Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 22 Aug 2023, 14:12

ባህላዊ ገቢሩ ሳይሆን እራሱ ቃሉ ምን ማለት ነው? ከአሸንዳ ጋር ተዛማጅ የሆኑት ሌሎች ቃላት የተኞቹ ናቸው?


DefendTheTruth
Member+
Posts: 9924
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by DefendTheTruth » 22 Aug 2023, 14:30

Horus wrote:
22 Aug 2023, 14:12
ባህላዊ ገቢሩ ሳይሆን እራሱ ቃሉ ምን ማለት ነው? ከአሸንዳ ጋር ተዛማጅ የሆኑት ሌሎች ቃላት የተኞቹ ናቸው?

ለአሸንዳ ጊዜ የለንም እባክህ፣ አሁን አንገብጋቢዉ ጉዳይ ኦሮሞን ና ኦሮሙማን መግደል ነዉ። እንዴት ሳትክ ዛሬ?

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 22 Aug 2023, 14:52


union
Member+
Posts: 6415
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by union » 22 Aug 2023, 14:57

አንበጣ ቆርጫሚ ትግሬ

ትክክል ነህ። ኦሮሙማን እና ኦነግን መግደል ነው የምንፈልገው። ነገር ግን ምስኪኑን የኦሮሞ ህዝብ ለቀቅ አድርግ። አንተ ለማኝ ትግሬ። ቅማላም :lol:
DefendTheTruth wrote:
22 Aug 2023, 14:30
Horus wrote:
22 Aug 2023, 14:12
ባህላዊ ገቢሩ ሳይሆን እራሱ ቃሉ ምን ማለት ነው? ከአሸንዳ ጋር ተዛማጅ የሆኑት ሌሎች ቃላት የተኞቹ ናቸው?

ለአሸንዳ ጊዜ የለንም እባክህ፣ አሁን አንገብጋቢዉ ጉዳይ ኦሮሞን ና ኦሮሙማን መግደል ነዉ። እንዴት ሳትክ ዛሬ?

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Meleket » 23 Aug 2023, 10:49

ወንድማችን Horus ኮርኳሪና ጐርጓሪ ጥያቄዎችና አስተማሪ ትንተናህ አመራማሪዎች ናቸውና ልትመሰገን ይገባል፤ ብዙዎቻችን እውቀትን እየገበየንበት ስለሆነ ግፋበት። ስንሳሳት እየታረምንበት የማናውቀውን እያወቅንበት ወዘተ ስለሆነ ግፋበት።

ያገራችን ሰዎች ሲተርቱ፡ “ናይ ኣቦኡ ዘጥፍእ ኪጠፍእ” ይላሉ መሠረታችሁን አትዘንጉ ለማለት ሲያሳስቡን መሆኑ ነው።

ኣሸንዳ ኦሪታዊ ምንጩን ካንዳንድ ጽሑፎች አንብበን እንደነበርን እናስታውሳለን፡ ከመጸሓፈ መሳፍንት ምዕራፍ 11 ታሪክ ጋር ኣያይዘው፡ በዚሁ መጸሐፍ ምዕራፍ 11፡40 ላይ እንደተጠቀሰው የጊልዓዳዊውን የይፍታሕ ብቸኛ ሴት ልጅን ለማወደስ እስራኤላውያን ሴቶች ካደረጉት ድርጊት ጋር አያይዘው ለመተንተን የሞከሩ ሰዎች አጋጥመውናል። . . .

ወደ መሠረታዊ ጥያቄህ ስንመለስ፡ እናቶቻችን እነሱን ተከትለውም አንዳንድ እህቶቻችን የእድሜ እኩያ ጓደኞቻቸውን “አዳነይ፡ ኣብሻይ፡ ሳንዳይ” ሲሉ ይሰማሉ። በተለዪ “ሰንዳይ" የሚለው ቃል “እታለም” ወይ ታላቅ እህቴ እንደሚለው የአማርኛ ቃል አግባብ እንዳለው እናውቃለን። አሸንዳ ላይ የሚጨፍሩት ደግሞ የእድሜ እኩያዎች በመሆናቸው እርስበእርስ “ሰንዳይ ሳንዳይ” መባባላቸውን በመላምት እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እንገምታለን። ሌላ ከዚህ የበለጠ አሳማኝና አርኪ የቃል ትንተና እስኪያጋጥመን፡ እንዲህ እዬተዝናናን ተፈላስፈናል!፡ የንዋይ ደበበን “ሁሉም የየራሱን ሲያደንቅ እሰማለሁ፡ የኔም ለኔ እኮ ናት እኮራባታለሁ እመካባታለሁ” የሚለውን ዜማ እያጣጣምን።

