላማው፣ሕዝባዊ ፋይዳው፣ ማህበራዊ መድረሻው ምንድን ነው የሚለው ጥያቄ በካልቸሩ ምንነት ይመለሳል፣ ይታወቃል ።

ስለዚህ ኢትዮጵያ እንደ አንድ ካልቸር ምን ላይ ነው ያለችው? እንዴት ነው በተግባር እየተከሰተች ያለው? የኢትዮጵያ ካልቸር ምን እየፈጠረ ነው? ኢትዮጵያ በምትባለው አገር ፍጥረትና ካልቸር ምን አይነት ጠብና ፍቅር አላቸው? ሳይንስና ኃይማንትስ? እኒህንና መሰል ፋይዳዎች ሁሉ የዚህ የኢትዮጵያ አጀንዳ ቁጥር 4 ጉዳዮች ናቸው ።
Last edited by Horus on 09 Feb 2024, 22:12, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 09 Feb 2024, 21:45


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 10 Feb 2024, 15:26

የመጀመሪያው እጅግ ግዙፍ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ችግር የመሪነት እጦት ነው። ኢትዮጵያ ላለፉት 50 ዓመታት በመሪነት እጦት ምክንያት ፋይዳቢስ እና ግብአልባ ሆና በጭለማ ውስጥ የምትመላለስ፣ የምትታመስ አገር ነች ። ኢትዮጵያ ያጣችው ከዚህ በታች የተጠቀሱት መሪዎችን ነው ።

In my view, the very basic national mission of Ethiopia is to achieve immortality and eternity of our nation. Ethiopia must continue to achieve eternal national unity and enduring cultural integration as a nation of visionary prophets, wise sages, saintly healers, and heroic warriors. Her visionary prophets will lead her to greatest harmony among her religions and give her deepest spiritual integration. Her sagely teachers will lead her to be a nation of sacred beauty, intelligence, knowledge, and wisdom. Her righteous political officials and saintly social leaders will give her a culture of truth, blameless moral standards, justice, family-hood, and love. Her heroic warriors will lead her to be a nation of creativity, innovation, industry, free expression, energy, prosperity, and happiness. This is the very first national mission of Ethiopia. This is one way of saying our most universal national purpose.

በሰው ልጆች አለም በግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉት ሁለት ነገሮች ናቸው፤ አንዱ እራሱ ሰው ነው ፤ ሌላው የሰው ስራ ወይም የሰው ባህሪ ነው። ለምሳሊ በኢትዮጵያ ያሉት ሁለት ነገሮች ኢትዮጵያዊያን እና ስራቸው (ወይም ባህሪያቸው) ነው ።

የሰው ስራ፣ የሰው ተግባር ግለሰባዊም ሆነ ማህበራዊ ስኬታማ ይህን ዘንድ አራት ነገሮች ሳይነጣጠሉ መሟላት አለባቸው ። እነሱም ፈጣሪነት፣ አዋቂነት፣ ጠቢብነትና ጀግንነት ናቸው። ፈጣሪ አንድን የሌለ ነገር ጸንሶ ወልዶ እውን አድጎ የሚከስት ባህሪ ነው። አዋቂ አንድን ነገር ከሌላ ነገር ለይቶ የሚገልጽ፣ የሚወስን፣ የሚለካ፣ የሚወጥን ባህሪ ነው ። ጠቢብ አንድን እንዴት እንደ ተሰራ እና እንዴት እንደ ሚሰራ የሰለጠነ ልሂቅ ነው። በእውቀት አለም ውስጥ እጅግ ከፍተኛውና የምር እውቀት ወይም ኧዠት (ዊስደም) የሚባለው ይህ ጥበብ ወይም ክህሎት ነው ። ጀግንነት አንድን ስራ፣ መደረግ ያለበትን ግዴታ በብርታት፣ ቆራጥነትና ዲሲፕሊን የሚተገብር ባህሪ ነው ።

በአንድ ቃል፣ አንድ መሪ እነዚህን አራት የማይነጣጠሉ ባህሪያት፣ ብቃቶችና ስብዕናዎች ከሌሉት የሕዝብ መሪ፣ የአገር አባት ሊሆን አይችልም።

ስለሆነም ወጣቶች፣ ጎረምሶች የሕዝብ መሪ፣ የአገር አባት ሊሆኑ በፍጹም አይችሉም። ኢትዮጵያ ከመንግስቱ ኃ/ማሪያም እስከ አቢይ አህመድ ድረስ በአራት ለአቅመ መሪነት ባልደረሱ ወጣቶች መሪነት አልባነት ስትፈርስ ስትታመስ እስከ ዛሬ አለች ። ጎረምሳ አገር መምራት በፍጹም አይችልም።

በጥንታዊ ግሪክና ሮማ ዘመን አንድ ሰው ለአገር መሪነት ለመታጨት ቢያንስ የ65 አመት እድሜ መድረስ ነበረበት ። የዚህ የእድሜ ገደብ ሎጂክ ከላይ የጠቀስኳቸው የመሪነት ብስለት መለኪያዎች ናቸው። አንድ ሰው ጥልቅና ሩቅ ራዕይ፣ ግልጽና ሰፊ እውቀት፣ ዙሪያ ገብና ረቂቅ ክህሎትን አካብቶ እና ብርቱና ርቱዕ ፈጻሚ ይሆን ዘንድ በግድ በረጅም እድሜ መሰልጠንና መገራት ይኖርበታል ።

ኢትዮጵያ መታመስና መፍረስ የጀመረችው አባቶች፣ ሽማግሎች፣ አዛውንቶች ባሊቆች፣ እናቶችና የእድሜ ሊቆች ወደ ጎን ተገፍተው ጎረምሶች፣ ወጠጤዎች፣ ጥጃዎች የሕዝብ መሪ የአገር አባት የሆኑ እለት ነው ።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚጀምረው በአልሰከኑ፣ ባልበሰሉ፣ በማያውቁ፣ ባልተገሩ ጎረምሶችና ጥጃዎች አንመራም ማለት ስንጀምር ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 11 Feb 2024, 02:35

የግርዝና ሴራ ምንድን ነው?

