Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 04 Mar 2024, 15:32

መካሪና ገሳጭ ያጣው ያቢይ አህመድ ኦሮሞ አገዛዝ ሆይ!

መላ ኢትዮጵያን ከፋፍለህ፣ አፈራርሰህ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን ከሰሜን ደቡብ ከምስራቅ መዕራብ በኮማንድ ፖስት አፍነህ በመድፍና ድሮን እየደበደብክ ኢትዮጵያ መምራት አይደለም መግዛት አትችልም ።

የአለምና ታሪክ መሳለቂያ ትሆናለህ ። ሰራዊትና ብረትክን ሰብስበህ ወደ ኢትዮጵያ ድምበር ሂድ። የራሱን ሕዝብ በቦምድ የሚጨፈጭፍ፣ ሃይማኖት የሚያረክስ፣ መነክሴ የሚገድል አረመኔ አገዛዝ ወድቆ የታሪክ ትቢያ ውስጥ የሚጣል ስርዓት ነው ።

በጁን 16 1858 ያሜሪካኑ አብራሃን ሊንኮን ይህን ብሎ ነበር!

"A house divided against itself, cannot stand.

I believe this government cannot endure permanently half slave and half free.

I do not expect the Union to be dissolved – I do not expect the house to fall – but I do expect it will cease to be divided.

It will become all one thing or all the other.

Either the opponents of slavery will arrest the further spread of it, and place it where the public mind shall rest in the belief that it is in the course of ultimate extinction; or its advocates will push it forward, till it shall become lawful in all the States, old as well as new – North as well as South."



Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 05 Mar 2024, 03:08

ይህ አስተያየት የዛሬ 2 ዓመት May 8, 2022 እዚሁ ፎረም ላይ ፖስት ያደረኩት ነበር ። እስቲ ደግማችሁ አንብቡት፣ ስለመሪነት ዕጦት ነው የሚያነሳው ።


ለምንድን ነው ኢትዮጵያ በዚህ ሆነ በዚያ አንድ ወጥ የሆነ መሪነት አጥታ የዉሃ ላይ ኩበት የሆነችው?

የፖለቲካ መሪዎች ሰዎች ናቸው። እያንዳንዳቸው የራሳቸው ልዩ የሆነ ስብዕና እና የፖለቲካ ባህሪ አላቸው። በዚያ ፐርሰናሊቲና ቢሄቪየር አማካይነት ነው አገሪቱን አይተው ወስነው፣ ይህ ይሁን፣ ያ አይሁን ብለው የሚያዙት የሚመሩት ።

እስከዛሬ ድረስ ፖለቲካል ሳይኮሎጂ የደረሰባቸው አራት አንድን የፖለቲካ መሪ የሚነዱ ፍላጎት ተለይተው ታውቀዋል። ልብ እንበል ከአቢይ አህመድ አንስቶ እስከ አንድ ተራ ካድሬ ስለ አገር አቀፍ አጀንዳም ሆነ ስለቀበሌው ጉዳይ ሲያስብ ከውስጥ ሆነው የሚነዱት ፍላጎትች ማለት ነው።

እነዚህ ፍላጎቶሽ
(1) ገንዘብ ወይም ሃብት
(2) ማንነትና የማንነት ክብር እውቅና ማግኘት
(3) ዝና እና ስኬታማ በመሆን አድናቆትን ማግኘት
(4) ባልስልጣን መሆንና ሃያል መሆን ናቸው ።

አሁን በነዚህ መለኪያዎች መሰረት ለምሳሌ የብልጽግና ፓርቲ ለምን መምራት እንዳቃተው እንመልከት፤

1
አንድ የፖለቲካ መሪ የራሱ ፖለቲካዊ ሳይኮሎጂ ፣ የፖለቲካ ባህሪ አለው ብለናል። አንድ የፖለቲካ መሪ ገንዘብ ከሌለው ድሃ ከሆነ የመጀመሪያ ገፊ ፍላጎቱ መሰረታዊ ፍላጎት (ምግብ፣ ልብስ፣ ቤት)፣ ገንዘብና ሃብት ነው። ምናልባት ከብልጽግና 5 ሚሊዮን አባል 99% በዚህ የገንዘብ ፍላጎት የሚነዱ ናቸው። ለዚህ ነው በኢትዮጵያ ትልቁ የመሪነት ችግር የሃብት የሙስና ችግር የሚሆነው። የአቢይ ተቀዳሚ ፍላጎት ገንዘብ ስላልሆነ ብዙሃኑን የበታች ታዛዦቹን ሌቦች ይላቸዋል ። በዚህ ምንክኛት እነሱም አያምኑትም፣ እሱም አያምናቸውም ።