የሚገርምህ እኒህ "ሳንዳይ" የሚባባሉት እህቶቻችንና እናቶቻችን(ከልጅነታቸው ጀምሮ 'ሳንዳይ' እንደሚባባሉ አትዘንጋ)፡ "በየት በኩል መጣህ?" ብለው ሲጠይቁ "ብአይቲ መጺ(ጪ)ካ?" ብለው ይጠይቁሃል። ብአይቲ የሚለው ቃል ምንጩ የግዕዙ አይቴ መሆኑን የሚያቁ፡ መሠረታቸውን ያልለቀቁ ቃላቶችን በመስማታቸው ሲደመሙ፡ አላዋቂዎች ደግሞ ሳያፍሩ ሊገለፍጡ ይችላሉ።

ኬር!
:mrgreen:
Horus wrote:
22 Aug 2023, 14:12
አሸንዳ ምን ማለት ነው?

ባህላዊ ገቢሩ ሳይሆን እራሱ ቃሉ ምን ማለት ነው? ከአሸንዳ ጋር ተዛማጅ የሆኑት ሌሎች ቃላት የተኞቹ ናቸው?


Abere
Senior Member
Posts: 11131
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Abere » 23 Aug 2023, 11:13

እኔ የማስታውሰው አሸንዳ እስላም ክርስቲያን ሳይሉ ልጃ ገረዶች ሙሉ አሸንዳ ታጥቀው ሙሉ ቀን የገጠር መንደሮችን ሁሉ እየዞሩ

አሽንዳ አበባ፤
እርግፍ በይ እንደ ወለባ።


እያሉ በመጨፈር በየገቡበት ቤት የቤቱን አባወራ

ያ የማነው ጋሻ ከመከታው ላይ፥
የእግሌ አባ በሉ - የጣምራ ገዳይ።


እመዋራዋን ደግሞ፥

ያ የማነው እንዝርት ከመከታው ላይ፥
ያ የማነው ደጋን ከመከታው ላይ፥
የእገሌ እማበሉ የቀጭን ፈታይ።

በማለት አታሞ ይዘው እየጨፈሩ ሲሸለሙ ይውላሉ። አሸንዳ የልጃ ገረዶች ሲሆን ቡሄ ደግሞ የወንዶች ልጆች ነው። አሸንዳ የሚባል የሚያምር አበባ ያለው ቅጠልም አለ - የሳር አይነት ግን ቅጠሉ የዘንባባ ቅጠል የመሰለ::

በከተሜው ዘንድ ደግሞ ቤቱ አሸንዳ አለው ሲባል የውሃ መውረጃ ጣርያው ላይ ተገጥሞለታል ማለት ነው። እንደት አሸንዳ ከቤት ጣርያ ጋር ትርጉም አገኘ?


ethiopian
Member+
Posts: 5343
Joined: 09 Oct 2011, 21:29

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by ethiopian » 23 Aug 2023, 11:45

Horus wrote:
22 Aug 2023, 14:12
ባህላዊ ገቢሩ ሳይሆን እራሱ ቃሉ ምን ማለት ነው? ከአሸንዳ ጋር ተዛማጅ የሆኑት ሌሎች ቃላት የተኞቹ ናቸው?

we the Oromo Ethiopians call it Agenda ---- heard my man yesterday

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 23 Aug 2023, 15:08

መለከትና አብረ፤

አሁን እንደ ምናስተውለው ይህ የሴቶች በዓል በኤርትራ፣ ትግራይ አማራና ጉራጌ ይከበራል ። በትግርኛ አሸንዳ፣ በአማርኛ አሸንዳዬ(ይ)፣ በጉራጌኛ አዳብና (አደይ አብና) ይባላል። እያንዳንዱ ማህበረሰብ ትንሽ ለየት ባለ መንገድ ቢያከብረውም በመሰረቱ ተመሳሳይ ነው ። ግሩም ግብአት ነው የሰጣችሁን።