ግርዝና የሚባለው የጉራጌ ስርዓት ዋና ቃሉ ጉርዝ ነው ። የጉራጌ ሕዝብ ሁሉ ለዘመናት የሚመሩበት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሴራ (ሴራ ስርዓት ማለት ሲሆን የግዕዝ ቃል ነው) በሁለት ስሞች ይጠራል ፤ የግርዝና ወይም የባሊቅ ስኛት ይባላል። ስኛት ስርዓት ወይም ሲስተም ማለት ነው ። ይህ የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ ፣ ሕጋዊ ካልቸር ብቸኛው የጉራጌ ብሄር የመሪነት ካልቸር ነው።

ማንኛውም የጉራጌ ጉዳይ ከአንድ ግለሰብ ስህተትና ወንጀል፣ እስከ ባልና ሚስት ጋብቻና ፍቺ፤ ከሁለት ሰዎች ጠብ እስከ ብሄር አቀፍ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ አስተዳደርና የፍርድ አፈጻጸም፣ በአንድ ቃል መንግስታዊ ተግባሮች ሁሉ የሚመሩት በግርዝና (በጉርዝና) እና በባሊቅ ሴራ (ስኛት) ነው።

ጉርዝ ምን ማለት ነው? ባሊቅ ምን ማለት ነው

ጉርዝ በተለይ የክስታኔኛ ቃል ሲሆን መሰረቱ ጥንታዊ ግብጽ ሆኖ ዛሬ በሰፊው የሚታወቀው በሂንዱ ካልቸር ነው ። በህንዶች ቅዱስ ቋንቋ በሳንስክሪት ጉሩ ማለት አዋቂ፣ አስተማሪ ፣ ቄስ ማለት ነው። በጥንታዊ ግብጽ የጸሃዩ ራ አምልኮ ዘመን የነበሩት የእምነቱ ቄሶች ጉሩ ይባሉ ነበር። ትርጉሙ በሶስቱም ካልቸሮች አንድ ነው ፤ አዋቂ፣ አስተማሪ፣ መሪ፣ የተከበረ ፣ ክቡድ ሰው ማለት ነው።

በጉራጌ የጉርዝ (የግርዝና) ባህል ይህ ስልጣንና ክብር የሚሰጠው እድሜ ጠገብ ሽማግሌ ቢያንስ 60 አመት በላይ የሆነው ዋይዝ አባት ብቻ ነው።

በመላ ጉራጌ ብሄር ውስጥ ያለው ሊላው የጉርዝ ቃል ባሊቅ ይባላል። ባሊቅ እጅግ ጥንታዊ የሴም ቃል ሲሆን በአረሜይክ (ክርስቶስ የተናገረው ቋንቋ) ሞሎክ ይባላል። ትርጉሙም ንጉስ ፣ ጌታ ማለት ነው። በአሲሪያና ዘመናዊ አረሜክ ማሊክ ይባላል። ትርጉሙ ያው ንጉስ፣ ጌታ ማለት ነው ። በአረብኛም በእንብራስጥም ቃሉ ያው ነው ።

ዛሬ ሊቅ ፣ የላቀ፣ ታላቅ፣ ልሂቅ የምንላቸው ቃላቶች ሁሉ ማሊክ፣ ማለቅ፣ ባሊቅ የሚባሉት የጥንት ጽንሶች ናቸው።

ጉርዝ፣ ባሊቅ በአማራኛ ሽማግሌ ማለት ነው።

በጥንታዊ ግሪክና ሮማዊያን ዘመንም አንድ ሰው የአገር መሪ ፣ የሕዝብ መሪ ለመሆን እድሜው ከ60 አመት በላይ መሆን ይጠበቅበት ነበር። የ ጎርቲ ሲስተም ይባል በነበረው የግሪኮች ትራይባል አስተዳደር ተመሳይ የሴኔኬ ስርዓት ነበር ። ዛሬ ሴኔተር (ሴኔቻ) የምንለው ቃል ሲኒየር ወይም ሽማግሌ፣ ባሊቅ፣ ኤልደር ማለት ነው።

የጉራጌ ባሊቅ ወይም ጉርዝና ሴራ ይህን ከመሰለ ጥንታዊ ግንድ የበቀለ ሲሆን በጉራጌ ብሄር ከሽማግሎች ቀድሞ ወጣት አይመራም ። የሽማግሎች ብያኔ፣ ውሳኔ ማኛውም የወጣቶች ቡድን ሊጥስ፣ ሊሽር አይችልም ። በነዚህ ሴናተሮች ጉባኤዎች (ምሳሌ የጆካ እና ጎርደና) የሚወሰኑ ሴራዎች ፣ ስኛቶችና ቅጫዎች የብሄሩ ሕገ መንግስት፣ የወንጀልና ፍትሃ ብሄር ሕግጋትና ቅጣቶች ናቸው ። ቅጫ ማለት ቅጣት ማለት ነው ። ሴራ ሌላ ትርጉሙ ሕግ ማለት ሲሆን ስኛት ሁሉም አይነት የስነ ምግባር መርሆዎችን ያጠቃልላል ።

