-
- Senior Member
- Posts: 14412
- Joined: 05 Jun 2013, 13:00
ለፈገግታ ፥ የዶክተር ኣብዮት የቁረጡልኝና እሰሩልኝ የናዚ ጩሀት በናዝሬት
ቦታው፥ የብልጽግና ስብሰባ ኣዳራሽ
ጊዜ ፥ 11፡55 ገደማ
ገጸ-ባህሪያቶች ፥ ወይዘሮ ኣቶና ዶክተር ኣብዮት
ወይዘሮ ፥ ( የዶክተር ኣብዮት ትኩረት ለመሳብ እየሞከሩ) ዶክተር ኣብዮት ዶክተር ኣብዮት !
ዶክተር ኣብዮት ፥ ( ሊሰማ ዝግጁ ባለመሆኑ በሚያሳይ ፊቱ ወደ የተከበረች ውድ ሙፍሪያት ያዞራል ፡ ከንቲባ ኣዳነች ኣበቤ ትስቃለች! ምን ይሆን ያሳቃት ?)
ወይዘሮ ፥ ዶክተር ኣብዮት ! ኣብዮትየ ! የኔ ኣብዮት ! የኔ ኣብዮት !
ኣቶ ፥ (በወይዘሮ ኣጠገብ የሚገኘው ) ቆይ እኔ ልሞክር ተውልኝ ! የኔ ህዝባዊ ኣብዮት! የኔ ህዝባዊ ኣብዮት !
ዶክተር ኣብዮት ፥ ( በንዴት) ኣንተ ቀልደኛ ፡ ቀልደኛ እየመሰልክ የማስፈራርያ መልእክት " ፋኖ በጀሮህን ኣጠገብ እያስተነፈሰ ነው " ምናምን ለማስተላለፍ ስለ ፈለግክ ወደ ወህኒ-ቤት እልክህኣለሁ ።
ወይዘሮ ፥ እንዴ ምነው የኔ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኣብዮት ተናደው ኣማራን ወደ እስር-ቤት ለመላክ ከፈለጉ ለምን ከወይዘሮ ዝናሽ በትዳር ይኖራሉ ? ኣማራን ጠልተህ ዝናሽን ወደህ ለመኖር ኣይቻልም ።
ዶክተር ኣብዮት ፥ ፈረንጆች " don't judge a book by its cover " ሲሉ ኣልሰማሽም መሰለኝ ። ለምሳሌ ልደቱ ኣያሌው ውሰጂ !
-
- Member
- Posts: 883
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
- Contact:
Re: ለፈገግታ ፥ የዶክተር ኣብዮት የቁረጡልኝና እሰሩልኝ የናዚ ጩሀት በናዝሬት
መልካም ኣዲስ ዓመት! Abe Abraham;
ለፈገግታም ባይሆን ለተሳትፎ እኔም ላዋጣ ...
የእንቁጣጣሽ ዕለት ነው … ሁለት ህፃናቶች የወይዘሮ ኣዳነች አበቤን ቤት የውጭ በር ያንኳኳሉ። ጥበቃው ከፍቶ “ምንድነው?” ብሎ ሲጠይቅ “የእንቁጣጣሽ ንድፍ (ሥዕል) ልንሰጥ ነው” ይላሉ። ወይዘሮዋ በረንዳ ላይ ቆመው እየተመለከቱ ነበርና ለጥበቃው እንዲያስገባቸው ትዕዛዝ በመስጠት ወደ ግቢው ሲዘልቁ … ሴትየዋ ለ EBC የሚሰጥ ለገፅታ ግንባታ የሚሆን ዜና ከመና እንደወረደላቸው በመቁጠር አጋጣሚው በሞባይል ስልክ እንዲቀረፅ ያደርጋሉ።
ከዛም … የህፃናቶቹን ጭንቅላት እያሻሻሹ “እንኳን አደረሳችሁ! ምን ይዛችሁልኝ መጣችሁ?” ሲሉ ይጠይቃሉ። ይሔኔ ኣንደኛው ልጅ ከወረቀቶቹ መሓል ሳብ አድርጎ የ Lionel Messi’ን ንድፍ ሲሰጣቸው … የውሸትም ቢሆን ግንባሩን በመሳም እርሳቸውም ከቤት ልብስ ኪሳቸው ውስጥ መዥረጥ በማድረግ የኣንድ ኮንዶሚኒየም ቤት ቁልፍ ይሸልሙታል።
ሁለተኛውንም ህፃን … እንደተለመደው ጭንቅላቱን እያሻሹ “አንተስ ምን ይዘህልኝ መጣህ ማሙሽዬ?” ሲሉ ... ልጁ የያዛትን ኣንድ ወረቀት በፈገግታ እየተመለከታቸው ለሴትየዋ ያቀብላል። ሥዕሉ ሲታይ የእስክንድር ነጋ ምስል ንድፍ ነው። ይሔኔ … በፍቅር ሲያሻሹት የነበረውን ጭንቅላት በእጃቸው በኩርኩም ቆፍረው በኣስቸኳይ የወላጆቹ ቤት እንዲፈርስ ትዕዛዝ ይሰጣሉ። ወዲያው ግን የልጁ ቤተሰቦች የግል ቤት እንደሌላቸውና የሚኖሩትም የመንግሥት ቤት ውስጥ እንደሆነ ሲነገራቸው … በቁጣ እንደነደዱ “ የጎረቤቱም ቢሆን ይፍረስ!” ይላሉ።
ትንሽ ቆየት ሲሉና ንዴታቸው ሲበርድላቸው … በሞባይል ስልክ እየተቀረፁ እንደሆነ የገባቸው ከንቲባ ... ፊታቸውን የሜሲን ንድፍ ወደ ሰጣቸው ህፃን በማዞር … “አንተ ጎበዝ ልጅ ነህ። ስታድግ እግር ኳስ ተጫዋች ነው መሆን የምትፈልገው?” ሲሉ ይጠይቁታል። ልጁም “አይደለም!” ሲል ይመልሳል። “ ምን መሆን ነው የምትፈልገው ታዲያ?” ከንቲባዋ ድጋሚ ጠየቁ ። “ፋኖ መሆን " ድንቡሽቡሽ ያለው ህፃን መለሰ። የከንቲባዋ ግራ እጅ ልጁ የጨበጠውን የኮንዶሚኒየም ቁልፍ በፍጥነት ሲነጥቅ ቀኝ እጃቸው ድጋሚ በፈርጣማው ተጨበጠ …
ከጥቂት ደቂቃ ቦኃላ ሁለቱም ህፃናቶች ጭንቅላታፈውን በሁለት እጃቸው ጨብጠው እያለቀሱ ከሰፈራቸው ይደርሳሉ። ሰውም ተሰብስቦ “ምን ሆናችሁ ነው?” ብሎ ሲጠይቅ “ከንቲባዋ ጭንቅላታችንን መቱት” ብለው ይመልሳሉ።
“በኩርኩም?” ሰፈሩ ጠየቀ
“አይደለም፥ በድሮን” ህፅናቶቹ መለሱ