Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Horus
Senior Member+
Posts: 29365
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኦሮሙማ ተረኛ ጎማ ሙሉ በሙሉ የሚተነፍሰው የፋኖ ጦር በኦሮሞ ክልል ሲሰፍን ብቻ ነው!

Post by Horus » 16 Sep 2023, 16:23

ጦርነቱ ወደ አቢይና ሺመልስ ግቢ ሲገባና ከሸክላ የተጠፈጠፈው ኦሮሚያ ክልል ሲፈረካከስ ብቻ ነው ኢትዮጵያ ሰላም አግኝታ እፎይ የምትለው !Abere
Member+
Posts: 9923
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የኦሮሙማ ተረኛ ጎማ ሙሉ በሙሉ የሚተነፍሰው የፋኖ ጦር በኦሮሞ ክልል ሲሰፍን ብቻ ነው!

Post by Abere » 16 Sep 2023, 18:33

ሆረስ፥

ፋኖን ለማዘናጋት በውጭ አገር ተልዕኮ የተሰጣቸው ልማደኛ አሳማዎች እየተልከሰከሱ ነው ይባላል። ደረጀ ሃብተወልድም በዚህ ቪድዮ ላይ የነካካው ይመስለኛል። እኔ ብዙ ዩቲዩቦች እራሱ ደረጀ ሃብተወልድ አሁንም ጭምር ድርድር እና ውይይት አልፎ አልፎ ሲያተኩር አደምጠዋለሁ። ከኦሮሙማ ጋር የሚያደራድር አንዳች ያህል የክር ያልህ እንኳን የቀጠነ የጋራ ነገር የለም። በጣም ነው የሚገርመኝ ከሌንጮ ጋር የሚታረቅ ሰው ምን አይነት ነው፤ ከኮሎኔል ገለቱ ጋር ምን አንድ የሚያስተሳስር ጉዳይ አለ። ኦሮሙማን ከመደምሰስ ውጭ ምንም አማራጭ በሌለበት ስለ ድርድር የሚያወሩ የጭንቅ ቀን የአብይ አህመድ ልማደኞች በውጭ አገር እየተርመሰመሱ ነው። በዚህ ጉዳይ ፋኖ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠት ያለበት አይመስልህም ወይ? አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በጦር ሜዳ ላይ ያለው ፋኖ በርዕዮተ አለም ብስለት ይሁን በትምህርት ደረጃ ብቃት ምዕራብ አገር ከሚኖረው ዱርዬ አይበልጥም ወይ? በተግባር ጦር ግንባር ያለው ፋኖ ማተቡን ያልበጠሰ፤ እንደ ድንች ጥቅም አይቶ ያልተገላበጠ፤ በእጁ ወንጀል ያልፈጸመ ንጹህ ኢትዮጵያዊ እያለ ከአብይ አህመድ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በምዕራቡ አለም እንደ ዝንብ የሚልከሰከሱ ዲያስፓራዎች በጣም በጣም እየቀፈፉን መጥተዋል። ምን ይመስልሃል?

እኔ መቸም ፋኖ ትግሉን ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ ያሸጋገረው እራሱ የሚመራው ጉዳይ ይመስለኛል። የመጨረሻው ግብ ደግሞ የኦነግ/ወያኔ የጎሳ ክልል በማፍረስ ኢትዮጵያን ነጻ በማውጣት እንደ አለም አገራት ሁሉ ዜጎች በሰላም የሚኖሩባት አገር ማድረግ ነው።

Fano should watch out itself from the ክፍት አፍ diaspora!

Horus
Senior Member+
Posts: 29365
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኦሮሙማ ተረኛ ጎማ ሙሉ በሙሉ የሚተነፍሰው የፋኖ ጦር በኦሮሞ ክልል ሲሰፍን ብቻ ነው!

Post by Horus » 16 Sep 2023, 23:25

Abere,
እኔ ስመለከተው ነገሩ እንዲህ ነው ። የፋኖ አደረጃጀት በአንድ እዝ ስር ገባም አልገባ፣ የአማራ ፖለቲካ ጥያቄ አንድ ወጥ ሆኖ መውጣት አለበት ። ጦሩም ቢሆን አገረጃጀቱ የተሰባጠረ ቢሆንም (ለሽምቅ ውጊያ እንዲያመች) ኋላ ላይ ግን በግድ አንድ ወታደራዊ ኃይል ለመሆን ይገደዳል ። ይህ አንደኛው ቁልፍ ጉዳይ ነው፤ ማለትም የአማራ ወታደራዊ ኃይል እንዴት ይደራጅ? እንዴት ይመራ የሚለው ።

ሁለተኛው የአማራ ፖለቲካ ጥያቄና አጀንዳ በተመለከተ ነው ። አሁን ላይ 4 የተለያዩ ግምባሮች እንዳሉ መሳይ ሲናገር ነበር ። በአላማ አንድ ወይም ተቀራራቢ ናቸው ይላል ። የእኔ ጥርጣሪ የወሎ አማራ፣ የጎንደር አማራ፣ የጎጃም እና የሸዋ አማራ የሚል እንዳይሆን እፈራለሁ። ጠላትና አቢይ ይህን መሰል ክፍፍል ይፈልጋሉ ።

ስለሆነም የአማራ ፖለቲካ በተመለከተ ሁለት ቁልፍ ነገሮች ግልጽ ሆነው ለአለም መታወቅ አለባቸው ፤ ፋኖ ለአማራ የረቀቀው ያማራ ፖለቲካ ጥያቄ ምንድን ነው? የአማራን ህልወና ለማስጠበቅ ባለፈ? ሁለተኛው ፋኖ ለኢትዮጵያ ያረቀቀው ጥያቄ ምንድን ነው? የሚል ነው ።