የዚህ ሁሉ መሪና ያገር አባቶች የጉራጌ ባሊቅ፣ የጉራጌ ጉርዝ፣ የጉራጌ ሽማግሎች ናቸው ። በጉራጌ ብሄር ሽማግሌ ይመራል ያዝዛል፤ ወጣት ይከተላል፣ ይታዘዛል ። ዊዝደም የሚባለው የባሊቆች ብቃት ወዠት፣ በወዠት ይባላል፤ እሱም ማየት ማስተዋል ማለት ነው ። ሕዝብና አገር መሪ ያገር አባት ለወዠት፣ ለዊዝደም የደረሰ ጉርዝ ባሊቅ ብቻ ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 12 Feb 2024, 16:02

ከሰካራሙ ኮነኔል መንግስቱ እስከ ጫታሙ መልሰ፣ ከፋይዳሚሱ ኃ/ማሪያም እስከ ዉሸታም ኮራጁ አቢይ፤ ሺ ወጠጤና ጥጃ አላዋቂ ቢወጠር፣ ቢፎክር፣ ቢባክን ቢበተን ኢትዮጵያን ማሻል እንጂ ማፍረስ እንደ ማይቻል የሚያውቁት አንድም ሲወርዱ አንድም ሲሞቱ ነው። መሬት አገር ብለው የተገነጠሉትም ከኢትዮጵያ የዉሸት ድምበር መቅፈፍ እንጂ ከኢትዮጵያ ተለይተው መኖር እንደ ማይችሉ አለም እየመሰከረ ነው። ይህው ከ60 አመት በኋላ አሁንም ድራማው የብሄር ጥያቄ ነው ። ኢትዮጵያን መጥላት ትችላለህ፣ ከኢትዮጵያ ተገንጥለህ መኖር ግን አትችልም ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 15 Feb 2024, 01:39

ግዜ ሁሉን ነገር ያሳያል። የንጉስ ምኒልክን ዘፈት መስማት አትችሉም ስንባል እንዳልነበረ እራሱ ኦሮሙማ ያለ ምኒልክ መግዛት አይቻልም ብሎ እርፍ! በዚህም ሳቢያ ኦነግ ጸጉር እየነጨች ነው ! ጃዋርን የበላው ጅብም አልጮህ ብሏል




Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 16 Feb 2024, 15:36

ቀደም ሲል የተጠቀሱት አራት የኢትዮጵያ አጀንዳዎች እውን ለማድረግ የመጀመሪያው ግ ብ አት መሪነት ነው።

የኢትዮጵያ ችግር ግዚያዊ የመሪነት ችግር እንጂ በውስጧ ታላቅነት አምቃ የያዘች ሃያል አገር ናት ። የዚህ ትውልድ ውድቀትን የሚሻገር የታላቅ አገር መሪነት ብርሃን መብራቱ የታሪክና ተፈጥሮ ሕግ ነው ።

የፍጥረት ሕግጋት በኢትዮጵያ ጎን ነው ቆመው ያሉት፤ ለምሳሌ አንድነት የፍጥረት ሕግ ነው ፣ ለውጥ የፍጥረት ሕግ ነው ፣ እድገት የፍጥረት ሕግ ነው ። ታላቅ ነገር ሁልግዜ ትንሹን ነገር የሚስብ ግራቪቲ ያለው መሆኑ የፍጥረት ሕግ ነው።

የአፍሪካ ቀንድ በሚባለው ምድር ያለችው ግዙፍ gravitational force ኢትዮጵያ ትባላለች ። ይህ ተረት ሳይሆን ፊዚክስ ነው!

ሌላው ዩኒቨርሳል የፊዚክስ ሕግ ክንስትራክታል ሕግ ይባላል ። እሱም ማንኛውም ነገር የሚቀረጸው፣ የሚወሰነው፣ የሚደራጀው በከባቢው ባለው ገደብ (constraint) አይነትና መጠን ነው የሚለው እጅግ መሰረታዊ መርህ ነው።

ስለሆነም የቀጠናችን አላዋቂና ስሜታም ንኡስ ከበርቴ ለዝንተ አለም በምናቡ እየተነዳ ቢባክን ከኢትዮጵያ ግራቪቲና ገደብ ሊላቀቅ አይችልም። ኢትዮጵያን ማሻሻል ማሳደግ እንጂ ማፍረስና ማክሰም አይቻልም።

ይህ የተፈጥሮ ሕግ ነው ። ይህን ናቹራል ሕግ ወደ ሶሺያልና ፖለቲካል ስርዓት የሚለውጥ መሪነት ነው ኢትዮጵያ ማብቀል ያለባት። ለምሳሌ ኢትዮጵያ የባህር ድምበርና የባህር ኃይል ያስፈልጋታል ማለት የማንኛውም ግዜያዊ ፓርቲና ገዢ ጥቅም አይደለም፣ ሊሆን አይችልም፤ የዘላለማዊ ኢትዮጵያ ጥቅም ነው።