2
ሁለተኛው የፖለቲካ መሪ ገፊ ፍላጎት ማንነቱ፣ ጎሳው፣ ብሄረተኝነቱ ወይም የኢትዮጵያ ብሄረትኝነቱ ናቸው ። እና ከዚህ ጋር የተያያዘው ዲግኒቲ፣ ክብር፣ በሌሎች ተቀባይነት ማግኘት ነው ። ማንነት ጠባብና ሌላውን የሚለይ ከሆነ ጎሳዊነት፣ ዘረኝነት ወይም ብሄረኘት ይሆናል፣ ያ ደሞ አግላይ ፍላጎት፣ የእኔ ከሌላው ይሻላል የሚል ዘረኘትን ያስከትላል። 5 ሚሊዮኑ ብልጽግናዎች በርዕዮተ አለም ደረጃ የሚያምኑት በጎሳ ማንነት ነው ። ሺ ግዜ ስለ ኢትዮጵያ አጀንዳ ቢያወሩ ከገንዘብ ቀጥሎ የሚነዳቸው ሞቲቬሽን የጎሳ ማንነታቸው ነው ። ለዚህ ነው አቢይ ዋና ችግራቸው የብሄርና ያውራጃ ማንነት ነው ያለው። ይህ ማለት ደሞ አማራ ኦሮሞውን አያምንም ። ኦሮሞው አማራውን አያምንም። ዛሬ የትግሬ ብልጽግናን ማን ሊያምን ይችላል? ታዲያ ይህን የመሰሉ የጎሳ ጥርቅሞች እንዴት ወጥ የሆነ ኢትዮጵያዊ መሪነት ሲሰጡ ይችላሉ?

3
ሶስተኛው ለራስ ዋጋ ከመስጠት (ከሰልፍ ኤስቲም) ጋር የተያያዘ ሲሆን ዝና፣ መታወቅን ፍለጋ ነው። ያ ደሞ የስኬት መለኪያ ሆኖ ይወሰዳል። ለምሳሌ አቢይ ስኬታማ መሆንን በጣም ይፈልጋል። ለምን? ዝነኛ ለመሆን። ለምን? ሌጋሲ ቅርስ አሻራ ለመተው። ለምን? ስም ከመቃብር በላይ ስለሆነ። ለምን? ላለመረሳት ። ኢሞርታል ለመሆን። ከትውልድ ትውልድ ለመዘከር፣ ለመታውስ። ይህ ትልቁ የአቢይ ነጂ ፍላጎት ነው። ሰው በስራው በስኬቱ ሲታወስ ይኖራል። አቢይ በዚህ እጅግ የሚገፋ መሪ ነው። ሰልፍ ኤስቲምና የስኬት ፍላጎት ነው የሚገፋው ። እሱ በዚህ ተገፍቶ ፕሮጀክቶች ለመፈጸም ሲፈልግ የቀሩት ካድሬዎች ገፊ ፍላጎት ዝና ሳላሆነ የነሱን ፍጹም ትብብር አያገኝም ። ለዚህ ነው የበላይ መሪዎች የበታቾቻውን በጥቅማ ጥቅም ለመግዛት የሚገደዱት ። አቢይ በንግግር፣ በስልጠና ሊያሸንፋቸው ቢሞክርም አልቻለም።

4
አራተኛውና ከፍተኛው ስልጣንና ሃይል መሻት ነው ። በግለሰብ ደረጃ የፓወር ፍላጎት ሳይኮሎጂ የሌላቸው መሪዎች ለስልጣን ግድ የላቸውም። ግን ሁልግዜ ስለስልጣንና ሃይል የሚያሰሉ መሪዎች አንድ ነገር ለማደግ ሲሰበሰቡ የሚያስጨንቃቸው ያገር አጀንዳ ሳይሆን እስታተስ ማኔጅመንት ይባላል። ስለስልጣናቸው ሲጋጋጡ ነው ግዜው የሚጠፋው ። በተለይ የስልጣን ክፍፍል በጎሳ በሚቀመርበት ፓርቲና መንግስት ይህ እጅግ ግዙፉ ቀውስ ነው። ይህ ሁለተኛው ያቢይ ዋና ገፊ ሞቲቬሽን ነው ። ለምሳሌ በአቢይና በትግሬዎቹ መሃል አልታረቅ ያለው ይህ ነጂ የስልጣን ፍላጎት ነው። ልብ በሉ ትግሬዎቹ ሃብት ነበራቸው ። የራሳቸው ጎሳ የነካባቸው አልነበረም ። ለዝናም ድግ የላቸውም። ስልጣንና ሃይል ብቸኛ ፍላጎታቸው ነው። አቢይም ከልጅነቱ ጀምሮ ስልጣን እና ሃይል የሚፈልግ ሰው ነው ።
ይህ ብቻ አይደለም ...