መለከት፤
አመሰግናለሁ። አሸንዳ የቅድመ ክርስትና ባህል ነው ወይስ ክርስትና ያጠናሁት ነገር አይደለም ። በቅድመ ክርስትና ብዙ ከልምላሜና የሴቶች ለምለምነት (ፈርቲሊቲ) የተያያዙ ባህሎችና አምልኮዎች ነበሩ ። ከመሬት ልምላሜና ከክረምት ጋር የተያያዙም እንዲሁ ። ባህሉ በብሉይም ሆነ አዲስ ኪዳን ዘመን ቢኖር አልገረምም። ማለትም ስለ ግልዓዳዊው ይፍታህ ሴት ልጅ ምንም እውቀት የለኝም።

ልጃገረድ እህቶቻችን ስለ ሚጠቀሟቸው የሞክሼ ስሞች በጣም ትክክል ነህ!

እናንተ ጋ አዳነይ የሚባባሉት ጉራጌዎቹ አዶዬ ይባባላሉ ። ሳንዳይ የሚለውም አዶዬ የሚለው አንድ ነው ። የናንተ ሴቶች አብሻይ የሚሉት የኛዎቹ ዬጎስቴ ይባባላሉ ። ትርጉሙማ አንተ ካልከው አይለይም፤ ዬጎስቴ ንግስቴ፣ እሜቴ እንደ ማለት ነው። የአንድ አሸንዳ ጓደኞች ሰንዳይ ሰንዳይ እንደ ሚባባሉት የአንድ አዳብና እኩዮች አዶዬ ይባባላሉ ። (በነገርችን ላይ ብአይቲ መጺካ ስትሉ እኛ ቢቲ መጣሽ እንላለን)

የቃል ትርጉም፣

አበረ እንደ ጠቀሰው አሸንዳ ሁለት ትርጉም አለው፤ አንዱ አበባ ነው፣ ሌላው ሳር ነው ። ግን በአሉ የሚታወቀው በአበባው ነው ። ይህ አበባ የአደይ አበባ (የመስቀል አበባ) ነው ። አበረ የጠቀሰው አበባ ከአደይ አበባ አንድ ይሁን አይሁን ጀባ ይለናል ።

አደይ አበባ ከፍልሰታ ጀምሮ እንቁጣጣሽን (የአበባ እንኩታታ ማለት ነው) ጨምሮ እስከ መስቀል ምድሪቱን የሚሸፍነው ታላቁ የመስቀል አበባ ነው። ይህ አበባ በግዕዙ ዘ አደይ (ጸአደይ፣ ጸደይ) ሲባል በአማርኛ አደይ፣ በጉራጌኛ አደየ ይባላል ።

አሸንዳ ውስት የተሸነቆረው ‘ነ‘ ገብቶበት ነው እንጂ ቃሉ ሰንዳይ፣ አሸዳይ ፣ዘ አደይ የሚለው ነው ። ዘ አደይ ዛሬ ጸደይ የሚባለው ወራት (መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር) የምጠራበት ቃል ነው ። ስለዚህ አሸንዳ (ትክክለኛው አሸንዳይ ነው) የአደይ አበባ ነው ።

አረንጓዴው ሳር ምንድን ነው?

አበረ በትክክል ጠቅሰሃዋል። ያ በአማርኛ ስንደዶ የሚባለው ነው ።እርግጥ ስሙ ከአደይ የተቀዳ ነው ። ያ ሳር እርጥብ ሆኖ አክርማ ይባላል። አክርማ አማርኛ ይመስለኛል ። የጉራጌ ልጃገረዶች አሸንዳና የአክርማ በዓላቸው ለያይተው ነው የሚያከብሩት። ስንደዶ ወይም አክርማ ስፌት የሚሰፉበት ሳር እኛ ፍቃቆ እንለዋለን። ትርጉሙ ፍካኮ የአበቦች መፍካት መፈንዳት ማለት ነው። ይህ የሳር ነቀላው በአሸንዳ ውስጥ ወገባቸው ላይ የሚያስሩት ለም ሳር ማለት ነው ።