ሁሉም ነገር በገደብ ይገደዳል ለሚለው ምሳሌ የሰሞኑን የኦሮሙማ ድራማ ይመለከቷል። አማራና ፋኖ ተነስቶ ኢትዮጵያነትን ሲጠቀልልና ኦሮሞነት ከገበያ የሚያነሳው ሲያጣ አዳነች አቤቤ እንደ ጣይቱ፣ አቢይ እንደ ምኒልክ ሆነው አድዋ ዜሮ ዜሮ ተዘፈነልን።

እውነተኛ መሪነት ግን እንደ እስ ስት ከወረተኛው ነፋስ ጋር የሚነፍስ ስብከት ሳይሆን በዚህ ማኒፌስቶ እንደ ተቀመጠው የኢትዮጵያን የመኖር ፕርፐዝ ለምን እንደ ሆነ አውቆ፣ አምኖና በይፋ አውጆ ሕዝብና አገር ለመምራት ብቁ መሆን ነው ።

ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ መሄዱን ጭርሳለች ። ወደ ኋላ የሳቧት ሁሉም ጸሃያቸው እየጠለቀች ነው ። የሁሉም ነገር መፍትሄ ፍትህ ነው፤ ፍትህ መፍትሄ ማለት ነው ። ፍትህ ያለ እኩልነት አይኖርም ። ፍትህ ከሌለ ሰላም የለም። ሰላም ስርዓት ማለት ነው ። ያለ እኩልነት ሰላም፣ ስርዓት፣ ፍትህ፣ መፍትሄ፣ እድገት ሆነ ነጻነት ሌላም ሌላውም አይኖርም ።

የኢትዮጵያ ቁጥር 1 ችግርና መከራ የመሪነት እጦት ነው !

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 24 Feb 2024, 22:33

ክላንና ጎሳ እንጂ አገር የሌላቸው የአፍሪካ ቀንድ ንዑስ ከብርቴ ለምን 24/7 እንደ ሚነዘንዙኝ አላቅም ። አኔ አገር አለኝ፤ እሷም ኢትዮጵያ ትባላለች ። አገሬ ምን መሆን፣ ምን መምሰል እንዳለባት ደም ሌላ ሰው ማኒፌስቶ አይጽፍልኝም ። እኔ የራሴ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፕሮግራም አለኝ ፤ የራሴ የኢትዮጵያ አጀንዳ አለኝ ። ይህን የሆነው አገር ስላለኝ ነው። አንተስ የአገር/ የአገርሽ ማኒፌስቶ ምንድን ነው? ይህን ማኒፌስቶ ሳትጽፍ እንዴት አድርገው በአገር ፖለቲካ ውስጥ መካፈል ትችላለህ? ለምን አላማስ ግዜህን ታባክናለህ?

Selam/
Senior Member
Posts: 11848
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Selam/ » 24 Feb 2024, 23:54

ወዳጄ ሆረስ - ማንፌስቶህ እየተሸጋሸገ ለመከታተል አስቸግሮኛል!

<> የዛሬ ሁለት ዓመት ዘፈንህም እንጉርጉሮህም ‘ጉራጌ ጉራጌ’ ብቻ ነበር። ከሁሉም ብሄሮች የፀዳንና የሰለጠንን ልዩ ህዝቦች ነን የሚለው ሌሎችን የማናናቅ ዜማም የሁልጊዜ ሳውንድ ትራክህ ነበር። ሆኖም ይሁን ምንም ችግር አልነበረውም። ግን በመቀጠል የተናጥል ጎሰኝነቱን ጠበቅ አድርገህ የጉራጌ ህዝብ ከማንም ጋር መተባበር አይፈልግም፣ ራሱ ብቻውን በሚፈልገው አቅጣጫ ፖለቲካውን አሽከርክሮ ኦሮሙማን አሽቀንጥሮ ይጥለዋል፣ የዓብይም መውደቂያ በጉራጌ ህዝብ ሃገር ነው የሚጀምረው ብለህ በወዳጅነት የዘረጋሁልህን እጂን አሻፈረኝ ብለህ መታኸው። ይኸም ችግር የለውም።

<> በመቀጠል ግን የጉራጌን አመፅ አስተባብራለሁ ብለህ የጀመርከውን ተስፋ ሰጪ ትግል እርግፍ አድርገህ ትተህ፣ የአማራና የፋኖ ትግል full time ቲፎዞና አቀንቃኝ ሆንክ። ይኸም ችግር የለውም። ለማስታወስ ያህል ግን የፋኖ ዋና አላማ በቅድሚያ የአማራን ህልውና ማስከበርና ማስቀጠል፣ በመቀጠልም ከሌላ ብሄረሰቦች ጋ በመተባበር ኢትዮጵያን ከወረሯት ገዳዮችና ጅቦች መታደግ ነው።

<> አሁን በስተመጨረሻ ደግሞ ስለ ብሄሮች በደልና ግፍ አታውሩ ምንም መስማት አልፈልግም፣ አንድና አንደኛ ኢትዮጵያ ብቻ ነች የምትል አዲስ የተከለሰች ዘፈን አውጥተሃል። ይኸም ይሁን ችግር የለውም እንበል። ግን ማነው የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት የሚስጠብቅልህ?