አቢይ ብዙ ግዜ በሰልፍ ኤስቲምና ስኬት ዝና ላይ ያለ ምሪ ነው ። ለምሳሌ አንድ አወዛጋቢ እርምጃ ወስዶ በሌሎች መጠላት የማይፈልገው ስሙ እንዳይጠፋ፣ እንዳይጠላ፣ አሻራው ሌጋሲው እንዳይበላሽበት ነው።

ሁለት ቁጥር ውስጥ ካሉት የጎሳ ማንነት ክብር ፈላጊዎች ጋር ችግር አለው። ከኢትዮጵያ ብሄረተኞች ጋርም ችግር አለው። እሱ የአፊሊዬሽን ጥማተኛ ስላሆነ ። በቅርብ ሲናገር የጎሳ ብሄረተኛም የኢትዮጵያ ናሽናሊስት ምሆን መጥፎ ነው ። ጥሩ ነገር አርበኛ መሆን ነው ብሏል ። የኢትዮጵያ ናሺናሊስት አትሁኑ ያለ የመጀምሪያው የኢትዮጵያ መሪ ነው። ይህ ትልቅ ችግር ነው። የሱ ጥማት የራስ ከፍታና ዝና ስለሆነ!

ትልቁ ጥያቄ አቢይ ስለ ፓወር ያለው ሳይኮሎጂ ምንድን ነው የሚለ ነው። ለምንድን ነው የሚናገረውና የሚሰራው አንድ መሆን ያልቻለው? አቢይ ጠንካራ የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ በሃይል አማካይነት ብዙ ነገር መለወጥ ሲችል ያ እንዳያደርግ ፐርሰናሊቲው ያግደዋል ። እሱ እንደ ዝነኛ አርቲስት መወደድን የሚሻ እንጂ ከማል አታቱርክ መሆን የሚችል ስብዕና የለውም ።

ለምሳሌ በዝና ጥማት የሚነዳ ሰው ለምን መደመርን ይፍለጋል? በስልጣንና ሃይል መገፋት የሌሎችን ፍቅር አያስገኝም። ኤፌክቲቭ እና ተግባሪ መሪ ምናልባት መፈራትን እንጂ በመወደድ ስመ ገናና እና ታዋቂ አይሆንም። ለዚህ ነው አቢይ በአፉ ስለ ጠንካራ እርምጃዎች ተናግሮ በትግባር ወደ ኋላ የሚለው!!

አቢይ በመወደድ ዝነኛ መሆንን እንጂ በመከበር ወይም በመፈራት ጠንካራ መሪ መባልን አይፈልግም! ፐርሶናሊቲው ስብ ዕና ያ ስላልሆነ!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 14 Mar 2024, 01:19

ኢትዮጵያ ምንድን ናት? ኢትዮጵያ ማለት ምን ማለት ነው? የኢትዮጵያ አጀንዳ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ይህ ነው!!!!


Fiyameta
Senior Member
Posts: 12679
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Fiyameta » 14 Mar 2024, 01:48

:P :P :P :P


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 19 Mar 2024, 21:40

የሆረስ ማኒፌስቶ ምንድን ነው?

የሆረስ ማኒፌስቶ የኢትዮጵያዊነት ማኒፌስቶ ነው ። ያ ምን ማለት ነው?

ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያዊያን ስርዓተ ሕይወት እና ስርዓተ ተግባር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካና ሶሺያል ሳይንስ ነው ። ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያ ፖለቲካና ሶሺያል ቴኦሪ ነው። በአንድ ቃል ኢትዮጵያዊነት አጀንዳ ነው ። ኢትዮጵያዊያን የተባሉት ሕዝብ በሶሺያ፣ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ካልቸር እራሣቸውን የሚያደራጁበትና የሚመሩበት ፍልስፍናና እና ንድፈ ሃሳብ ነው።

ለኢትዮጵያ ተበሎ የተጻፈ ወይም የተነደፈ ሌላ የውጭ ሃሳብ፣ ርዕዮተ አለም ወይም ርዕዮተ ፖለቲካ የለም ። ያለው ለኢትዮጵያ ተበሎ የተቀመረው፣ ከኢትዮጵያዊያን ሕይወት የተቀዳውና የተሰራው ኢትዮጵያዊነት የተባለው ፍልስፍና ቲኦሪ ወይም ርዕዮተ ኢትዮጵያ ነው ።

በተግባራዊ ጭብጦቹ የዚህ ርዕዮተ ኢትዮጵያ ይዘቶች ከላይ የኢትዮጵያ አጀንዳ ብዬ በ4 መደቦች ጠቅሻቸኋለሁ ።

ይህን፣ ነው የኢትዮጵያ (የሆረስ) ማኒፌስቶ የምለው
Last edited by Horus on 20 Mar 2024, 02:45, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 20 Mar 2024, 02:16

ኢትዮጵያዊነት አርት ነው! ካልቸር ነው!


Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 20 Mar 2024, 23:21

ይህን ሃሳብ ደጋግሜ የማነሳው አንባቢ ኢትዮጵያዊያን የምር እንዲያሰላስሉት ነው ።

ኢትዮጵያዊ የሚባሉት ሕዝብ እራሳቸውን በስነ አገር፣ በስነ ፖለቲካ፣ በስነ ኢኮኖሚና በስነ ካልቸር ለማደራጀትና በስልጣኔ ለመግነን ለሌላ ሕዝብ የተቀመረን ሃሳብ ሊኮርጁ አይችሉም ። የስልጣኔ ሞዴል መፈለግ ጠቃሚ ቢሆንም በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያለን ግድፈት ለማረም እንጂ የሌላን አገር ሳይንስ ለመኮረጅ ሊሆን አይገባም ።

ከላይ እንዳልኩት ኢትዮጵያዊነት እራሱ ሳይንስ ነው ፤ እራሱ ፍልስፍና ነው፣ እራሱ ቲኦሪ ነው ፣ እራሱ ዘዴ፣ እራሱ ተግባር ነው።

ኢትዮጵያዊነት የተባለው ሳይንን የኢትዮጵያ አገረ መንግስት ፍልስፍና፣ ቲኦሪ፣ ዘዴና ተግባር ነው

ኢትዮጵያዊነት የተባለው ሳይንን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፍልስፍና፣ ቲኦሪ፣ ዘዴና ተግባር ነው

ኢትዮጵያዊነት የተባለው ሳይንን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ፍልስፍና፣ ቲኦሪ፣ ዘዴና ተግባር ነው

ኢትዮጵያዊነት የተባለው ሳይንን የኢትዮጵያ ካልቸር ፍልስፍና፣ ቲኦሪ፣ ዘዴና ተግባር ነው

አሁን በትንሹም ቢሆን ሃሳቤ የገባችሁ ይመስለኛል ። ሃሳብ የሚወለደው ከታሪክ፣ ከልምድና ከተግባር ነው። ኢትዮጵያዊያን ለሺዎች ዘመናት እራሳቸውን ያደራጁበት ከራሳቸው ህልውና፣ ታሪክ፣ ልምድና ተግባር የተፈተለ የራሳቸው የኑሮ ሳይንስ አላቸው ።

የዚህ ትውልድ ሃላፊነት ደሞ እዚም እዛም እየኮረጀ መለጠፍ ሳይሆን ይህን ኢትዮጵያዊነት የተባለውን ሳይንስ ምን እንደ ሆነ ማየትና መተግበር ነው !

