አንድ ተማሪ ጋሼ ስለ ጠቅላላ እዉቀት ጥያቄ አለኝ ብሎ ተነሳ።
ተማሪ፦ ዝሆንን ፍሪጅ ዉስጥ ለማስገባት ብንፈልግ እንዴት አድርገን እናስገበዋለን?
መምህር፦አላወኩም
ተማሪ፦ቀላል እኮነዉ ፤ፍሪጁን በመክፈት፥
ሌላም ጥያቄ አለኝ መምህር፦እሺ ቀጥል
ተማሪ፦አህያንስ ፍሪጅ ዉስጥ ማስገባት ብንፈልግስ እንዴት አድርገን ነዉ የምናስገባት?
መምህር፦ይችማ ቀላል አይደለች፣ ፍሪጅን በመክፈት
ተማሪ፦አይደለም ፤መጀመርያ ዝሆኑን ማዉጣት
መምህር፦ይገርማል
ተማሪ፦አሁንም ጥያቄ አለኝ
መምህር፦እሺ
ተማሪ፦ሁሉም እንስሳ የነብር ልደት ሆኖ ሄደዋል አንድ እንስሳ ብቻ ቀረ ማነዉ እሱ?
መምህር፦አንበሳ ምክንያቱም ሁሉንም እንስሳት ስለሚበላቸዉ።
ተማሪ፦አይደለም፣አህያ ነች ምክንያቱም ከሰሀታት በፊት ፍሪጅ ዉስጥ ስለነበረች።
መምህር፦እየቀለድክ ነዉ?
ተማሪ፦አሁን የመጨረሻ ጥያቄ ባህር ተሻግረህ ለማለፍ ፈራህ ምክንያቱም አዞ አለ ብለህ ስለምታስብ።እንዴት ብለህ መሻገር ትችላለህ?
መምህር፦በጀልባ ነዋ !
ተማሪ፦ አይደለም ፣እየዋኘህ ምክንያቱም አዞ የነብርን ልደት ለማክበር ስለሄደ