<> በተለይ ከእናት ሃገሩ በፖለቲካ ምክንያት ሸሽቶ በስደት በውጪ የሚኖር ሰው፣ መሬት ላይ የሚገደለውን፣ በእስር የሚንገላታውንና በየጊዜው በድሮን የሚወቃውን ህዝብ፣ በደልህን ለጊዜው ዋጥና ቻል አድርገህ ገዳይህ ስለኢትዮጵያ የቀረፀውን የውጪ ፖሊሲ ደግፍ አጨብጭብ ማለት ነውርና ግብዝነት ነው። የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች በዕኩልነት ተከባብረው እስካልኖሩ ድረስ፣ መታሰር፣ መገፋትና መገደል እስካልቆመ ድረስ ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ልትቆም አትችልም። አንተ በስደት ጥለሃት የሄድካትን ሃገር ሌላው ህዝብ እንዲጠብቅልህ ለምንስ ትፈልጋለህ? 30-40 ሚሊዮን የሚሆነው ወጣት ልክ እንዳንተ ኩራት፣ አርበኝነትና ቅብርጥሶውን አልፈልግም፣ ህይወቴን ለማስቀጠል ለመሰደድ እፈልጋለሁ ቢል ምን ልትለው ነው?


Horus wrote:
24 Feb 2024, 22:33
ክላንና ጎሳ እንጂ አገር የሌላቸው የአፍሪካ ቀንድ ንዑስ ከብርቴ ለምን 24/7 እንደ ሚነዘንዙኝ አላቅም ። አኔ አገር አለኝ፤ እሷም ኢትዮጵያ ትባላለች ። አገሬ ምን መሆን፣ ምን መምሰል እንዳለባት ደም ሌላ ሰው ማኒፌስቶ አይጽፍልኝም ። እኔ የራሴ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፕሮግራም አለኝ ፤ የራሴ የኢትዮጵያ አጀንዳ አለኝ ። ይህን የሆነው አገር ስላለኝ ነው። አንተስ የአገር/ የአገርሽ ማኒፌስቶ ምንድን ነው? ይህን ማኒፌስቶ ሳትጽፍ እንዴት አድርገው በአገር ፖለቲካ ውስጥ መካፈል ትችላለህ? ለምን አላማስ ግዜህን ታባክናለህ?

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 25 Feb 2024, 01:13

ሰላም,
የዘረዘርካቸው ነገሮች ሁሉ አሁንም የማምንባውና ኮንሲስተንት ሃሳቦች ናቸው ።

አንድ፣
አው እኔ በጎሳ ጉራጌ ነኝ በቃ!

ሁለት፤
አው የጉራጌን ባህል እሴት ባህሪ እና ህሳቤ በብዙ መስክ ሞዴል ሕዝብ ነው ። ሌሎች ያንሳሉ ብዬ አላውቅም ። ስለ ጉራጌ ሕዝብ ሞዴልነት ሳላፍር እናገራለሁ ።

ሶኦስት፣

እኔ ጉራጌ የሚባል ጎሳ አለኝ፤ ኢትዮጵያ የምትባል ውብ ድንቅ አገር አለችኝ። እኔ ጉራጌነቴና ኢትዮጵያዊነቴ 100% ተገጣጣሚ ነገሮች ናቸው ። ለኢትዮጵያ ያለኝ ማኒፌስቶ ቃል በቃል ለጉራጌ ያለኝ ማኒፌስቶ ነው ።

አራት፣
ዘረኞችና እብሪተኞች ጉራጌ ትንሽ ነው እንውጠዋለን ! ጉራጌ አማራኛ ተናጋሪ ስለሆነ አማራ ነው በአማራ ስር ይደራጅ የሚሉት ሁሉ ተቃውመናል ። ጉራጌ እንደ ጎሳ የማንም ሌላ ጎሳ ተለጣፊ አይደለም ፣ ሌላ ጎሳም ነጻ አያወጣውም ። ይህ ለእብሪተኛው ትግሬም ፣ ለሰልቃጩ ኦሮሞም ለሌላም ያው ነው ።

የአባ ዱላን ክለላ በቻልነው ልክ ታግለን የቻልነውን ያልክ ኢንፍሉወንስ አድርገው አሁን እስቴሜት ላይ እንገኛለን ። ጉራጌ ተገዶ እንጂ የክልል ስራዓት ጨርሶ እንዲጠፋ የሚፈልግ ሕዝብ ነው ።

እኔ የአማራን ሕዝብ ትግለ እደግፋለሁ ፣ ከፈለጉ ተገንጥለውም አገር ቢሆኑ ግድ የለኝም ። የአማራ ትግል የኢትዮጵያ ትግል ነው ካሉ ደሞ ለኢትዮጵያ ያረቀቁት ብሄራዊ ፕሮግራም ለመላ ኢትዮጵያ ማሳውቅ አለባቸው ። እስከ ዛሬ ፋኖ የተሳካ የትጥቅ ትግል እያደረገ ነው ። ብሄራዊ የፖለቲካ ፕሮግራም ግን የለውም ።

እኔ የኦሮሙማ ኒዎ ፋሺስት መንግስት አምርሬ እቃወማለሁ ፣ ያ ማለት ግ ን ኦሮሞን ለመቃወም የሱማሌ ደጋፊ አልሆንም ።

ስለዚህ ያልኳቸው ነገሮች ሁሉ ለ50 አመት ሳላቋርጥ ያሰብኳቸው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያለኝ ሕይወት ነጸብራቆች ናቸው