Dark Energy
Member
Posts: 1091
Joined: 24 Feb 2022, 14:08

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Dark Energy » 20 Mar 2024, 23:57

Oldie Guragie Horus,

Ethiopian population has not reached the 130 million landmark yet. :lol: :lol: Your masta…. The little twerp’s prediction for the next ten years put it as the 130 million milestone population size. :lol: :lol: Guragies always boast out of proportion when it comes to numbers. :lol: :lol: We are not talking about dollars you know ! :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 21 Mar 2024, 01:04

Dark Energy wrote:
20 Mar 2024, 23:57
Oldie Guragie Horus,

Ethiopian population has not reached the 130 million landmark yet. :lol: :lol: Your masta…. The little twerp’s prediction for the next ten years put it as the 130 million milestone population size. :lol: :lol: Guragies always boast out of proportion when it comes to numbers. :lol: :lol: We are not talking about dollars you know ! :lol: :lol: :lol:
World Bank reported Ethiopian population at 123 million for 2022. The well established rate of growth is that population doubles every 20 years.

In 2042 Ethiopia will have 250 million people.

So, get out of your dark energy, join the Light! Knowledge is not only power, KNOWLEDGE IS LIGHT!
https://www.worldbank.org/en/country/ethiopia/overview

Dark Energy
Member
Posts: 1091
Joined: 24 Feb 2022, 14:08

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Dark Energy » 21 Mar 2024, 01:49

Horse,
If you don’t know the concept of Dark Energy, it is the energy that is pushing galaxies apart. Since the amount of Energy in space is constant, more space translates dispersed energy, possibly leading the end of the Universe to a freezing hollow space. The end for sure will be either freezing or reversing back to the previous of the Big Bang state. See you then. :lol: :lol: :lol:

https://en.m.wikipedia.org/wiki/Dark_energy

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 21 Mar 2024, 02:30

Dark Energy wrote:
21 Mar 2024, 01:49
Horse,
If you don’t know the concept of Dark Energy, it is the energy that is pushing galaxies apart. Since the amount of Energy in space is constant, more space translates dispersed energy, possibly leading the end of the Universe to a freezing hollow space. The end for sure will be either freezing or reversing back to the previous of the Big Bang state. See you then. :lol: :lol: :lol:

https://en.m.wikipedia.org/wiki/Dark_energy
This is a thread about a nation called Ethiopia located on planet earth. An intelligent student would know the distinction between the cosmology of black holes and the science of human society. Please no more comment. I repeat my advice to you - get out of darkness & stop wasting your time.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 24 Mar 2024, 22:56

ኢትዮጵያ በአራት ብሄራዊ ቀውሶች ውስጥ ተወጥራለች ፤ እነሱም አንድነት ማጣት፣ ፍትህ መጥፋት፣ እድገት መቆርቆዝ እና የባህል መላሸቅ ናቸው።

በዚህ አለም ላይ ማንኛውም ነገር አንድ ካልሆነ ሊቆም፣ ሊጸና አይችልም። አንድነት የሌለው ነገር ሁሉ ደካማና ፍርስ ነው ። ስለሆነም ኢትዮጵያ ዛሬ እንደ አገር አንድነት አልባ እጅግ ደካማ አገር ነው ። ለዚህ የኢትዮጵያ መፍረክረክና አገራዊ ደካማነት በቁጥር አንድ ደረጃ ተጠያቂው የጎሳ ፖለቲካና የጎሳዎች ክፍፍል፣ የጎሳዎች ቅራኔ ሲሆን የዚህ ቀውስ አጠንጣኞች በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉት የጎሳ ፖለቲካ መሪዎች ናቸው ።

ይህ የጎሳ ፖለቲካና ቅራኔ በመላ አገሪቱ የሰፈነውን ሁከት፣ አመጽ፣ ጦርነትና ታሪካዊ ሰላም አጥነትን አስከትሏል ። ስለሆነም የጎሳ ፖለቲካ በዜጋ ፖለቲካ ሳይተካ ኢትዮጵያ እንደ አገርም ሆነ እንደ ሕዝብ ሰላም ሊያገኙ በፍጹም አይችሉም ።

ሁለተኛው የፍትህ መጥፋት ቀውስ ነው። በአንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ውስጥ ፍትህ ብቸኛው የችግሮች ሁሉ መፍትሄ ነው። ሰዎች መገዛት ያለባቸው በሰው ሳይሆን በሕግ ነው ። ሕግ ገዝነትም ሆነ ማኛውም የሕግ ሴራ መቆሚያ መሰረቱ ፍትህ ነው ። ፍትህ ልጆች፣ የዜጋዎች እኩልነጥ የመብቶችና ግዴታዎች ሚዛናዊነት፤ ከዚያ ሲያልፍም በሰዎች ወንድማማችነት፣ ስምምነትና ፍቅር ላይ የሚቆም ብቸኛው የአገር ፣ የሕዝብ ፣ የማህበረሰብ ማደራጃ መሳሪያ ነው።