በትግርኛ እና አማርኛ ካልቸር አሸንዳ የሴቶች ብቻ በዓል ሲሆን በጉራጌ አሸንዳ አዳብና ይባላል፤ እሱም አደይ አብና ወይም አደይ አበባ መሰጣጫ ማለት ነው ። ልክ አበረ እንዳለው የሴቶች እንዞሪቴ ወይም ሆያ ሆዬ ነው ። ከቤት ቤት እየዞሩ እየዘፈኑ እየተሸለሙ የአደይ አበባ ይሰጣሉ ። ይህ የሴቶቹ የብቻ በዓል ነው ።

የመስቀል አዳብና፣
ሁለተኛው አዳብና ከመስቀል ቀን ጀምሮ ሴቶችና ጎረምሶች ለመፋቀር፣ ለመተጫጨት ሎሚ የሚዋጉበት በአልም እኛ አዳብና እንለዋለን ።

አበረ፣
የገለጽከው አሸንዳዬ እንዳለ የኛ ልጃገረዶች የሚያደርጉትን ነው። ሴቶቹ አሸንዳ አበባ ሲሉ በትክክል አደይ አበባ ማለታቸው ነው!

እንዳልከው ...
“ አሸንዳ የልጃ ገረዶች ሲሆን ቡሄ ደግሞ የወንዶች ልጆች ነው። አሸንዳ የሚባል የሚያምር አበባ ያለው ቅጠልም አለ - የሳር አይነት ግን ቅጠሉ የዘንባባ ቅጠል የመሰለ ነው”

የሚገርመው ነገር ግን የውሃ መቀበያው የቤትና የጠበል አሸንዳ ነው። ያጠናሁት ነገር አይደለም ። እዚህ አጭር ውይይት ውስጥ ማንዛዛት ያልፈለኩት የአደይ ኢቲሞሎጂ ነው ።አደይ ክረምት፣ መከር፣ መስከረም፣ እርጥብ ፣ ከሚሉት የክረምትና ዝናብ ወይም ውሃ ስረ ቃላት የተነሳ ነው ። አሸንዳ የሚባለው ውሃ መቀበያ ከዚያ የመጣ ሊሆን ይችላል ። አላጠናሁትም ።

ሰላም!
Last edited by Horus on 23 Aug 2023, 18:15, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 23 Aug 2023, 17:59

ሃዬ ሃዬ (ሆያ ሆዬ)
ለፊቃቆ በዓል የተዘፈነ
ፊቃቆ = የአክርማ ሰንደዶ ሳር

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Meleket » 24 Aug 2023, 03:07

ሳንዳ - ስንዱ እስቲ ተንበሽበሹ፡ ወዳጃችን ኣበረ አሸንዳ ጥሬ ቃሉ በአሁኑ ወቅት ከጣርያ ውሃ ማንቆርቆርያ ጋር ስለመያያዙም ስትጠቁመን ስንዱ የሚለውን ግሩም ቃል እንዴት ዘነጋሀው?

ኣሸንዳና ሳንዳ የሚሉ ቃላትን የኛዎቹ ሰዎች እንዲህም ተርጉመዋቸዋል

ኣሸንዳ የሚለውን ቃል ልጃገረዶች በገጠር የሚጫወቱት ጨዋታ ብለው ተርጉመው ሲያበቁ ሁለተኛውን ትርጉም ደግሞ ኒፎፍያ Kniphofia species የተባለ የተክል ዝርያ ብለው ሴቶች በፍልሰታ ግዜ እራሳቸው ላይ የሚያስሩት የተክል ቅጠል ብለው ተርጉመውታል።

ሳንዳ ዕረ፡ በማለት በቆላም በደጋም በወይናደጋም የሚበቅል የቅጠሉ ጭማቂ ለፈውስነት የሚያገለግል፡ ንብን ለመሰብሰብ እንዲሁም የአፈር መሸርሸርን ለመታደግ የሚጠቅም፡ የተክሉ ቁመት አንድ ሜትር ገደማ የሆነ በማለት በሳይንሰኛ አጠራሩ ኣሎም ማክሮካርፓ ኣ.ኣቢሲኒካ (Aloe macrocarpa A. abyssinica) ብለውታል። የኛዎቹ ተርጓሚዎች በትክክል ተርጉመውታል ብለን ካሰብን፡ ጎግል እንደጠቆመን ይህኛው ተክል እሬት ቢጤ ሁኗል፡ ያ ከሆነ ደግሞ የጊልዓዳዊውን ይፍታሕ መራራ ሃዘን ጠቁሞናል ብለን ተርጉመን ብንፈላሰፍበት ምን ይለናል።