ባልኳቸው ነገሮች ውስጥ ቅራኔ የሚያዩ እራሳቸው የፖለቲካ ብልሰትና ልምዳቸው አጭር የሆነ በአንድ ነገር ላይ አቋም ይዘው ሌሎች ነገሮች ሁሉ ለዚያ ጋር የሚያቋልፉ ሰዎች ናቸው ። በአጭሩ

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12679
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Fiyameta » 25 Feb 2024, 01:38


Selam/
Senior Member
Posts: 11848
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Selam/ » 25 Feb 2024, 01:42

“እኔ የኦሮሙማ ኒዎ ፋሺስት መንግስት አምርሬ እቃወማለሁ ፣ ያ ማለት ግን ኦሮሞን ለመቃወም የሱማሌ ደጋፊ አልሆንም ።”

አጭር መልስ - ዓብይ ያጨማለቀው መንገድ ትክክል አይደለም ማለት፣ ሶማሌን መደገፍ አይደለም። የሄደበት አቅጣጫ ስህተት ከሆነ ደግሞ፣ ሶማሌያ አሁን ለምታደርገው ድርጊት ተጠያቂው እሱ ነው ማለት ነው። ይኸንን የዕንጭጭ የዲፕሎማሲ ጥፋት ባይፈፅም ኖሮ ጠላታችን ግብፅ ምክንያት ፈጥራ ድንበራችን ላይ አትመጣም ነበር። እኔ ቱርክን እንደ ሜርሲነሪ ነው የማያት። ትናንትና መሳሪያ ለኢትዮጵያ ትሸጥ ነበር፣ አሁን ደግሞ ሃገር የሚሸጥ መንግስት ስታገኝ ሰተት ብላ ገባች። ስለዚህ መጀመሪያ ዕርጉሙ ዓብይ እስካልተወገደ ድረስ ከዚህም የከፋ ነገር በሃገራችን ላይ ሊደርስ ይችላል። እሱ እያለ አይደለም ባህር ሃይል እስከአሁን የምንጠቀምባቸውን የቀይ የባህር ወደቦችንም ልናጣ እንችላለን።
Horus wrote:
25 Feb 2024, 01:13
ሰላም,
የዘረዘርካቸው ነገሮች ሁሉ አሁንም የማምንባውና ኮንሲስተንት ሃሳቦች ናቸው ።

አንድ፣
አው እኔ በጎሳ ጉራጌ ነኝ በቃ!

ሁለት፤
አው የጉራጌን ባህል እሴት ባህሪ እና ህሳቤ በብዙ መስክ ሞዴል ሕዝብ ነው ። ሌሎች ያንሳሉ ብዬ አላውቅም ። ስለ ጉራጌ ሕዝብ ሞዴልነት ሳላፍር እናገራለሁ ።

ሶኦስት፣

እኔ ጉራጌ የሚባል ጎሳ አለኝ፤ ኢትዮጵያ የምትባል ውብ ድንቅ አገር አለችኝ። እኔ ጉራጌነቴና ኢትዮጵያዊነቴ 100% ተገጣጣሚ ነገሮች ናቸው ። ለኢትዮጵያ ያለኝ ማኒፌስቶ ቃል በቃል ለጉራጌ ያለኝ ማኒፌስቶ ነው ።

አራት፣
ዘረኞችና እብሪተኞች ጉራጌ ትንሽ ነው እንውጠዋለን ! ጉራጌ አማራኛ ተናጋሪ ስለሆነ አማራ ነው በአማራ ስር ይደራጅ የሚሉት ሁሉ ተቃውመናል ። ጉራጌ እንደ ጎሳ የማንም ሌላ ጎሳ ተለጣፊ አይደለም ፣ ሌላ ጎሳም ነጻ አያወጣውም ። ይህ ለእብሪተኛው ትግሬም ፣ ለሰልቃጩ ኦሮሞም ለሌላም ያው ነው ።

የአባ ዱላን ክለላ በቻልነው ልክ ታግለን የቻልነውን ያልክ ኢንፍሉወንስ አድርገው አሁን እስቴሜት ላይ እንገኛለን ። ጉራጌ ተገዶ እንጂ የክልል ስራዓት ጨርሶ እንዲጠፋ የሚፈልግ ሕዝብ ነው ።

እኔ የአማራን ሕዝብ ትግለ እደግፋለሁ ፣ ከፈለጉ ተገንጥለውም አገር ቢሆኑ ግድ የለኝም ። የአማራ ትግል የኢትዮጵያ ትግል ነው ካሉ ደሞ ለኢትዮጵያ ያረቀቁት ብሄራዊ ፕሮግራም ለመላ ኢትዮጵያ ማሳውቅ አለባቸው ። እስከ ዛሬ ፋኖ የተሳካ የትጥቅ ትግል እያደረገ ነው ። ብሄራዊ የፖለቲካ ፕሮግራም ግን የለውም ።

እኔ የኦሮሙማ ኒዎ ፋሺስት መንግስት አምርሬ እቃወማለሁ ፣ ያ ማለት ግ ን ኦሮሞን ለመቃወም የሱማሌ ደጋፊ አልሆንም ።

ስለዚህ ያልኳቸው ነገሮች ሁሉ ለ50 አመት ሳላቋርጥ ያሰብኳቸው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያለኝ ሕይወት ነጸብራቆች ናቸው