ሊኖሩ የሚችሉት የአቋም አይነቶች የሚከተሉት ናቸው ፤
(1) ያማራ ፒፒን አስወግዶ፣ አቢይ ሰራዊቱን ካማራ አውጥቶ ከዚያም ካቢይ መንግስት ጋር የስልጣን ድርድር ማድረግ ። እነአቢይ ይህን የሚፈልጉት ነገር ነው ። አሁን ያለው የጎሳ ፌዴሬሽን እንዲቀጥል እሚፈልጉ ሁሉ ይህን መሰል ያማራ አቋም ይፈልጋሉ ።
(2) ሁለተኛው ሊኖር የሚችለው አቋም የጎሳ አደረጃጀት ሳይፈርስ አገር አቀፍ ጥገና አድርጎ ሁሉም ጎሳ ራስ ገዝ የሚያደርግ ተሃድሶ ጎሳዊ ፌዴራሊዝም የሚያዋቅ ድርድር ሊሆን ይችላል ። ይህ ከሆነ ፒፒ ምን ይሆናል? ኦሮሙማ ምን ይሆናል? አሁን ያለው ሰራዊት ምን ይሆናል ? ብዙ ጥያቄዎች ያሉበት መፍትሄ ነው ።
(3) አማራ በያዘው ጦርነት ገስፍቶ የቀሩትን ብሄረ ሰቦች አስተባብሮ ፣ ትግሬ የፈጠረውን የጎሳ ስርዓት የብሄረሰቦ መብት የሚከበርበት ግን የዜጋ ስርዓት ላይ የቆመች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው ። አማራ ይህ መስመር ከያዘ ጥያቄው የስርዓት ለውስጥ ይሆናል ማለት ነው።

ለምሳሌ የሻለቃ ዳዊት አቋም የዛሬው ምን እንደ ሆነ ባላውቅም ቀደም ሲል በቁትር 3 ያነሳሁትን ሃሳብ ለመተግበር የድርድሩ ትያቄ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ነው ብሎ ነበር ።

ማለትም ነገ የሚደረገው የድርድር ውይይት ያቢይ መንግስት እንዴት ፈርሶ በሽግግር መንግስት ይተካ የሚል ከሆነ አንተም እዚያ ተገኝተህ ድምጽህን ታስቆጥራልህ ማለት ነው ።

ቁጥር 1 እና 2 አማራን ለግዜው ለማለዘብና ትጥቁን የሚያስፈታ መሰመር ነው ።

Abere
Member+
Posts: 9923
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የኦሮሙማ ተረኛ ጎማ ሙሉ በሙሉ የሚተነፍሰው የፋኖ ጦር በኦሮሞ ክልል ሲሰፍን ብቻ ነው!

Post by Abere » 17 Sep 2023, 13:15

ሆረስ፤

የፋኖ የትግል መዳረሻ ፕላን ሀ እና ፕላን ለ ሊኖረው አይገባም። አንድ መዳረሻ ብቻ ሊኖረው የግድ ይላል። አማራጭ ግቦች በፍጹም ምርጫ ሊሆኑ አይችሉም -አይገባቸውም። ከ32 አመታት በላይ የወያኔ-ኦነግ ግፍ በመተጋለ የተሰውት ወገኖች እና የጠፋው የአገር ሃብት ጊዜ ዐመድ እንደ ማድረግ ይቆጠራል። ከ 1 -3 የዘረዘርካቸው የሚገመቱ ፤በተለይ 1 - 2 በኦነግ/ወያኔዎች የሚፈለግ እራሳቸው በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የሚዘሩ እንክርዳድ ነው።

ምርጫው የጠቀስከው 3ኛው ብቻ ነው።
<< (3) አማራ በያዘው ጦርነት ገስፍቶ የቀሩትን ብሄረ ሰቦች አስተባብሮ ፣ ትግሬ የፈጠረውን የጎሳ ስርዓት የብሄረሰቦ መብት የሚከበርበት ግን የዜጋ ስርዓት ላይ የቆመች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው ። አማራ ይህ መስመር ከያዘ ጥያቄው የስርዓት ለውስጥ ይሆናል ማለት ነው። >>

Horus
Senior Member+
Posts: 29365
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኦሮሙማ ተረኛ ጎማ ሙሉ በሙሉ የሚተነፍሰው የፋኖ ጦር በኦሮሞ ክልል ሲሰፍን ብቻ ነው!

Post by Horus » 17 Sep 2023, 16:32

አበረ፤
ወለንጪቲ ዜና ውስጥ ገብታለች! አሁን ፋኖ በሞጆና ናዝሬት ጀርባ ነው ያለው ። እመነኝ ፋኖ ናዝሬት ሲገባ መላ ሕዝቡ ተሰልፎ በልልታ ነው የሚቀበለው! አይደለም ወለንጪቲ ፋኖ ገና የዛቋላ አቦን ያስከብራል !

አማራ በያዘው ጦርነት ገስፍቶ የቀሩትን ብሄረ ሰቦች አስተባብሮ ፣ ትግሬ የፈጠረውን የጎሳ ስርዓት የብሄረሰቦ መብት የሚከበርበት ግን የዜጋ ስርዓት ላይ የቆመች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው ። አማራ ይህ መስመር ከያዘ ጥያቄው የስርዓት ለውስጥ ይሆናል ማለት ነው።


Post Reply