ሳንዳ ኮረዳ፡ ልጃገረድ፡ ጓደኛ፡ ዘመድ፡ በእድሜ ግን ካንተ በጥቂትም ቢሆን ልትበልጥ የምትችል ሴት እህት፡ በሴቶችም በወንዶችም ሳንዳ ትባላለች፡ የኔ እህት እትዬ የኔ ጓደኛ ለማለት ደግሞ ሳንዳይ ይባላል። ቤት ገዛ እንደሚባለው የኔ ቤት ለማለት ገዛይ እንደሚባለው ማለት ነው። ማብራርያው መቼም አይከፋም ኣይደል . . . .

ወደ ቁምነገራችን ስንሄድ ትግርኛም ኣማርኛም ጉራጊኛም ኦሮምኛም ኣረብኛም ወዘተኛም እርስበርሳቸው የተጋመዱና የተወሃሃዱ ለመሆናቸው አንዲት በትግርኛችንና በአማርኛችን መካከል ያለች ምሳሌ ለማቅረብ እንሞክራለን፦

አማሮች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ስንዱ ብለው ስም ሲያወጡስ ኣላጋጠሟችሁምን? ስንዱ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እንደሚገባን የተሰናዳች፡ የተዘጋጀች፡ የተቃረበች ማለትንም ያሰማል፤ ለምኑ? ብትሉ፤ ለአቅመ ሄዋን የደረሰች ለትዳር የተዘጋጀች፡ ወልዶ ለመሳም የተቃረበች ልጃገረድ ስንዱ የምትባል ይመስለናል። አይደለም እንዴ በመሆኑም ሳንዳ እና ስንዱ ሁለቱም አንድና አንድ ሆነው ይሰሙናል። እስቲ ስንዱን ይዛችሁ ደግሞ ተፈላሰፉ፡ አንዳንዶቻችሁ የመጻሕፈ መሳንፍንት ምዕራፍ 11 ላይ ታሪኳ የተገለጠው የጊልዓዳዊው ይፍታሕ ልጃገረድ ትክክለኛ ስሟ ስንዱ ነው እንዳትሉን እንጂ። እስቲ የመጸሐፈ መሳፍንቱን ምዕራፍ 11ን በሙሉ ለማንበብ ሞክሩና ምዕራፍ 11፡40 ላይ ደግሞ ደጋግማችሁ ኣንብቡት። ኮረዶቹ ይቺን ሴት እያስታወሱ ሳንዳይ ኣሸንዳይ ስንዱዋ እህታችን ብለው እያወደሷት ይሆንን? ፈላስፎችና ተመራማሪዎች አጥንተው እስኪነግሩን በዚህ እንዝናና እንጂ።

አንዳንድ ጸሐፊዎቻችን መጻሕፍቶቻቸውን ሲያሳትሙ "አዘጋጅ እገሌ" ለማለት "አዳላዊ እገሌ" ወይም "አሰናዳዊ እገሌ"ም ሲሉ አጋጥመውናል። አሰናዳዊ ፡ ኣዘጋጅ፡ . . . ስንዱ . . .

ኬር! :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Meleket » 25 Aug 2023, 11:15

Abere wrote:
23 Aug 2023, 11:13
. . .

በማለት አታሞ ይዘው እየጨፈሩ ሲሸለሙ ይውላሉ። አሸንዳ የልጃ ገረዶች ሲሆን ቡሄ ደግሞ የወንዶች ልጆች ነው። አሸንዳ የሚባል የሚያምር አበባ ያለው ቅጠልም አለ - የሳር አይነት ግን ቅጠሉ የዘንባባ ቅጠል የመሰለ::

በከተሜው ዘንድ ደግሞ ቤቱ አሸንዳ አለው ሲባል የውሃ መውረጃ ጣርያው ላይ ተገጥሞለታል ማለት ነው። እንደት አሸንዳ ከቤት ጣርያ ጋር ትርጉም አገኘ?