ባልኳቸው ነገሮች ውስጥ ቅራኔ የሚያዩ እራሳቸው የፖለቲካ ብልሰትና ልምዳቸው አጭር የሆነ በአንድ ነገር ላይ አቋም ይዘው ሌሎች ነገሮች ሁሉ ለዚያ ጋር የሚያቋልፉ ሰዎች ናቸው ። በአጭሩ

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 02 Mar 2024, 14:31

Semma Adam wrote:
01 Feb 2024, 22:28
Brother Horus
Your Ethiopian Manifesto post IMHO in it's fundamental logic and highest Ideal and objective is of course laudable since basically stated it points Ethiopians to first of all establish Unity based on the greater Ethiopian Identity rather than their narrow identification with their tribal ethnicity.
I have no doubt that you are pin pointing to the ultimate basic solution for Ethiopia. Actually, your suggested Solution/ Agendas.. does not just apply to Ethiopia's current sad state of affairs of disunity and division among her ethnics but across the board is reflects the sad state of affairs that is inclusive of all humans and their problems who dwell on this planet earth.
That being said,...so.. what am here to share or add to your 'manifesto ?
Well..only this>> For this 'ideal Solution' to be implemented where Peace Justice Equality and Love could reign here on our planet ( not just in Ethiopia and among Ethiopians).it all comes down to the level of Consciousness under which humans will conduct their state of affairs called 'Living Life on Earth in the best way possible'.
So far humans have not been able to achieve this highest of all Consciousness, which is Unity Consciousness that they actually can implement the idea and Live it too.
The real root of the problem is then truly elsewhere:
We know that humans like all nature are under the forces of Evolution. Evolution of Consciousness is still ongoing. Thus Humans are not a finished product. The human brain is still evolving. While in evolutionary terms (time).. we humans did just receive our Neo-cortex, our old Reptilian
( animal/egoic/ selfish survival of 'me' motivated) brain is still with us and very much operative as is evidenced by the fact that we still have WARS and more Wars going on the planet. We humans have not reached the State of Peaceful co-existence among our fellow humans. We as a species have a very very long way to go to reach that lofty State of Unity Consciousness.
Yes Horus..you are absolutely right >> Unity Consciousness states that We are All ONE..All are equal ..and there is actually no substantial difference at all among the races of the world, the original Substance of their makeup being One and the very same and their outer demarcation (individuality) being highly superficial and temporal.
Call this underlying substance God if you like or Universal Field of Unity, the Ground of Being or Existence or whatever is your preferred term for it, perhaps based on your religious conviction/ experience, your education or even your own mind's fancy.

In conclusion..I think..the poster Axumezana .. perhaps has a beneficial point to add to your overall suggestion for Ethiopia's / Ethiopians current chaos and state of affairs:
Unity in Diversity maybe the approachable ( doable?) goal for Ethiopians at the current level of Consciousness IMHO. With that in mind then..
There is no doubt in my mind..first things first... Ethiopia needs to get rid of the Apartheid TPLF installed current Constitution which accentuates Division rather than Unity among all ethnics in Ethiopia.
Despite the current chaos and darkness and disunity and PAIN..we Ethiopians are survivors being and ancient dwellers on the planet earth...we don't easily despair and vanish from the face of the earth...we [deleted] our wounds of evolution and keep going..because we have Faith ..we know there is always Light at the end of the dark tunnel. We will Prevail >>>Order out of Chaos as is the universal law.
Thank you Horus for writing this valuable manifesto. It's bright and righteous content actually matches your user name lol.
Horus is the name of the Egyptian Christ = Light!!
Yes,,,I agree with you also:
the visionary among Ethiopians (such as yourself)... should hold this Light Torch high..so that all those who are still in need of Light may find their way out of Darkness to Light.
Semma Adam,

I agree. We are still evolving in terms of the development of our collective consciousness. But as you well know all human problems, in fact all problems, are handled or solved at their scale of solution. (ተረ በተራና ደራጃ በደረጃ) I have disagreement. Differences and diversity don't lead to unity. In fact, the need for unity arises precisely because there are differences. What we must do is manage differences and diversity while intentionally and actively pursuing the path of unity and integration.

The goal of national unity, political community and regional integration is an intentional purposive collective behavior; we must do it because we want it and we want to do it. That is why I call it our national agenda - the purpose of Ethiopia.

HEER TEDY AFRO TELLING US THAT IT IS OUR STATED PURPOSE, OUR NATIONAL OBJECTIVE THAT BECOMES OUR NATIONAL UNITY. IT IS THE PURPOSE OF ETHIOPIA THAT LEADS TO A UNITED ETHIOPIA.


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 03 Mar 2024, 16:16

የፖለቲካ መሪነት እጦት በኢትዮጵያ

የአቢይ አህመድ አሊ ኦሮሞ ቡድን አገዛዝ ኢትዮጵያን መምራት አልቻለም ሲባል ምን ማለት ነው?