ፍትህ ሲጠፋ የሚከተለው ግፍ፣ ጭቆና፣ አመጽና ሰላም አጥነት ነው ። ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ፍጹም ሰላም አጥ የሆነችው ፍትህ አልባ የግፍና ጭቆና ምድር ስለሆነች ነው ። ለዚህ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኦሮሞ ጎሳ አገዛዝ ነው።

ሶስተኛው የእድገት መቀጨጭ ቀውስ ነው ። ኢትዮጵያ ዛሬም ሰው በረሃብ የሚሞትባት አገር ነች ። ኢትዮጵያ ዛሬም በምዕራብ የምግብ እርዳታ የምትኖር፣ የምድሃኒት እራዳታ፣ የትምህርት እርዳታ የምትኖር አገር ነች ።

ለዚህ የኢኮኖሚ ቀውስና እድገት መቀጨጭ ዋና ተጠያቂዎቹ የጎሳ ክፍፍል፣ የጎሳ ገበያ ተዋቅሮ፣ ከኢኮኖሚ ሳይይንስ የተጻረረ የጎሳ ቩዱ ወይም ጥንቆላ ኢኮኖሚ ህሳቤ ናቸው ። የጎሳ ንድፈ ሃሳብ የኢኮኖሚ እድገት ፍጹም ተጻራሪ ህሳቤ ነው ።

የኢኮኖሚ ቀውስና ድህነትና ጎሰኛነት ሲዋሃዱ የሚንሰራፋው ሌብነት፣ ዝርፊያ፣ ሙስና ፣ኢኮኖሚያዊ ግፍ ነው። ስለሆነም በጎሳ ስሌትና ኮታ ላይ የቆመ ኢኮኖሚና ቢሮክራሲ እስካሉ ድረስ የተደራጀ መንግስታዊ ሌብነትና ቆሻሻ ሙስና በፍጹም ሊወገዱ አይችሉም። የተደራጀ መንግስታዊ ሙስና የፍትህ መጥፋትና የግፍ አገዛዝ ሌላው ገጽታ ነው ።

አራተኛው ቀውስ የባህል መላሸቅ ነው። የግፍ አገዛዝ የፖለቲካ ካልቸር ነው። መንግስታዊ ሙስናና ሌብነት ኢኮኖሚ ካልቸር ነው። የሞራልና ስነምግባር መላሸቅ ማህበራዊ ጥፉ ካልቸር ነው ።

ይህን መሰል የካልቸር ውድቀት ማለት ደሞ የማይፈጥር ካልቸር፣ ችግር የማይፈታ ካልቸር፣ ፈሪሃ ፈጣሪ የራቀው ብሽቅ ካልቸርና ከተፈጥሮ ጋር የተጣላ አውዳሚ ባህል ማለት ነው ።
ለምሳሌ አራቱ አቢይ የስራ ማደራጃ ጽንሰ ነገሮችን ብቻ እንመልከት፤ አንድነት፣ ትብብር፣ ቅንብርና ቅንጅት።

የአንድነት እጦት፣ የተለያዩ ጎሳዎች አንድ አይነት ስራ በአንድ ቦታና በአንድ ግዜ በአንድነት መስራት አይችሉም ። ይህ የኮላቦሬሽን እጦት ይባላል።

የትብብር እጦት፣ የተለያዩ ጎሳዎች የተለያዩ ስራዎችን አንድ ቦታ፣ በአንድ ግዜ በትብብር መስራት አይችሉም። ይህ የኮኦፐሬሽን እጦት ይባላል።

የቅንብር እጦት፣ የተለያዩ ጎሳዎች አንድ አይነት ስራ በተለያየ ቦታና በተለያየ ግዜ ተቀናብረው ሊሰሩ አይችሉም። ይህ የኮኦርዲኔሽን እጦት ይባላል።

የቅንጅት እጦት፣ የተለያዩ ጎሳዎች የተለያየ ስራ በተለያየ ቦታና በተለያየ ግዜ በቅንጅት መስራት አይችሉም ። ይህ የአላይንመንት (አላያንስ) እጦት ይባላል።