ሳንዳ (እታለም፡ ኮረዳ፡ ድንግል፡ ልጃገረድ፡ ታላቅ እህት) . . . ኣሸንዳ . . . ስንዱ . . . ብለን ከተፈላሰፍን ዘንድ፡ የአገውኛ ቋንቋ እና የኦሮምኛ ቋንቋ ከነዚህ ቃላት ኣኳያና ከ"አሸንዳ" ታሪክ ኣኳያ ምን ዓይነት ትርክት ይኖራቸው ይሆናል? የቋንቋው ተጠቃሚዎች እይታቸውን ቢያካፍሉን ግሩም ነው። የላሊበላ ፍልፍል አብያተክርስትያናት የውሃ ኣሸንዳ ኣላቸውን? ካላቸውን በአገውኛ ምን ብለው ይጠሩታል? ወዘተ ብለን ከጠዬቅን አይታወቅም የወንድማችን አበረ ጥያቄ ምላሽ ያገኝ ይሆናል ብለን እናስባለን። :mrgreen:

ኬር!

union
Member+
Posts: 6415
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by union » 25 Aug 2023, 11:24

Ascari akaleguzi calling himself oromo :lol: :lol: :lol: :lol:

Anbeta qorchame :lol:

ethiopian wrote:
23 Aug 2023, 11:45
Horus wrote:
22 Aug 2023, 14:12
ባህላዊ ገቢሩ ሳይሆን እራሱ ቃሉ ምን ማለት ነው? ከአሸንዳ ጋር ተዛማጅ የሆኑት ሌሎች ቃላት የተኞቹ ናቸው?

we the Oromo Ethiopians call it Agenda ---- heard my man yesterday

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Meleket » 26 Aug 2023, 03:08

አዬ የ ፲ አለቃ ልጆች፡ በቃ ያ ጠባያችሁ እስካሁን አልተቀዬረም ማለት ነውን? ለመሆኑ ፲ አለቃ ተሻላቸው ወይ? ወንድሞችህና እህቶችህስ እንዴት ናቸው? https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=325462& ካቲካላና ጠላ በ Seven-Up መጠጣቱንስ አልተዋችሁትምን? :mrgreen:

ይህ ውይይት ስለ አሸንዳ ሆኖ ሳለ የ ፲ አለቃ ልጆች ደግሞ ስለ አንበጣ ታወራላችሁ? ስለ አንበጣ ከፈለጋችሁ የቅዱስ ዮሃንስ ሰሞን አውሩን። ቅዱስ ዮሃንስ ምግቡ አንበጣ ነበር አሉ፤ አንበጣ መብላት የቅድስና ምልክት ነው መቼም ኣንላችሁም፤ ምክንያቱም ጨዋታችንና ወጋችን ስለ ሳንዳ . . . አሸንዳ . . . ስንዱ . . . ነውና!

union wrote:
25 Aug 2023, 11:24
Ascari akaleguzi calling himself oromo :lol: :lol: :lol: :lol:

Anbeta qorchame :lol:
. . .
Meleket wrote:
25 Aug 2023, 11:15
Abere wrote:
23 Aug 2023, 11:13
. . .

በማለት አታሞ ይዘው እየጨፈሩ ሲሸለሙ ይውላሉ። አሸንዳ የልጃ ገረዶች ሲሆን ቡሄ ደግሞ የወንዶች ልጆች ነው። አሸንዳ የሚባል የሚያምር አበባ ያለው ቅጠልም አለ - የሳር አይነት ግን ቅጠሉ የዘንባባ ቅጠል የመሰለ::

በከተሜው ዘንድ ደግሞ ቤቱ አሸንዳ አለው ሲባል የውሃ መውረጃ ጣርያው ላይ ተገጥሞለታል ማለት ነው። እንደት አሸንዳ ከቤት ጣርያ ጋር ትርጉም አገኘ?