ሃተታና ዝብዝብ ሳላበዛ ብቁና ትክክለኛ የፖለቲካ መሪነት ማለት የኢትዮጵያን ብሄራዊ አጀንዳ ምን እንደ ሆነ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በዚህ አጀንዳ ውስጥ የተዘረዘሩት ብሄራዊ ግቦችን ውጤታማ ማድረግ ማለት ነው ። እነዚህ የአጀንዳ ዝርዝሮች ምንድን ናቸው? የውጤቱ አይነቶችስ ምንድን ናቸው ።

በማንኛውም የሰው ልጅ ተግባሮች አማካይነት የሚጠበቁት መልካም ውጤቶች አራት ናቸው ። እነሱም አንድን ጥሩ ነገር ባለበት መጠበቅ፣ አንድን ጥሩ ነገር ካለበት ወደ ላይ ማሳደግ፣ አንድን የማይፈለግ ነገር ወደ ጥሩ ነገር መለወጥ፣ እና አንድን የሌለ ጥሩ ነገር እንዲኖር መፍጠር ናቸው ። ከዚህ ወጭ ሆን ተብለው የሚፈለጉ መልካም ውጤቶች የሉም ። ይህ ሳይንስ ነው።

ከዚህ በታች በተጠቀሱት አራት የኢትዮጵያ ብሄራዊ መሰረታዊ አጀንዳዎች ላይ የአቢይ አህመድ ኦሮሞ አገዛዝ ቡድን ያመጣቸው ውጤቶች ከላይ የሰፈሩት አራት የመልካም ውጤቶች ሳይሆኑ የጥሩ ውጤት ተቃራኒዎች ናቸው ።

አጀንዳ 1
ኢትዮጵያ የምትባለው ሕዝብና አገር ብሄራዊ አንድነቷ የጸና፣ ጠንካራና የተረጋጋች (እስቴብል) አገር መሆን አለባት፣ መሆን ነው አላማዋ ። ይህ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ቁጥር አንድ ነው ። ይህ መንግስት የኢትዮጵያን አንድነት፣ ጥንካሬና መረጋጋት መጠበቅ፣ ማሻሻል፣ መለወጥም ሆነ መፍጠር አልቻለም ። እያደረገ ያለው የኢትዮጵያን አንድነት ማፍረስ፣ አገሪቱን ማዳከምና ፍጹም አለመረጋጋትን መፍጠር ነው ።

አጀንዳ 2
ኢትዮጵያዊ የተባለው ሕዝብ እንደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ (Political መCommunity) ፍትህ (እኩልነት)፣ ነጻነት እና ዴሞክራሲ መፈለግ ብቻ አይደለም፤ ያለ ፍትህ፣ ነጻነትና ዴሞክራሲ መኖር አይችልም። ሰላም የሚባል ነገር እስከ አለም ፍጻሜ አያገኝም። ስልጣኔም ሆነ እድገት የሚባል ነገር አይኖሩትም ። ስለዚህ 2ኛው የኢትዮጵያ ፋይዳ፣ የኢትዮጵያ አላማ፣ የኢትዮጵያ ፐርፐዝ ዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነትን መወለድና ማሳደግ፣ ማለትም ነጻና ፍትሃዊ ሕዝብ መሆን ነው ። ይህ መንግስት በዚህ ቁልፍ ሁለተኛ አጀንዳ ዙሪያ ፈጽሞ መውደቅ ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ፣ ፍትህ፣ ነጻነት፣ እኩለትና ሕጋዊነት ፍጹም ተጻራሪ ኒዎ ፋሺሽስት አገዛዝ ነው ።

አጀንዳ 3
3ኛው የኢትዮጵያ አጀንዳ ኢትዮጵያዊያን የሚባሉት ሕዝብን፣ ዜጋዎችን የበለጸጉ፣ ያደጉ፣ የለሙ፣ የተማሩ እና ጤንነታቸው የተጠበቀ ሕዝብ፣ ዜጋ ማድረግ ነው 3ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳና ፋይዳ ። ኢትዮጵያ እንደ አንድ አገር፣ እንደ አንድ ሕዝብ፣ እንደ አንድ ማህበር፣ እንደ አንድ ሲስተም አላማ፣ ፋይዳ አላት ። ይህን ፋይዳ ለመተግበር ነው ህያው ሆና ምትቀጥለው ። ይህ መንግስት የኢትዮጵያን ብልጽግና ፣ ትምህርትና ጤንነት መጠበቅ፣ ማሳደግ፣ መለወጥና አዲስ መፍጠር ሳይሆን እየሆነ ያለው በተቃራኒው ነው ።

አጀንዳ 4
በመጨረሻም 4ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ የሚፈጥር፣ ችግር የሚፈታ፣ የሚራመድ፣ ከከባቢውና ኢኮሎጂው ጋር የታረቀ፣ አፈሩን። ዉሃውን፣ እንሳሳውን፣ እጸዋቱን፣ አየሩን በሃላፊነት የሚንከባከብ ፣ መንፈሳዊ ፣ በፈጣሪ ኃይል የሚያምን በሞራልና ስነ ምግባር ምርሆዎች የተለጎመ ካልቸር መፍጠር፣ መገንባት እና መጠበቅ ነው የመጨረሻው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር መሆን ያለበት ይህ ነው ። ይህ አገዛዝ ይህን መሰል ካልቸር መጠበቅ፣ ማሳደግ፣ መለወጥና መፍጠር ሳይሆን እያደረገ ያለው ይህ መሰሉ የኢትዮጵያ ካልቸር መደምሰስ ነው ።

በአንድ ቃል የኦሮሞ አገዛዝ ቡድን ኢትዮጵያን መምራት አልቻለም፣ አይችልም ሲባል ስድብ ሳይሆን የኢትዮጵያን አጀንዳ ተሸክሞ ይህን ብሄራዊ ተልኮ መምራት አልቻለም ማለታችን ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 03 Mar 2024, 16:33


Post Reply