በአንድ ቃል በጎሳ ፖለቲካ፣ በጎሳ ኢኮኖሚና በጎሳ ቅራኔ የተቃወሰ ማህበረሰብ ስራውን በአንድነት፣ በትብብር፣ በቅንብርና በቅንጅት ማከናወን አይችልም ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 29 Mar 2024, 22:43

የኢትዮጵያ አጀንዳ ቁጥር 1 ሶስት ነገሮችን ይዟል፤ አንድነት፣ ጥንካሬና መረጋጋት ። የመንግስት መረጋጋት ወይም እስታቢሊቲ ምን ማለት ነው? የአንድ መንግስት ጽናትና መንገዳደግ እንዴት ይለካል? እንዴት ይታወቃል? መልሱ እነሆ። ይህን የጻፍኩት ልክ የዛሬ 29 አመት ነበር ።

አንድ የፖለቲካ ስርዓት የጸና ነው ወይስ አይደለም ለማለት መኖር ያለባቸው ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
May 19, 1995
1
ስርዓቱ ፕሉራሊስት ወይም ብዝሃዊ መሆን አለበት። የጥቅሞችን ልዩነት የሚገነዘብ የልዩነት አንድነት አንድነት መሆን አለበት፤ ማለትም ልዩነቶች ያቀፈ አንድነት ሳይሆን አንድ የሆኑ ልዩነቶች ሲሆን ነው። አንድነት በሚመስል ስርዓት ውስጥ ልዩነቶች ማራመድ ሳይሆን ልዩነቶችን እንዳሉ አውቆ በአንድነት ስርዓት ውስት መደራጀት ማለት ነው።
2
የስርዓቱ መሰረት ግለሰቦች መሆን አለባቸው። ማለትም ከቡድኖች በተለይም ከጎሳ ቡድኖች ይልቅ ግለሰቦች ሉአላዊና፣ የበላይና ወሳኝ መሆን አለባቸው።
3
የተወሰኑ ሕዝቡን የሚወክሉ ተቋማት ካሉ ያልተወከሉትን ለመጨመር ፈቃደኛና ክፍት መሆን አለባቸው። መስፋት የሚችሉ ሆነው በየግዜው ያልተወከለው ክፍል እየተነሳ አዲስ ነጻ ተቋም የማይፈጥርበትና ያሉትን የማያርስበት ስርዓት መሆን አለበት ።
4
የህብረተሰቡ ኤልቶች ልሂቃን ወይም የገዥ ክፍሎች ሌላውን የሚያካፍሉ መሆን አለባቸው። የአንድ ኃይማኖት፣ የአንድ ጎሳ፣ የአንድ ልማድ ወገኖች ብቻ መሆን የለባቸውም።
5
በቁጥር 2 ከተጠቀሰው ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ ውስጥ ሰፊ ወይም በቂ መሃል ሰፋሪ መደብ (ሚድል ክላስ) ወይም የከበርቴ ክፍል የሆነ የሲቪል ኃይል መኖር አለበት ።
6
ያለው የመንግስት ጸባይ ወይም ባህርይ ወይም አይነት ሴኩላር ኢኃይማኖታዊ ማለትም ዘመናዊ የሲቪል መንግስት በኃይማኖት ላይ ያልተመሰረተ መሆን አለበት ።
7
ስርዓቱ (መንግስቱ) የተወሰኑ የጥቅም ግጭቶችን እንደ ጤነኛ ነገር ተቀብሎ ለማስተናገድ ተቋማትን ማዘጋጀት አለበት፤ እነዚህ ተቋማት በሃብታምና ድሆች መሃል ፣ በባህሎች መሃል፣ በቋንቋዎች መሃል የሚነሱ የጥቅም ግጭቶችን የሚያካትት መሆን አለበጥ
8
በስርዓቱ ውስጥ ያለው የኃብት ልዩነት ሰማይና ምድር መሆን የለበትም። በጣም ሃብታም ጥቂቶች እና በጣም ድሃ ብዙዎች የተከፋፈለ ስርዓት አይረጋም፤ ለምሳሌ ስራ አጥነት 40% የደረሰበት መንግስት ። የኃብት ልዩነት በሰፋበት ስርዓት የፖለቲካ እኩልነት ሊኖር አይችልም።
9
የኢኮኖሚ እድገት ወይም ብልጽግና በረጅሙም ቢሆን መኖር አለበት ።
10
ሕብረተሰብ እራሱን ከወረራ የሚጠብቅበት ሰራዊትና ዲፕሎማሲ እንዲኖረው ያስፈልጋል ፤ነገር ግን የጦር ሰራዊቱን ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና ከመፈንቅለ መንግስት መቆጣጠር የሚችል መንግስት መሆን አለበት ።
11
በስርዓቱ ውስጥ በግላዊ ሕይወትም ሆነ ማሕበራዊ ሕይወይ የሲቪል ነጻነቶች መኖር አለባቸው።
12
በስርዓቱ ውስጥ የፖለቲክስ ውይይትና ሙግት ባህል ማለትም በአማራጭ ፖሊሲዎች ማሻሻያዎች ላይ የመፋጨት ባህል መኖር አለበት ።
13
የገዥው ክፍል መሪዎች የፖለቲካ ፈቃድ ወይም መሻት ማለትም በዴሞክራሲና ፍትህ የሚያምኑ መሆን አለባቸው ።

