መስከረም 15 ቀን 2016 ዓም
አሁናዊ የፋኖ አላማ ምንድን ነው? የፋኖ ግዜያዊ ግብ ከተሞችን በመቆጣጠር መንግስትና አስተዳዳሪ መሆን አይደለም። የሲቪል መንግስትና አስተዳደር በየከተማው ቢያቋቁም ለነዚያ ሁሉ ፖሊስና ደህንነት በማዘጋጀት የሽምቅ ተዋጊም መንግስትም ሊሆን አይችልም ። ዛሬ ላይ ያን ለማድረግ እሚያስችለው የሲቪል አደረጃጀት የለውም ። ስለሆነም እስከ ተወሰነ ድሮ የነበረው የአስተዳደር መዋቅር አገልግሎት በመስጠት እንዲቀጥል ይፈልጋል። በማንኛውም ግዜ መንግስት ከሌለ የሚከተለው አናርኪና ስርዓትአልበኝነት ስለሆነ።
በመሆኑም የፋኖ ግዜያዊ አላማ የብልጽግናን የበላይ አለቆችን የፖሊስና ሚሊሺያ አለቆችን በማስወገድ የአቢይ አህመድ አስተዳደር በአማራ ምድር ሽባ ማድረግ ነው ። በድሮ አዮታዊ ቋንቋ ይህ የትግሉ ኔጋቲቭ ፕሮግራም ይባላል፤ ያለው ስርዓት ማፈራረስ ይባላል ። የፋኖ መንግስት ማቋቋም የትግሉ ፖዘቲቭ ፕሮግራም ይባላል።
በመላ አማራ ተዘርቶ ያለው የፋኖ ኃይል በአንድ እዝ የሚመራ ወጥ ሰራዊት ይሁን ወይ አይሁን የሚለው በቀላሉ የሚታይ ጥያቄ አይደለም ። አሁን ላይ አንዱ ትልቁ የፋኖ አድቫንቴጅ ያልተማከለ፣ ራስ እዝ፣ እንደ አካባቢው ሁኔት በነፋስ ፍጥነት የሚንቀሳቀስ አደረጃጀት መሆኑ ነው ። ያልተማከለ ሰራዊትን ማኔጅ ማድረግ እጅግ ይቀላል ። ስለሆነም ምን ምን አይነት ነገሮች ሲሟሉ ነው አንድ እዝ ያለው ወጥ ሰራዊት መሆን የበለጠ አድቫንቴጅ የሚኖረው የሚለው ቁልፍ ጥያቄ የሚያውቁት ራሳቸው የፋኖ ታክቲከኞች ናቸው ።
የአቢይ አህመድ አሁናዊ አላማ ምንድን ነው? የብርሃኑ ጁላ ስሌት ፋኖን በየከተማው እና ባላገሩ እያሳደደ ማጥፋት (የሽምቅ ተዋጊን በዚያ ዘዴ ማጥፋት ስለማይቻል) አይደለም። በያንዳንዱ የአማራ ከተሞች ውስጥም የብልጽ ግና አስተዳደር ለመመለስ ወይም ለማስፈን እና ለመከላከል አይደለም። ፋኖ እነዚህን አስተዳደሮች በማንኛውም ግዜ ሊያፈርሳቸው ስለሚችልና እንዲሁ ፋኖ ከተሞችን ይዞ የማስተዳደር አሁናዊ አላማ እንደ ሌለው ስለሚታወቅ ።
የአቢይ አህመድ አሁናዊ ዋና ስጋት ፋኖ ማዕከላዊ መንግስትን ለመገዳደር የሚያስችለው ወታደራዊ አደረጃጀትና ቁመና እንዳይዝ ለማድረግ ነው ። አሁን ያለው ዉጊያ በዚሁ መልክ ከቀጠለና የመከላከያ ወታደሮችና መሳሪያቸው ቀስ በቀስ ቀደ ፋኖ ከተሸጋገረ ፋኖ እራሱ ብሄራዊ መከላከያነት ማደርጉ የግዜ ጉዳይ ብቻ ስለሚሆን ። ለዚህም ነው ዛሬ ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ኮንሰንትሬት አድርጎ የጄኔራል ሙሃባውን ጦር ሊወጋ እየተዘጋጀው ያለው ። የሙሃባው ፋኖ ከሁሉም በላይ የተደራጀ ሰራዊት ነው ስለሚባል ።
በእኔ እምነት ይህን የብርሃኑ ዘመቻን ፊት ለፊት ገጥሞ ኃይል ማባከን አያስፈልግም ። ብርሁን ሰሜን ወሎ ሲመጣ ፋኖ ደቡብ ወሎ ወርዶ ሌላ ጥቃት ማድረግ ነው ያለበት ። ጠላት አድቫንስ ሲያደርግ አፈግፍግ ይላል ሳይንሱ ። ከዚያ የብርሃኑን ሰራዊት በትናንሽ ቡድን በመከፋፈል ማምከን ነው ።