ሳንዳ (እታለም፡ ኮረዳ፡ ድንግል፡ ልጃገረድ፡ ታላቅ እህት) . . . ኣሸንዳ . . . ስንዱ . . . ብለን ከተፈላሰፍን ዘንድ፡ የአገውኛ ቋንቋ እና የኦሮምኛ ቋንቋ ከነዚህ ቃላት ኣኳያና ከ"አሸንዳ" ታሪክ ኣኳያ ምን ዓይነት ትርክት ይኖራቸው ይሆናል? የቋንቋው ተጠቃሚዎች እይታቸውን ቢያካፍሉን ግሩም ነው። የላሊበላ ፍልፍል አብያተክርስትያናት የውሃ ኣሸንዳ ኣላቸውን? ካላቸውን በአገውኛ ምን ብለው ይጠሩታል? ወዘተ ብለን ከጠዬቅን አይታወቅም የወንድማችን አበረ ጥያቄ ምላሽ ያገኝ ይሆናል ብለን እናስባለን። :mrgreen:

ኬር!
አገው ነን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ! ከአገው ነን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ . . . ስለ 'ሶለል' ሆነ 'አሸንዳ' የቃል ትርጉም አጫውቱን!

ሲጠቃለል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እንዲህ ነው ያስቀመጥነው በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር

ሳንዳ (እታለም፡ ኮረዳ፡ ድንግል፡ ልጃገረድ፡ ታላቅ እህት) . . . ኣሸንዳ . . . ስንዱ . . .
:mrgreen:

Horus
Senior Member+
Posts: 30924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አሸንዳ ምን ማለት ነው?

Post by Horus » 26 Aug 2023, 03:53

መለከት፣
በትግርኛ ቃል ውስጥ አሸንዳ ምን እንደ ሆነ ቦታኒካል ስሙን እና የላቲን አሽፎዴለስ እንደ ሚባል ስለ ኣወቅከን እናመሰኛለን ። ይህ ጸጉራማ እጽ እርግጥም በቆላ ኤርትራና ኢትዮጵያ እንዳለ መራጃ ያሳያል ። በኔ እምነት እናንተ ለአሸንዳ የምትጠቀሙት ሳርና ጸጉራማ አበባ ያ ሊሆን እንደ ሚችል አምኛለሁ ።

ግን አሽፎዴሉስ በኔ ግምት የሾክ አበባ እና በደጋ ኢትዮጵያ ያለው አደየ፣ አደይ አበባ (ዴይዚ ቢጫው ለስላሳው የመስቀል አበባ) በፍጹም አን

ይህ እጽ ግሪኮች አሪስታቱስ ይሉታል፣ እሱም እንደ ጸጉር የቆሙ አበቦች ያሉት እጽ ማለት ነው።

አሁን ችግሩ አሸ (ን) ዳ እና አሽ (ፎ) ዴል ያላቸውን ዝምድና መመርመር ያሻል ። ማለትም ለምን በትግርኛ አሸንዳ ተባለ ለሚለው!

ወደ አማራና መሃል ኢትዮጵያ ስንመጣ አሽፎዴል የለም (Knifofia) የቦታኒስቱ ሰው ስም ስለሆነ እሱን መጠቀም ለኢቲሞሎጂ ዋጋ ቢስ ነው። እኛ ሸዋ ውስጥ የምንጠቀመው አደየ ወይም አደይ አበባ የቃሉ ስር ዉሃ፣ ለም፣ እርጥብ ማለት ሲሆን ክቃቆ መፍካት ማበብ ማለት ነው። አደይ ጸደይ (እስፕሪንግ) ማለት ስለሆነ ቀጥታ ትርጉም አለው ከዘመን መለወጫና ክረምት ጋር ።

ይህም ሆነ ያ አሽፎዴል ማለት አሸንዳ ከሆነ ቃሉ በቀጥታ ላቲንና ግሪክ ነው ። ትርጉሙ እንደ እሾክ፣ እንደ ጸጉር ያሉ ሻርፕ አበቦች ያሉት ፕላንት ወይም እጽ ነው።

በፍልሰታ ራስ ላይ የሚጽረው አር በሸዋና ጎጃም በጉራጌ እንጊጫ ይባላል ፣ ከአሽፎዴል የተለየ ነው። እንጊጫ ለፍልሰታ እንጂ ለልጃ እረዶቹ በዓል አይደረግም ። የኛ ልጃገረዶች ከቤት ቤት የሚሰጡት አደየ ወይም አደይ አበባ ነው ። የሚነቅሉት ሳር የስፌት መስሪያ ፍቃቆ ወይም አክርማ ይባላል። ክርማን ክረምት ማለት ነው !

Post Reply