እነዚህ 13 ሁኔታዎ ወይም አብዛኛዎቹን የሚያካትት መንግስት ብቻ ነው የተረጋጋ ወይም እስቴብል አስተዳደር የሚባለው ። በዚህ መለኪያ መሰረት የአቢይ አህመድ ኦሮሞች መንግስት አንዱንም እንኳ ሙሉ በሙል አያሟላም ። ለምሳሌ ቁጥር 10ን ብንመለከት የተወሰነ መከላከያ ቢኖረውም ዲፕሎማሲ የለውም ።

በነዚህ 13 መለኪያ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ በሙሉ ያልተረጋጋ አነስቴብል መንግስት ነው።

ሆረስ ዐይነ ብርሃን




Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 22 Apr 2024, 00:36

ሁሌም እንደምለው በአንድ ማህበረ ሰብ ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ መፍትሄው ፍትህ ነው ። ፍትህ ብቸኛው መፍትሄ ነው ። ፍትህ ደሞ ያለ እኩልነት ሊኖር አይችል። ነገሮች ሁሉ እኩል፣ ተመጣጣኝ፣ ሚዛናዊ ፣ ልክ፣ ቅጥ የሚሆኑት እኩልና ፍትሃዊ ሲሆኑ ነው። የነዚህ ሁሉ መሰረት ደሞ ፍቅር ነው። በሰዎች መካከል ፍቅር ከሌለ ለምንም ነገር ትክክለኛ ፍትሃዊ መፍትሄ ሊኖር አይችልም።

Digital Weyane
Member+
Posts: 8540
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Digital Weyane » 22 Apr 2024, 02:24

ግዙፍ የውጪ እዳ ያለባት እና በምፅወታ ብቻ የምትኖር አገር ይዘን በምግብ ራሳችንን ለመቻል ጥረት ከማድረግ ይልቅ እውነቱን እያድበሰበስን <<ማኔፌስቶ>> ገለመሌ እያልን ራሳችንን ሁሌ እንሸውዳለን። ከሙታን የማንሻል በቁም የሞትን ሬሳ ነን። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ! :cry: :cry: :cry: :cry:

Selam/
Senior Member
Posts: 11849
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Selam/ » 22 Apr 2024, 08:23

ኡኛ የኤርትራ ኩፍለ ሃገር ዜጎች፣ በበቅሎና በፈረስ የሚጠቀም ሶስት ሚሊዮን ህዝብ ይዘን፤ ሶስት ሚሊዮኑን ደግሞ እርዳታ ወደሚሰጡት ሰዎች ሃገር አባርረን፣ ኢትዮጵያ እንዴት የውጪ እዳዋን በፍጥነት አስወግዳ በምግብ ራሷን እንደምትችል ከሰሜን ኮርያ ጋር ሆነን ለ30 ዓመት ያካብትነው ልምድ ያለሙንም ስስት ለማካፈል ዝግጁ ነን። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ! :roll: :roll: :roll:
Digital Weyane wrote:
22 Apr 2024, 02:24
ግዙፍ የውጪ እዳ ያለባት እና በምፅወታ ብቻ የምትኖር አገር ይዘን በምግብ ራሳችንን ለመቻል ጥረት ከማድረግ ይልቅ እውነቱን እያድበሰበስን <<ማኔፌስቶ>> ገለመሌ እያልን ራሳችንን ሁሌ እንሸውዳለን። ከሙታን የማንሻል በቁም የሞትን ሬሳ ነን። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ! :cry: :cry: :cry: :cry:

Post Reply